AAU - Muslim Students Union
7.85K subscribers
2.91K photos
184 videos
54 files
835 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሙስሊም ተማሪዎችን ጥያቄ አስመልክቶ የአአዩ ሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ምላሽ ምን ነበር?

https://vt.tiktok.com/ZSVggku7N/ በመግባት አዳምጡ፤ ለሌሎችም አሰራጩ።

@aaumsu
🔥133🫡1
Live stream started
እንዲመለሱ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች @Niqab_issueBot ላኩ።
👍8🫡3
Live stream finished (1 hour)
የቀድመው የጅግጂጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይኮሎጂ ዲፕርትመንት ሌክቸር ድጋፋችንን ይሻሉ !

ዶክተር አብዱናሲር አሕመድ በአንድ ወቅት ጂግጂጋ ዩኒቨርስቲን በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉ አንጋፋ ምሁር ናቸው። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህር ሲሆን ባደረበት ፅኑ ሕመም ምክንያት በውጭ ሀገር እንዲታከም ስለተወሰነና ከሕክምና እና ከአንዳንድ ወጪዎች ጋር ተያይዞ የገንዘብ እጥረት ስላጋጠመው እርዳታ ይደረግለት ዘንድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጠይቋል።

ነብያችን ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ሙስሊም ከሌላኛው ሙስሊም ልክ እንደ አንድ አካል ነው ብለዋልና የዶክተርን ችግር ችግራችን አድርገን እንተባበራቸው ዘንድ ጥሪያችን ነው። የአንድን ሙዕሚን ጭንቀት በዱንያ ላይ ያቃለለ አላህ ከአኼራ ጭንቀቱ ያቃልልለታልና በቻልነው አቅም ከዶክተር ጎን በመቆም ጭንቀታቸውን እናቃል። መልዕክቱን ለሌሎችም በማዳረስ በኸይር ስራው ላይ ተሳታፊ እንሁን።

የንግድ ባንክ አካውንት፦ 1000003646096 (Abdenasir Ahmed Ibrahim). የላካችሁበትን screenshot በማድረግ @Niqab_issueBot ላኩልን።

አላህ ሙሉ አፊያቸውን ይመልስ፤ የመጨረሻም ያድርገው።

@aaumsu
😢135👍2🫡2
AAUMSU - Orientation on Admission
AAU - Muslim Students Union
ፕሮግራማችን ባምረ ሁኔታ ተጠናቋል። ሁላችሁም ጥሩ መረጃዎችን እንዳገኛችሁበት ባለሙሉ ተስፋ ነን።

ከጥያቄዎች ብዛት አንጻርና ከመዘናጋትም ያልተመለሰ ጥያቄ ካለ፤ ከላይ በሪከርዱ ላይ ያልተዳሰሰ ጥያቄ ካላችሁ በማንኛውም ሰዓት በ @Aaumuslimstudentsunion1 አናግሩን!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!

@aaumsu
🫡5👏43👍1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት የኢንስታግራም ገፅን https://www.instagram.com/aaumuslimstudents?igsi=MWZyMHZjNW1paWo4Mg==የቲክቶክ ገፅን ደግሞ https://vt.tiktok.com/ZSVggku7N/ Follow አድርጉ። ለሌሎችም Share ያድርጉ።

@aaumsu
🫡51
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሒጃቡ ጀርባ !

በቲክቶክ https://vt.tiktok.com/ZSVG8tMAY/ በመግባት አዳምጡት፤ ሪፖስትም አድርጉ።

@aaumsu
🔥113
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስኮላርሺፕ ለመግባት አስባችሁ ለUAT ፈተና ክፍያ፤ የትራንስፖርት ወጪ አቅማችሁ የማይችል ሙስሊም ተማሪዎች፦

   ጀመዓችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በዚህ ችግር ምክንያት ተማሪዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከመቀላቀል ወደሗላ እንዳይሉና የሙስሊም ተማሪዎችን ተሳትፎ ለማበረታት በማሰብ የጥቂት ተማሪዎችን የUAT ክፍያ፤ የመመዝገቢያ ወጪ እና የትራንስፖርት ክፍያ ለመሸፈን አስቧል። ስለሆነም አቅሙ የሌላችሁና ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተማሪዎች https://forms.gle/Bap5GQQZMigtBKES6 አመልክቱ።

ለማመልከት ዛሬ የመጨረሻ ቀን ሲሆን በቅርቡም ወጭ የሚሸፈንላቸው ተማሪዎችን ይፋ የምናደርግ ይሆናል።

ማስታዎሻ፦ ወጪው የሚሸፈነው አቅሙ ለሌላቸው ተማሪዎች ብቻ ነው። የሚሸፈነውም ለጥቂት ተማሪዎች ብቻ ነው። አላህ ኡማውን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ።

@aaumsu
🥰106👍4🔥2👌2
የሀገራዊ ምክክሩ አንደምታ ... በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ እንገናኝ !

    የሀገራዊ ምክክሩ በዘርፈ ብዙ ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር አድርጎ ምክረ ሀሳቦችን ካጠናቀረ ቀናቶች አልፈዋል። ሕዝበ ሙስሊሙም አጀንዳዎቹን አቅርቦ የመድረኩ አካል እንዲሆኑ አድርጎ ነበር። ለመሆኑ ሀገራዊ ምክክር ምንድን ነው? በምክክር መድረኩ የሕዝበ ሙስሊሙ አጀንዳዎችስ ምን ምን ነበሩ? ምክክሩ ስኬታማ ይሆን ዘንድ መደረግ ያለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ከሀገራዊ ምክክሩስ ልንወስዳቸው የሚገቡ ትምህርቶች ምን ምን ናቸው?

   እነዚህ እና ሌሎች ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት ልዩ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) የሚዘጋጅ ይሆናል።

ቀን፦ እለተ እሁድ ነሐሴ 24 / 2018 ዓ.ል
ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ

  ቀጠሯችንን ቀጠሯችሁ አድርጉ። በሰዓቱ እንገኝ፤ ለሌሎችም እናሰራጭ።

@aaumsu
🔥184🫡3👏1
ስቶሪ እና ፕሮፋይል ቻለንጅ !
ለሱመያ ልጆች
ለኢማም አሕመድ ኢብን ኢብራሒም አል- ጋዚ ልጆች

በመድረካችን አሁናዊ ተጨባጫችንን እናውቃለን፤ ነገ የሚጠብቀንንም እንረዳለን። ስለሀገራዊ ምክክሩ አንደምታ በስፋት ይዳሰሳል። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ አሰራጩት። ስቶሪ እና ፕሮፋይል በማድረግ ለጓደኞቻችሁ አድርሱ። ፕሮግራሙ ለመጪው አመት መሠረት ነውና እንገኝ።

ነገ እሁድ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) እንገናኝ።

@aaumsu
🔥161👌1
የሀገራዊ ምክክሩ ተቋቁሞ ወደ ስራ ሲገባ እንደ ሙስሊም በበቂ ሁኔታ አልተወከልንም ቅሬታችን ነበር። ያ አልፎ የአጀንዳ ማሰባሰቡ ሲጀመር ደግሞ አጀንዳዎቻችን በበቂ ሁኔታ አልተያዙምን በቅሬታ መልኩ አቅርበን ነበር። ያ ሁሉ ታልፎ ምክክሩ ከተቋጨ ሳምንት ሞላው።

እኛም 5 አመታትን ስለፈጀው የምክክር ኮሚሽኑ ሂደት እና ስለሚጠበቀው ውጤት ውይይት ልናደርግ ቀጠሮ ይዘናል። የሀገራዊ ምክክሩ አንደምታ 24 ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል። እንዲነሱ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች ከአሁን ሰዓት ጀምሮ @Niqab_issueBot ላኩልን። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድም በሁሉም መንገድ አሰራጩ። የስቶሪ እና ፕሮፋይል ቻለንጁንም ተቀላቀሉ።

ነገ እሁድ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ... በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) እንገናኝ።

@aaumsu
🔥131
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሙስሊም ተማሪዎችን የፍትሕ ጥያቄ አስመልክቶ የፋና ምላሽ ምን ነበር። https://vt.tiktok.com/ZSVWUFjV9/ ያዳምጡ። ሪፖስት በማድረግም ተደራሽነቱን ያስፉ።

@aaumsu
15🔥4🤬1
AAU - Muslim Students Union
ለግፍ ያላጐነበሰው ንጉሥ 👑 ክፍል 1 ከዘመናት በኋላ በታሪክ ውስጥ አሻራውን ጥሎ ያለፈ አንድ ታላቅ ሰው ወዳፈራችዉ ምድር እንሻገር………… በዙሪያው ያለው ኃይል ሁሉ በእጁ በነበረበት ጊዜ በምሕረቱ፣ ማንም ሊገዳደረው በማይችልበትና ሊበድል ቢፈልግ አንዲት ስራው በቂ በነበረችበት ሰዓት ደግሞ በፍትሑና በዕኩልነቱ የታወቀ ንጉሥ። ዓለም በሩን የከፈተለት፣ ተግባሩ ምንም ኃይልና አቅም የሌላቸውን…
ለግፍ ያላጐነበሰው ንጉሥ 👑

ክፍል 2


ቅንነት ካለ፣
ሰብአዊነት ካለ ፣
ሰላም የሆነውን እምነታችንን እና ሙስሊሞችን ለመቀበል ልቦች በሮቻቸውን ይከፍታሉ።

ነጃሺም ያደረገው ይህንን ነው። ቅን ነበር፣ለቅኖችም ልቡን ክፍት አደረገ፣አላህም በሂደት የሂዳያን መንገድ አገራለት።

የነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች በሀበሻ የገጠማቸውን እንዲህ ሲሉ መስክረዋል:-

“ሀበሻ ገባን። መልካም ጎረቤቶችንም አገኘን። በሃይማኖታችን ምክንያት የሚደረግብን ተጽእኖ አልነበረም። አላህን በሰላም መገዛት ጀመርን። አንድም ችግርና መከራ አላጋጠመንም። የምንጠላውን ነገር አልሰማንም።”


ይህ ሰላም ፣ ሰላም የነሳቸው ቁረይሾች ሀበሻን ቀደም ሲል በንግድ የሚያውቋትን ሁለት ግለሰቦች ያቀፈ ልዑክ ለመላክ ወሰኑ::
ዐብደሏህ ቢን አቢ ረቢዓህ እና ዐምር ኢብኑል ዓስ ስጦታዎችን ይዘው ሐበሻ ደረሱ፡፡ በነጃሺ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደርም እርሱን ከማናገራቸው በፊት ለቀሳውስቱ ስጦታዎችን በማበርከት የመጡበትን ዓላማም አስረዷቸው::
ቀሳውስቱም ደገፏቸው:: ከነጃሺ ፊት በቀረቡ ጊዜም ዐምርኢብኑል ዓስ እንዲህ ሲል ተናገረ፡-

“ንጉሥ ሆይ! በአገርዎ የኛ ሕዝብ አካል የሆኑ ቂላቂል ልጆች ይገኛሉ:: የሕዝባቸውን ሃይማኖት ትተዋል:: ወደ እርስዎ ሃይማኖትም አልገቡም:: እኛም ሆንን እርስዎ የማናውቀውን አዲስና መጤ ሃይማኖት አምጥተዋል:: እኛም ከሕዝባቸው መሪዎችና ልዑላን እንዲሁም ከአባቶቻቸው፣ ከአጎቶቻቸውና ከቅርብ ዘመዶቻቸው ነው የተላክነው:: ወደነርሱ ይመልሷቸው ዘንድ እንሻለን:: እነርሱ (ሹማምንቱ) ከነርሱ የላቀ አመለካከት ያላቸው ናቸው:: በእነርሱ ላይ የፈጸሙትንም ነውር በሚገባ ያውቃሉ:: ለዚህም የሚገባቸውንም ቅጣት ይሰጧቸዋል::”

በስፍራው የነበሩት ቀሳውስትም፡-

“ንጉሥ ሆይ! እኝህ ሁለት ሰዎች የሚሉት እውነት ነው:: የራሳቸው ወገኖች ስለስደተኞቹ የሚያቀርቡት ነገር ይበልጥ ተቀባይነት አለው። በእነርሱ ላይ የፈጸሙትንም ነውር የሚያውቁት እነርሱ ናቸው። ስለዚህ አሳልፈው ይስጧቸውና ወደ ሀገራቸው ይመልሷቸው “
አሉ።

ንጉስ አስሃማ ግን ሁለቱንም ወገን ለመስማት ወሰኑ። ከሰሀቦችም መሪ የነበረው ጃዕፈር ኢብኑ አቡ ጧሊብ ከልብ የወጣ ልብ ይገባል እንዲሉ እንዲህ ሲል ተናገረ:-


“ንጉሥ ሆይ! የድንቁርና ሥርዓት ተከታይ ሕዝቦች ነበርን፡፡

ጣዖታትን እንገዛለን፤የበከተ እንበላለን፤ ዝሙት እንፈጽማለን፡፤ዝምድና እንቆርጣለን፡ በጎረቤቶቻችን ላይ እኩይ ተግባርን እንሠራለን::

ጠንካራው የደካማውን ገንዘብ ይበላል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ላይ እያለን ነበር ….ዘሩን፣ እውነተኛነቱን፣ ታማኝነቱንና ጨዋነቱን የምናውቀው መልዕክተኛ አላህ የላከልን፡፡

ይህ ነብይ ወደ አላህ ጠራን፣አላህንም አንድ አድርገን እንድንገዛው፣ እኛም ሆንን አባቶቻችን ስንገዛ የነበረውን ድንጋይና ጣዖት እንድንተው አስተማረን፡፡

እውነት እንድንናገር፣ አደራ እንድንጠብቅ፣ ዝምድናን እንድንቀጥል፣ ለጎረቤቶቻቸን መልካም እንድንውል መከረን፤ እንዲሁም እርም ከሆኑ ነገሮችና ደም (ያለ አግባብ) ከማፍሰስ እንድንቆጠብ አዘዘን፡፡

(በተጨማሪም) ዝሙት ከመፈጸም፣ በሐሰት ከመመስከር፣ የየቲሞችን ገንዘብ ከመብላት፣ ጥብቅና ንጽሕት የሆኑ ሴቶችን ከማነወር እንድንቆጠብ አዘዘን፡፡

አላህን ብቻ እንድናመልክና በርሱ ላይ አንድም ነገር ላናጋራ፣ ሶላትንም ልንሰግድ፣ ዘካንም ልናወጣ፣ ጾምም ልንጾም አሳስበን፡፡

እውነት ብለን ተቀበልነው:: ከአላህ ይዞ በመጣው ነገር ተከተልነው፤ አላህን ብቻ መገዛት ጀመርን ፤ በርሱም ላይ ማጋራትን አቆምን::

አላህ ሐራም ያደረገውን ክልክል አደረግን፤ የፈቀደውን ነገርም መፈጸም ጀመርን::

በዚህ የተነሳ ነው ወገኖቻችን ጠላት አድርገው የያዙንና
ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን የፈጸሙብን:: መከራ ሲበዛብን፣ ከኃይማኖታችን ሊቀለብሱን ሲጫኑን ወደርስዎ አገር መጣን፡፡ ከሌሎች ንጉሶች እርስዎን መርጠን ጥገኝነት ጠየቅን፡፡ ከርስዎ ዘንድም እንደማንበደል እርግጠኞች ነን።”

ዐምር በዚህ ጊዜ ኢስላም ኢየሱስን በመጥፎ እንደሚያወሳ ለንጉሡ ተናገረ። በጃዕፈር ንግግር ልባቸው የተነካው ንጉሥ ከቁርኣን እንዲያሰማቸው ጠየቁ:: ጃዕፈርም ከቁርኣን የመርየምን ምዕራፍ አነበበላቸው፡፡

ንጉሡ እጅግ ጥልቅ በሆነ ስሜት ያደምጡ ነበር፡፡ እንባቸው ጺማቸውን እስኪያርስ ድረስ አለቀሱ

………ይቀጥላል

@aaumsu
18🥰2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰዓታት ብቻ ይቀሩታል !

የሀገራዊ ምክክሩ አንደምታ ... ምሽት 3:00 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) እንገናኝ።

በሰዓቱ መገኘት፤ መልዕክቱን ለሌሎች ማድረስ እንዳይዘነጋ።

@aaumsu
🔥104
ፕሮግራሙ 30 ደቂቃዎች ብቻ ይቀሩታል። ሌሎችን ማስታወስ አይዘንጋ፤ @aaumsu በሰዓቱ እንገኝ። ርዕሳችን የሀገራዊ ምክክሩ አንደምታ ነው።

@aaumsu
🔥7🫡2👌1
Live stream started