AAU - Muslim Students Union
7.94K subscribers
2.95K photos
186 videos
57 files
841 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን በ Self sponsorship የተመዘገቡ ተማሪዎች ወደ የትምህርት መስኮች መግቢያ ነጥብን ይፋ አድርጓል።

@aaumsu
1
Don't forget to bring A4 size paper and pencil for the consultation.
🔖Thursday Sep 17, morning at 3:00 LT.
ሕያው ምስክር
AAU Muslim Students Union
ሕያው ምስክር - 2

የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል!

አቅራቢ፦ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

አዘጋጅ፦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት !!

@aaumsu
👏8👌2
AAU - Muslim Students Union
AAU Muslim Students Union – ሕያው ምስክር
የምስጋና እና አክብሮት መልዕክት ከቀድሞ የጅማ ዩኒቨርሲቲ (አግሪ ግቢ) አሚር አብዲ ኮርማ የተላለፈ ፦

በቅድሚያ ለሁላችሁም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። በአላህ ፈቃድ በግልም ሆነ በህብረት ለሰራችሁት ትልቅ ስራ፣ በተለይም ደግሞ ሌሎች ሰዎችን በማነቃቃት እና በማበረታታት በኩል ለነበራችሁ ሚና የከበረ ምስጋና እና አክብሮት አለኝ። አላህ በቀጣይም ለሌሎች ችግሮች መፍትሔ እንዲያደርጋችሁ እመኛለሁ።

በ 2016/17 ዓ.ል በነበረው ፈታኝ ወቅት፣ በቀንም ሆነ በሌሊት የ 24 ሰዓት መረጃዎችን እና ጥሪዎችን በመለዋወጥ፣ ምክር እና ድጋፍ በመስጠት አብራችሁን ስትታገሉ ነበር። ምስጋና ከሁሉም በላይ ለሆነው ለአላህ ይሁን፤ ከእሱ በመቀጠል ግን እናንተ መንገድ በማሳየት እና በመደገፍ ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ትልቅ ክብር ይገባችኋል። ውጤት የሚመጣው እንዲህ አይነት አንድነት እና ድምር ጥረት ሲኖር ነው!

በተለይም በወቅቱ በተማሪዎች ግሩፕ ውስጥ የነበሩ አባላት ያሳዩት ትልቅ አንድነት የሚደነቅ ነበር። ያንን ውስብስብ ሁኔታ ለመፍታት ከ Remedial እስከ GC ተማሪዎች ድረስ ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ እህቶችም ጭምር እጅ ለእጅ ተያይዘው ትልቅ እገዛ አድርገዋል።

በዚህ አጋጣሚ ለሰራችሁት ሁሉ ጀዛኩሙላሁ አህሰነል ጀዛእ እያልኩኝ፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት (AAU MSU)፤ እና ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ለሆኑት ወንድማችን ሙሀመድ አሚን ካሳው በወቅቱ ላሳዩት የስራ አመራር፣ ላደረጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ እና አብሮነት የላቀ ምስጋናዬን እና አክብሮቴን ማቅረብ እወዳለሁ።

በመጨረሻም፣ ይህ አዎንታዊ ተሞክሮ እና ህብረት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና አብረን መስራት እንድንችል መልእክቴን አስተላልፋለሁ። ጠንክሩ!

@aaumsu
7🔥6👏1
AAU - Muslim Students Union
AAU Muslim Students Union – ሕያው ምስክር
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ያስተላለፋት መልዕክት:

አሰላም አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ
​ቢስሚላህ በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ በመገኘት ወንድም ሱደይስ፣ አብዲ ኮርማ፣ አብሮን ሊታደም ያልቻለውን ዶ/ር አብዱሰላምን ጨምሮ፣ እንዲሁም መላው ተሳታፊ ወንድም እና እህቶች በአላህ ስም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።

​በመቀጠል እኛ እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጀመዓ እና ተማሪዎቻችን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጀመዓ ያለፈ ( ከኮሮና ጀምሮ እስከ ረመዳን 2017) የትግል ጉዞ ብዙ የወሰድናቸው ትምህርቶች አሉ። ከዛም መካከል አንድ የወንድማችን ንግግር ማስታወስ እወዳለሁ፡

​ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር): "ችግር ሲመጣ ሌላ የሚፈታ አካል እንዲመጣ መፈለግ ሳይሆን "እኔ አለሁለት!" የሚል አቋም ሊኖራችሁ ይገባል።" የሚለው ምክራቸው ሁላችንም ልብ ውስጥ ተቀምጧል ብዬ አስባለሁ።

አጠቃላይ በእንቅስቃሴያቸው ውስጥ የነበረው ጥንካሬ እና ህብረት እጅግ የሚያስደንቅ ነው። በአላህ ፈቃድ ትግል ካለ ድል እንደሚመጣ ህያው መስክር ሆኖ ቀርቦልናል።

​ይህንን ተከትሎ ጀመዓችን ወይም አአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ጅማ ላይ ጀግንነት እና ቁርጠኝነት ባሳዩት ወንድም እና እህቶች እንዲሁም በጀማአቸው ስም ስጦታ ማበርከት ይፈልጋል። ስጦታውንም በአዲሱ ዓመት መግቢያ ፕሮግራም ላይ አሚሮች መጥተው ይቀበሉ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።

ሙሐመድ ኢድሪስ
ፕሬዝዳንት

@aaumsu
15🔥5👏5🫡1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቦሌ ቡልቡላ ከሚገኘው አንሷር መስጂድ ከተላለፈ የኹጥባ መልዕክት፦

በቅርብ ቀናት ውስጥ የሚገኙት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተለይም ምክንያቶች ሃይማኖታቸውን፣ የሃይማኖታቸውን ድንጋጌ እንዳይስፋፋ የሚገፉ፣ ከትምህርት ማዕከል ራሳቸውንም፣ ቤተሰቦቻቸውንም ሃገራቸውን እንዳይመጥኑ ከሚያደርጉት ጥረት፣ ከሚያደነቃፏቸው አካላት አላህ ሱብሃነ ወተዓላ እንዳያግዛቸው በምንችለው ነገር ሁሉ በሃሳባችን፣ በምክራችን እንዲሁም በዱዓችን እነሱን ማገዝ ይገባናል። ይህ በእኛ ላይ ትንሹ ግዴታ ነው።

@aaumsu
22👌9
ደጋግሜ ብየዋለሁ የሆነ ተቋም መብታችሁን ቢነፍግና ቢከለክል ምን ልታደርጉ ነው? ልትሸሹ?! ልትተዉ?! ሌላ ቦታ፤ ሌላ ሀገር፤ ሌላ ተቋም፤ ሌላ ዩኒቨርስቲ ልትፈልጉ?!!!! አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኒቃብ ይከለክላል ወይ? ኒቃብ የማይከለከልበት ዩኒቨርስቲ የቱ ነው? ሶላትስ? ጀለብያስ? ቁርዓንስ? ሌላም ሌላም እያሉ የሚጠይቁ ብዙ ናቸው። የእኔ ጥያቄ ደግሞ ከላይ እንዳልኩት እዚህ ስለተከለከለ ጅቡቲ ወይንም ሴኔጋል ሄዳችሁ ልትማሩ ነው?!

ሰዎች፦ ኢትዮጵያኮ ሀገራችሁ ናት። እነዚህም ተቋማት በእናንተ ግብር እና ላብ የተገነቡ ናቸው። ሌላው ቢቀር በበደል ላይ እንዲዘወተር ስላደረጋችሁ በአላህ ፊት እንጠየቃለን ብላችሁ አታስቡም?! እስልምና ደግሞ ሀይማኖታችሁ ነው። በር ላይ ጥለነው የምንገባው ሀይማኖት አይደለም። እንድንኖረው ነው የታዘዝነው። እንኖረዋለንም።

ቀደምቶች ባደረጉት ትግል አሁን ላይ ያለው ሁኔታ የተሻለ ቢሆንም አሁን ያለው ሁኔታ እንዲፀና፤ የተሻለ ጊዜም እንዲመጣ መትጋት ግዴታችሁ ነው። ያለፈው ትውልድ የከፈለው ዋጋ ለእናንተ አማና ነው። ቀጣዩ ትውልድ በተሻለ ይኖር ዘንድ ደግሞ እናንተም አማና አለባችሁ። በዚያ ልክ አስቡ። ሁላችንም መንገደኞች ነው። የዚህ አለም ሰዎች አይደለንም። ያማረች ዱንያን ሰርተን እናልፍ ዘንድ እናልም።

©️

@aaumsu
👏20🔥74💯2🫡1
AAU - Muslim Students Union
Don't forget to bring A4 size paper and pencil for the consultation. 🔖Thursday Sep 17, morning at 3:00 LT.
If you lost the location or training place, you can call to:
0956053643
■ They are waiting for you to come up!!
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:-

በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን። ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን። እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለማስተናገድ ዝግጅቱን አጠናቋል። ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን።
    
📌 AAU MUSLIM STUDENTS UNION - 0909524252

Main and FBE Campus
📌 አሊፍ ሓጂ - Main Campus - 0955942642

AAiT (5 Kilo) Campus
📌 ሙሐመድ አብራር - AAIT - 0953442423

4 Kilo Campus
📌 አይመን ሙሐመድ - 4kilo - 0977207747

Sefere Selam Campus
📌 አብዱልዓዚዝ ዩሱፍ - s.selam campus - 0951907014

Ldeta Campus
📌 አብዱልዓዚዝ ጁማቶ - Ldeta Campus - 0961497962

Tikur Anbessa Campus
📌 አይመን ሚፍታህ - Tikur Anbessa Campus -
0977777095

Bishoftu Campus
📌 መነልከሪም አብዱልጀባር - Bishoftu Campus -
0917962262

📌 የትኛውንም ካምፓስ የሚመለከት ጥያቄ፡ 0909524252 ወይም @Aaumuslimstudentsunion1

https://t.me/aaumsu
🥰74