AAU - Muslim Students Union
7.85K subscribers
2.91K photos
184 videos
54 files
835 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
ሀሳን ኢብኑ ሳቢት ልዩ የስነ-ፅሁፍ ውድድር !

በተደረገው ጥሪ መሠረት ብዙዎች ብዕራቸውን አንስተው ስንኞችን በመቋጠር፤ ሐሳቦችንም በመደርደር በውድድሩ ላይ ተሳትፈዋል። ውድድሩ ስለሕዝበ ሙስሊም የመብት ጥያቄ፤ ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጉዳይ፤ ስለክብራችን፤ ስለነፃነታችን የመክተብ ነው። በግጥምም ሆነ በዝርው፤ ገጠመኝም ሆነ ማንኛውንም ሐሳብ ማቅረብ ይቻላል።

ከ1-3 የሚወጡ ተሸላሚ የሚሆኑ ይሆናል።

1ኛ፦ 1500 ብር፤ የምስክር ወረቀት እና ተጨማሪ ልዩ ስጦታዎች

2ኛ፦ 1000 ብር፤ የምስክር ወረቀት እና ተጨማሪ ልዩ ስጦታዎች

3ኛ፦ 500 ብር፤ የምስክር ወረቀት እና ተጨማሪ ልዩ ስጦታዎች

የጥበብ ውጤቶቻችሁን @Niqab_issueBot ላኩልን።

@aaumsu
🔥93
ለግፍ ያላጐነበሰው ንጉሥ 👑

ክፍል 1

ከዘመናት በኋላ በታሪክ ውስጥ አሻራውን ጥሎ ያለፈ አንድ ታላቅ ሰው ወዳፈራችዉ ምድር እንሻገር…………

በዙሪያው ያለው ኃይል ሁሉ በእጁ በነበረበት ጊዜ በምሕረቱ፣

ማንም ሊገዳደረው በማይችልበትና ሊበድል ቢፈልግ አንዲት ስራው በቂ በነበረችበት ሰዓት ደግሞ በፍትሑና በዕኩልነቱ የታወቀ ንጉሥ።

ዓለም በሩን የከፈተለት፣ ተግባሩ ምንም ኃይልና አቅም የሌላቸውን ምስኪን እንግዶች ዕጣ ፈንታ መቀየር የቻለ ታላቅ ሰው።


ከዚህም ጋር እንግዶቹ በመጡ ጊዜ ስለ ኃይላቸው፣ ስለ ብዛታቸው ወይም ለእርሱ ሊያበረክቱት ስለሚችሉት ነገር አንዳችም ጥቅማ ጥቅምን አልጠየቀም።

ይልቁንም አዳመጣቸው፤
ከዚያም ቀላል የማይባል፣ የታሪክ ሚዛኑን ሙሉ በሙሉ የቀየረና ያስዋበን ፤እስከ ዛሬ ድረስ በዚች ምድር ላይ አሻራውን ያኖረ ቆራጥ ውሳኔን ወሰነ።

የታሪክ መጻሕፍት በፍትሕ የመሰከሩለት፣

በሙስሊሞች ልብ ውስጥም ስሙ ከትልልቅ የፍትሕና የሰላም ምዕራፎች ጋር ተያይዞ የሚነሣ ታላቅ ስብዕና።

ታዲያ ይህ ንጉሥ ማን ነው?

ወደ ምድሩ የተሰደዱትስ እነማን ናቸው?

ከሐበሻ ምድር ታሪክ ውስጥስ የእርሱ አቋም ለምን ትልቁን ቦታ ያዘ?

ይህ ሰውስ እንዴት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ ዋና አካል ሊሆን ቻለ?

የዛሬው ትግላችን ሊጀምር ሚገባው ከትላንቱ ታሪካችን ከዚህ ነው።

💫ዉዱ ንጉሣችን…………
💫አርአያችን ……..
💫የፍትህ ምሳሌያችን……..
💫ዉቡ ታሪካችን…….

ስንታገል ርቀታች እኛው ለእኛው ከመሆን አልፎ ለሌላው እስከመድረስ  ጭምር  እንዲሆን ተምሰሌት የሆነን መሪ

ይህ ታላቅ ስብዕና👇

ንጉሥ አል-አስሐማ ቢን አብጀር (ነጃሺ) ነው።

የኢስለም አሀዳዊ ጥሪን ፈጽሞ መስማት ያልፈለጉት የመካ ቁራይሾች በሙስሊሞች ላይ የቅጣት በትራቸውን አሳረፉ።

አማኞች ግፍና መከራን አስተናገዱ። ችግርና እንግልት ተከተላቸው። ከእምነታቸው በመመለስ እንደነርሱ የጣኦት አምልኮን ይከተሉ ዘንድ ማዕቀብ ስቃይና ጥቃት ተፈጸመባቸው።


ነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) በባልደረቦቻቸው ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ሊከላከሉ እንደማይችሉ ሲገነዘቡ ወደ ሀበሻ ምድር እንዲሰደዱ መከሯቸው። እንዲህም አሏቸው :-

“ወደ ሀበሻ ተሰደዱ። በእርሷ ዘንድ አንድንጉስ አለ። ከእርሱ ፊት ማንም ተበዳይ አይሆንም፣ስለዚህ ተሰደዱ። አላህ ካላችሁበት ሁኔታ አውጥቶ ድልን እስክንጎናጸፍ ድረስ። “

በዚህም መሰረት የነብያቸውን ትእዛዝ ተቀብለው በ5ኛው የነብይነት አመት የመጀመሪያውን ስደት 12 ሆነው በጀልባ ለ1 ሰው ግማሽ ዲናር ከፍለው ወደ ሀበሻ ተጓዙ።

በገዛ ሀገራቸው ያጡትን የአምልኮ ነጻነት በሀበሻው መሪ አስሃማ ወይም ነጃሺ አገዛዝ ስርም ተጎናጸፉ።

የነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች በሀበሻ የገጠማቸውን እንዲህ ሲሉ መስክረዋል:-


……..ክፍል 2 ይቀጥላል

@aaumsu
11👍6🔥2
ሕያው ምስክር - 1
Ustaz Nureddin Abdellah
ሕያው ምስክር - 1

በ11 ብርሃናማ ሌሊቶች መፍትሔ የተገኘለት የ11 አመታት የመብት ጥያቄ --- በዲላ ዩኒቨርስቲ !

አቅራቢ፦ ኡስታዝ ኑረዲን አብደላህ (የዲላ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት የቀድሞ አሚር)

አዘጋጅ፦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት !!

@aaumsu
🔥14🏆32👌21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Haqni hawaasa tokkoof dhabame, hawaasa hundaaf balaadha. Gaaffiin barattoota Muslimaa AAU gaaffii mirga namummaa ti malee dhimma amantii qofa miti!

Sagaleen keenya namoota dabalataatiin akka gahuuf viidiyoo kana share godhaa: https://www.tiktok.com/@aaumsu/video/7677097862420811029

@aaumsu
🔥17
ጀመዓችን የኢንስታግራም አካውንት በከፈተ አንድ ወር ውስጥ

፨ ከ3000 በላይ ተከታዮች
፨ 259,355 View
፨ 19,769 Like

ማግኘት ተችሏል። በመድረኩ የተለያዩ ይዘቶችን በማጋራት ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥሰት ድምፅ ለመሆን፤ ስለተለያዩ ጉዳዮች ግንዛቤ ለመፍጠር ተሞክሯል። ሚዲያ ሀሳቦቻችንን የምንሸጥበት፤ መልዕክታችንን የምናስተላልፍበት ብሎም አጀንዳዎቻችንን የሁሉም አጀንዳ የምናደርግበት መድረክ ነውና https://www.instagram.com/p/DcYr4y-jfXo/?img_index=3&igsi=dmc1d3VnbGg5OHg5 በመግባት አካውንታችንን Follow አድርጉ። ለሁሉም ተደራሽ ይሆን ዘንድም አሰራጩ።

እንኳን ደስ አለን 🎉🎉🎉 !!!

@aaumsu
🎉324🔥1🤩1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሒጃቧ እምነቷ !

ለሁሉም ይደርስ ዘንድ በቲክቶክ https://vt.tiktok.com/ZSVHmXxjj/ በመግባት ኮፒሊንክ ሪፖስት ያድርጉ።

@aaumsu
🔥15👏2🫡2
UG_Extension_Program.pdf
1.3 MB
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መቀላቀል የምትፈልጉ የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች የማመልከቻ ጊዜ ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ክፍት እንደሚሆን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ዝርዝር መረጃ ከላይ የተያያዙት ፋይሎች ላይ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን ማንኛውም የሚያስፈልጋችሁ መረጃ ወይም እገዛ የሚኖር ከሆነ https://t.me/Aaumuslimstudentsunion1 ላይ ጻፉልን።

@aaumsu
👍101🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሒጅራ ካላንደር ከነባሩ ካላንደር ጎን ለጎን እውቅና ተሰጥቶት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰነ በምክክር ፍትሕ ሊመጣ እንደሚችል ያመላከተ ነው !

ቪድዮው ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZSVxo8NXc/ በቲክቶክ በመግባት ኮፒሊንክ ሪፖስት አድርጉ።

@aaumsu
🔥71
የሀገራዊ ምክክሩ አንደምታ --- ታላቅ የውይይት መድረክ ... በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ !

የሀገራዊ ምክክሩ በዘርፈ ብዙ ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር አድርጎ ምክረ ሀሳቦችን ካጠናቀረ ቀናቶች አልፈዋል። ሕዝበ ሙስሊሙም አጀንዳዎቹን አቅርቦ የመድረኩ አካል እንዲሆኑ አድርጎ ነበር። ለመሆኑ ሀገራዊ ምክክር ምንድን ነው? በምክክር መድረኩ የሕዝበ ሙስሊሙ አጀንዳዎችስ ምን ምን ነበሩ? ምክክሩ ስኬታማ ይሆን ዘንድ መደረግ ያለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ከሀገራዊ ምክክሩስ ልንወስዳቸው የሚገቡ ትምህርቶች ምን ምን ናቸው?

እነዚህ እና ሌሎች ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት ልዩ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) የሚዘጋጅ ይሆናል።

ቀን፦ ነሐሴ 24 / 2018 ዓ.ል
ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ

ቀጠሯችንን ቀጠሯችሁ አድርጉ። በሰዓቱ እንገኝ፤ ለሌሎችም እናሰራጭ።

@aaumsu
🔥12👌86👏2
ከወሎ ደሴ ነው ---

ስለ ሒጃብ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ስለደረሰው የመብት ጥሰት፤ ስለሙስሊም ተማሪዎች መብት፤ ስለሕዝበ ሙስሊሙ አጀንዳዎች ጥያቄ አለን ብለዋል። ለሁሉም ጥያቄዎችም ፍትሐዊ መልስ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፍትሕ፤ እኩልነት እና ነፃነት እስኪሰፍን ጥያቄ አለን!

ሒጃብ ለብሶ መማር መብት ነው!!

በሀገር ውስጥ በእኩልነት መተዳደር፤ የሚገባንን በፍትሕ ማግኘት መብት ነው!!!

@aaumsu
🔥1852
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የሶማሌ ክልል ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው ሒጃብን በመከልከል ያወጣው መመሪያ ከልጅነት ጀምሮ ያደጉበትን ባህል እውቅና እንደሚነፍግ ፤ የሐይማኖት ነፃነታቸውን እንደሚፃረር ፤ የክልሉ ተወላጆች በትምህርት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የሚቀንስ እንደሆነ በመጥቀስ መመሪያው ይሻሻልና ሁሉንም አቃፊ የሆነ የትምህርት ስርዓት ይዘረጋ ዘንድ የክልሉ መንግስት እንዲሰራ ጠይቀዋል።

መመሪያው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በትምህርት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ወደሗላ የሚያስቀር ስለሆነ ይስተካከል ዘንድ ሁሉም አካል ሊረባረብ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

@aaumsu
🔥284👍3👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሒጃቧ ታሪኳ !

በቲክቶክ https://vt.tiktok.com/ZSVXjj6CP/ በመግባት ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሪፖስት ያድርጉ።

@aaumsu
🥰10👍1
በዘንድሮው አመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ለወሰዳችሁና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን መቀላቀል ለምትፈልጉ ተማሪዎች፦

ለዚህ ስኬት እንድትበቁ ላደረሳችሁ ጌታችን አላህ ምስጋና ይድረስ። የአመታት ጥረት እና ልፋታችሁን ለትልቅ ስኬት መሠረት የሚሆን ያድርግላችሁ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስገዝ መሆኑን ተከትሎ ከመግቢያ ፈተና እና አጠቃላይ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ማወቅ ያሉባችሁ ነገሮች ስለሚኖሩ ጀመዓችን ነገ ማለትም ሐሙስ ነሐሴ 21 / 2018 ዓ.ል ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በሕብረቱ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ (@aaumsu) የኦረንቴሽን ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ስለሆነም ቀጠሯችንን ቀጠሯችሁ በማድረግ፤ መልዕክቱንም ለሌሎች በማሰራጨት በሰዓቱ እንገኝ። አላህ ከተሻሉ ስኬቶች ያድርሳችሁ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት !

@aaumsu
🔥106😭1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኒቃቢስቷ መልዕክት
በአስኮ በድር መስጂድ የሴቶች ፕሮግራም ላይ የተላለፈ፦

"ኒቃብ ለብሼ መንቀሳቀስ፤ መማር፤ መስራት መብቴ ነው። መብታችን ሊከበር ይገባል።"

ሙሉ መልዕክቱን https://vt.tiktok.com/ZSVVMbPqD/ በመግባት አዳምጡ። ለሌሎች ይደርስ ዘንድም ኮፒሊንክ ሪፖስት አድርጉ።

@aaumsu
🔥15👌5
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስኮላርሺፕ ለመግባት አስባችሁ ለUAT ፈተና ክፍያ፤ የትራንስፖርት ወጪ አቅማችሁ የማይችል ሙስሊም ተማሪዎች፦

   ጀመዓችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በዚህ ችግር ምክንያት ተማሪዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከመቀላቀል ወደሗላ እንዳይሉና የሙስሊም ተማሪዎችን ተሳትፎ ለማበረታት በማሰብ የጥቂት ተማሪዎችን የUAT ክፍያ፤ የመመዝገቢያ ወጪ እና የትራንስፖርት ክፍያ ለመሸፈን አስቧል። ስለሆነም አቅሙ የሌላችሁና ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተማሪዎች https://forms.gle/Bap5GQQZMigtBKES6 አመልክቱ።

ማስታዎሻ፦ ወጪው የሚሸፈነው አቅሙ ለሌላቸው ተማሪዎች ብቻ ነው። የሚሸፈነውም ለጥቂት ተማሪዎች ብቻ ነው። አላህ ኡማውን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ።

@aaumsu
🔥415
AAU - Muslim Students Union
በዘንድሮው አመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ለወሰዳችሁና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን መቀላቀል ለምትፈልጉ ተማሪዎች፦ ለዚህ ስኬት እንድትበቁ ላደረሳችሁ ጌታችን አላህ ምስጋና ይድረስ። የአመታት ጥረት እና ልፋታችሁን ለትልቅ ስኬት መሠረት የሚሆን ያድርግላችሁ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስገዝ መሆኑን ተከትሎ ከመግቢያ ፈተና እና አጠቃላይ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ማወቅ ያሉባችሁ ነገሮች ስለሚኖሩ ጀመዓችን…
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን መቀላቀል ለምትፈልጉ በሙሉ!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስገዝ መሆኑን ተከትሎ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ከመግቢያ ፈተና እና ከአጠቃላይ የካምፓስ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ማወቅ የሚገቧችሁን ወሳኝ መረጃዎች የምንዳስስበት ልዩ መድረክ አዘጋጅቶላችኋል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ከሚነሱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፦

- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የኢንትራንስ ውጤቴ ስንት መሆን አለበት?
- የዩኒቨርሲቲው የትምህርት እድሎች (Self-sponsored, Government-sponsored/Cost-sharing, Presidential Scholarship, Teaching Scholarship) ልዩነታቸው ምንድን ነው?
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና (UAT) ምን ይመስላል? ምን ዓይነት ጥያቄዎችስ ይካተታሉ? ለመፈተን ምን ማሟላት ያስፈልገኛል?
- እንደ Medicine, Software Engineering እና Law ያሉ ከፍተኛ ውድድር የሚታይባቸውን ትምህርት ክፍሎች ለመቀላቀል ምን ያህል እድል አለኝ?

- ኒቃብ ለብሼ በነጻነት መማር እችላለሁን? ከትምህርቴስ እስተጓጎላለሁን?
- በካምፓስ ቆይታዬ የሃይማኖት ግዴታዎቼን (ሶላት፣ ጾም፣ ዒድ እና ሌሎች የዲን ተግባራትን) ለመፈጸም አመቺ ሁኔታዎች አሉ ወይ?

እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎቻችሁን ይዛችሁ በመምጣት በቂ ምላሽ እንድታገኙ ሁላችሁንም በክብር ጋብዘናል።

📅 ቀን፦ ነገ ሐሙስ
ሰዓት፦ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በህብረቱ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ ስርጭት (Live) 👉 [
@aaumsu]

መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ለምታውቋቸው ሁሉ ሼር በማድረግ ያካፍሉ!

@aaumsu
22🔥4🥰3👍1👏1