AAU - Muslim Students Union
7.85K subscribers
2.91K photos
184 videos
54 files
835 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
ከወሎ ደሴ ነው ---

ስለ ሒጃብ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ስለደረሰው የመብት ጥሰት፤ ስለሙስሊም ተማሪዎች መብት፤ ስለሕዝበ ሙስሊሙ አጀንዳዎች ጥያቄ አለን ብለዋል። ለሁሉም ጥያቄዎችም ፍትሐዊ መልስ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፍትሕ፤ እኩልነት እና ነፃነት እስኪሰፍን ጥያቄ አለን!

ሒጃብ ለብሶ መማር መብት ነው!!

በሀገር ውስጥ በእኩልነት መተዳደር፤ የሚገባንን በፍትሕ ማግኘት መብት ነው!!!

@aaumsu
🔥1852
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የሶማሌ ክልል ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው ሒጃብን በመከልከል ያወጣው መመሪያ ከልጅነት ጀምሮ ያደጉበትን ባህል እውቅና እንደሚነፍግ ፤ የሐይማኖት ነፃነታቸውን እንደሚፃረር ፤ የክልሉ ተወላጆች በትምህርት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የሚቀንስ እንደሆነ በመጥቀስ መመሪያው ይሻሻልና ሁሉንም አቃፊ የሆነ የትምህርት ስርዓት ይዘረጋ ዘንድ የክልሉ መንግስት እንዲሰራ ጠይቀዋል።

መመሪያው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በትምህርት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ወደሗላ የሚያስቀር ስለሆነ ይስተካከል ዘንድ ሁሉም አካል ሊረባረብ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

@aaumsu
🔥284👍3👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሒጃቧ ታሪኳ !

በቲክቶክ https://vt.tiktok.com/ZSVXjj6CP/ በመግባት ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሪፖስት ያድርጉ።

@aaumsu
🥰10👍1
በዘንድሮው አመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ለወሰዳችሁና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን መቀላቀል ለምትፈልጉ ተማሪዎች፦

ለዚህ ስኬት እንድትበቁ ላደረሳችሁ ጌታችን አላህ ምስጋና ይድረስ። የአመታት ጥረት እና ልፋታችሁን ለትልቅ ስኬት መሠረት የሚሆን ያድርግላችሁ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስገዝ መሆኑን ተከትሎ ከመግቢያ ፈተና እና አጠቃላይ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ማወቅ ያሉባችሁ ነገሮች ስለሚኖሩ ጀመዓችን ነገ ማለትም ሐሙስ ነሐሴ 21 / 2018 ዓ.ል ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በሕብረቱ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) የኦረንቴሽን ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ስለሆነም ቀጠሯችንን ቀጠሯችሁ በማድረግ፤ መልዕክቱንም ለሌሎች በማሰራጨት በሰዓቱ እንገኝ። አላህ ከተሻሉ ስኬቶች ያድርሳችሁ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት !

@aaumsu
🔥106😭1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኒቃቢስቷ መልዕክት
በአስኮ በድር መስጂድ የሴቶች ፕሮግራም ላይ የተላለፈ፦

"ኒቃብ ለብሼ መንቀሳቀስ፤ መማር፤ መስራት መብቴ ነው። መብታችን ሊከበር ይገባል።"

ሙሉ መልዕክቱን https://vt.tiktok.com/ZSVVMbPqD/ በመግባት አዳምጡ። ለሌሎች ይደርስ ዘንድም ኮፒሊንክ ሪፖስት አድርጉ።

@aaumsu
🔥15👌5
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስኮላርሺፕ ለመግባት አስባችሁ ለUAT ፈተና ክፍያ፤ የትራንስፖርት ወጪ አቅማችሁ የማይችል ሙስሊም ተማሪዎች፦

   ጀመዓችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በዚህ ችግር ምክንያት ተማሪዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከመቀላቀል ወደሗላ እንዳይሉና የሙስሊም ተማሪዎችን ተሳትፎ ለማበረታት በማሰብ የጥቂት ተማሪዎችን የUAT ክፍያ፤ የመመዝገቢያ ወጪ እና የትራንስፖርት ክፍያ ለመሸፈን አስቧል። ስለሆነም አቅሙ የሌላችሁና ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተማሪዎች https://forms.gle/Bap5GQQZMigtBKES6 አመልክቱ።

ማስታዎሻ፦ ወጪው የሚሸፈነው አቅሙ ለሌላቸው ተማሪዎች ብቻ ነው። የሚሸፈነውም ለጥቂት ተማሪዎች ብቻ ነው። አላህ ኡማውን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ።

@aaumsu
🔥415
AAU - Muslim Students Union
በዘንድሮው አመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ለወሰዳችሁና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን መቀላቀል ለምትፈልጉ ተማሪዎች፦ ለዚህ ስኬት እንድትበቁ ላደረሳችሁ ጌታችን አላህ ምስጋና ይድረስ። የአመታት ጥረት እና ልፋታችሁን ለትልቅ ስኬት መሠረት የሚሆን ያድርግላችሁ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስገዝ መሆኑን ተከትሎ ከመግቢያ ፈተና እና አጠቃላይ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ማወቅ ያሉባችሁ ነገሮች ስለሚኖሩ ጀመዓችን…
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን መቀላቀል ለምትፈልጉ በሙሉ!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስገዝ መሆኑን ተከትሎ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ከመግቢያ ፈተና እና ከአጠቃላይ የካምፓስ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ማወቅ የሚገቧችሁን ወሳኝ መረጃዎች የምንዳስስበት ልዩ መድረክ አዘጋጅቶላችኋል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ከሚነሱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፦

- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የኢንትራንስ ውጤቴ ስንት መሆን አለበት?
- የዩኒቨርሲቲው የትምህርት እድሎች (Self-sponsored, Government-sponsored/Cost-sharing, Presidential Scholarship, Teaching Scholarship) ልዩነታቸው ምንድን ነው?
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና (UAT) ምን ይመስላል? ምን ዓይነት ጥያቄዎችስ ይካተታሉ? ለመፈተን ምን ማሟላት ያስፈልገኛል?
- እንደ Medicine, Software Engineering እና Law ያሉ ከፍተኛ ውድድር የሚታይባቸውን ትምህርት ክፍሎች ለመቀላቀል ምን ያህል እድል አለኝ?

- ኒቃብ ለብሼ በነጻነት መማር እችላለሁን? ከትምህርቴስ እስተጓጎላለሁን?
- በካምፓስ ቆይታዬ የሃይማኖት ግዴታዎቼን (ሶላት፣ ጾም፣ ዒድ እና ሌሎች የዲን ተግባራትን) ለመፈጸም አመቺ ሁኔታዎች አሉ ወይ?

እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎቻችሁን ይዛችሁ በመምጣት በቂ ምላሽ እንድታገኙ ሁላችሁንም በክብር ጋብዘናል።

📅 ቀን፦ ነገ ሐሙስ
ሰዓት፦ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በህብረቱ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ ስርጭት (Live) 👉 [
@aaumsu]

መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ለምታውቋቸው ሁሉ ሼር በማድረግ ያካፍሉ!

@aaumsu
22🔥4🥰3👍1👏1
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስኮላርሺፕ ለመግባት አስባችሁ ለUAT ፈተና ክፍያ፤ የትራንስፖርት ወጪ አቅማችሁ የማይችል ሙስሊም ተማሪዎች፦

   ጀመዓችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በዚህ ችግር ምክንያት ተማሪዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከመቀላቀል ወደሗላ እንዳይሉና የሙስሊም ተማሪዎችን ተሳትፎ ለማበረታት በማሰብ የጥቂት ተማሪዎችን የUAT ክፍያ፤ የመመዝገቢያ ወጪ እና የትራንስፖርት ክፍያ ለመሸፈን አስቧል። ስለሆነም አቅሙ የሌላችሁና ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተማሪዎች https://forms.gle/Bap5GQQZMigtBKES6 አመልክቱ።

ማስታዎሻ፦ ወጪው የሚሸፈነው አቅሙ ለሌላቸው ተማሪዎች ብቻ ነው። የሚሸፈነውም ለጥቂት ተማሪዎች ብቻ ነው። አላህ ኡማውን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ።

@aaumsu
👏2410
ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀሩት!

ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቀላቀል ለምታስቡ ተማሪዎች በሙሉ የተዘጋጀው ልዩ የውይይት መድረክ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በይፋ ይጀምራል!

ስለ ዩኒቨርሲቲው አሰራር፣ የመግቢያ ፈተና እና የካምፓስ ህይወት ያሏችሁን ጥያቄዎች ይዛችሁ ከወዲሁ ዝግጁ ሁኑ።

በፕሮግራሙ የሚዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
📌 UAT ፈተና፦ የፈተናው ይዘት፣ ዝግጅት እና የመግቢያ መስፈርቶች
📌 የትምህርት እድሎች፦ Self-sponsored, Cost-sharing እና የስኮላርሺፕ ዓይነቶች
📌 የውድድር ክፍሎች፦ Medicine, Software Engineering, Law እና የቅበላ እድሎች
📌 የካምፓስ ህይወት፤ የኒቃብ ሁኔታ እና የዲን ተግባራትን በነጻነት የመፈጸም ሁኔታዎች

📅 ቀን፦ ዛሬ ሐሙስ
ሰዓት፦ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በህብረቱ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ ስርጭት (Live)

👉 @aaumsu

🔔 ቀጠሮዎን እንዳይረሱ አሁኑኑ ማስታወሻ ይያዙ፤ መረጃው ለሚጠቅማቸው ወዳጆችዎም ሼር ያድርጉ!

@aaumsu
8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሙስሊም ተማሪዎችን ጥያቄ አስመልክቶ የአአዩ ሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ምላሽ ምን ነበር?

https://vt.tiktok.com/ZSVggku7N/ በመግባት አዳምጡ፤ ለሌሎችም አሰራጩ።

@aaumsu
🔥133🫡1
Live stream started
እንዲመለሱ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች @Niqab_issueBot ላኩ።
👍8🫡3
Live stream finished (1 hour)
የቀድመው የጅግጂጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይኮሎጂ ዲፕርትመንት ሌክቸር ድጋፋችንን ይሻሉ !

ዶክተር አብዱናሲር አሕመድ በአንድ ወቅት ጂግጂጋ ዩኒቨርስቲን በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉ አንጋፋ ምሁር ናቸው። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህር ሲሆን ባደረበት ፅኑ ሕመም ምክንያት በውጭ ሀገር እንዲታከም ስለተወሰነና ከሕክምና እና ከአንዳንድ ወጪዎች ጋር ተያይዞ የገንዘብ እጥረት ስላጋጠመው እርዳታ ይደረግለት ዘንድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጠይቋል።

ነብያችን ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ሙስሊም ከሌላኛው ሙስሊም ልክ እንደ አንድ አካል ነው ብለዋልና የዶክተርን ችግር ችግራችን አድርገን እንተባበራቸው ዘንድ ጥሪያችን ነው። የአንድን ሙዕሚን ጭንቀት በዱንያ ላይ ያቃለለ አላህ ከአኼራ ጭንቀቱ ያቃልልለታልና በቻልነው አቅም ከዶክተር ጎን በመቆም ጭንቀታቸውን እናቃል። መልዕክቱን ለሌሎችም በማዳረስ በኸይር ስራው ላይ ተሳታፊ እንሁን።

የንግድ ባንክ አካውንት፦ 1000003646096 (Abdenasir Ahmed Ibrahim). የላካችሁበትን screenshot በማድረግ @Niqab_issueBot ላኩልን።

አላህ ሙሉ አፊያቸውን ይመልስ፤ የመጨረሻም ያድርገው።

@aaumsu
😢135👍2🫡2
AAUMSU - Orientation on Admission
AAU - Muslim Students Union
ፕሮግራማችን ባምረ ሁኔታ ተጠናቋል። ሁላችሁም ጥሩ መረጃዎችን እንዳገኛችሁበት ባለሙሉ ተስፋ ነን።

ከጥያቄዎች ብዛት አንጻርና ከመዘናጋትም ያልተመለሰ ጥያቄ ካለ፤ ከላይ በሪከርዱ ላይ ያልተዳሰሰ ጥያቄ ካላችሁ በማንኛውም ሰዓት በ @Aaumuslimstudentsunion1 አናግሩን!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!

@aaumsu
🫡5👏43👍1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት የኢንስታግራም ገፅን https://www.instagram.com/aaumuslimstudents?igsi=MWZyMHZjNW1paWo4Mg==የቲክቶክ ገፅን ደግሞ https://vt.tiktok.com/ZSVggku7N/ Follow አድርጉ። ለሌሎችም Share ያድርጉ።

@aaumsu
🫡51
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሒጃቡ ጀርባ !

በቲክቶክ https://vt.tiktok.com/ZSVG8tMAY/ በመግባት አዳምጡት፤ ሪፖስትም አድርጉ።

@aaumsu
🔥113
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስኮላርሺፕ ለመግባት አስባችሁ ለUAT ፈተና ክፍያ፤ የትራንስፖርት ወጪ አቅማችሁ የማይችል ሙስሊም ተማሪዎች፦

   ጀመዓችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በዚህ ችግር ምክንያት ተማሪዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከመቀላቀል ወደሗላ እንዳይሉና የሙስሊም ተማሪዎችን ተሳትፎ ለማበረታት በማሰብ የጥቂት ተማሪዎችን የUAT ክፍያ፤ የመመዝገቢያ ወጪ እና የትራንስፖርት ክፍያ ለመሸፈን አስቧል። ስለሆነም አቅሙ የሌላችሁና ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተማሪዎች https://forms.gle/Bap5GQQZMigtBKES6 አመልክቱ።

ለማመልከት ዛሬ የመጨረሻ ቀን ሲሆን በቅርቡም ወጭ የሚሸፈንላቸው ተማሪዎችን ይፋ የምናደርግ ይሆናል።

ማስታዎሻ፦ ወጪው የሚሸፈነው አቅሙ ለሌላቸው ተማሪዎች ብቻ ነው። የሚሸፈነውም ለጥቂት ተማሪዎች ብቻ ነው። አላህ ኡማውን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ።

@aaumsu
🥰106👍4🔥2👌2