AAU NEWS
10.7K subscribers
3.11K photos
79 videos
393 files
1.1K links
First and best source of information in AAU.
NOT OFFICIAL!

For any information contact
@Bisrat_Y
@Lincoln0012
Download Telegram
#Reminder

የፋይዳ መታወቂያ አውጥተዋል?

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ተፈታኞች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ሊያወጡ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባውን በጊዜ በማድረግ የፋይዳ መታወቂያዎን ይያዙ።

@tikvahuniversity



@AAUNEWS1
Welcome to AfriYAN Chapter  Ethiopia! 💚

We're  dynamic youth-led network championing SRHR, Gender Equality, and Youth Empowerment across Ethiopia.We believe that meaningful youth participation is the key to sustainable development and social change.This is your sign to join a movement that's all about YOU and your power to transform our future.💡

SCAN the QR code and become part of the change!😀 Together, we rise!🙌


#AfriYANChapterEthiopia
#YouthPower #AfriYAN #SRHR #GenderEquality #YouthLeadership #FollowForChange


Telegram | LinkedIn | Instagram


@AAUNEWS1
🌟 Hey Future Scholars! 🇯🇵

Guess what? The Embassy of Japan is rolling out the red carpet with 120 amazing scholarship opportunities just for you! 🎉 Whether you're dreaming of studying in Japan or just want to dive into a new culture, this is your chance to make it happen!

Why You Should Be Excited:

Get Ahead of the Game! Attend our upcoming event and score priority consideration for these awesome scholarships. Trust us, you don’t want to miss this!

What’s Up for Grabs?
1. Research Scholarships: Perfect for those of you ready to take your Master’s or Doctorate to the next level. Dive deep into your research passion!

2. Undergraduate Scholarships: Got your sights set on a bachelor’s degree? This is your ticket to an unforgettable college experience in Japan!

3. College of Technology Scholarships: For all the tech whizzes out there, this one's for you! Get hands-on training and skills that will take you places.

🔗 Ready to jump in?
Japan Embassy Scholarships

@AAUNEWS1
ከ31 ባንኮች መካከል 28ቱ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸው ተገልጿል! በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አለው!

የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ በተሰረቁ የATM ማሽኖች፣ በሐሰተኛ ቼኮች፣ በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርትን ጠቅሶ የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሞሽን ነው ይፋ ያደረገው፡፡

Source: theethiopianeconomistview
@AAUNEWS1
#ፓስፖርት #ፋይዳ

ፓስፖርት ለማውጣት ፋይዳ / ዲጂታል መታወቂያ እንደሚያስፈልግ እና ቅድመ ሁኔታ እንደሚሆን ተገለፀ።

ከሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ሰነዶች ፋይዳ / ዲጂታል መታወቂያ አንዱ እንደሚሆን ተገልጿል።

ፓስፖርት ለመውሰድ በቀጠሮ ላይ የሚገኙ ዜጎችም የፋይዳ / ዲጂታል መታወቂያ እንዲይዙ ይጠበቃል ተብሏል።

ፋይዳ / ዲጂታል መታወቂያን ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ሰነዶች ውስጥ በማካተት አገልግሎት ለመስጠት የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እና የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት በትብብር ለመስራት ከስምምነት መደረሳቸው ተነግሯል።

ከዚህ በኃላ ከፓስፖርት ጋር በተያያዘ ለሚሰጠው አገልግሎት ዲጂታል መታወቂያ እንደ ዋና ሰነድ ያገለግላል። 

#National_ID #FAYDA #EPA




@AAUNEWS1
Any one who lost these exercise book in the behind Kennedy library you can contact

@Kuch21


Share it

@AAUNEWS1
ቁራ ሲታመም... እራሱን በጉንዳን ያስወርራል

ቁራ ሲታመም ጉዳን በሚገኝበት አካባቢ ሄዶ ይቀመጣል። ከዚያም ክንፉን በመዘርጋት ጉንዳኖቹ ሰውነቱን እንዲወሩትና እንዲነክሱት ያፈቅዳል።

ቀራዎች ይህንን የሚያደርጉበት አስገራሚ ምክንያት አላቸው: ጉንዳኖች ሰውነታቸው ፎርሚክ አሲድ የተባለ የተፈጥሮ ፀረ-ተባይ ንጥረ ነገር ይረጫል። ይህ አሲድ ቁራው ፈንገሶችን፣ ባክቴሪያዎችን እና ጥገኛ ተህዋሲያንን ከሰውነቱ ላይ እንዲያስወግድ ይረዳዋል፤ ይህም ህክምና ሳያስፈልገው እንዲያገም ያስችለዋል።

ይህ ባህሪ "አንቲንግ" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በተለያዩ የአእዋፍ ዝርያዎች ላይ ተስተውሏል። ይህ የእንሰሳት ራስን የማከም ጥበብ ግሩም ምሳሌ ነው።

ተፈጥሮ ግን ድንቅ ናት!

Source፦ Feedy Healthy




@AAUNEWS1
#ጥቆማ

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ባሉበት ሆነው ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

በተሰጠው ስምንት ሳምንት ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትልዎታል።

@tikvahuniversity


@AAUNEWS1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለመፍረድ አንቸኩል

ሁለት አስተማሪ ቁምነገሮች አንዱ በዚህ ፅሁፍ አንዱ ከላይ ባለው ቪዲዬ

አባትና ልጅ በባቡር እየሄዱ ነው።

ልጁ 24 ዓመቱ ነው። የውጩን ውበት ለማየት ከመጓጓቱ የተነሳ አንገቱን በመስኮቱ አውጥቶ እንደ ህጻን እየቦረቀ ነው።

ልጁ ድንገት ጮኸና "አባዬ ተመልከት ዛፎቹ ከኛ ተቃራኒ እየተጓዙ ነው" አለ። ተሳፋሪው በሙሉ ልጁን ገላመጠው አንዳንዶቹም ከንፈራቸውን መጠጡ። አባትየው ግን ፈገግ አለ።

ለሁለተኛ ጊዜ ልጁ ጮክ ብሎ "አባዬ እይ ደመናው ከእኛ ጋር እየተጓዘ ነው" አለው። አባትየው አሁንም ፈገግ አለ። ተሳፋሪው ግን አጉተመተመ ።

"ምን እንደ ህጻን ያደርገዋል...ትልቁ ሰውዬ ..የትልቅ ቀላል... ጠፍ ነገር ነው እንዴ... ሞኝ አይሙት እንዲያጫውት... አባቱ ደግሞ ፈገግ ይልለታል.. ምኑ ቂል ነው.. ወዘተ"  ተሳፋሪዎች የማይሉት ነገር የለም ሁሉም አጉተመተመ።

ከአባትየው ጎን የተቀመጠች አንዲት ሴት ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ "ምን አለበት ለሐኪም ብታሳየው አባቱ አደለህ?!" አለችው።

አባትዮው ፈገግ ብሎ መለሰ "አሁን አሳይቸው ከሐኪም ቤት መምጣታችን ነው ። ልጄ ከልጅነቱ ጀምሮ ዐይኑ አያይለትም ነበር ዛሬ ግን ታክሞ ሁላችንም የምናየውን ማየት ችሏል። አሁን ከሐኪም ቤት ወጥተን ወደ ቤታችን እየሄድን ነው " አላት።

ሰናይ እሁድ

👇👇👇👇👇
@AAUNEWS1
ናሚቢያ ትምህርት በነፃ ❗️
የሀገሪቱ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ኔቱምቦ ናንዲ
ከ2026 በሃገሪቱ ባሉ በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ተቋማት  ዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ትምህር በነፃ እንደሚሰጥ ገለፁ

ፕሬዘዳንቷ ሀሙስ ማምሻውን ባደረጉት ንግግር
ሀገሪቱ የሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክ ኮሌጆች “ምንም የምዝገባ [ወይም] የትምህርት ክፍያ አይከፍሉም ለተማሪዎቹም የምግብና መሰረታዊ ወጭዎች በመንግሥት ይሸፈናል ።አቅም ለሌላቸዉም   ድጎማ እና  የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ።

አክለዉም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በሁሉም የሀገሪቱ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ነፃ በሚሰጥባት ናሚቢያ ለትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ከቀጣይ አመት ጀምሮ  የሀገሪቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በነፃ ለማስተማር መንግስታቸው ከፍተኛ በጀት መመደቡን ገልፀዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነዉ ።

የ72 ዓመቷ ናንዲ-ንዳይትዋህ ከተመረጡ በኋላ በአንፃራዊነት ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ያለች ሲሆን በዋነኛነት በነዳጅ፣ በጋዝ እና በአረንጓዴ ሃይድሮጅን ዘርሮች ትክረት አድርገው በመስራት
ከፍተኛ የስራ አጥነት መጠንን በመቅረፍ በግብርናው ዘርፍ ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ እና በሀብት ላይ ያተኮረ ኢኮኖሚ በመገንባት ለዉጥ ማምጣታቸውን ይነገራል ።

ናንዲ-ንዳይዋህ ዜጐችን የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ከአገራችን የተፈጥሮ ሀብት እሴት በመጨመር ከፍተኛ ጥቅም እንዲያገኙ” ለማስቻል እንደሚሰሩ ሲገልፁ ይደመጣሉ ።


Share it for more information
👇👇👇👇👇

@AAUNEWS1
#ጥቆማ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ Oral and Maxillofacial Surgery Speciality አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

የምዝገባ ጊዜ፦
ከሚያዝያ 20-24/2017 ዓ.ም በኮሌጁ ሬጅስትራር ቢሮ

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ ከታወቀ የመንግሥት ወይም የግል ተቋም በጥርስ ሀክምና የመጀመሪያ ዲግሪ፣
➫ ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገለ/ች፣
➫ ዕድሜ ከ 45 አመት ያለበለጠ/ች፣
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ።



@AAUNEWS1
AAU NEWS
Photo
#የጤናባለሙያዎችድምጽ

“ መጀመሪያ እየሰራሁ ወደነበረበት ሳቢያን ሆስፒታል ተመልሸ ስራዬን እንድቀጥል ይደረግልኝ ” - የጠቅላላ ሀኪሙ ዶ/ር ሀብታሙ አለሙ
 
“ የዝውውር ዓላማ ክፍት ቦታ ሲኖር ሥራንና ሠራተኞቸን ማገናኘት ነው እንጂ ዝውውር የቅጣት ውጤት አይደለም ” - ማኀበሩ

በድሬዳዋ ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል የጠቅላላ ሀኪም ዶክተር ሀብታሙ አለሙ ደረሰብኝ ላሉት በደል ፍትህ እንዲያሰጣቸው በኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር በኩል በደብዳቤ አቤት ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የአቤቱታ ደብዳቤያቸው ምን ይላል ?

በጠቅላላ ሀኪምነት ከአዲስ  አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ ወዳስተማረቻቸውና ያሳደገቻቸው ድሬዳዋ ከተማ ለሦስት ወራት የነፃ አገልግሎት እንደሰጡ ይገልጻል።

በኋላም በአስተዳደሩ በወጣ ማስታወቂያ ወድድር አልፈው በ2016 ዓ/ም በሆስፒታሉ በትጋትና ከፍተኛ ፍቅር ህብዝን ሲያገለግሉ እንደነበር ያስረዳል።

ከሰሞኑን እንደ ሀገር በተጀመሩ የጤና ባለሙያዎች የመብት ጥያቄዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ በፅሑፍ ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም ሌሎችን በማንቃት ሲሳተፉ የጤና ቢሮው ኃላፊዎች ከዚህ እንዲታቀቡ ቢያስጠነቅቋቸውም የመብት ጥያቄ ማንሳት እንደማያቆሙ ማሳወቃቸውን ይጠቅሳል።

ይህን ባሳወቁ ማግስትም (ማክሰኞ ሚያዚያ 14/2017 ዓ/ም) በተፃፈላቸው ደብዳቤ ጥፋት እንዳለባቸው ተገልጾ የሥራ ቦታ እንዲቀይሩ መደረጋደቸውን ያትታል።

ሀኪሙ ይህንኑ እርምጃ፣ “ ህገ ወጥና ስርዓቱን ያልተከተለ በቂም በቀል የተጻፈ ደብዴቤ አግባብ አለመሆኑ እና የሥም ማጥፋት መሆኑን ” ገልጸው፣ ውሳኔው ተቀልብሶ ሲሰሩበት ወደነበረው ሳቢያን ሆስፒታል እንዲመለሱ እንዲደረግላቸው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበርን በደብዳቤ ጠይቀዋል።

ማኀበሩ ለድሬዳዋ ጤና ቢሮ የጻፈው ደብዳቤስ ምን ይላል ?

ሀኪሙ ወደ ሌላ ጣቢያ እንዲዘዋወሩ መደረጋቸውን ገልጾ፣ “በፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ መሠረት የዝውውር ዋና ዓላማ ክፍት ቦታ ሲኖር ሥራንና ሠራተኞቸን ማገናኘት ነው እንጂ ዝውውር የቅጣት ውጤት አይደለም” ብሏል።

ይሁን እንጂ ለሠራተኛው የውስጥ ዝውውር ምክንያቱ " የዲስፕሊን ችግር " መባሉን ጠቅሶ፣ በሀኪሙ ላይ በመረጃ የተደገፈ የዲሲፕሊን ግድፈት ባለመኖሩ ወደ ስራ ቦታቸው እንዲመለሱ ሲል ቢሮውን ጠይቋል።

(የሀኪሙና የማኅበሩ ደብዳቤዎች ከላይ ተያይዘዋል)



@AAUNEWS1
ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሔዱ የሚያደርግ ሕግ ሊተገብር መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

ሕጉን ወደ መሬት ለማውረድ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች እና ከዘርፉ አመራሮች ጋር ውይይት ለማድረግ ዕቅድ ይዟል፡፡

በሕጉ ዙሪያ ሸገር ኤፍኤም ያነጋገራቸው መምህራን ውሳኔው ጥሩ መሆኑን ገልፀው፤ ሊታዩ የሚገባቸው ሌሎች ነገሮች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

ተማሪዎች አሁን ላይ ክፍል ውስጥ ሞባይል ስልክ ይዘው ሲማሩ ‘’ትምህርታቸው ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ፣ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን መከታተል እንደሚያበዙ" ጠቅሰዋል፡፡

ስልክ መያዛቸው ከትምህርታቸው እንዲናጠቡ እያደረጋቸው መሆኑን ያነሱት መምህራኑ፤ መፅሐፍት እና ጥናት ላይ ከማተኮር ይልቅ ሌሎች ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎች ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ትምህርት ቤቶች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዳሉ ገልፀዋል፡፡ በቂ የመፅሐፍት አቅርቦት፣ የICT ላብ፣ የኮምፒውተር ግብዓቶች እንዲሁም የተለያዩ አጋዥ መፅሐፍት ሊሟሉ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡




@AAUNEWS1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
The wait is over! Culture Day 🇪🇹 is here!
Join us for a day full of color, culture, unity — and pride!

Date: Saturday, May 3, 2025
Time: 5:00 LT
📍 Location: 4 Kilo Campus

Wear your cultural clothes and come celebrate with us.

  All 4 Kilo students are invited — don’t miss this colorful celebration!


📌 Brought to you by Demak Events & 4 Kilo GC Committees