AAU - Muslim Students Union
7.94K subscribers
2.95K photos
186 videos
57 files
840 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
"የጀመዓ ትልቁ ኃላፊነት የተማሪዎችn መብት እና ደህንነት ማስጠበቅ ነው።"

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
👌351
ችግሩን እንፈታለን ብለው ቃል የገቡ አካላት መጨረሻ ላይ ፈሩ፤ ችግሩን መፍታት አልቻሉም።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
🔥221
እንደ ኃገር አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች፤ ሽማግሌዎች ከጀመዓው ጋር ተወያዩ፤ ለችግሩም መፍትሄ እንደሚያመጡ ቃል ገቡ። ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀረ።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
👌11😭5🔥31
ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ሳምንት በኃላ ፈታለሁ ብሎ ቃል ከገባ በኃላ እንደገና ቃሉን በማጠፍ "እንደዚህ አይነት ነገር አላልኩም" በማለት ቃሉን አጠፈ።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
😡21
2017 ዓ.ል ረመዳን ሲደርስ ተማሪው ከኒቃብ ጨምሮ ያሉትን ጥያቄዎች ሰብስቦ ቢያቀርብም ዩኒቨርሲቲው ምንም የተነሳ ጥያቄ እንደሌለ አድርጎ አቀረበ። ይህ ሲሆን ተማሪው ሙሉ ትኩረቱን ወደ ኒቃቡ ጉዳይ ሙሉ ትኩረቱን አዞረ።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
🔥173
እስከ 2016 ዓ.ል ድረስ ብዙ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። ከሁሉም ካምፓስ ተማሪዎች ፒትሽን ተሰብስቧል፤ ብዙ ደብዳቤዎች ተጽፈዋል፤ ፌደራል መጅሊስ ድረስ ተኪዷል፤ ከሐገር ሽማግሌዎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች ሲካሄዱ ነበር።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
🔥8👌71
ጉዳዩ እየከረረ ሲመጣ ጉዳዩን ለማረጋጋት እና ለመሸንገል ሞከሩ። የተለያዩ የዩኒቨርሲቲው፤ የከተማው እና የጸጥታ አካላት በጉዳዩ ዙሪያ ለስብሰባ ቢቀመጡም ተማሪው "እኛ ሽምግልና አንፈልግም፤ ችግሩን የምትፈቱ ከሆነ ፍቱ!" የሚል የጸና አቋም ያዘ።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
👌10🔥41
ጀመዓው ከዚህ በፊት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት ስለነበረው የአካባቢው ማህበረሰብ ከጎናችን ነበር።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
🔥8👌4
በተለይ ሓረማያ፣ አዲስ አበባ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎች እና ሌሎች ጀመዓዎችም ከጎናችን ነበሩ።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
11🥰3👌1
ችግሩ ከተፈታም በኃላ ወደ መሬት ማውረዱ በራሱ ብዙ ስራ ፈጅቷል። ላይብረሪ፤ ካፌ፤ ካምፓሶች እና ሌሎች ቦታዎች በተግባር ለማውረድ ከወር በላይ ፈጅቷል። ቀጣይ አመት ፍሬሾች እስኪገቡ ድረስ ስራውን አላቆመም ነበር።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
12🫡5🔥3
አላህም ወቅቱን መርጦት ይመስላል በረመዳን መሆኑ

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
20👌31
ችግር ሲመጣ ሌላ የሚፈታ አካል እንዲመጣ መፈለግ ሳይሆን "እኔ አለሁለት!" የሚል አቋም ሊኖራችሁ ይገባል።

- ሱደይስ አብዱረህማን (የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አሚር)

@aaumsu
👌205🔥3💯1
Live stream finished (1 hour)
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات

ፕሮግራማችን ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል።

የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎችን ታሪካዊ የመብት ትግል ላጋሩን፤ ወንድማችን ሱደይስ አብዱረህማን፤ እንዲሁም በኔትዎርክ ምክንያት ሊቀላቀለን ያልቻለውን ወንድም አብዲ ኮርማን ከልብ እናመሰግናለን።

እንዲሁም ፕሮግራሙ እንዲሳካ ለተነቀሳቀሱ እህት እና ወንድሞች ሁሉ ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ ማለት እንወዳለን!

በቀጥታ መከታተል ላልቻላችሁ ሪከርድ የሚለቀቅ ይሆናል።

ህያው ምስክር ፕሮግራማችን በቀጣይም ከሌላ እንግዳና ሌላ አስተማሪ የትግል ታሪክ ጋር የሚመለስ ይሆናል።

@aaumsu
👏36🔥72🥰2
በዛሬው ዕለት በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ልዩ የሆነ የዳዕዋ እና ፓናል ውይይት ተዘጋጅቷል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ከደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመሆን  የተዘጋጀው ይህ ልዩ መድረክ ሊጀምር ደቂቃዎች ብቻ ነው የቀሩት!

@aaumsu
🔥13👌4
አል በያን - ቅ1.pdf
13 MB
🔥 አዲስ ነገር!!! 🔥
በአዲሱ የትምሕርት ዘመን!!
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ኅብረት!


በመነሻችን ላይ «ስለመንገዱ» መክረን ነበር... መንገዱ የሚጠይቀውን ሁሉ አንዳች ሳንሰስት ለመስጠት ቃል ተጋብተንም ጭምር!... እነሆ አሁን ደግሞ በመንገዳችን ላይ የነበሩትን አጠቃላይ ሂደቶች በምንዳስስበት «አል-በያን!» በተሰኘ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የተዘጋጀ መጽሔት ብቅ ብለናል። ይህ በችሮታው እንጂ በሌላ አልሆነምና፥ ሰዎችን መግለጽ ያስተማረው ጌታ ምሉዕነቱን የሚመጥን ምስጋና የተገባው ይሁን!!!

መጽሔታችን በሚቀጥሉት ጊዜያት በሙስሊም ተማሪዎች ጉዳዮች ላይ በማተኮር የተለያዩ ሀገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ አርዕስቶችን በተከታታይ እየዳሠሠ፥ ለተማሪዎች እንዲሁም ውጪ ላለው ማኅበረሰብ ሰፊ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ይሆናል።

ይህ ከ«ጥያቄ አለን!» ትውልድ ዘላቂ አሻራዎች ውስጥ አንዱ ነው! መንገዳችን ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ... በጊዜ ሐዲድ ላይ ብሩህ መዳረሻን እናኖር ዘንድ... ለትውልድ ነጻነትን እናወርስ ዘንድ... እስክሪብቷችንን አለመጣላችንን ያረጋገጥንበት ሌላ ክስተት።

መጽሔቱን በማዘጋጀት ሂደት ላይ «እኔም ለትውልድ የማወርሰው ብሩህ ነገ አለ!» ብላችሁ ብዕራችሁን የጨበጣችሁ ውድ ተማሪዎቻችን፥ አላህ (ሱ.ወ) መልካም ሥራችሁን ይባርክላችሁ። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን!!!

አላህ ለመልካም ለውጥ ሰበብ የምንሆን ያድርገን።

መልካም ንባብ!

@aaumsu
🔥30👏83👍1🥰1
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በGovernment Sponsorship መግባት ለሚፈልጉ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብን ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት፦

📌 ለNatural Science፡ 76.17
📌 ለSocial Science: 58.75


ውጤት የሚሰላው 50% Entrance exam፤ 50% UAT በማድረግ ከ100% ይሆናል።

@aaumsu
9👏5😭1
#ሚሽካት
ከበኒ ኢስራኢል ምድር ....ጧሉትና ጃሉት


ክፍል 1

ጊዜው ከሙሳ ዐለይሂ ሰላም በኋላ ነው፤ የኢስራኢል ልጆች በሙሳ መንገድ ፀንተው በተወራትም ህግጋት ሲመሩ ነበር። ዘመናት በራቀ ቁጥር ግን ቀልቦቻቸው ደረቁ፤ በዲናቸውም አዳዲስ ነገሮችን አስገቡ፤ ከፊሎቻቸውም ጣኦታትን ማምለክ ጀመሩ። ከክፋታቸው ይመለሱ፣ በመልካም ይታዘዙ፣ ከክፉም ነገር ይታቀቡ ዘንድ እንዲሁም በመካከላቸው በተውራት ህግጋት እንዲፈርዱ አሏህ መልእክተኞችን አከታትሎ መላክን ቀጠለ።

ቀደም ባለ ጊዜ የኢስራኢል ልጆችን የሚዋጋ ሁሉ ይሸነፍ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ከአላህ ጋር በቀጥታ ከተነጋገሩት ሙሳ ዐለይሂ ሰላም ጀምሮ ከትውልድ ወደ ወደ ትውልድ ሲወራረሱት የነበረ ተውራትና ታቦትን ይዘው ስለነበር ነው። (ይህ ሲባል ታቦቱ /ሳጥኑ ውስጥ የሙሳ እና ሀሩን ቅርስ የነበረ ሲሆን ጦርነት ሲሄዱ ተሸክመውሄደው ከአላህ በሆነ ተአምር በርሱ በረካ ነስርን ያረጋግጥላቸው ነበር)

የኢስራኢል ልጆችም እነዚያን ክፉ ስራዎች መፈጸማቸውን በቀጠሉ ጊዜ አላህ ጠላቶቻቸውን በእነርሱ ላይ ሾመባቸው። ብዙዎች ጦር ሜዳ ላይ አለቁ፣ ልጆቻቸው እና ሴቶቻቸው ተማረኩ፣ጠላቶቻቸው በሀገራቸው ሰፊ ክፍሎችን ተቆጣጠሩ፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው በቃ የአንድ ህዝብ ልቅናውም ሆነ ውድቀቱ ሚጀምረው ለጌታውን ትእዛዝ ከሚሰጠው ቦታ ነው።አሁን ላለንበት የበታችነትና በካፊሮች እጅ ስር መጨፍደድ አንዱ ምክንያት ከአሏህ መራቅ ነው።ሙስሊሙ ውጥንቅጡ ወጥቷል፤ ከቁርአን ብርሀን፣ ከነብዩም፣ ከሰሀቦቻቸው፣ ከድንቅ ተተኪዎችም በኋላ መርህ እንደሌለው ተራ ሰው ዘቀጥን ዱንያም ዋጠችን...ውጤቱንም እንደምናየው ነው– በየቦታው ችግራችን በዛ ከብዛታችንም ሀይል አጣን ተዳከምን።

የኢስራኢል ልጆች ታቦቱንና ተውራትን በአንድ የጠላት ንጉስ እስኪያስነጥቁ ድረስ በጥመት መቀጠላቸውን አላቆሙም ነበር። ከዚህም በኋላ ከመካከላቸው አንድን ነብይ አሏህ ላከ። ወደ አላህ እርሱን ብቻ እንዲያመልኩ እንዲጠራ አዘዘው። ነብያቸውም የኢስራኢል ልጆችን ወደ አላህ ጠራቸው።እነርሱም በመካከላቸው ንግስና አብቅቶ ነበርና ጠላቶቻቸውን በእርሱ መሪነት በአሏህ መንገድ ለመዋጋት አንድን ንጉስ እንዲሾምላቸው ጠየቁ።
<<أَلَمْ تَرَ إِلَى الْمَلَإِ مِن بَنِي إِسْرَائِيلَ مِن بَعْدِ مُوسَىٰ إِذْ قَالُوا لِنَبِيٍّ لَّهُمُ ابْعَثْ لَنَا مَلِكًا نُّقَاتِلْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ>>

"ከኢስራኢል ልጆች ከሙሳ በኋላ ወደ ነበሩት ጭፍሮች ለነቢያቸው ፡- «ለእኛ ንጉሥን አስነሳልን በአላህ መንገድ እንዋጋለን፤» ባሉ ጊዜ አላየህምን? (አላወቅህምን?)"

ነብያቸውም እንዲህ አላቸው:-
<<قَالَ هَلْ عَسَيْتُمْ إِن كُتِبَ عَلَيْكُمُ الْقِتَالُ أَلَّا تُقَاتِلُوا ۖ>>

"ከአሏህ ዘንድ በግዳጅነት ቢፃፍባችሁ ላለመዋጋት ትሻላችሁን??"

<< قَالُوا وَمَا لَنَا أَلَّا نُقَاتِلَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَقَدْ أُخْرِجْنَا مِن دِيَارِنَا وَأَبْنَائِنَا>>

"ከሀገሮቻችን እና ከልጆቻችን የተባረርን ስንሆን በአላህ መንገድ የማንዋጋ ለእኛ ምን አለን?" በማለትም መልሱ

መሪ እንዲሰጣቸው ጠየቁ.....ነገር ግን ፈተናውን ለመቀበል ዝግጁ ነበሩ ይሆን!?

ይቀጥላል....
133👏1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ከደሴ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር በመሆን "የኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ ከትላንት እስከ ዛሬ!" - በሚል ርዕስ ያዘጋጁት ታላቅ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ተካሄደ።

በመድረኩ ከሸይኽ ሙሐመድ አንሲ ነፍስን የሚያናግሩ እና ለሕይዎት ስንቅ የሚሆኑ ምክሮች ተላልፈዋል። በወንድም ሙሐመድአሚን ካሳው ስለሙስሊም ተማሪዎች ውጣወረድ እና መፍትሄዎቻቸው ዳሰሳ ቀርቧል።

መድረኩ በደቡብ ወሎ ዞን ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሐሰን አህመድ የተመራ ሲሆን ከታዳሚዎችም ጋር ገንቢ ውይይቶች እና የኃሳብ ልውውጦች ተካሂደዋል።

መሰል ፕሮግራሞች በተሻለ አቀራረብ ሌሎች ቦታዎችም በአላህ ፈቃድ የሚቀጥሉ ይሆናል።

@aaumsu
🔥24👏76👌2👍1🥰1