AAU - Muslim Students Union
AAU Muslim Students Union – ሕያው ምስክር
የምስጋና እና አክብሮት መልዕክት ከቀድሞ የጅማ ዩኒቨርሲቲ (አግሪ ግቢ) አሚር አብዲ ኮርማ የተላለፈ ፦
በቅድሚያ ለሁላችሁም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። በአላህ ፈቃድ በግልም ሆነ በህብረት ለሰራችሁት ትልቅ ስራ፣ በተለይም ደግሞ ሌሎች ሰዎችን በማነቃቃት እና በማበረታታት በኩል ለነበራችሁ ሚና የከበረ ምስጋና እና አክብሮት አለኝ። አላህ በቀጣይም ለሌሎች ችግሮች መፍትሔ እንዲያደርጋችሁ እመኛለሁ።
በ 2016/17 ዓ.ል በነበረው ፈታኝ ወቅት፣ በቀንም ሆነ በሌሊት የ 24 ሰዓት መረጃዎችን እና ጥሪዎችን በመለዋወጥ፣ ምክር እና ድጋፍ በመስጠት አብራችሁን ስትታገሉ ነበር። ምስጋና ከሁሉም በላይ ለሆነው ለአላህ ይሁን፤ ከእሱ በመቀጠል ግን እናንተ መንገድ በማሳየት እና በመደገፍ ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ትልቅ ክብር ይገባችኋል። ውጤት የሚመጣው እንዲህ አይነት አንድነት እና ድምር ጥረት ሲኖር ነው!
በተለይም በወቅቱ በተማሪዎች ግሩፕ ውስጥ የነበሩ አባላት ያሳዩት ትልቅ አንድነት የሚደነቅ ነበር። ያንን ውስብስብ ሁኔታ ለመፍታት ከ Remedial እስከ GC ተማሪዎች ድረስ ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ እህቶችም ጭምር እጅ ለእጅ ተያይዘው ትልቅ እገዛ አድርገዋል።
በዚህ አጋጣሚ ለሰራችሁት ሁሉ ጀዛኩሙላሁ አህሰነል ጀዛእ እያልኩኝ፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት (AAU MSU)፤ እና ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ለሆኑት ወንድማችን ሙሀመድ አሚን ካሳው በወቅቱ ላሳዩት የስራ አመራር፣ ላደረጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ እና አብሮነት የላቀ ምስጋናዬን እና አክብሮቴን ማቅረብ እወዳለሁ።
በመጨረሻም፣ ይህ አዎንታዊ ተሞክሮ እና ህብረት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና አብረን መስራት እንድንችል መልእክቴን አስተላልፋለሁ። ጠንክሩ!
@aaumsu

❤10🔥6👏1
AAU - Muslim Students Union
AAU Muslim Students Union – ሕያው ምስክር
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ያስተላለፋት መልዕክት:
አሰላም አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ
ቢስሚላህ በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ በመገኘት ወንድም ሱደይስ፣ አብዲ ኮርማ፣ አብሮን ሊታደም ያልቻለውን ዶ/ር አብዱሰላምን ጨምሮ፣ እንዲሁም መላው ተሳታፊ ወንድም እና እህቶች በአላህ ስም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።
በመቀጠል እኛ እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጀመዓ እና ተማሪዎቻችን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጀመዓ ያለፈ ( ከኮሮና ጀምሮ እስከ ረመዳን 2017) የትግል ጉዞ ብዙ የወሰድናቸው ትምህርቶች አሉ። ከዛም መካከል አንድ የወንድማችን ንግግር ማስታወስ እወዳለሁ፡
ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር): "ችግር ሲመጣ ሌላ የሚፈታ አካል እንዲመጣ መፈለግ ሳይሆን "እኔ አለሁለት!" የሚል አቋም ሊኖራችሁ ይገባል።" የሚለው ምክራቸው ሁላችንም ልብ ውስጥ ተቀምጧል ብዬ አስባለሁ።
አጠቃላይ በእንቅስቃሴያቸው ውስጥ የነበረው ጥንካሬ እና ህብረት እጅግ የሚያስደንቅ ነው። በአላህ ፈቃድ ትግል ካለ ድል እንደሚመጣ ህያው መስክር ሆኖ ቀርቦልናል።
ይህንን ተከትሎ ጀመዓችን ወይም አአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ጅማ ላይ ጀግንነት እና ቁርጠኝነት ባሳዩት ወንድም እና እህቶች እንዲሁም በጀማአቸው ስም ስጦታ ማበርከት ይፈልጋል። ስጦታውንም በአዲሱ ዓመት መግቢያ ፕሮግራም ላይ አሚሮች መጥተው ይቀበሉ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ሙሐመድ ኢድሪስ
ፕሬዝዳንት

❤17🔥5👏5🫡1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቦሌ ቡልቡላ ከሚገኘው አንሷር መስጂድ ከተላለፈ የኹጥባ መልዕክት፦
በቅርብ ቀናት ውስጥ የሚገኙት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተለይም ምክንያቶች ሃይማኖታቸውን፣ የሃይማኖታቸውን ድንጋጌ እንዳይስፋፋ የሚገፉ፣ ከትምህርት ማዕከል ራሳቸውንም፣ ቤተሰቦቻቸውንም ሃገራቸውን እንዳይመጥኑ ከሚያደርጉት ጥረት፣ ከሚያደነቃፏቸው አካላት አላህ ሱብሃነ ወተዓላ እንዳያግዛቸው በምንችለው ነገር ሁሉ በሃሳባችን፣ በምክራችን እንዲሁም በዱዓችን እነሱን ማገዝ ይገባናል። ይህ በእኛ ላይ ትንሹ ግዴታ ነው።

❤26👌9
ደጋግሜ ብየዋለሁ የሆነ ተቋም መብታችሁን ቢነፍግና ቢከለክል ምን ልታደርጉ ነው? ልትሸሹ?! ልትተዉ?! ሌላ ቦታ፤ ሌላ ሀገር፤ ሌላ ተቋም፤ ሌላ ዩኒቨርስቲ ልትፈልጉ?!!!! አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኒቃብ ይከለክላል ወይ? ኒቃብ የማይከለከልበት ዩኒቨርስቲ የቱ ነው? ሶላትስ? ጀለብያስ? ቁርዓንስ? ሌላም ሌላም እያሉ የሚጠይቁ ብዙ ናቸው። የእኔ ጥያቄ ደግሞ ከላይ እንዳልኩት እዚህ ስለተከለከለ ጅቡቲ ወይንም ሴኔጋል ሄዳችሁ ልትማሩ ነው?!
ሰዎች፦ ኢትዮጵያኮ ሀገራችሁ ናት። እነዚህም ተቋማት በእናንተ ግብር እና ላብ የተገነቡ ናቸው። ሌላው ቢቀር በበደል ላይ እንዲዘወተር ስላደረጋችሁ በአላህ ፊት እንጠየቃለን ብላችሁ አታስቡም?! እስልምና ደግሞ ሀይማኖታችሁ ነው። በር ላይ ጥለነው የምንገባው ሀይማኖት አይደለም። እንድንኖረው ነው የታዘዝነው። እንኖረዋለንም።
ቀደምቶች ባደረጉት ትግል አሁን ላይ ያለው ሁኔታ የተሻለ ቢሆንም አሁን ያለው ሁኔታ እንዲፀና፤ የተሻለ ጊዜም እንዲመጣ መትጋት ግዴታችሁ ነው። ያለፈው ትውልድ የከፈለው ዋጋ ለእናንተ አማና ነው። ቀጣዩ ትውልድ በተሻለ ይኖር ዘንድ ደግሞ እናንተም አማና አለባችሁ። በዚያ ልክ አስቡ። ሁላችንም መንገደኞች ነው። የዚህ አለም ሰዎች አይደለንም። ያማረች ዱንያን ሰርተን እናልፍ ዘንድ እናልም።
©️

👏24🔥8❤5💯2🫡2
AAU - Muslim Students Union
Don't forget to bring A4 size paper and pencil for the consultation. 🔖Thursday Sep 17, morning at 3:00 LT.
If you lost the location or training place, you can call to:
0956053643
■ They are waiting for you to come up!!
0956053643
■ They are waiting for you to come up!!
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:-
በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን። ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን። እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለማስተናገድ ዝግጅቱን አጠናቋል። ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን።
📌 AAU MUSLIM STUDENTS UNION - 0909524252
Main and FBE Campus
📌 አሊፍ ሓጂ - Main Campus - 0955942642
AAiT (5 Kilo) Campus
📌 ሙሐመድ አብራር - AAIT - 0953442423
4 Kilo Campus
📌 አይመን ሙሐመድ - 4kilo - 0977207747
Sefere Selam Campus
📌 አብዱልዓዚዝ ዩሱፍ - s.selam campus - 0951907014
Ldeta Campus
📌 አብዱልዓዚዝ ጁማቶ - Ldeta Campus - 0961497962
Tikur Anbessa Campus
📌 አይመን ሚፍታህ - Tikur Anbessa Campus -
0977777095
Bishoftu Campus
📌 መነልከሪም አብዱልጀባር - Bishoftu Campus -
0917962262
📌 የትኛውንም ካምፓስ የሚመለከት ጥያቄ፡ 0909524252 ወይም @Aaumuslimstudentsunion1
https://t.me/aaumsu

Telegram
AAU - Muslim Students Union
This is the official channel of AAU-MSU.
Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303
Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com

🥰12❤9👍1
ወደ ዩኒቨርሲቲ ለምትገቡ አዲስ ተማሪዎች፦
ከላይ የተቀመጠው መረጃ የየዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎችን መረጃ የያዘ ሲሆን በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ስለ ዩኒቨርስቲዎቹ፤ ጀመዓዎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች መጠየቅ ትችላላችሁ።
አላህ ለስኬት መሠረት የሆነን ቆይታ ያድላችሁ።
©EHEMSU

❤17🔥6👍2👏1
ትምህርት ቅንጦት አይደለም
~
ያ ኡመተል ኢስላም! ልጆችህን ትምህርት አስተምር። ካልሆነ ግን በገዛ ምድርህ ባይተዋር ትሆናለህ። ካልሆነ ግን ሌላው በተቋም እና በመዋቅር ሲዋጋህ አንተ በለቅሶ ነው የምትከላከለው። ካልሆነ ግን በገዛ ቀየህ ላይ "የእስላም አገሩ መካ፣ የአሞራ አገሩ ዋርካ" ይተረትብሃል። ካልሆነ ግን ግብር የምትከፍልበት ተቋም የምትወገርበት ዱላ ይሆናል። ካልሆነ ግን ለሚደርስብህ መድሎና መገለል ምላሽህ ለቅሶ ብቻ ይሆናል። ካልሆነ ግን መብትህን የምታገኘው ሌሎች ሰፍረው ለክተው በሚሰጡህ መጠን ብቻ ይሆናል። ካልሆነ ግን በአስተማሪነት፣ በሰራተኝነት በሚመጡ አካላት በገዛ ቀየህ ላይ የባህል ወረራ ይፈፀምብሃል። ማንነትህ ይደባለቃል።
አለመማር አንድምታው ብዙ ነው። አላስተምርም ካልክ ሚሽነሪ ገብቶ ልጆችህን በትምህርትና በጤና አገልግሎት ስም ይወስድልሃል። እነ ላጲሶ የሚሸነሪ ሰለባዎች ናቸው። አላስተምርም ካልክ ሴረኛ ፖሊሲዎችና ደንቦች እየተረቀቁ ከንግዱ ሴክተር ሳይቀር በካልቾ ትባረራለህ። አላስተምርም ካልክ ታሪክህን እያወላገደ፣ እምነትህን እያንጋደደ ለሚያጠለሽ አካል ቦታውን ትለቃለህ። አለመማር በጤናው፣ በፀጥታው፣ በአስተዳደሩ፣ ... ሴክተር የሚኖረው ክፍተት ከምናስበው በጣም የራቀ ነው። በዚህ ዘመን በስልኩ የተላከለትን መልእክት የማያነብ፣ የሰፈሩ አጥር ላይ የተለጠፈን ማሳሰቢያ የማያውቅ፣ ባንክ ቤት ገብቶ ስሙን መፃፍ አቅቶት ሰው የሚጠብቅ ወጣት ማፍራት እጅግ አደገኛ ነገር ነው። አስተምር ልጆችህን። በትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ችግሮችን ልጆችህን በማራቅ አትፈታቸውም። አንተ ራስህን ካራቅክላቸው በኋላ ላንተ በመቆርቆር ምቹ ከባቢ አደላድለው ይጠሩኛል ብለህ እንዳትጠብቅ። ይልቁንም እየተማርክ፣ እያስተማርክ ታገል። ጎን በጎን ክፍተቶችን በራስህ በቤትህ ወይም ተደራጅተህ ሙላ። ብታስተምር ይሻልሃል!
ልጆችህን አስተምር። በተለያዩ የዓለም ጫፎች የምንሰማቸው ሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ግፎች አንዱ ምክንያታቸው የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን እና ጠላትን መገዳደር የሚያስችሉ ዘመኑን የዋጁ የጦር መሳሪያዎችን ማምረት ላይ ስለሌለን ነው። እነዚህ ቴክኖሎጂዎችና የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎች ደግሞ የዘመናዊ ትምህርት ውጤቶች ናቸው። ጠላት እጅግ አውዳሚና ጅምላ ጨራሽ፣ አህጉር አቋራጭ መሳሪያ እስከ አፍንጫው ታጥቆ ሳለ አንተ በኮንትሮባንድ ያገኘኸውን ጥቂት ክላሽንኮቭ ይዘህ እንገጅ እንገጅ ብትል ውጤቱ የትም የማይደርስ ሰሞንኛ መፈራገጥ ብቻ ነው የሚሆነው።
ባጭሩ ስለ ትምህርት ሲወራ ስለ ቅጥር እንጀራ ብቻ አናስብ። የመማር ትርጉሙ ከዚያ ያለፈ ነው። ስለ ትምህርት ሲወራ ከአንድ ከሁለት አቅጣጫ ብቻ መመልከት አይገባም። መማርም፣ አለመማርም ተጽእኗቸው መልኩም አይነቱም ብዙ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ አካባቢያችን፣ ወገናችን ከሌሎች በትምህርት ወደ ኋላ እንዳይቀር እንዴት የተሻለ ስራ እንስራ በሚል ልንመካከር በሚገባን ጊዜ ከፊሉ ገና የመማርን አስፈላጊነትና ያለመማርን አደጋ ለመረዳት ማገዶ እየፈጀ ነው ያለው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 10/2017)

👏21❤11👍5🔥2👌2😭2🤝1
AAU - Muslim Students Union
#ሚሽካት ከበኒ ኢስራኢል ምድር ....ጧሉትና ጃሉት ክፍል 2 የኢስራኢል ልጆች ለነብያቸው በአላህ መንገድ እንደሚዋጉ ቃል ቢገቡም ፈተናው በእውነት ሲመጣ ግን በዚያ ቃል መጽናት አልቻሉም። <<فَلَمَّا كُتِبَ عَلَيْهِمُ الْقِتَالُ تَوَلَّوْا إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِالظَّالِمِينَ>> <<በእነርሱ ላይ መዋጋት…
#ሚሽካት
ከበኒ ኢስራኢል ምድር ....ጧሉትና ጃሉት
ክፍል 3
አሏህ ሱብሀነ ወተዓላ አንድን ሰው(ህዝብ) አምናለሁ ስላለ ብቻ አይተወውም። ይፈትነዋል።
<< ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን>>(ሱረቱል ዐንከቡት:2)
ኢማን ውድ ነገር ነው —እንደ ወርቅ ነው። የወርቅ ዋጋው የሚታወቀው በእሳት ሲፈተን እንደሆነ ሁሉ የኢማን እውነተኝነትም የሚገለጠው በፈተና ጊዜ ነው።
ጧሉት ሰራዊቱን ይዞ ወደ ጠላታቸው ተነስቷል። ምናልባት ብዙዎቹ ፈተናው ጃሉትን ሲገናኙ እንደሆነ አስበዋል። ነገር ግን አሏህ ከጦርነት በፊት ሌላ ፈተናን አዘጋጅቶላቸዋል—ወንዙን —ጣሉትም፦አላህ በወንዝ ይፈትናችኋል፣ ከእርሱ የጠጣ ሰው ከእኔ አይደለም ያልቀመሰው፣ በእጁ መዝገንን የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው አላቸው።አሁን የተጠየቁት ሰይፍ ማንሳት አልነበረም። ራሳቸውን መቆጣጠር ብቻ ከወንዙ አለመጠጣት።
አብዝሀኞቹ ጠጡ ያጧሉትን ትእዛዝ የጠበቁቶ ጥቂቶች ብቻ ነበሩ። ሰራዊቱ ቁጥሩ በእጅጉ ቀነሷል አሁን የቀሩት ፈተናውን ያለፉት ብቻ ናቸው። ሌላ ፈተና ደግሞ መጣ.... ጃሉትና ብዙሃኑ ሰራዊቱ የጠላት ብዛት አዩ፤የራሳቸውንም ጥቂትነት ተመለከቱ ።
ከፊሎችም በጃሉትና ሰራዊቱ ላይ አቅም እንደሌላቸው አሰቡ።
<<قَالُوا لَا طَاقَةَ لَنَا الْيَوْمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِ>>
«ጃሉትንና ሠራዊቱን በመዋጋት ለኛ ዛሬ ችሎታ የለንም» አሉት፡፡
እነዚያ በእምነታቸው የጸኑት፣ ጌታቸውንም እንደሚገናኙ የጠረጠሩት ሁኔታውን በሌላ መንገድ ነበር ያዩት።ምላሻቸው እንዲህ ነበር፦
<<كَم مِّن فِئَةٍ قَلِيلَةٍ غَلَبَتْ فِئَةً كَثِيرَةً بِإِذْنِ اللَّهِ وَاللَّهُ مَعَ الصَّابِرِينَ >>
«ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህም ከታጋሾች ጋር ነው»
ጉዳዩ ስንት ነን አይደለም! አሏህ ከማን ጋር ነው!?የሚለው ነው።
ሀቅ ላይ ነን? ተበድለናል?ተገፍተናል?ትክክለኛ መመካትን በአሏህ ላይ ተመክተናል?በቃቃቃቃ አብሽሩ
إن الله معنا
ይህ ነው የአማኝ መለያ የብዛቱ ማነስ አያስፈራውም
ምነኛ ያማረ ንግግር ነው??
የአሏህ መልክተኛ: ከልብ ጓደኛቸው ጋር ዋሻ ውስጥ ሆነው በዛ አጣብቂኝ ሊያበቃላቸው በሚመስል ሁኔታ ላይ አትዘን አሏህ ከኛ ጋር ነው ሲሉት
ምነኛ ያማረ ንግግር ነው??
ኢብራሂም:እሳት ፊት ሆኖ ጌታዬ በቂ ነው ሲል
ምነኛ ያማረ ንግግር ነው??
ሙሳ: ተከታዮቹ አለቀልን ባሉት ጊዜ ጌታዬ ከኔ ጋር ነው ሲል
ምነኛ ያማረ ንግግር ነው??
ሀጀራ: በዚያ በረሃ አሏህ አይተውኝም ስትል
ያ ኡመተ መሀመድ!!ፅናታችን፣ኢማናችን፣በአሏህ ላይ ያለን እምነት እንጂ ቁጥራችን ነፃ አያወጣንም!።
ይቀጥላል .....

❤20🔥4
AAU - Muslim Students Union
#ሚሽካት ከበኒ ኢስራኢል ምድር ....ጧሉትና ጃሉት ክፍል 3 አሏህ ሱብሀነ ወተዓላ አንድን ሰው(ህዝብ) አምናለሁ ስላለ ብቻ አይተወውም። ይፈትነዋል። << ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን>>(ሱረቱል ዐንከቡት:2) ኢማን ውድ ነገር ነው —እንደ ወርቅ ነው። የወርቅ ዋጋው የሚታወቀው በእሳት ሲፈተን እንደሆነ ሁሉ የኢማን እውነተኝነትም የሚገለጠው በፈተና ጊዜ…
#ሚሽካት
ከበኒ ኢስራኢል ምድር ....ጧሉትና ጃሉት
የመጨረሻ ክፍል
ጃሉትና ሰራዊቱ ከፊታቸው ቆመዋል። የሚጠብቁት ጊዜ ደርሷል። እነዚህ ጥቂት ሙእሚኖች ወደ ራሳቸው ኃይል አልተመለሱም። ወደ አሏህ ተመለሱ። እንዲህም አሉ፦
<<رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ>>
«ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አንቧቧ፤ ጫማዎቻችንንም አደላድል፤ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን»
የዱዐቸውን ቅደም ተከተል ተመልክቱ—
ትዕግሥት ⟶ ጽናት ⟶ ድል ምክንያቱም ውጪ ያለውን ጠላት ከመጋፈጣቸው በፊት በውስጣቸው ያለውን ፍርሃትና ድክመት መቋቋም ነበረባቸው።
ለአሏህ ተብሎ የተጀመረ መንገድ ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍል ትእግስት ቁልፍ ነው። አላህ እንዳለው ነው
وَكَأَيِّن مِّن نَّبِيٍّ قَاتَلَ مَعَهُ رِبِّيُّونَ كَثِيرٌ فَمَا وَهَنُوا لِمَا أَصَابَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَمَا ضَعُفُوا وَمَا اسْتَكَانُوا ۗ وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ
ከነቢይም ብዙ ሊቃውንት ከርሱ ጋር ኾነው የተዋጉ ብዙ ናቸው፡፡ በአላህም መንገድ ለሚደርስባቸው ነገር አልፈሩም፤ አልደከሙምም፡፡ (ለጠላት) አልተዋረዱምም፡፡ አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡
ኢስላምን ሊረዳ የተነሳ አይርበውም። አይደክመውም። ትንሽ ደከም ብሎ ይህ ስሜት ቢሰማው እንኳን ይታገሳል ይጸናል።
ጦርነቱ ተጀመረ።የአሏህም ድል መጣ።
<<﴿فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ﴾>>
<<በአላህ ፈቃድ አሸነፏቸው፤ ዳውድም ጃሉትን ገደለው።>>
በአሏህ ፈቃድ ሆነ። ማይቻል የመሰለው ተሳካ።
ድፍረታቸው አስፈላጊ ነበር፣
ትእግስታቸው አስፈላጊ ነበር፣ ጥረታቸውም አስፈላጊ ነበር።
ነገር ግን ልባቸው ድሉ በመጨረሻ ከአሏህ እንደሚመጣ ያውቅ ነበር።
ሰበቡን አደረሱ።
ጸኑ።
ፍርሃታቸውን ተቋቋሙ።
ከዚያም አላህ ድልን ሰጣቸው።
ከእነዚያ ጥቂቶች መካከል ዳውድ (ዐ.ሰ) ነበር።
<<ዳውድ ጃሉትን ገደለ።>>(በቀራህ 251)
እዚህ ላይ ታሪኩ ለእኛ አንድ ታላቅ ነገር ያስተምረናል።አንዳንድ ጊዜ አላህ ድሉን የሚያመጣው ሰዎች ከማይጠብቁት ሰው ነው።ዛሬ ማንም የማያውቀው ሰው ነገ ታላቅ ኃላፊነት የሚሸከም ሊሆን ይችላል።በሰዎች ዘንድ ጥቂት የሚመስሉ ሰዎች በአላህ ዘንድ ታላላቅ ሊሆኑ ይችላሉ።ስለዚህ ድልን በቁጥር ብቻ አንለካም።ሰውንም በደረጃው ብቻ አንመዝንም።
የነገንም ነገር በዛሬ ዓይናችን ብቻ መወሰን አይቻለንም።እኔ ምንም አላመጣም ማለትም አያዋጣንም፣የኔ ድርሻ ምንድነው ሚለውን መለየት ነው የሚጠበቅብን፤ብዙ እኔዎች ናቸው እኛ ወደሚለው የሚያድጉት።
ምናልባት ዛሬ ከጃሉት ፊት አልቆምንም።ነገር ግን ብዙ ሙስሊሞች ከራሳቸው ፈተና ፊት ቆመዋል።
አንዳንዶች ግፍን ይጋፈጣሉ።
አንዳንዶች ፍርሃትን ይጋፈጣሉ።
አንዳንዶች ኢማናቸውን ለመጠበቅ ይታገላሉ።
አንዳንዶች ማንም የማያውቀውን ከባድ ትግል በልባቸው ይሸከማሉ።
አንዳንዶችም ብቻቸውን ቢመስላቸውም እውነት ላይ ለመቆም ይሞክራሉ።
እኛም አንዳንድ ጊዜ ችግሩን ተመልክተን፦
“ይህን እንዴት እናልፈዋለን?”
እንላለን።
ከዚያ ቁርአን ወደ እነዚያ ሙእሚኖች ዱዓ ይመልሰናል፦
﴿رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا﴾
“ጌታችን ሆይ፣ ትዕግሥትን በእኛ ላይ አፍስስ፤ እግሮቻችንን አጽና፤ እርዳንም።”
ባለንበት ሁኔታ ውስጥ እኛን እንዲያጠነክረን እንጠይቀዋለን🤲።
ከዚያም የምንጠብቀው ድል በእኛ ኃይል ሳይሆን
بِإِذْنِ اللَّهِ☝️☝️
በአላህ ፈቃድ ይመጣል።
ተፈፀመ

❤6⚡4🥰3👍1🔥1
#NOTICE
ADDIS ABABA UNIVERSITY
OFFICE OF THE REGISTRAR
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመኝታ አገልግሎት ፈላጊ ተማሪዎች በሙሉ:
የመኖሪያ አድራሻቸው በሸገር ከተማ የሆኑ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ሆነው በከተማዋ ዳርቻ አካባቢ የሚገኙ አዲስና ነባር ተማሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲው ያሉትን የመኖሪያ ክፍሎች አቅም እና ተገኝነት መሠረት በውድድር ለመመደብ የሚያስችል የመኝታ አገልግሎት ማመልከቻ በኦንላይን እንዲያቀርቡ ያስታውቃል።
ስለሆነም የመኝታ አገልግሎቱን መጠቀም የምትፈልጉ ተማሪዎች ከታች በተጠቀሰው ሊንክ በመግባት ማመልከቻችሁን በኦንላይን እንድታስገቡ ያሳውቃል። https://isims2.aau.edu.et/apply/dormitory

👍10❤4
ለፍሬሽ ተማሪዎች!
እንደሚታወቀው አብዛኞቹ ኮሌጆች የአንደኛ ሴሚስተር የትምህርት ክፍለ ጊዜ ይፋ እያደረጉ ይገኛል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ለአመታት ባደረገው ጥረት ከ2 አመት በፊት ጀምሮ በጁሙዓ ዕለት በዩኒቨርሲቲው የሚወጡ ሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች፤ ፈተናዎች፣ ላቦራቶሪዎች እና ሌሎች የመማር ማስተማር ተግባራት ከ05፡30 በፊት እንዲያልቁ እንዲሁም ከሰዓት ከ07፡30 በፊት እንዳይጀመሩ አቅጣጫ የወጣ በመሆኑ፤ ከዚህ መመሪያ በተቃራኒ በመሆን የወጣ ማንኛውም ፕሮግራም ካለባችሁ በ @Aaumuslimstudentsunion1 በፍጥነት እንድታሳውቁ እናሳስባለን።

🔥17👏8❤6👍2🫡2
#الإيمان
تصديق بالقلب، وقولُ باللسان، وعملُ بالجوارح؛
يزيدُ بالطاعة، وينقصُ بالمعاصي والزلّات.
له أركانُه، له نورُه، له طعمُه وحلاوتُه.
فَلْتُحَقِّقِ الأمةُ الإيمانَ،
لِتكونَ أهلًا لنُصرةِ الرحمنِ الرحيم.
🍂Iman is the affirmation of the heart, the declaration of the tongue, and the deeds of the limbs; it increases through obedience and decreases through sins and shortcomings.
It has its pillars, its light, its taste, and its sweetness.
Let the Ummah revive true faith within its hearts, so that it may become worthy of the help and victory of the Most Merciful, the Most Compassionate.

🔥18❤5👏3😍2
AAU - Muslim Students Union
Photo
#من_هم_الذين_ينصرون_الله ؟!
🍂 الذين ينصرون دينَ الله باطنًا بمحبّتِه والخوفِ منه، والصدقِ في طاعتِه، واجتنابِ نواهيه، والوقوفِ عند حدودِه.
🍂 وينصرون دينَ الله ظاهرًا بالأخذِ بالأسبابِ المشروعة، والقيامِ بما أوجب الله، والأمرِ بالمعروفِ والنهيِ عن المنكر.
فمن جمع بين صلاحِ سريرته واستقامةِ علانيته، وأقام أمرَ الله في نفسه، وسعى فيما استطاع في إصلاحِ مجتمعه، كان من أهلِ نصرةِ دينِ الله.
🍃 They are the ones who support the cause of Allah inwardly through love of Him and fear of Him, sincerity in obeying Him, avoiding what He has forbidden, and remaining within His limits.
🍃And they support the cause of Allah outwardly by taking the lawful means, fulfilling what Allah has commanded, enjoining what is good, and forbidding what is wrong.
So whoever combines inner uprightness with outward striving, upholds Allah’s commands in his own life, and strives, within his ability, to bring about good in his community, is among those who uphold and serve the cause of His religion.
@aaumsu
﴿الَّذِينَ إِن مَّكَّنَّاهُمْ فِي الْأَرْضِ أَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ وَأَمَرُوا بِالْمَعْرُوفِ وَنَهَوْا عَنِ الْمُنكَرِ ۗ وَلِلَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ﴾
እነርሱም እነዚያ በምድር ላይ ብናስመቻቸው ሶላትን እንደሚገባ የሚያስተካክሉ፣ ዘካንም የሚሰጡ፣ በደግ ነገርም የሚያዝዙ፣ ከመጥፎ ነገርም የሚከለክሉ ናቸው። የነገሮቹም ሁሉ መጨረሻ ወደ አላህ ነው።
🍂 الذين ينصرون دينَ الله باطنًا بمحبّتِه والخوفِ منه، والصدقِ في طاعتِه، واجتنابِ نواهيه، والوقوفِ عند حدودِه.
🍂 وينصرون دينَ الله ظاهرًا بالأخذِ بالأسبابِ المشروعة، والقيامِ بما أوجب الله، والأمرِ بالمعروفِ والنهيِ عن المنكر.
فمن جمع بين صلاحِ سريرته واستقامةِ علانيته، وأقام أمرَ الله في نفسه، وسعى فيما استطاع في إصلاحِ مجتمعه، كان من أهلِ نصرةِ دينِ الله.
🍃 They are the ones who support the cause of Allah inwardly through love of Him and fear of Him, sincerity in obeying Him, avoiding what He has forbidden, and remaining within His limits.
🍃And they support the cause of Allah outwardly by taking the lawful means, fulfilling what Allah has commanded, enjoining what is good, and forbidding what is wrong.
So whoever combines inner uprightness with outward striving, upholds Allah’s commands in his own life, and strives, within his ability, to bring about good in his community, is among those who uphold and serve the cause of His religion.
@aaumsu
❤13⚡8👍3🔥1👏1
💥ልዩ የዳዕዋ፤ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የትውውቅ ፕሮግራም!
💡ታላላቅ ኡስታዞች እና መሻይኾች ተጋብዘዋል። አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከቀደምቶች ጋር ይተዋወቃሉ። ሕብረቱ ሲሰራው የነበረው እና ሊሰራው ያቀደው ተግባራት ይብራራሉ።
⏳መስከረም 23 / 2019 ዓ.ል !
የሁላችንም ቀጠሮ በታላቁ አል-አቅሷ መስጂድ ይሁን። በአዲሱ አመት፤ ከአዲስ ተማሪዎች ጋር፤ በአዲስ መንፈስ ወደ ተሻለ ደረጃ የምንሸጋገርበት ቀን ይሆናል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት !!

🔥19❤5👍2🥰2👏2💔1
ታላቅ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የዳዕዋ መድረክ በታላቁ አል-አቅሷ መስጂድ !!!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በ2019 ዓ.ል ወደ ጀመዓው የተቀላቀሉ ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት፤ ያለፈውን አመት የስራ ሪፖርት እንዲሁም የዘንድሮውን አመት እቅድ ለማብሰር፤ ከታላላቅ ኡስታዞች እና መሻይኾች ዳዕዋ ምክር እና ትምህርት ለመውሰድ ታላቅ መድረክ አዘጋጅቷል። በእለቱ፦
፨ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል የሙስሊም ተማሪዎች አበርክቶ ምን መሆን እንዳለበት በጥልቅ ያስቀምጡልናል።
፨ ዶክተር ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን በዩኒቨርስቲ ቆይታችን ምን ይዘን መውጣት እንዳለብን ይነግሩናል።
፨ ሸይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጠፋ አለማዊ ትምህርት በእስልምና ስላለው ቦታ ያብራሩልናል።
ቦታ፦ አፍንጮበር፤ አል-አቅሷ መስጂድ
ቀን፦ እለተ ቅዳሜ መስከረም 23 / 2019 ዓ.ል
ሰዓት፦ ከጧቱ 2:30 ጀምሮ
የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች፤ የኮሌጅ እና ሀይስኩል ተማሪዎች፤ የአካባቢው ማህበረሰብ መድረኩ የሁላችሁም ነውና አብረን ደምቀን እንውል ዘንድ ጥሪያችን ነው። የሰማው ላልሰማ ያሰማ! በሕብረት ወደፊት!!!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት !!!

🔥28😡14❤4👏2🫡2😢1👌1
🚙 ጉዞ ነበር…………
አዎን ጉዞ ነበር። ✨ባለፈው የታሪክ ማህደር ውስጥ ራሳችንን እንፈትሽ ዘንድ ፣ቁም ነገር ይዘን በመቀጠልም ከተማርነው ሰንቀን ዛሬ ላይ ስህተት እንዳንሰራና ነገን በተሻለ መልኩ አቅደን እንጓዝ ዘንድ 3 ታሪኮችን አይተናል።
#ሚሽካት
🟢በሰኢድ ኢብኑ ጁበይር ውስጥ ያለውን ለእውነት የመቆም ጽናትንና የነበረውን ጥልቅ ፈተና እውን ከተረዳን በህይወታችን ውስጥ ለውጥ የሚያመጣን የጽናት ውሳኔ ለመወሰን ብዙ አንቸገርም።
🟢ለግፍ ያላጎነበሰው ንጉስ
የራስን ታሪክና ማንነት ማወቅ ይበል የሚያሰኝ በጎ ተግባር ነው። ነጃሺ ፍትህን ባሰፈኑባት እና አሁን ላይ እኔ በተተካሁባት ፡ የኢትዮጵያ ምድር ላይ ምን እየተካሄደ ነው? ከእኔስ ምን ይጠበቃል? ብሎ ማውጠንጠን ደግሞ የብልህ ሰው አካሄድ ነው።
🟢እንማር፣ እንገሰጽ እንዲሁም አስተንትነን እንረዳ ዘንድ ደግሞ ከበኒ ኢስራኢል ምድር የተወሰኑ ገጾችን ወደ ኋላ ተጉዘን አይተናል።
🫴እነሆ ምን ያህል ተገነዘብን? የሚለውን ለመፈተሽ ያመቸን ዘንድ በጥያቄና መልስ ወደ እናንተ ተመልሰን መጥተናል።
#ሚሽካት ጥያቄና መልስ
ካለፉት 3 ታሪኮች ….
💥ምን ተማርን?
💥ምንስ ተረዳን?
💥ሽልማቱስ ምን ይሁን?
⚡️Stay Tuned……..⚡️

👍5🔥4❤3👏2
AAU - Muslim Students Union
🚙 ጉዞ ነበር………… አዎን ጉዞ ነበር። ✨ባለፈው የታሪክ ማህደር ውስጥ ራሳችንን እንፈትሽ ዘንድ ፣ቁም ነገር ይዘን በመቀጠልም ከተማርነው ሰንቀን ዛሬ ላይ ስህተት እንዳንሰራና ነገን በተሻለ መልኩ አቅደን እንጓዝ ዘንድ 3 ታሪኮችን አይተናል። #ሚሽካት 🟢በሰኢድ ኢብኑ ጁበይር ውስጥ ያለውን ለእውነት የመቆም ጽናትንና የነበረውን ጥልቅ ፈተና እውን ከተረዳን በህይወታችን ውስጥ ለውጥ የሚያመጣን የጽናት…
እነሆ እውቀታችንን የምንፈሽትሽበት
#ሚሽካት ጥያቄና መልስ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይለቀቃሉ።
አሸናፊው ማን ይሆን?
እኛስ ጥያቄዎቹን ምን ያህል እንመልሳለን?
ይጠብቁን!🔥🔥
@aaumsu
#ሚሽካት ጥያቄና መልስ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይለቀቃሉ።
አሸናፊው ማን ይሆን?
እኛስ ጥያቄዎቹን ምን ያህል እንመልሳለን?
ይጠብቁን!🔥🔥
@aaumsu
🔥4🥰1