የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ከደሴ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመሆን "የኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ ከትላንት እስከ ዛሬ!" - በሚል ርዕስ ያዘጋጁት ታላቅ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ተካሄደ።
በመድረኩ ከሸይኽ ሙሐመድ አንሲ ነፍስን የሚያናግሩ እና ለሕይዎት ስንቅ የሚሆኑ ምክሮች ተላልፈዋል። በወንድም ሙሐመድአሚን ካሳው ስለሙስሊም ተማሪዎች ውጣወረድ እና መፍትሄዎቻቸው ዳሰሳ ቀርቧል።
መድረኩ በደቡብ ወሎ ዞን ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሐሰን አህመድ የተመራ ሲሆን ከታዳሚዎችም ጋር ገንቢ ውይይቶች እና የኃሳብ ልውውጦች ተካሂደዋል።
መሰል ፕሮግራሞች በተሻለ አቀራረብ ሌሎች ቦታዎችም በአላህ ፈቃድ የሚቀጥሉ ይሆናል።
@aaumsu

🔥24👏7❤6👌2👍1🥰1
#ሚሽካት
ከበኒ ኢስራኢል ምድር ....ጧሉትና ጃሉት
ክፍል 2
የኢስራኢል ልጆች ለነብያቸው በአላህ መንገድ እንደሚዋጉ ቃል ቢገቡም ፈተናው በእውነት ሲመጣ ግን በዚያ ቃል መጽናት አልቻሉም።
<<فَلَمَّا كُتِبَ عَلَيْهِمُ الْقِتَالُ تَوَلَّوْا إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِالظَّالِمِينَ>>
<<በእነርሱ ላይ መዋጋት በተጻፈባቸውም ጊዜ ከእነርሱ ጥቂቶች ሲቀሩ አፈገፈጉ፡፡ አላህም በዳዮቹን ዐዋቂ ነው፡፡>>
አንድን ነገር እንመኛለን፣ እንጠይቃለን፣ እንዲለወጥም እንሻለን ነገር ግን ከለውጡ ጋር የሚመጣውን ፈተና ለመቀበል ዝግጁ ነን??
ይህ ሁላችንም ልናጤነው የሚገባ ነገር ነው!።የትኛውም ድል ከመስዋትነት ጋር እንጂ አልተገኘም። ዛሬ ላይ እኛ በድሎት የምናደርጋቸው፣ ያለስጋት የምናጸባርቃቸው የዲናችን ምልክቶች ከዚህ ቀደም ብዙ አባቶችን፣ እናቶችን፣ ወንድሞችንና እህቶችን ዋጋ ያስከፈለ ነው። ዛሬ እኔ ለታናሼ፣ ለቀጣዩ ትውልድ ዋጋን ለመክፈል ዝግጁ ነኝ??
ነቢያቸውም መሪ እንዲሾምላቸው በጠየቁት መሰረት አሏህ ጧሉትን እንደሾመላቸው ይነግራቸዋል። የኢስራኢል ልጆች ግን ምርጫውን ተቃወሙ። መመዘኛቸው ሀብትና ጎሳ ሆነና ጧሉትን እንደ መሪ ለመቀበል ተቸገሩ። አላህ ጧሉትን ከእነሱ በላይ በ2 ነገሮች አስበለጠው— እውቀትና የአካል ጥንካሬን ሰጠው። በእነሱም ላይ ሾመባቸው፤ አላህም የተሻለ አዋቂ ነው።
<<وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ اللَّهَ قَدْ بَعَثَ لَكُمْ طَالُوتَ مَلِكًا ۚ قَالُوا أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُ الْمُلْكُ عَلَيْنَا وَنَحْنُ أَحَقُّ بِالْمُلْكِ مِنْهُ وَلَمْ يُؤْتَ سَعَةً مِّنَ الْمَالِ ۚ قَالَ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُ بَسْطَةً فِي الْعِلْمِ وَالْجِسْمِ ۖ وَاللَّهُ يُؤْتِي مُلْكَهُ مَن يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ>>
<<ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «አላህ ጧሉትን (ሳኦልን) ንጉሥ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ» አላቸው፡፡ (እነርሱም)፡- «እኛ ከእርሱ ይልቅ በንግሥና ተገቢዎች ስንኾን ከሀብትም ስፋትን ያልተሰጠ ሲኾን ለእርሱ በኛ ላይ እንዴት ንግሥና ይኖረዋል?» አሉ፡፡
(ነቢያቸውም)፡-«አላህ በእናንተ ላይ መረጠው፡፡ በዕውቀትና በአካልም ስፋትን ጨመረለት፡፡ አላህም ንግሥናውን ለሚሻው ሰው ይሰጣል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» አላቸው፡፡>>
ነብያቸውም ጧሉት በእርግጥ ከአሏህ የተመረጠ ንጉስ መሆኑን የሚያሳየው ምልክት ከሙሳና ከሀሩን ቤተሰቦች ቅሪት፣ ከጌታቸውም ሰኪና የሆነውን ታቦት ወይም ሳጥን ማስመለሱ መሆኑን ነገራቸው።
<<وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ آيَةَ مُلْكِهِ أَن يَأْتِيَكُمُ التَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ آلُ مُوسَىٰ وَآلُ هَارُونَ تَحْمِلُهُ الْمَلَائِكَةُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ>>
ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሳ ቤተሰብና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ ሳጥኑ ሊመጣላችሁ ነው፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አልለ» አላቸው፡፡
ጧሉትም በአሏህ መንገድ ሊጋደል ሰራዊቱን ይዞ ወጣ...እስከ መጨረሻው ማን በአሏህ መንገድ ይፀናል??
ይቀጥላል ....

❤10👍3🥰3👏2🔥1🤝1
የ SBE ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት Architecture department መቀላቀል ለምትፈልጉ አዲስ ተማሪዎች ( 2nd year ) ለ መግቢያ ፈተና consultation እያዘጋጀ ይገኛል። እንዲዘጋጅ ትፈልጋላችሁ?
Anonymous Poll
73%
አዎ ይመቸኛል እመጣለሁ።
27%
አይ ይቅር አያስፈልግም
AAU - Muslim Students Union
አል በያን - ቅ1.pdf
የኒቃቢስቷ መልዕክት!
ከአል-በያን ገጾች የተወሰደ...
የሰው ልጅ በሚኖርበት ምህዋር ውስጥ ይህቺ የሚኖርባት አለም: አለም ሆና ማንነቷን ይዛ ትቀጥል ዘንድ ሚናቸውን የተወጡ ብዙ ትናንሽ አለሞች አሉ። እምነት በራሱ አለምን አለም ያደረጋት አንዱ ግብአት ነው። ከእምነት ውስጥ ደግሞ እስልምና የአለሞች ሁሉ ውብ አለም ነው። ሰላት፣ ዱአ፣ ኢባዳ፣ ሰደቃ ፣ መሃባ እና ብዙ ደግሞ ኢስላምን ውብ የሆነ አለም አድርገው ያቆሙት የኢስላም የተዋቀሩ ጌጦች አሉ።
እነዚህ የተሰደሩ የሆኑ ጌጦች በጥንቃቄ እየተጠበቁ ካልቀጠልን የአንዱ ጌጥ መውጣት ስርዓተ-ጥለቱን ያጠፋል። የዲናችንን ውበትም ያደበዝዛል። ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ ደግሞ ሌሎች ጌጦቻችንን አውድሞ ከአለሞች ሁሉ ደካማው አለም የሚል ስያሜን ያሰጠናል።
ወዳጄ!! አለም ላይ ያሉ በጣም ውድ ነገሮች በሙሉ ለማንም ክፍት አይደሉም። የተሸፈኑና ከዛም በላይ በጥበቃ ውስጥ ያሉ ናቸው። ኢስላም ሴትን በሂጃባ ወይም በኒቃቧ ሊጠብቃት ኖሯል። ኒቃብ ጨርቅ ቢመስልም ከጨርቅ በላይ ነው። የኢስላም 1 ጌጥ፣ መጠበቂያ፣ መታወቂያ፣ መከበሪያ፣ የሴትነት ክብር መገለጫም ጭምር ነው። አንድን ሰው ኒቃብ ጠል ሆኖ ስታገኘው ጨርቅ ጠል ሆኖ ሳይሆን ጥብቅነትን፣ ስርአትንና ኢስላምን ጠልቶ ነው። እናም ጥላቻውን፣ ግፉንና በደሉን እሰየው ብለህ የተቀበልክ ቀን ሰላትህም፣ ጀማዐህም፣ መስጂድህም፣ ዲንህም ይጎዳ ዘንድ እሰየው ብለህ እንደተቀበልክ ቁጠረው። ስለዚህ ጠላት ኒቃብ አይሆንም ሲል ኢስላማ አይሆንም እንዳለ የተረዳህ ቀን ደግሞ ታጋይ መሆን ትጀምራለህ። ጥልቅ የሆነና እምነትህን የሚገባ የሆነ ቦታው ላይ ሆኖ እስክታየው ድረስ እንቅልፍ የሚነሳህ፣ ያለህበትን ሁኔታ የሚገልጥልህ፣ ያለፈውን አስታውሶ የሚያነቃህ፣ ለዲንህ ደግሞ መስዋእትነትን የሚያስከፍልህ ትግል ማለት ነው።
ወዳጄ!! እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለዲናችን መስዋእት የመሆን፣ ጠላት ፊት ቆሞ ለሞትና ለሸሂድነት ዝግጁ የመሆን ችግር የለብንም። ግን ያ ድሮ ወይ ዘንድሮም ቢሆን ለታጣቂ እንጂ ለእኛ አይሆንም። ምክንያቱም እንደምናየው በደም ትግል ውስጥ የመጡ መብቶቻችን በሙሉ ጊዜያዊ መብት እየሆኑ ተቸግረናል። ስለዚህ ልንነቃ ይገባል። ጊዜያዊ ሳይሆን ቋሚ የሆነ የትግል መስመር ሊኖረን ይገባል። በየትኛውም የህይወት እርከን ላይ ስናልፍ የሀገራችን እና የኢስላማዊ መብታችንን ሁኔታ ሳንዘነጋ ከስራችንም ከላያችንም ካለው ሙስሊም ወገናችን ጋር በየመሳጂዶቻችን፣ ስራዎቻችን እና ትምህርት ቤቶቻችን የተጠና እቅድ እና እምቅ የሆነ ኃይል ኖሮን መሃላችን ላይ ያለውን ክፍተት በሙሉ እየደፈንን ልንጓዝ ይገባል።
መልእክቴ ነቃቤ ተነክቷል፤ መማር አቅቶኛል። እርዱኝ ሳይሆን በኒቃብ ስያሜ ሊያጠቁ ያሰቡት የጋራ እስልምናችንን ነውና እንንቃ!! ነው።

👌16❤3💯3🥰2👍1
ለ2019 ዓ.ል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመደበኛው መርሃ ግብር ለመማር ቅበላ ላገኛችሁ የአንደኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ
ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች መስከረም 06 እና 07 2019 ዓ.ል በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ
1. የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ኮፒ፣
2. አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
3. የማደሪያ ምድብ (Dormitory) ለተሰጣችሁ ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ ያስታውቃል፡፡
4. ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል የዩኒቨርሲቲውን የመግቢያ ፈተና በተፈተናችሁበት UGA2019…. ቁጥር በመጠቀም ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ https://portal.aau.edu.et/NewStudents/DormitoryPlacement
5. በተጠቀሱት ቀናት (መስከረም 06 እና 07) ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡ ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች እንዲሁም በቦሌ የአገር ውስጥ አውሮፕላን ጣቢያ ዩኒቨርስቲው ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ወደሚገኙት ካምፓሶቻችን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
6. ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ ሆኖ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ል መሆኑን ያሳውቃል፡፡
7. ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ስለ ዩኒቨርስቲዉ ገለፃ የሚደረገዉ ዐርብ መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ል ይደረጋል፡፡
8. ዘግይቶ የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ል ሲሆን
9. የ2019 ዓ.ል የመጀመሪያዉ ሴሚስተር ትምህርት የሚጀመረዉ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ል ይሆናል፡፡
10. ስለመቁረጫ ነጥብ ስለምዝገባ ሂደቶች በተመለከተ እና ተጨማሪ መረጃ ከታች ካሉት ሊንኮች ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን::
Ø https://portal.aau.edu.et/NewStudents/Welcome
Ø www.aau.edu.et
Ø https://t.me/aauGAT
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር

❤11👍4
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን በ Self sponsorship የተመዘገቡ ተማሪዎች ወደ የትምህርት መስኮች መግቢያ ነጥብን ይፋ አድርጓል።
@aaumsu
@aaumsu
AAU - Muslim Students Union
Don't forget to bring A4 size paper and pencil for the consultation. 🔖Thursday Sep 17, morning at 3:00 LT.
Please note that the exam has been rescheduled to Friday, September 18, instead of September 21.
ሕያው ምስክር
AAU Muslim Students Union
ሕያው ምስክር - 2
የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል!
አቅራቢ፦ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)
አዘጋጅ፦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት !!

👏7👌2