AAU - Muslim Students Union
#ሚሽካት ከበኒ ኢስራኢል ምድር ....ጧሉትና ጃሉት ክፍል 3 አሏህ ሱብሀነ ወተዓላ አንድን ሰው(ህዝብ) አምናለሁ ስላለ ብቻ አይተወውም። ይፈትነዋል። << ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን>>(ሱረቱል ዐንከቡት:2) ኢማን ውድ ነገር ነው —እንደ ወርቅ ነው። የወርቅ ዋጋው የሚታወቀው በእሳት ሲፈተን እንደሆነ ሁሉ የኢማን እውነተኝነትም የሚገለጠው በፈተና ጊዜ…
#ሚሽካት
ከበኒ ኢስራኢል ምድር ....ጧሉትና ጃሉት
የመጨረሻ ክፍል
ጃሉትና ሰራዊቱ ከፊታቸው ቆመዋል። የሚጠብቁት ጊዜ ደርሷል። እነዚህ ጥቂት ሙእሚኖች ወደ ራሳቸው ኃይል አልተመለሱም። ወደ አሏህ ተመለሱ። እንዲህም አሉ፦
<<رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ>>
«ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አንቧቧ፤ ጫማዎቻችንንም አደላድል፤ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን»
የዱዐቸውን ቅደም ተከተል ተመልክቱ—
ትዕግሥት ⟶ ጽናት ⟶ ድል ምክንያቱም ውጪ ያለውን ጠላት ከመጋፈጣቸው በፊት በውስጣቸው ያለውን ፍርሃትና ድክመት መቋቋም ነበረባቸው።
ለአሏህ ተብሎ የተጀመረ መንገድ ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍል ትእግስት ቁልፍ ነው። አላህ እንዳለው ነው
وَكَأَيِّن مِّن نَّبِيٍّ قَاتَلَ مَعَهُ رِبِّيُّونَ كَثِيرٌ فَمَا وَهَنُوا لِمَا أَصَابَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَمَا ضَعُفُوا وَمَا اسْتَكَانُوا ۗ وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ
ከነቢይም ብዙ ሊቃውንት ከርሱ ጋር ኾነው የተዋጉ ብዙ ናቸው፡፡ በአላህም መንገድ ለሚደርስባቸው ነገር አልፈሩም፤ አልደከሙምም፡፡ (ለጠላት) አልተዋረዱምም፡፡ አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡
ኢስላምን ሊረዳ የተነሳ አይርበውም። አይደክመውም። ትንሽ ደከም ብሎ ይህ ስሜት ቢሰማው እንኳን ይታገሳል ይጸናል።
ጦርነቱ ተጀመረ።የአሏህም ድል መጣ።
<<﴿فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ﴾>>
<<በአላህ ፈቃድ አሸነፏቸው፤ ዳውድም ጃሉትን ገደለው።>>
በአሏህ ፈቃድ ሆነ። ማይቻል የመሰለው ተሳካ።
ድፍረታቸው አስፈላጊ ነበር፣
ትእግስታቸው አስፈላጊ ነበር፣ ጥረታቸውም አስፈላጊ ነበር።
ነገር ግን ልባቸው ድሉ በመጨረሻ ከአሏህ እንደሚመጣ ያውቅ ነበር።
ሰበቡን አደረሱ።
ጸኑ።
ፍርሃታቸውን ተቋቋሙ።
ከዚያም አላህ ድልን ሰጣቸው።
ከእነዚያ ጥቂቶች መካከል ዳውድ (ዐ.ሰ) ነበር።
<<ዳውድ ጃሉትን ገደለ።>>(በቀራህ 251)
እዚህ ላይ ታሪኩ ለእኛ አንድ ታላቅ ነገር ያስተምረናል።አንዳንድ ጊዜ አላህ ድሉን የሚያመጣው ሰዎች ከማይጠብቁት ሰው ነው።ዛሬ ማንም የማያውቀው ሰው ነገ ታላቅ ኃላፊነት የሚሸከም ሊሆን ይችላል።በሰዎች ዘንድ ጥቂት የሚመስሉ ሰዎች በአላህ ዘንድ ታላላቅ ሊሆኑ ይችላሉ።ስለዚህ ድልን በቁጥር ብቻ አንለካም።ሰውንም በደረጃው ብቻ አንመዝንም።
የነገንም ነገር በዛሬ ዓይናችን ብቻ መወሰን አይቻለንም።እኔ ምንም አላመጣም ማለትም አያዋጣንም፣የኔ ድርሻ ምንድነው ሚለውን መለየት ነው የሚጠበቅብን፤ብዙ እኔዎች ናቸው እኛ ወደሚለው የሚያድጉት።
ምናልባት ዛሬ ከጃሉት ፊት አልቆምንም።ነገር ግን ብዙ ሙስሊሞች ከራሳቸው ፈተና ፊት ቆመዋል።
አንዳንዶች ግፍን ይጋፈጣሉ።
አንዳንዶች ፍርሃትን ይጋፈጣሉ።
አንዳንዶች ኢማናቸውን ለመጠበቅ ይታገላሉ።
አንዳንዶች ማንም የማያውቀውን ከባድ ትግል በልባቸው ይሸከማሉ።
አንዳንዶችም ብቻቸውን ቢመስላቸውም እውነት ላይ ለመቆም ይሞክራሉ።
እኛም አንዳንድ ጊዜ ችግሩን ተመልክተን፦
“ይህን እንዴት እናልፈዋለን?”
እንላለን።
ከዚያ ቁርአን ወደ እነዚያ ሙእሚኖች ዱዓ ይመልሰናል፦
﴿رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا﴾
“ጌታችን ሆይ፣ ትዕግሥትን በእኛ ላይ አፍስስ፤ እግሮቻችንን አጽና፤ እርዳንም።”
ባለንበት ሁኔታ ውስጥ እኛን እንዲያጠነክረን እንጠይቀዋለን🤲።
ከዚያም የምንጠብቀው ድል በእኛ ኃይል ሳይሆን
بِإِذْنِ اللَّهِ☝️☝️
በአላህ ፈቃድ ይመጣል።
ተፈፀመ
@aaumsu

❤7⚡4🥰3👍1🔥1
#NOTICE
ADDIS ABABA UNIVERSITY
OFFICE OF THE REGISTRAR
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመኝታ አገልግሎት ፈላጊ ተማሪዎች በሙሉ:
የመኖሪያ አድራሻቸው በሸገር ከተማ የሆኑ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ሆነው በከተማዋ ዳርቻ አካባቢ የሚገኙ አዲስና ነባር ተማሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲው ያሉትን የመኖሪያ ክፍሎች አቅም እና ተገኝነት መሠረት በውድድር ለመመደብ የሚያስችል የመኝታ አገልግሎት ማመልከቻ በኦንላይን እንዲያቀርቡ ያስታውቃል።
ስለሆነም የመኝታ አገልግሎቱን መጠቀም የምትፈልጉ ተማሪዎች ከታች በተጠቀሰው ሊንክ በመግባት ማመልከቻችሁን በኦንላይን እንድታስገቡ ያሳውቃል። https://isims2.aau.edu.et/apply/dormitory

👍10❤4
ለፍሬሽ ተማሪዎች!
እንደሚታወቀው አብዛኞቹ ኮሌጆች የአንደኛ ሴሚስተር የትምህርት ክፍለ ጊዜ ይፋ እያደረጉ ይገኛል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ለአመታት ባደረገው ጥረት ከ2 አመት በፊት ጀምሮ በጁሙዓ ዕለት በዩኒቨርሲቲው የሚወጡ ሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች፤ ፈተናዎች፣ ላቦራቶሪዎች እና ሌሎች የመማር ማስተማር ተግባራት ከ05፡30 በፊት እንዲያልቁ እንዲሁም ከሰዓት ከ07፡30 በፊት እንዳይጀመሩ አቅጣጫ የወጣ በመሆኑ፤ ከዚህ መመሪያ በተቃራኒ በመሆን የወጣ ማንኛውም ፕሮግራም ካለባችሁ በ @Aaumuslimstudentsunion1 በፍጥነት እንድታሳውቁ እናሳስባለን።

🔥17👏8❤6👍2🫡2
#الإيمان
تصديق بالقلب، وقولُ باللسان، وعملُ بالجوارح؛
يزيدُ بالطاعة، وينقصُ بالمعاصي والزلّات.
له أركانُه، له نورُه، له طعمُه وحلاوتُه.
فَلْتُحَقِّقِ الأمةُ الإيمانَ،
لِتكونَ أهلًا لنُصرةِ الرحمنِ الرحيم.
🍂Iman is the affirmation of the heart, the declaration of the tongue, and the deeds of the limbs; it increases through obedience and decreases through sins and shortcomings.
It has its pillars, its light, its taste, and its sweetness.
Let the Ummah revive true faith within its hearts, so that it may become worthy of the help and victory of the Most Merciful, the Most Compassionate.

🔥18❤5👏4😍2
AAU - Muslim Students Union
Photo
#من_هم_الذين_ينصرون_الله ؟!
🍂 الذين ينصرون دينَ الله باطنًا بمحبّتِه والخوفِ منه، والصدقِ في طاعتِه، واجتنابِ نواهيه، والوقوفِ عند حدودِه.
🍂 وينصرون دينَ الله ظاهرًا بالأخذِ بالأسبابِ المشروعة، والقيامِ بما أوجب الله، والأمرِ بالمعروفِ والنهيِ عن المنكر.
فمن جمع بين صلاحِ سريرته واستقامةِ علانيته، وأقام أمرَ الله في نفسه، وسعى فيما استطاع في إصلاحِ مجتمعه، كان من أهلِ نصرةِ دينِ الله.
🍃 They are the ones who support the cause of Allah inwardly through love of Him and fear of Him, sincerity in obeying Him, avoiding what He has forbidden, and remaining within His limits.
🍃And they support the cause of Allah outwardly by taking the lawful means, fulfilling what Allah has commanded, enjoining what is good, and forbidding what is wrong.
So whoever combines inner uprightness with outward striving, upholds Allah’s commands in his own life, and strives, within his ability, to bring about good in his community, is among those who uphold and serve the cause of His religion.
@aaumsu
﴿الَّذِينَ إِن مَّكَّنَّاهُمْ فِي الْأَرْضِ أَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ وَأَمَرُوا بِالْمَعْرُوفِ وَنَهَوْا عَنِ الْمُنكَرِ ۗ وَلِلَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ﴾
እነርሱም እነዚያ በምድር ላይ ብናስመቻቸው ሶላትን እንደሚገባ የሚያስተካክሉ፣ ዘካንም የሚሰጡ፣ በደግ ነገርም የሚያዝዙ፣ ከመጥፎ ነገርም የሚከለክሉ ናቸው። የነገሮቹም ሁሉ መጨረሻ ወደ አላህ ነው።
🍂 الذين ينصرون دينَ الله باطنًا بمحبّتِه والخوفِ منه، والصدقِ في طاعتِه، واجتنابِ نواهيه، والوقوفِ عند حدودِه.
🍂 وينصرون دينَ الله ظاهرًا بالأخذِ بالأسبابِ المشروعة، والقيامِ بما أوجب الله، والأمرِ بالمعروفِ والنهيِ عن المنكر.
فمن جمع بين صلاحِ سريرته واستقامةِ علانيته، وأقام أمرَ الله في نفسه، وسعى فيما استطاع في إصلاحِ مجتمعه، كان من أهلِ نصرةِ دينِ الله.
🍃 They are the ones who support the cause of Allah inwardly through love of Him and fear of Him, sincerity in obeying Him, avoiding what He has forbidden, and remaining within His limits.
🍃And they support the cause of Allah outwardly by taking the lawful means, fulfilling what Allah has commanded, enjoining what is good, and forbidding what is wrong.
So whoever combines inner uprightness with outward striving, upholds Allah’s commands in his own life, and strives, within his ability, to bring about good in his community, is among those who uphold and serve the cause of His religion.
@aaumsu
❤14⚡8👍3🔥2👏1
💥ልዩ የዳዕዋ፤ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የትውውቅ ፕሮግራም!
💡ታላላቅ ኡስታዞች እና መሻይኾች ተጋብዘዋል። አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከቀደምቶች ጋር ይተዋወቃሉ። ሕብረቱ ሲሰራው የነበረው እና ሊሰራው ያቀደው ተግባራት ይብራራሉ።
⏳መስከረም 23 / 2019 ዓ.ል !
የሁላችንም ቀጠሮ በታላቁ አል-አቅሷ መስጂድ ይሁን። በአዲሱ አመት፤ ከአዲስ ተማሪዎች ጋር፤ በአዲስ መንፈስ ወደ ተሻለ ደረጃ የምንሸጋገርበት ቀን ይሆናል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት !!

🔥19❤5👍2🥰2👏2💔1
ታላቅ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የዳዕዋ መድረክ በታላቁ አል-አቅሷ መስጂድ !!!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በ2019 ዓ.ል ወደ ጀመዓው የተቀላቀሉ ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት፤ ያለፈውን አመት የስራ ሪፖርት እንዲሁም የዘንድሮውን አመት እቅድ ለማብሰር፤ ከታላላቅ ኡስታዞች እና መሻይኾች ዳዕዋ ምክር እና ትምህርት ለመውሰድ ታላቅ መድረክ አዘጋጅቷል። በእለቱ፦
፨ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል የሙስሊም ተማሪዎች አበርክቶ ምን መሆን እንዳለበት በጥልቅ ያስቀምጡልናል።
፨ ዶክተር ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን በዩኒቨርስቲ ቆይታችን ምን ይዘን መውጣት እንዳለብን ይነግሩናል።
፨ ሸይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጠፋ አለማዊ ትምህርት በእስልምና ስላለው ቦታ ያብራሩልናል።
ቦታ፦ አፍንጮበር፤ አል-አቅሷ መስጂድ
ቀን፦ እለተ ቅዳሜ መስከረም 23 / 2019 ዓ.ል
ሰዓት፦ ከጧቱ 2:30 ጀምሮ
የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች፤ የኮሌጅ እና ሀይስኩል ተማሪዎች፤ የአካባቢው ማህበረሰብ መድረኩ የሁላችሁም ነውና አብረን ደምቀን እንውል ዘንድ ጥሪያችን ነው። የሰማው ላልሰማ ያሰማ! በሕብረት ወደፊት!!!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት !!!

🔥30😡14❤6👏2🫡2😢1👌1
🚙 ጉዞ ነበር…………
አዎን ጉዞ ነበር። ✨ባለፈው የታሪክ ማህደር ውስጥ ራሳችንን እንፈትሽ ዘንድ ፣ቁም ነገር ይዘን በመቀጠልም ከተማርነው ሰንቀን ዛሬ ላይ ስህተት እንዳንሰራና ነገን በተሻለ መልኩ አቅደን እንጓዝ ዘንድ 3 ታሪኮችን አይተናል።
#ሚሽካት
🟢በሰኢድ ኢብኑ ጁበይር ውስጥ ያለውን ለእውነት የመቆም ጽናትንና የነበረውን ጥልቅ ፈተና እውን ከተረዳን በህይወታችን ውስጥ ለውጥ የሚያመጣን የጽናት ውሳኔ ለመወሰን ብዙ አንቸገርም።
🟢ለግፍ ያላጎነበሰው ንጉስ
የራስን ታሪክና ማንነት ማወቅ ይበል የሚያሰኝ በጎ ተግባር ነው። ነጃሺ ፍትህን ባሰፈኑባት እና አሁን ላይ እኔ በተተካሁባት ፡ የኢትዮጵያ ምድር ላይ ምን እየተካሄደ ነው? ከእኔስ ምን ይጠበቃል? ብሎ ማውጠንጠን ደግሞ የብልህ ሰው አካሄድ ነው።
🟢እንማር፣ እንገሰጽ እንዲሁም አስተንትነን እንረዳ ዘንድ ደግሞ ከበኒ ኢስራኢል ምድር የተወሰኑ ገጾችን ወደ ኋላ ተጉዘን አይተናል።
🫴እነሆ ምን ያህል ተገነዘብን? የሚለውን ለመፈተሽ ያመቸን ዘንድ በጥያቄና መልስ ወደ እናንተ ተመልሰን መጥተናል።
#ሚሽካት ጥያቄና መልስ
ካለፉት 3 ታሪኮች ….
💥ምን ተማርን?
💥ምንስ ተረዳን?
💥ሽልማቱስ ምን ይሁን?
⚡️Stay Tuned……..⚡️

👍7🔥4❤3👏2
AAU - Muslim Students Union
🚙 ጉዞ ነበር………… አዎን ጉዞ ነበር። ✨ባለፈው የታሪክ ማህደር ውስጥ ራሳችንን እንፈትሽ ዘንድ ፣ቁም ነገር ይዘን በመቀጠልም ከተማርነው ሰንቀን ዛሬ ላይ ስህተት እንዳንሰራና ነገን በተሻለ መልኩ አቅደን እንጓዝ ዘንድ 3 ታሪኮችን አይተናል። #ሚሽካት 🟢በሰኢድ ኢብኑ ጁበይር ውስጥ ያለውን ለእውነት የመቆም ጽናትንና የነበረውን ጥልቅ ፈተና እውን ከተረዳን በህይወታችን ውስጥ ለውጥ የሚያመጣን የጽናት…
እነሆ እውቀታችንን የምንፈሽትሽበት
#ሚሽካት ጥያቄና መልስ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይለቀቃሉ።
አሸናፊው ማን ይሆን?
እኛስ ጥያቄዎቹን ምን ያህል እንመልሳለን?
ይጠብቁን!🔥🔥
@aaumsu
#ሚሽካት ጥያቄና መልስ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይለቀቃሉ።
አሸናፊው ማን ይሆን?
እኛስ ጥያቄዎቹን ምን ያህል እንመልሳለን?
ይጠብቁን!🔥🔥
@aaumsu
🔥5❤1🥰1
1, በሁለት አመታት ልዩነት የተወለዱት የታላቅ ትምህርት ባለቤት የሆኑት ሰዎች ማን ናቸው ?
ሀ, ሰኢድ ቢን ጁበይር እና ሰኢድ ቢን አብዱልወቃስ
ለ, ኢብኑ አባስ እና ኢብኑ አብዱላህ
ሐ, ሰኢድ ቢን ጁበይር እና ሃጃጅ ቢን ዩሱፍ
መ, አብዱል መሊክ ኢብኑ መርዋን እና አብዱላህ ኢብኑ ዙበይር
2, ሃጃጅ ቢን ዩሱፍ ታቢዒዮችን ማሳደድ ፣ ማሰር እና መግደል ላይ የተጠመደበት ጊዘ ምን በመባል ይታወቃል?
ሀ, ሃርቡል ቁራ
ለ, ፊትነቱል ቁራ
ሐ, ፊትነቱ ሃጃጅ
መ, ሃርቡ ሃጃጅ
3, ሰኢድ ቢን ጁበይር ጨቋኙ ንጉስ ፊት ሊቀርብ እየተጎተተ በሚሄድ ጊዜ እያለቀሰች ስትከተለችው የነበረችው እና ቃልን እንድትልክለት የነገራት ሴት ማን ነበረች?
ሀ, የሰኢድ ብን ጁበይር ወላጅ እናት
ለ, የሰኢድ ብን ጁበይር እህት
ሐ, የሰኢድ ብን ጁበይር ባለቤት
መ, የሰኢድ ብን ጁበይር ሴት ልጅ
4, የሃጃጅ ብን ዩሱፍ የህይወት ፈተና ምን ነበር ?
ሀ, ስልጣን
ለ,ሃላፊነትን በአግባቡ መወጣት
ሐ, የሰኢድ ቢን ጁበይር መወለድ
መ, የአብዱልመሊክ ሹመት
5, ሃጃጅ ቢን ዩሱፍ ሰኢድ ቢን ጁበይርን ካስገደለ በኋላ ምን ሆነ?
ሀ, ስለተበቀለው ደስ አለው
ለ, ለልጁ ካሳ ሰጣት
ሐ, በጣም ተጸጽቶ እና ተቆጭቶ ነበር
መ, ሀ እና ለ
6, እንግዶቹ በመጡ ጊዜ ስለ ኃይላቸው፣ ስለ ብዛታቸው ወይም ለእርሱ ሊያበረክቱት ስለሚችሉት ነገር አንዳችም ጥቅማ ጥቅምን ያልጠየቀ ፍትሃዊ እና ከሰሀቦች መካከል የሆነን ሰው ያሰለሙ ኢትዮጵያዊው ንጉስ ማን ነው ?
ሀ, አል- አስሐመ ቢን አብጀር (ነጃሺ) ረሂመሁላህ
ለ, ኢማም አህመድ አል-ጋዚ
ሐ, ኢማም መህፉዝ
መ, መልስ የለም
7, "እኛ ከሕዝባቸው መሪዎችና ልዑላን እንዲሁም ከአባቶቻቸው፣ ከአጎቶቻቸውና ከቅርብ ዘመዶቻቸው የተላክን ነን ወደ አባቶቻቸው ይመልሷቸው እና ይቀጡ " ያሉ እና ስጦታዎችን ይዘው ወደ ንጉስ ነጃሺ እንዲወስዱ የተላኩት የቁረይሽ ተወካዮች ማን ናቸው?
ሀ, ዐምር ኢብኑል ዓስ እና ዐምር ብን አቢ ረቢዓህ
ለ, ዐብዱላህ ኢብኑል ዓስ እና ዐምር ቢን አቢ ረቢዓህ
ሐ, ዐምር ኢብኑል ዓስ እና ዐብዱላህ ቢን አቢ ረቢዓህ
መ, ዐምር ኢብኑል ዓስ እና ዐብዱላህ ቢን ጃዕፈር
መልሶቻቹን በ @Niqab_issueBot ላኩ

❤7🔥1👌1
🫡5
AAU - Muslim Students Union
1, በሁለት አመታት ልዩነት የተወለዱት የታላቅ ትምህርት ባለቤት የሆኑት ሰዎች ማን ናቸው ? ሀ, ሰኢድ ቢን ጁበይር እና ሰኢድ ቢን አብዱልወቃስ ለ, ኢብኑ አባስ እና ኢብኑ አብዱላህ ሐ, ሰኢድ ቢን ጁበይር እና ሃጃጅ ቢን ዩሱፍ መ, አብዱል መሊክ ኢብኑ መርዋን እና አብዱላህ ኢብኑ ዙበይር 2, ሃጃጅ ቢን ዩሱፍ ታቢዒዮችን ማሳደድ ፣ ማሰር እና መግደል ላይ የተጠመደበት ጊዘ ምን በመባል ይታወቃል?…
የጥያቄዎቹ መልሶች!
1. ሐ፡ ሰኢድ ቢን ጁበይር እና ሃጃጅ ቢን ዩሱፍ
ሰኢድ ቢን ጁበይር رحمه الله ከታላላቅ ታቢዒዮች እና የዒልም ባለቤቶች ነበሩ። ሃጃጅ ቢን ዩሱፍ ደግሞ በዚያን ዘመን በስልጣኑና በጭካኔው የታወቀ ገዥ ነበር። በሁለቱ መካከል ያለው የእድሜ ልዩነት 2 አመታት አካባቢ ነበር።
2. ለ፡ ፊትነቱል ቁራ
ሃጃጅ ቢን ዩሱፍ በኢብኑ ዙበይር ዘመን እና ከዚያ በኋላ የተለያዩ ታቢዒዮችንና እርሱን የተቃዎሙ አካላትን በመከታተል፣ በማሰርና በመቅጣት ያሳለፈበት ዘመን እንዲሁም ይህን በመቃወም በእርሱ ላይ አብዱረህማን ኢብን አል-አሽዓስ እና ወታደሮቹ የወጡበት ዘመን ፊትነቱል ቁራእ በመባል ይታወቃል
3. መ፡ የሰኢድ ቢን ጁበይር ሴት ልጅ
ሰኢድ ቢን ጁበይር رحمه الله ወደ ሃጃጅ ሲወሰዱ ቤተሰቦቻቸው በእጅጉ አዘኑ። ሴት ልጃቸውም እያለቀሰች ስትከተለው ነበር።
4. ሀ፡ የሃጃጅ ቢን ዩሱፍ የሕይወት ፈተና - ስልጣን
የሃጃጅ ታሪክ ሲታይ ስልጣን ከተሰጠው በኋላ ያንን ስልጣን እንዴት የተጠቀመበት መንገድ ትልቁ የሕይወቱ ፈተና እንደሆነ እንረዳለን። ስልጣን ራሱ ችግር ባይሆንምል ሰው ስልጣንን በፍትሕ ወይም በግፍ መጠቀሙ ግን ስልጣኑ ለሰውዬው ፈተና ወይም የበረከት ምንጭ እንዲሁን ያደርገዋል።
5. ሐ
ሰኢድ ቢን ጁበይር رحمه الله ከተገደሉ በኋላ ሃጃጅ በጣም እንደተጸጸተና እንደተቆጨ በታሪካዊ ዘገባዎች ይጠቀሳል። ይህም የሰኢድ ቢን ጁበይር رحمه الله ቦታና በሰዎች ዘንድ የነበራቸውን ክብር ያሳያል።
6. ሀ፤ አል-ነጃሺ፤ እንግዶቹን በፍትሕ የተቀበለው ኢትዮጵያዊ ንጉስ
አል-ነጃሺ رحمه الله ሙስሊሞች ወደ ሐበሻ ሲሰደዱ የተቀበላቸው ፍትሓዊ ንጉስ ነበር። ቁረይሾች ሙስሊሞቹን እንዲመልስ የስጦታ መዓት ይዘው በመምጣት ሊገፋፉት ቢሞክሩም ሁለቱንም ወገኖች አዳምጦ በፍትሕ የወሰነ ፍትሓዊ መሪ ነበር።
7. ሐ፤ ዐምር ኢብኑል ዓስ እና ዐብዱላህ ቢን አቢ ረቢዓህ
ቁረይሾች ሙስሊሞች ወደ ሐበሻ ከተሰደዱ በኋላ እነርሱን ለማስመለስ ሁለት ተወካዮችን ወደ ሓበሻ ልከው ነበር። እነሱም ዐምር ቢን አል-ዓስ እና ዐብዱላህ ቢን አቢ ረቢዓህ ነበሩ። ከነጃሺ ፊት ቀርበውም ሙስሊሞቹን ወደ መካ እንዲመልስ ቢጠይቁም ነጃሺ ግን ሁለቱንም ወገኖች ሳይሰማ ውሳኔ እንደማያስልፍ ገልጾ የሙስሊሞቹን በኩል ከሰማ በኃላ የቁረይሽ ተወካዮች በባዱ መልሷቸዋል።
የዛሬው ጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊወንድማችን ተባረክ ከ6 ኪሎ ካምፓስ ሆኗል። ወንድማችን እንኳን ደስ ያለህ! ሽልማቱ የሚደርሰው ይሆናል ኢንሻላህ!
ሁላችሁም እንደተጠቀማችሁበት ተስፋ እናደርጋለን፤ በቀጣይም በተመሳሳይ መድረኮች የምንመለስ ይሆናል ኢንሻላህ!

የዛሬው ጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊ

🔥12👏6❤2