AAU - Muslim Students Union
7.84K subscribers
2.91K photos
185 videos
54 files
836 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
AAU - Muslim Students Union
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስኮላርሺፕ ለመግባት አስባችሁ ለUAT ፈተና ክፍያ፤ የትራንስፖርት ወጪ አቅማችሁ የማይችል ሙስሊም ተማሪዎች፦    ጀመዓችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በዚህ ችግር ምክንያት ተማሪዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከመቀላቀል ወደሗላ እንዳይሉና የሙስሊም ተማሪዎችን ተሳትፎ ለማበረታት በማሰብ የጥቂት ተማሪዎችን የUAT ክፍያ፤ የመመዝገቢያ ወጪ እና የትራንስፖርት…
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ለዩኒቨርሲቲው የUAT ፈተና፣ መመዝገቢያ እና ትራንስፖርት ወጪ ሽፋን በለቀቀው ፎርም መሰረት በቂ አመልካቾችን አጊኝተናል።

በአሁኑ ሰዓት የተላኩልንን መረጃዎች የማጣራት እና የማረጋገጥ ስራ እየሰራን የምንገኝ ሲሆን፤ መረጃቸውን አጣርተን ላፀደቅናቸው ተማሪዎች ነገ ኢንሻአላህ የምናሳውቅ ይሆናል።

በተጨማሪም የሌሎች ተማሪዎችን ወጪ ለመሸፈን የሚያስችል ተጨማሪ ቦታ ካገኘን በቀጣይ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

አላህ ኡማውን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ!

@aaumsu
19👏7
በቀና ልቦች ከተደረገ ርብርብ መካከል ... በሕክምና ላይ ለሚገኙት የዩኒቨርስቲያችን መምህር ዶክተር አብዱናሲር!

አላህ ጥሪያችሁን ሁሉ አሚን ብሎ በኸይር ይመልስ። ሁልጊዜም ኸይርን የምታገኙ፤ በመጥፎ የማትገኙ ያድርጋችሁ። አፊያችሁን ይሙላ፤ ኢማናችሁን ይሙላ፤ ሪዝቃችሁን ያስፋ፤ መዘውተሪያችሁን ፊርደውሰል አዕላን ያድርግ።

በአንድ ወቅት የጅግጂጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት፤ አሁን ደግሞ በAAU ሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት ሌክቸር ነበሩ። አሁን ግን የጉበት ንቅለተከላ ግዴታ ሆኖ በውጭ ሕክምና ላይ ናቸው። እገዛችን ያስፈልጋቸዋልና በቻልነው እንረባረብ። ለሙዕሚን የውንድም ሕመም ሕመሙ ነው። እንደ አንድ ግንብ ሆኖ መተጋገዝ ከአማኝ መገለጫ ነው።

የንግድ ባንክ አካውንት፦ 1000003646096 (Abdenasir Ahmed Ibrahim). የላካችሁበትን screenshot በማድረግ @Niqab_issueBot ላኩልን።

  አላህ ሙሉ አፊያቸውን ይመልስ፤ ኸይር ጀዛችሁንም ይክፈል!!

@aaumsu
🔥84
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን !!!

የቀድሞው የጅግጂጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት፤ አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህር የነበሩት ዶክተር ዶክተር አብዱናሲር አህመድ ወደ አኼራ ሄደዋል። አላህ በጀነተል ፊርደውስ ይቀበላቸው። ለቤተሰባቸውም መፅናናትን ይለግስ።

@aaumsu
💔86😭36😢112
AASTU / ASTU መግባት ለምትፈልጉ፦
ነገ ሐሙስ ከምሽቱ 2:50 ጀምሮ

የመግቢያ ፈተናው ምን ይመስላል፤ አጠቃላይ ማድረግ ያለብኝ ዝግጅት ምንድን ነው፤ የዩኒቨርስቲዎቹ ሁኔታ እንዴት ነው፤ ምን ምን ዲፓርትመንቶች አሉ፤ ምንስ ይጠብቀኛል በሚሉት ነጥቦች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘናል።

ተጋባዥ እንግዶች፦

ኢብራሒም ኸዲር፦ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አካዳሚክ ሴክተር አሚር

መስዑድ ሙስጠፋ፦ በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ

ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ BAIS ተማሪ በሆነው ሚፍታሕ ኢብራሒም የሚመራ ይሆናል። እንዲነሳ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች ከአሁኑ ሰዓት ጀምራችሁ @MOHAMMADAMMINM ላኩ።

ፕሮግራሙ ነገ ሐሙስ ነሐሴ 28 / 2018 ዓ.ል ከምሽቱ 2:50 ጀምሮ @MohammadamminKassaw Live ይካሄዳል። ለሁሉም ይደርስ ዘንድ share አድርጉት።

@MohammadamminKassaw
12
#ሕያው_ምስክር_2

በ ቅርብ ቀን ይጠብቁን!

@aaumsu
🔥15👏6
በአባጂፋሯ ጅማ የተገፈፈ ክብር፤ የተከለከለ ሒጃብ ... በአባጂፋር ልጆች የተደረገ ትግል፤ የተከፈለ መስዋዕትነት፤ የተረጋገጠ ክብር --- በጅማ ዩኒቨርስቲ !

ሕያው ምስክር - 2

አባጂፋር (ረህመቱላሂ ዐለይሂ) ከጅማ መምለካ ተሻግረው፤ ሐበሻንም አቋርጠው ስለሙስሊሞች መብት የሚብሰለሰሉ፤ የሚታገሉ፤ መስዋዕትነት የከፈሉ ታላቅ እና ፍትሐዊ ንጉስ ነበሩ። ሆኖም ግን ከአመታት ቡሃላ፤ በጅማ ከተማ፤ በጅማ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች ባይተዋር ሆኑ። ሙስሊም ስለሆኑ ሊለብሱት ግዴታ የሆነውን ሒጃብ (ኒቃብ) ከመልበስ ተከለከሉ። ለተከታታይ አስር አመታት ያክል በተለያየ ጊዜ፤ በተለያዩ ሰዎች ክብራቸው ተደፈረ።

ይህ እየሆነ ባለበት በ2017 ዓ.ል የአባጂፋር ልጆች መብታቸውን ያስከብሩ ዘንድ የአላህ ፍቃድ ሆነ። በወርሐ ረመዷን ከተራዊህ መልስ ኒቃቢስት ተማሪዎች ወደ ግቢ ካልገቡ እኛም አንገባም በማለት ለተከታታይ አራት ቀናት ታገሉ። መሪዎቻቸው ቢታሰሩም ፀንተው ቆሙ። በአላህ ፈቃድም በፍትሐዊው ንጉስ ሐገር የተነፈገው ነፃነት ተከብሮ ፍትሕ ፀና።

የነበረውን ሂደት፤ የተፈጠሩትን ክስተቶች፤ የመጣውን ውጤት በሕያው ምስክር - 2 የምንዳስስ ይሆናል።

መስከረም - 1
ጁምዓ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ !


በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) እንገናኝ። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ share ያድርጉ።

@aaumsu
🔥23👏32
"የተማሪዎችን እርካታ አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ፖሊስ ምርምር፤ የአመራር ልማት መርሐግብር እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2018 አፈፃፀም ዙሪያ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የቀረበው ጥናት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሁኔታ በግልፅ ያሳየ ነው።" - የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት

ሸገር FM ባወጣው ዘገባ እንዳስቀመጠው የተማሪዎች እርካታን አስመልክቶ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ 47 ዩኒቨርስቲዎች በመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ይህ ውጤት ባለፉት ሁለት አመታት ዩኒቨርስቲው የተማሪዎችን ሐይማኖታዊ እና ሰብዓዊ መብቶች የሚጥሱ መመሪያዎችን በማውጣት፤ በሐይማኖታቸው ጣልቃ ገብቶ ሒጃብ መልበስን በመከልከል፤ ተማሪዎች ትኩረታቸውን ወደ መብት ጥያቄ እንዲያደርጉ በማድረግ የፈፀመውን የአመራር ውድቀት በግልፅ ያሳያል። የተፈጠሩ ችግሮችን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ለተማሪዎች ምላሽን በመንፈግ ውጪ እንዲያድሩ በማድረግ፤ በምርቃት ቀናቸው ከእስር ቤት እንዲውሉ በማድረግ፤ ከተመረቁም ቡሃላ መብታቸውን የጠየቁ ተማሪዎችን ዲግሪ በመከልከል የፈፀማቸው አንጋፋ የመብት ጥሰቶች ተጠቃሽ ናቸው።

መሠል ስህተቶች እንደ ሀገር አርዓያ ሊሆን የሚገባው ተቋም ሀገር ውስጥ ከሚገኙ ተቋማት ጭራ እንዲሆን ከማድረጋቸው ባሻገር የመጪውን ትውልድ ተስፋ የሚያቀጭጩ በመሆናቸው ውጤቱን ከመገምገም ባሻገር መሬት ላይ ያለውን ችግር በመፍታት እና ይህንን አንጋፋ ቅሌት ያመጡ አካላትን ተጠያቂ በማድረግ የሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲረባረብ እንጠይቃለን።

@aaumsu
🔥286👌4💯3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ የሐሩን ሚዲያ ምላሽ ምንድን ነበር? https://vt.tiktok.com/ZSq85g9u5/ ያዳምጡ፤ ሪፖስትም ያድርጉ።

@aaumsu
👍12👌2