ምስሉን ፕሮፋይል እናድርግ
በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ
ቻናል እና ግሩፕ ያላችሁ መልዕክቱን በዚያ በኩል አድርሱ
ኢንቦክስ በመግባትም ለምናውቃቸው ሁሉ እንላክ!
ጁምዓ (ነሐሴ 15) ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንገናኝ !
ልብ ጭቆናን አሻፋረኝ ብሎ የሰራውን ተዓምር የዲላ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ትግል ሕያው ምስክር ሆኖ እንቃኛለን። የሌቱ ጨለማ ከሚደርሰው በደል በላይ አያስፈራም ብለው 11 ምሽቶችን ከውጪ ስላሳለፉ እንቁዎች ታሪክ እንዳስሳለን።
ቻለንጁን እንቀላቀል !
@aaumsu

🫡19👏3❤1
💥አደለም ማስክሽን ከ አንገት በላይ ራሱ መከፈት አለብሽ ገና❕
🔥ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከ ሙተነቂቦች መንደር~3
መስጂድ ውስጥ ዙሁር ተሰግዶ ሱና ለመስገድ ልቆም ስል ወደ መስጅድ ስትገባ አየዋት፣ ደና አትመስልም ... ወደ እኔ እየተጠጋች ስትመጣ ሁኔታዋ ግራ ገባኝ። ስሟን እየጠራው በ አትኩሮት ሳያት እያለቀሰች ነው፣ ሄጄ 'ምን ሆነሽ ነው!?' ብዬ አቀፍኳት፣ ጥያቄዎቼ ሳያበቁ ለቅሶዋ እየጨመረ እዛው እንዳቀፍኳት ራሷን ሳተች። በ ድንጋጤ አጠገቤ የነበረችውን ልጅ ጠርቼ ለ ሁለት ይዘናት መሬት ቁጭ አልን፣ ስሟን ደጋግመን እየጠራን ለመቀስቀስ ብንሞክርም ልትነቃ አልቻለችም። እንደ ምንም ራሳችንን አረጋግተን ወደ ክሊኒክ ልንወስዳት ይዘናት ወጣን...
ነርሶቹ 'ተረጋጉ ተረጋጉ ደና ናት!' እያሉ አልጋ ላይ አስተኝተው ግሉኮስ ሰኩላት። ግራ እንደተጋባን እስክትነቃ አጠገቧ ቁጭ ብለን ጠበቅን፣ የግልኮስ ማነስ ነው ሲሉን ወደ መስጂድ ስትገባ ይዛው የነበረውን ምግብ አስታውሼ ቁርስ አልበላችም ማለት ነው ከድካሙ ከፀሀዩጋ ተደማምሮ ይሆናል ብለን ገመትን ግን ለምን እንደዛ አለቀሰች ?!?ከመብሰልሰል እና ከመገመት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻልንም.....
አልሃምዱሊላህ ከሰዓታት ቆይታዎች በሗላ ነቃች፣ ነገር ግን አሁንም ከቅድሙ በባሰ እምባዋ ግጥም ብሎ መንሰቅሰቅ ጀመረች !!
"ይቅርታ አድርጉልኝ"
"ይቅርታ አድርጉልኝ" እያለች ታለቅሳለች
የሆነችው ምኑም ሳይገባን አብረናት ማልቀስ ጀመርን... "በ አላህ አፍው በሉኝ ይቅርታ!" እያለች እየደጋገምች ታለቅሳለች እንደምንም አንዴ በልመና፣ነርሶቹ ሲቆጡም ተረጋጋች። የዚህን ሁሉ ምክንያትም በለቅሶ ታጅባ መንገር ጀመረች .....
ምግብ ይዤ በ ዋናው በር ወደ ግቢ ለመግባት ስሄድ ማስክሽን አውልቂ ብለው በጣም አስቸገሩኝ፣ ዋናው በር ማለት እንግዲ እኛ ሃራም ነው የተባልን ይመስል ድርሽ ማንልበት በር ነው፣ እንኳ ኒቃብ ማስክም እሺ ብለው አያስገቡም። ቀጠለች እኔም ፊቴን አልከፍትም ብዬ በ ሁለተኛው በር ለመሞከር በዛ ጠራራ ጸሐይ ዞሬ ሄድኩኝ። እሱ በር ደሞ ለመስጂድ የቀረበ እና አብዛኛውን ጊዜ ሙስሊም ተማሪዎች ሚጠቀሙት በር ነው እና እንደ ዋናው በር አያስቸግሩም ነበር፣ ምንም እንደማይሉኝ ተስፋ እያረኩ መታወቂያዬን ለ ጥበቆቹ እያሳየው ወደ ውስጥ ልገባ ስል "ነይ ነይ ፊትሽን ክፈቺ እንጂ!!" አሉኝ የቆሙት ጥበቆች አሷ ትፈትሸኝ ለሷ አሳያለው አልኩኝ ወደ ሴቷ ጥበቃ እየጠቆምኩኝ በጣም እየተባባሰባቸውም ስለሆነ ሊሰሙኝ አልቻሉም፣ ረጅም ሰዓት ቆሜ ተከራከርኩ ግን ከማመናጨቅ ውጪ ሊያስገቡኝ ፍቃደኛ አልነበሩም። በጣም ደክሞኝም ስለነበር ማስኩን ከፍቼ አሳየዋቸው እና አለፍኩ።ወደ ውስጥ እየገባሁ ማስኬን ሳስተካክል አይቶኝ በድጋሚ ጠርቶ "ጭራሽ አውልቂ አይቻልም ስልሽ ትለብሺያለሽ እንዴ!!" አለ በቁጣ ••"የምን ማስክ! የምን ፊት መሸፈን ነው! አደለም ማስክሽን ከ አንገት በላይ ራሱ መከፈት አለብሽ ... " እያለ ስለጅልባቤ እንኳ ሳይቀር ለመስማት በሚሰቀጥጥ መልኩ ሲያወራ አልቻልኩም እና ምግቡን እንደያዝኩ ቀጥታ ወጥቼ ወደ መስጅድ ነበር የሄድኩት፣ እዛ እናንተን ሳይ ደሞ ብላ አሁንም መንሰቅሰቅ ጀመረች።
"እናንተ ኒቃቡን አናወልቅም ብላችሁ ለሱ ስትታገሉ እኔ ግን ማስኬን ዝቅ አደረኩኝ, ጭራሽ ማስኬን ዝቅ ሳረግላቸው ደሞ ጸጉርሽን አንገትሽን አሉኝ!!!"
በአሏህ አውፍ በሉኝ••
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
🍂ሁሉም ስለምንታገልለት እስልምና እና ስለ ትግሉ በደምብ እስከተረዳ ድረስ!
🍂የ አንዱ ህመም ሌላውን እስከተሰማው ድረስ!
🍂ጠላት ፊት በ 1 እስከቆምን ድረስ
በ ጥንካሬ እስከጸናን ድረስ፣ በ አላህ እስከተመካን እና እስከታገልን ድረስ የ አሸናፊዎች መንገድ ላይ ነን!!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
✨ሕያው ምስክር ~ 1 ~ በ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ስለተደረገው ታሪካዊ የ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል ሙሉ ሁኔታ ሚዳሰስበት ልዩ መድረክ!
🗓 (ነሐሴ, 15) ጁምዐ ምሽት 3:00LT
በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል @aaumsu

😭28😡16❤7🤬3💔1
🔥ለ ሱመያ ልጆች የተዘጋጀ ታላቅ መድረክ!
🔥ለ ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራህም አል ጋዚ ልጆች የተዘጋጀ ታላቅ መድረክ!
" የ ጥያቄ አለን ትውልድ ሚዘነጋው ትግል የለም!"
የ ትግስት፣ የ ታማኝነት፣ የ ጽናት፣ የ ጥንካሬ፣ የ አንድነት ምሳሌ ሆነው ስላለፉ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!! በ ሕያው ምስክር 1!
🗓ነገ(ጁምዐ) ከ ምሽቱ 3:00 በዚው ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን!

🔥16❤3👍2👌1🏆1
🗯ድምጽ አልባው እምባ!
🔥ከዛው ከዲላ ከሙተነቂቦች መንደር..ነፃነት'ን በልመና!¡
'በመንገዱ' ላይ ላላችሁ ሁሉ ያጠነክራችሁ ዘንድ ዛሬ የ አንዷን እህቴ ታሪክ ፈተና ላጋራችሁ ወደድኩ...
ትላለች••
ከመስጂድ መልስ ቁርስ ሰአት ሲደርስ ሁሌም በምንገባበት የጀርባ በር ሄድኩ። እንደሁሌውም ተረኛ ጠባቂው ማን ይሆን ..¿ እያልኩ ። ኡፍ ያቺ ሴት ከሆነች በቃ አታስገባኝም !! ሳልወድ በግዴ ጠዋት ወደ መስጂድ ስወጣ << ሰላም አደራቹ ለ2 ወር ብቻ >> ብዬ የምለማመጣቸው ነገር ትዝ አለኝ። ክላስ ልንጨርስ 2 ወር ነበር የቀረን። እስከዛው ድረስ ነጻነት'ን በልመና !¡
እንደፈራሁት አትገቢም አለኝ። <<እንዲ ለብሶ መግባት አይቻልም !! ከላይ የተሰጠን ትእዛዝ ነው። ከዚ ቡሃላ በዚ በር እንዳትመጪ>>አለኝ። በፊት በር ሄድኩ። የዋናው በር ጋር ስደርስ የተወሰኑ ሰዎች ሰብሰብ ብለው ስለነበር ልብ አላሉኝም። አልሃምዱሊላህ id አሳይቼ ብቻ ገባሁ።
በሰላም በመግባቴ ደስ እንዳለኝ ክላስ እንዳላረፍድ እየተሯሯጥኩ ወደ ካፌ ሄድኩ። ያለ ወትሮ ከካፌ ውጪ በሩ ላይ ዳቦ እየሰጡ ነበርና ተጠግቼ ሚልካርዴን ሰጠሁት።
<<ይሄን ለብሳችሁ አትምጡ አልተባላቹም!! አይሰሙምኮ>> እያለ አምባረቀብኝ። እንዴት ክው እንዳልኩ: ጸጥ አልኩት። መልስ ከምመላለስ ብዬ ትቼው መንገድ ስጀምር <<ነይ!! ነይ!! >>አለኝ ።
ስመለስ አይዲሽን አምጪ ሲለኝ ሁሌም እንደምለው ID አልያዝኩም ብዬ ሚል ካርዴን ሰጠሁት።
"ያለ id መስጂድ መሄድ አይታሰብም" እያልኩ በ ውስጤ።
"አይዲሽን ስታመጪ ሚልካርዱ ይመለሳል!" አለኝ።
ከእህቶች ጋር ባወራም መፍትሄ አላገኘሁም። ካፌ ሳልደርስ ሳምንታት አለፉ ምግብ መግዣ ብርም አለቀብኝ። ከበፊትም ቤተሰቦቼን ብር መጠየቅ አልወድም ነበር። አሁን ግን ግድ ሆነብኝ።ሳገኝ እየበላው ብዙውን ጊዜ በ ባዶ እያሳለፍኩ ቀስ በ ቀስ እየደከምኩ በመጨረሻ ታምሜ ሆስፒታል የሄድኩበትን ጊዜ አልረሳም።
እጄ ላይ ካኑላ እንደተደረገ ወደ ካፌ ስሄድ ያለ ሚልካርድ አናስገባም ብለው አባረሩኝ፣ ውጪ ያገኘውት ጥላ ስር ቁጭ ብዬ ሳለቅስ <<እዚህ ጋር እንዲ ለብሶ መቀመጥ አይቻልም !!ልጆች ይደነግጣሉ !!>> ያሉኝን ቀን መቼም አረሳውም ።
ታድያ ምን ይሻላል?!?
ከዶርምሜቴ ጋር እያውጠነጠንን 1 አስደናቂ ሃሳብ ጓደኛዬ ፈለቀላት። የሚገርመው እስልምናን ምታከብር ክርስቲያን ነበረች።
ያኔ የሚሰጠን ሚል ካርድ ወረቀት ነበርና ቲክ ተደርጎ ሲያልቅ ሌላ ይተካል። የሷ ወረቀት ስላለቀ ሳታስረክብ አዲስ ወረቀት ተቀበለች። ያለቀውን ሚልካርድ ስም በውሃ አነካክተን አስለቀቅነው።በቦታው የኔን ስም ጽፈንበት ሚልካርድ ወደ ሚቀየርበት ቢሮ ሄደን አስቀየርን። ከዛ በዛ አድርጌ ካፌ መግባት ጀመርኩ።
አቤት ዱዓ፣ ጭንቀት .. ለምን ኒቃብ ለበሽ ብቻ !!"
ብዙ ያልተነኩና የልተዳሰሱ አሻራዎች ያሉበት መንገድ!
✨ሕያው ምስክር ~ 1 ~ ዲላ ዩኒቨርስቲ የነፃነት ትግል!!
🗓ነገ(ጁምዐ) ከ ምሽቱ 3:00 እንገናኝ!

💔22😢10❤8😡4😭1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎉ደርሷሷልል ❕
🔥 ሕያው ምስክር ~ 1 ~ 🔥
ዘመናትን ሲሸጋገር የቆየው የ ጭቆና ብትር በ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ!!
እነሆ ታሪካዊው መድረካችን 1 ብሎ ለ ዛሬ ቀጠሮውን ይዟል! እውነታዎችን በማስተንተን ማንነትን በ አግባቡ መገንባት ላይ ያተኮረው "የሕያው ምስክር" መድረክ በ ታሪክ ገጽ ደምቆ የሰፈረወን የ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል ሊያስቃኛቹ ዝግጅቱን አጠናቋል !!
🗯የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የነፃነት ጉዞ ምን ይመስል ነበር !?
🗯አምስቱ ዋና ጥያቄዎቻቸው ምን ምን ነበሩ ?!
🗯እጅግ ፈታኝና ተስፋ አስቆራጭ የነበረው ትግል በምን መልኩ መፍትሄ ሊያገኝ ቻለ ?!
በ ሙስሊምነታቸው ሲደርስባቸው የነበረውን መራራ በደል "ከሙተነቂቦች መንደር" በ ጥቂቱ ልናስቃኛችሁ ሞክረናል፣ በ ዛሬው ምሽት በ 2017 ስለ ተደረገው የተቀናጀ እና ብዙዎችን ስላስደመመው፣ ጠይቆ ታግሎ ማንነትን እና መብትን በማስከበር ረገድ ትልቅ ተምሳሌት ሆኖ ስላለፈው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል በ ጥልቅ እንዳስሳለን።
✨ከ ሃይስኮል እስከ ኮሌጅ
✨ከ ዩኒቨርሲቲ እስከ ሥራው ዓለም ድረስ ስለ ችግሮቻችን ያሰሰበው ሁሉ፣ ለተጨነቀ እና ለመፍትሄው ለተብሰለሰል ሁሉ ለመንገዳችን ትልቅ ስንቅ ምንሰንቅበት ልዪ መድረክ ነው!
🗓ዛሬ(ጁምዐ) ማታ 3:00 በቀጠሯችን እንገናኝ!

🫡18❤7🤝3
ሰዓታት ብቻ ይቀሩታል!
ምስሉን ፕሮፋይል እናድርግ
በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ
ቻናል እና ግሩፕ ያላችሁ መልዕክቱን በዚያ በኩል አድርሱ
ኢንቦክስ በመግባትም ለምናውቃቸው ሁሉ እንላክ!
ዛሬ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንገናኝ !
@aaumsu
ምስሉን ፕሮፋይል እናድርግ
በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ
ቻናል እና ግሩፕ ያላችሁ መልዕክቱን በዚያ በኩል አድርሱ
ኢንቦክስ በመግባትም ለምናውቃቸው ሁሉ እንላክ!
ዛሬ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንገናኝ !
@aaumsu
🔥12👍2❤1
AAU - Muslim Students Union
https://t.me/aaumsu?livestream=734f01b6cb97f0269e ፕሮግራማችን ሊጀምር ስለሆነ ተቀላቀሉ።
ፕሮግራማችን የተጀመረ ሲሆን የስድስት ኪሎ ካምፓስ ምክትል አሚር የሆኑት ኡስታዝ ኢብራሂም ኸይረዲን በቁርዓን እየከፈቱት ይገኛል።
እንቀላቀል፤ ሌሎችንም እንጋብዝ!
https://t.me/aaumsu?livestream=734f01b6cb97f0269e

Telegram
AAU - Muslim Students Union
This is the official channel of AAU-MSU.
Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303
Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com

🔥10👏4👍1🫡1
👌10❤6🫡2💯1😭1
🫡21⚡5❤2🥰2
"በሰላማዊ መንገድ መጓዝን ምርጫችን አድርገን እየተንቀሳቀሰን ሳለ እነሱ ግን ወደ ማስፈራራት፤ መረበሽ፤ ልጆችን አትመረቁም በማለት፣ ቤተሰብን በመጥቀስ ለማስፈራራት ሞክረዋል።"
@aaumsu
@aaumsu
🔥18✍1
«ኢማን ባይሆን! የአኺራ ጉዳይ ባይሆን ኖሮ ለማለፍ አስቸጋሪ ነበር!»
ሊከለክሉን የሞከሩት ሰዎች ያልገባቸውና እኛ ብቻ የሚገባን ቁልፍ ነገር ይህ ነው።
ሁሉ የሆነው ለዚያ ነው። ... ኢማን ስለሆነ!!!

🔥20👌7❤4💯2🤗2
🔥28👌5🥰3❤2👍2🏆1
❤19🔥11👏6🤗2
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات
ፕሮግራማችን ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲን ታሪካዊ የመብት ትግል ላጋሩን፤ እንደ ታላቅ ወንድም፤ እንደ አሚር እና እንደ ኡስታዝ ሆነው ምክራቸውን ላካፈሉን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የቀድሞ አሚር ኡስታዝ ኑረዲን አብደላህ ከልብ እናመሰግናለን።
እንዲሁምፕሮግራሙ እንዲሳካ ለተነቀሳቀሱ እህት እና ወንድሞች ሁሉ ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ ማለት እንወዳለን!
መጀመሪያ አካባቢ ስለነበረው የኔትዎርክ መቆራረጥ ይቅርታ እየጠየቅን፤ በቀጥታ መከታተል ላልቻላችሁ ሪከርድ የሚለቀቅ ይሆናል።
ህያው ምስክር ፕሮግራማችን በቀጣይም ከሌላ እንግዳና ሌላ አስተማሪ የትግል ታሪክ ጋር በቅርቡ የሚመለስ ይሆናል።

❤21🔥11👏2🫡2🥰1👌1