AAU - Muslim Students Union
7.84K subscribers
2.91K photos
185 videos
56 files
836 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን !!!

የቀድሞው የጅግጂጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት፤ አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህር የነበሩት ዶክተር ዶክተር አብዱናሲር አህመድ ወደ አኼራ ሄደዋል። አላህ በጀነተል ፊርደውስ ይቀበላቸው። ለቤተሰባቸውም መፅናናትን ይለግስ።

@aaumsu
💔86😭36😢112
AASTU / ASTU መግባት ለምትፈልጉ፦
ነገ ሐሙስ ከምሽቱ 2:50 ጀምሮ

የመግቢያ ፈተናው ምን ይመስላል፤ አጠቃላይ ማድረግ ያለብኝ ዝግጅት ምንድን ነው፤ የዩኒቨርስቲዎቹ ሁኔታ እንዴት ነው፤ ምን ምን ዲፓርትመንቶች አሉ፤ ምንስ ይጠብቀኛል በሚሉት ነጥቦች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘናል።

ተጋባዥ እንግዶች፦

ኢብራሒም ኸዲር፦ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አካዳሚክ ሴክተር አሚር

መስዑድ ሙስጠፋ፦ በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ

ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ BAIS ተማሪ በሆነው ሚፍታሕ ኢብራሒም የሚመራ ይሆናል። እንዲነሳ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች ከአሁኑ ሰዓት ጀምራችሁ @MOHAMMADAMMINM ላኩ።

ፕሮግራሙ ነገ ሐሙስ ነሐሴ 28 / 2018 ዓ.ል ከምሽቱ 2:50 ጀምሮ @MohammadamminKassaw Live ይካሄዳል። ለሁሉም ይደርስ ዘንድ share አድርጉት።

@MohammadamminKassaw
13
#ሕያው_ምስክር_2

በ ቅርብ ቀን ይጠብቁን!

@aaumsu
🔥15👏6
AAU - Muslim Students Union
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ለዩኒቨርሲቲው የUAT ፈተና፣ መመዝገቢያ እና ትራንስፖርት ወጪ ሽፋን በለቀቀው ፎርም መሰረት በቂ አመልካቾችን አጊኝተናል። በአሁኑ ሰዓት የተላኩልንን መረጃዎች የማጣራት እና የማረጋገጥ ስራ እየሰራን የምንገኝ ሲሆን፤ መረጃቸውን አጣርተን ላፀደቅናቸው ተማሪዎች ነገ ኢንሻአላህ የምናሳውቅ ይሆናል። በተጨማሪም የሌሎች ተማሪዎችን ወጪ ለመሸፈን የሚያስችል…
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ለዩኒቨርሲቲው የUAT ፈተና፣ መመዝገቢያ እና ትራንስፖርት ወጪ መሸፈን የማይችሉ ልጆችን ለመደገፍ በለቀቀው ፎርም ተመዝግባችሁ እስካሁን ያልተደወለላችሁ ወንድም እና እህቶች፤ ስልካችሁን ማግኘት ስላልቻለን በ @Aaumuslimstudentsunion1 እንድታናግሩን እንጠይቃለን።

@aaumsu
5🔥2👍1🥰1
በአባጂፋሯ ጅማ የተገፈፈ ክብር፤ የተከለከለ ሒጃብ ... በአባጂፋር ልጆች የተደረገ ትግል፤ የተከፈለ መስዋዕትነት፤ የተረጋገጠ ክብር --- በጅማ ዩኒቨርስቲ !

ሕያው ምስክር - 2

አባጂፋር (ረህመቱላሂ ዐለይሂ) ከጅማ መምለካ ተሻግረው፤ ሐበሻንም አቋርጠው ስለሙስሊሞች መብት የሚብሰለሰሉ፤ የሚታገሉ፤ መስዋዕትነት የከፈሉ ታላቅ እና ፍትሐዊ ንጉስ ነበሩ። ሆኖም ግን ከአመታት ቡሃላ፤ በጅማ ከተማ፤ በጅማ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች ባይተዋር ሆኑ። ሙስሊም ስለሆኑ ሊለብሱት ግዴታ የሆነውን ሒጃብ (ኒቃብ) ከመልበስ ተከለከሉ። ለተከታታይ አስር አመታት ያክል በተለያየ ጊዜ፤ በተለያዩ ሰዎች ክብራቸው ተደፈረ።

ይህ እየሆነ ባለበት በ2017 ዓ.ል የአባጂፋር ልጆች መብታቸውን ያስከብሩ ዘንድ የአላህ ፍቃድ ሆነ። በወርሐ ረመዷን ከተራዊህ መልስ ኒቃቢስት ተማሪዎች ወደ ግቢ ካልገቡ እኛም አንገባም በማለት ለተከታታይ አራት ቀናት ታገሉ። መሪዎቻቸው ቢታሰሩም ፀንተው ቆሙ። በአላህ ፈቃድም በፍትሐዊው ንጉስ ሐገር የተነፈገው ነፃነት ተከብሮ ፍትሕ ፀና።

የነበረውን ሂደት፤ የተፈጠሩትን ክስተቶች፤ የመጣውን ውጤት በሕያው ምስክር - 2 የምንዳስስ ይሆናል።

መስከረም - 1
ጁምዓ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ !


በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) እንገናኝ። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ share ያድርጉ።

@aaumsu
🔥244👏3
"የተማሪዎችን እርካታ አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ፖሊስ ምርምር፤ የአመራር ልማት መርሐግብር እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2018 አፈፃፀም ዙሪያ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የቀረበው ጥናት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሁኔታ በግልፅ ያሳየ ነው።" - የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት

ሸገር FM ባወጣው ዘገባ እንዳስቀመጠው የተማሪዎች እርካታን አስመልክቶ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ 47 ዩኒቨርስቲዎች በመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ይህ ውጤት ባለፉት ሁለት አመታት ዩኒቨርስቲው የተማሪዎችን ሐይማኖታዊ እና ሰብዓዊ መብቶች የሚጥሱ መመሪያዎችን በማውጣት፤ በሐይማኖታቸው ጣልቃ ገብቶ ሒጃብ መልበስን በመከልከል፤ ተማሪዎች ትኩረታቸውን ወደ መብት ጥያቄ እንዲያደርጉ በማድረግ የፈፀመውን የአመራር ውድቀት በግልፅ ያሳያል። የተፈጠሩ ችግሮችን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ለተማሪዎች ምላሽን በመንፈግ ውጪ እንዲያድሩ በማድረግ፤ በምርቃት ቀናቸው ከእስር ቤት እንዲውሉ በማድረግ፤ ከተመረቁም ቡሃላ መብታቸውን የጠየቁ ተማሪዎችን ዲግሪ በመከልከል የፈፀማቸው አንጋፋ የመብት ጥሰቶች ተጠቃሽ ናቸው።

መሠል ስህተቶች እንደ ሀገር አርዓያ ሊሆን የሚገባው ተቋም ሀገር ውስጥ ከሚገኙ ተቋማት ጭራ እንዲሆን ከማድረጋቸው ባሻገር የመጪውን ትውልድ ተስፋ የሚያቀጭጩ በመሆናቸው ውጤቱን ከመገምገም ባሻገር መሬት ላይ ያለውን ችግር በመፍታት እና ይህንን አንጋፋ ቅሌት ያመጡ አካላትን ተጠያቂ በማድረግ የሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲረባረብ እንጠይቃለን።

@aaumsu
🔥317👌5💯4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ የሐሩን ሚዲያ ምላሽ ምንድን ነበር? https://vt.tiktok.com/ZSq85g9u5/ ያዳምጡ፤ ሪፖስትም ያድርጉ።

@aaumsu
👍15👌3
ኢማን ሬድዋን እንኳን ደስ አለሽ!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ4ተኛ አመት ፋርማሲ ተመሪ የሆነችው እህታችን ኢማን ሬድዋን እንደ አፍሪካ በተደረገ የጤና ስርዓት ኢንተርፕረይነሮች ውድድር ላይ በመሳተፍ አሸናፊ ሆና 2500 ዶላር ተሸላሚ ሆናለች። ይህ ስኬት የትጋቷ እና ጥረቷ ውጤት ነው። ከሷ አልፎ ለሁሉም ተማሪዎች አርአያ በመሆን ሙስሊሙ ጠንክሮ መማርና የሆነ አስተዋጽኦ ለማህበረሰቡ ማበርከት እንዳለበት መልእክት ያስተላልፋል ።

አላህ ይባርክልሽ! ከላቁ ስኬቶችም ደጋግሞ ያድርስሽ!!!! መብሩክክክክክክ!!!

@aaumsu
👏51🎉129🔥7🥰5
ወደ ዩኒቨርስቲዎች በተለይም ጂማ እና ሐረማያ ለመግባት ላሰባችሁ በዘንድሮ ኢንትራንስ ላለፋችሁ ተማሪዎች፦

ዩኒቨርስቲዎቹ ምን ይመስላሉ? ምን ምን አይነት ዲፓርትመንቶቹ አሉ? በየትኞቹ ዘርፎችስ የተሻሉ ናቸው? ከእኛስ ምን ይጠበቃል በሚሉ እና በሌሎች ነጥቦች ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘናል። ስለ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ጠቅለል ያለ መረጃ ይሰጣል።

ተጋባዥ እንግዶች፦

፨ Muhammaddin Muhidin (በጅማ ዩኒቨርስቲ የ5ተኛ አመት ሜዲስን ተማሪ እና የጀመዓው ምክትል አሚር)

፨ Faris Mustefa (የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ምክትል አሚር)

የፕሮግራሙ አስተባባሪ፦ ሚፍታህ ኢብራሒም ነው።

ፕሮግራሙ፦ ነገ ማለትም እሁድ ጷጉሜ 1 / 2018 ዓ.ል ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ @MohammadamminKassaw ይሰጣል። በፕሮግራሙ ላይ መመለስ አለባቸው የምትሏቸውን ጥያቄዎች @MOHAMMADAMMINM ላኩልን። መረጃውን ለሁሉም ይደርስ ዘንድም Share አድርጉት።

@aaumsu
👍41
1_UAT_Test_Taker_Schedule_–_AAU_Test_Site_–_September_7–8,_2026.xlsx
574.7 KB
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ፈተና ጷጉሜ 2 እና 3 ይሰጣል። የተፈተኞች ዝርዝር እና የመፈተኛ ቦታ፣ እንዲሁም የፈተና ሰዓት ከላይ ተያይዟል።

@aaumsu
4