AAU - Muslim Students Union
7.85K subscribers
2.91K photos
184 videos
54 files
835 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
እህቶች ብቻ የተጋሩት ታሪክ!
በ እህቶች ብቻ የታበሰ እምባ!
💭ዝምተኛው ትግል!


🔥ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከ ሙተነቂቦች መንደር 1

ልክ እንደ ትናንት ከ 3 ዓመት በፊት አንዷ እህቴ ላይ የደረሰውን ነገር ሳይ ነበር ውስጤ የ ትግል እሳት የተቀጣጠለው! ግቢ መግብያ 2 ሰዓት ነበር። በ ሰዓቱ በማላስታሰው ምክኒያት ሙስሊም ተማሪዎች የምንጠቀመው ከ መስጅዳችን(ሙሃጂሪን) ፊት ለፊት ያለውን የ መግብያ በር መጠቀም እንደማንችል እና በ ዋናው በር እንድንዞር ተደረገ፣ ሄድንም!
ከዛ ጥበቆች ፊታችሁን እየከፈታችሁ ... አሉን። በጊዜው ብዙ በ ኒቃብ ኒያህ ማስክ ሚጠቀሙ፣ በ ግቢው ፍርሃት ኒቃብ ማይለብሱ እህቶች ነበሩ። ነገር ግን አንዲት ብቸኛና ጠንካራ ሙተነቂብ ጓደኛችን ነበረች፣ ቀላል ባይሆንም ከ ID ያችን ጋር እያስተያዩን እኛ እንደምንም ገባን፣ ቀድሚያት ስለነበር ኒቃቢስት ጓደኛችንን ወደ ሗላ ዞሬ ሳገኛት ከ ድንጋጤ የተነሳ ትንፋሿ ይቆራረጥ ነበር፣ ሁኔታዋ አሁንም ከ አዕምሮዬ አይጠፋም!
በጋለ ስሜት ለምን ሚለውን 'መልስ የሌለውን ጥያቄ' ጠየኩ፣ ለምን ?! እንዴት ሂጃብ መልበስ ሀበሻ ውስጥ ይከለከላል!? አልኩ... ግን መልስ የለም!!!
የዛች ቀን ለኔ ትልቅ ማንቂያ እና ለ ጽናትም ሰበቤ ነበረች!

ዓመቱ ID ሲቀማ፣ ሲመለስ፣ ሲፈረም እንደምንም አለቀ።
ጊዜ ጊዜን ተክቶ ወደ ግቢ መመለሻ ጊዜያችን ደርሶ እኛም ተመለስን፣ ግቢውም ያደርስ የነበረውን በደል አክርሮ እና አጠናክሮ ጠበቀን! መሳቀቅ ዚክርና ዱዓ እያረጉ ገብቶ መውጣት፣ መሰደብ፣ መደበቅ የዚህ ዓመት ዋና ስራችን ሆነ ሲመታ እንደሚጠነክር ሚስማር እንደሚባለ የ ኒቃቢስቶች ቁጥር ከ 1 ወደ 2, 3 እየጨመረ መጣ! ቢሆንም ከ ስድብና እንግልታቸው የተነሳ ማስክ ለብሰን እንኳ ብቻችንን መንቀሳቀስ ለኛ ሰቀቀን ነበረ፣ ክላስ ካፌ፣ የግቢ በር ብቻችንን መግባት ልክ እንደ ምድር ጀሀነም ነበር ለኛ።

የተማሪዎች ካፌ ቲከሩ "ፊታችሁን ካልከፈታችሁ አትገቡም" ብሎ የምሩን ከመለሰን ቀን ቦሃላ ድርሽ ብለን አናቅም ..... ወሰንንንንንን!
ምናልባት ካፌ በመቅረት ውስጥ ከ ጥበቆቹ ፊትም ዞር እንል ይሆናል፣ በዚህ ሚቀንስልን ጭቅጭቅ እና መጋተት ካለ ብለን ድጋሜ ካፌ ላንመጣ ወስንን!

በ ታሪክ ከተነገረን ግቢያችን በ ቁጥር በዛ ያሉ ወደ 43 ሚጠጉ ኒቃብስቶችን ፊታችሁን ሸፈናችሁ ብሎ ጠቅልሎ ያባረረበት ጊዜ ነበር፣ የኛ ሁኔታም ኒቃብ ከሚለብሱት እኩል ወደዛ ሚያቀና ይመስል ነበር...በዚም መልኩ ጊዜያት ያልፉ ነበር••

እናም 1 ቀን ወደ መስጂድ እየሄድን ሳለን ወደ መውጫው በር እንደተቃረብን የየቀን ዱዓችን ውስጥ ሚኖረው የጥበቃው ኃላፊ አገኘን፣ ከብዙ ስድብ፣ አድካሚና አሰልቺ ንግግር ቦሃላ "ቆይ ግን አሁን አንቺ አዲስ እዚ ያመጣሽው ነገር ነው እንጂ ታች ሀገርሽ ስትማሪ እንዲ ትለብሺ ነበር?!" አለ ወደ ለበስኩት ማስክ እየጠቆመ ..

ጓደኛዬ እጄን ጥብቅ እያረገች ዝም በይው ትለኛለች፣ "አዎ እኔ እንዲው ለብሼ ነው የተማርኩት አዲስ ነገር አደለም!" አልኩት የ ጥላቻ ንዝነዛውን እንደቀጠለ "እሺ አሁን አንቺ ጁንታ ሁኚ ሸኔ ሁኚ ፋኖ ሁኚ በምንድነው ማቀው?!"

ሕያው ምስክር ~ 1
የ ፊታችን ጁምዐ ማታ ከ ምሽቱ 3 ሰዓት ይጠብቁን !

@aaumsu
💔234😡2🔥1🤬1
🚫"የ ጥበብ መጀመርያ እየሱስን ማወቅ ነው"❗️

🔥ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከ ሙተነቂቦች መንደር~2
በ ጊዜ ውስጥ እኔም ያ ውድ የሆነውን ባለ ግርማ ሞገሶቹን ስብስብ ለመቀላቀል ታደልኩ!! ፊታቸውን በመሸፈን ጥሩ ነገር ለማበርከት ከሚታገሉት ውስጥ ለመሆን በቃው🍂!!

የ አዲስ ተማሪዎች መግብያ ጊዜ ደረሰ! ተማሪን ለመቀበል ዋናው በር ላይ በ ኒቃብ መታየት ስለማይታሰብ እኔም በ ማስክ ከተምኩ። እንደዛም ሆኖ አንዱ ኃላፊ እየተከታተለኝ እንደነበር አስተውያለው በኔ አቅጣጫ መምጣት ጀመረ: ሲደርስ "አንቺ!!" ብሎ አንገቴ ላይ ያደረኩትን የ ክበብ መታወቅያ ያዝ በማድረግ፣ "ይሄ የ ምን ክበብ ነው?!" አለኝ •• እኔም "ተማሪ..."
ሕዝብ ፊት እሱንም ስንት አይነት ተማሪ እያለ መቶ ያደረኩትን መታወቅያ በ ንቀት ይዞ እያናገረኝ መሆኑ ሴትነቴን ቢፈታተነውም ዋጥ አድርጌው "የ ሴቶች ማህበር ነው!" አልኩት በ ኩራት እና በ ድፍረት!! እያፌዘ 'የ ሴቶች ማህበር ነው' ብሎ አመናጭቆ ከ አንገቴ ላይ ወረወረው! እንደዛም እየሆነ  አዲስ ግቢውን ከሚቀላቀሉ ተማሪዎች መካከል ኒቃብ ሚልብሱ እህቶች አይጠፉም ነበር። ነገራቶች በጣም የከረሩበት ዓመት ላይ 1 ፍሬሽ ኒቃቢስት ወደ ግቢው ልትገባ ስትል ተመለከትኩ፣ ደስታም ሃዘንም እየተፈራረቀብኝ ምን ሊሏት እንደሚችሉ እያሰብኩ ወደሷ አመራው ... አዲሱ ኃላፊ የተባለው እንዳየን "ቆይ ቆይ ቆይ!! ወዴት ነው!? ሕጉን አታውቁም?! እንዲ ለብሶ መግባት አይቻልም! " አለ ተኮሳትሮ።
ያ ራህማን ዛሬ ደሞ ይሄ ከየት ነው የመጣው እያልኩ በ ውስጤ "አይ አዲስ ስለሆነች ነው፣ ለ ዛሬ ትግባ! አስፈላጊ ከሆነ በ ሴት መፈተሽ ትችላለች" አልኩ ፈጠን ብዬ "አይ አይ!! በጭራሽ ውስጥ አውልቃው ትግባ" አለኝ!
"እንደዛማ አይሆንም! ፍሬሽ ነች ለ ዛሬ ትግባ .."
እንዲው እየተከራከርን ቆይተን በ አቋሙ እንደጸና የ ግል ሃብቱ ይመስል በፍጹም አላስገባም ብሎ መለሳት!

በማስታውሰው ከነሱ ጋር የነበረው የመጨረሻ ንግግሬ ክላስ እየሄድኩ ID የቀሙን ጊዜ ነበር!
🍃ካፌውንም ላይብረሪውንም ምኑንም ምኑንም ከተውነው ቦሃላም አንዳንዴ ደስ ሲላቸው ዶርም ድረስ እየመጡ ኒቃብ መልበሳችንን ሲያዩ id ያችንን ወስደውት ይሄዳሉ። ከሁሉም በላይ ሚገርመኝ ደሞ ፈርመንም ቢሆን መታወቅያችንን ለመቀበል ቢሮ ስንሄድ እንደ ወጉ ሕጎችን ስለማክበር እና ስለ secularism ምክር ቢጤ ነገር ሲሰጡን ሁሌም ማፈጥበት ከራሳቸው ግድግዳው ራስጌ ላይ ያለው "የ ጥበብ መጀምርያ እየሱስን ማወቅ ነው" ሚለው ግልፅፅፅ ብሎ ሚታየው ጽሑፍ ነው ...

ሁለት ሆነን ክላስ ለመግባት እየሄድን ነበር አንዱ የ ጥበቃ ኃላፊ id አምጡ ብሎ ጠራን  ••• 'እእ አልያዝንም' አልነው! በቃ ሁሌም እንደዛ ነው ምንለው፣ ቀምተው ዲሲፕሊን አስፈርመው ስለሆነ ሚሰጡን •• "ወደ ክላስ እየሄድን ነው id ደሞ አልያዝንም" እያልን እንደምንም ለማለፍ ሞከርን፣...ግትር ሲልብን ኃላፊው በ ቅርብ ተቀይሮ የገባም ስለሆነ፣ እስኪ እናሳየው ምንም አያመጣም ብለን አውጥተን አሳየነው። ተቀበለንና "ሂዱ በቃ!" አለን ንቀት በተሞላበት አነጋገር!
"እንዴ ምን ማለት ነው?! ከፈለክ በ ሴት ጥበቃ እንፈተሽ ግን id ወስደህብን እንዴት ነው ግቡ ውስጥ ምንንቀሳቀሰው, ተማሪ መሆናችንን ለማረጋገጥ አልነበር ?! ይሄው id ያችን፣ ተማሪ ነን! ክላስ ረፍዶብናል ስጠን!" እያልን መጠይቅ ያዝን...
መለሰ "ሲጀመር እናንተ እንደ አሸባሪ አልሸባብ ስትሆኑ ነው እንጂ እምነታችሁ እኮ ይሄን አያዝም!" ብሎ "ID ከፈለጋችሁ እሱን ነገር አውልቁና ማስክ አድርጋችሁ መጣችሁ ውሰዱ!" እያለ ስለ ኒቃብ ሲያወራ
"በቃ በቃህ አንተ ስለ እምነታችንም ሆነ ስለ ልብሱ ምንም አታውቅም id ውንም ከፈለክ ውሰደው" ብለን በ ንዴት እየበገንን ወደ ክላስ ሄድን።

ሕያው ምስክር ~ 1
🗓: የ ፊታችን ጁምዐ(ነሐሴ,15) ከ ምሽቱ 3:00LT በ ልዩ መድረክ!

@aaumsu
😡11🤬43😢2🫡2🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሕያው ምስክር - 1

መብታቸው ይከበር ዘንድ 11 ምሽቶችን ከውጪ አድረዋል። መብታቸው ይከበር ዘንድ ለ11 ቀናት ያክል ከክላስ፣ ከምግብ እና ንባብ እንዲርቁ ተደርገዋል። የዲላ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ማለት ነው። ሆኖም በምንም ሳይሸበሩ፤ ምንምም ወደሗላ እንዲሉ ሳያደርጋቸው ታገሉ። መብታቸውን እንዳስከበሩም ያለፋቸውን በክብር ተምረው፤ በነፃነት ሕያዎታቸውን ቀጠሉ።

ሙሉ ታሪኩን በመጪው ጁምዓ ከምሽቱ 3 ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል (@aaumsu) ይጠብቁ። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZSVSeWBf3/ በቲክቶክ በመግባት ኮፒሊንክ ሪፖስት ያድርጉ።

@aaumsu
🔥20🫡21
ምስሉን ፕሮፋይል እናድርግ
በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ
ቻናል እና ግሩፕ ያላችሁ መልዕክቱን በዚያ በኩል አድርሱ
ኢንቦክስ በመግባትም ለምናውቃቸው ሁሉ እንላክ!

ጁምዓ (ነሐሴ 15) ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንገናኝ !

ልብ ጭቆናን አሻፋረኝ ብሎ የሰራውን ተዓምር የዲላ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ትግል ሕያው ምስክር ሆኖ እንቃኛለን። የሌቱ ጨለማ ከሚደርሰው በደል በላይ አያስፈራም ብለው 11 ምሽቶችን ከውጪ ስላሳለፉ እንቁዎች ታሪክ እንዳስሳለን።

ቻለንጁን እንቀላቀል !

@aaumsu
🫡19👏31
💥አደለም ማስክሽን ከ አንገት በላይ ራሱ መከፈት አለብሽ ገና

🔥ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከ ሙተነቂቦች መንደር~3

መስጂድ ውስጥ ዙሁር ተሰግዶ ሱና ለመስገድ ልቆም ስል ወደ መስጅድ ስትገባ አየዋት፣ ደና አትመስልም ... ወደ እኔ እየተጠጋች ስትመጣ ሁኔታዋ ግራ ገባኝ። ስሟን እየጠራው በ አትኩሮት ሳያት እያለቀሰች ነው፣ ሄጄ 'ምን ሆነሽ ነው!?' ብዬ አቀፍኳት፣ ጥያቄዎቼ ሳያበቁ ለቅሶዋ እየጨመረ እዛው እንዳቀፍኳት ራሷን ሳተች። በ ድንጋጤ አጠገቤ የነበረችውን ልጅ ጠርቼ ለ ሁለት ይዘናት መሬት ቁጭ አልን፣ ስሟን ደጋግመን እየጠራን ለመቀስቀስ ብንሞክርም ልትነቃ አልቻለችም። እንደ ምንም ራሳችንን አረጋግተን ወደ ክሊኒክ ልንወስዳት ይዘናት ወጣን...
ነርሶቹ 'ተረጋጉ ተረጋጉ ደና ናት!' እያሉ አልጋ ላይ አስተኝተው ግሉኮስ ሰኩላት። ግራ እንደተጋባን እስክትነቃ አጠገቧ ቁጭ ብለን ጠበቅን፣ የግልኮስ ማነስ ነው ሲሉን ወደ መስጂድ ስትገባ ይዛው የነበረውን ምግብ አስታውሼ ቁርስ አልበላችም ማለት ነው ከድካሙ ከፀሀዩጋ ተደማምሮ ይሆናል ብለን ገመትን ግን ለምን እንደዛ አለቀሰች ?!?ከመብሰልሰል እና ከመገመት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻልንም.....


አልሃምዱሊላህ ከሰዓታት ቆይታዎች በሗላ ነቃች፣ ነገር ግን አሁንም ከቅድሙ በባሰ እምባዋ ግጥም ብሎ መንሰቅሰቅ ጀመረች !!
"ይቅርታ አድርጉልኝ"
"ይቅርታ አድርጉልኝ" እያለች ታለቅሳለች

የሆነችው ምኑም ሳይገባን አብረናት ማልቀስ ጀመርን... "በ አላህ አፍው በሉኝ ይቅርታ!" እያለች እየደጋገምች ታለቅሳለች እንደምንም አንዴ በልመና፣ነርሶቹ ሲቆጡም ተረጋጋች። የዚህን ሁሉ ምክንያትም በለቅሶ ታጅባ መንገር ጀመረች .....

ምግብ ይዤ በ ዋናው በር ወደ ግቢ ለመግባት ስሄድ ማስክሽን አውልቂ ብለው በጣም አስቸገሩኝ፣ ዋናው በር ማለት እንግዲ እኛ ሃራም ነው የተባልን ይመስል ድርሽ ማንልበት በር ነው፣ እንኳ ኒቃብ ማስክም እሺ ብለው አያስገቡም። ቀጠለች እኔም ፊቴን አልከፍትም ብዬ በ ሁለተኛው በር ለመሞከር በዛ ጠራራ ጸሐይ ዞሬ ሄድኩኝ። እሱ በር ደሞ ለመስጂድ የቀረበ እና አብዛኛውን ጊዜ ሙስሊም ተማሪዎች ሚጠቀሙት በር ነው እና እንደ ዋናው በር አያስቸግሩም ነበር፣ ምንም እንደማይሉኝ ተስፋ እያረኩ መታወቂያዬን ለ ጥበቆቹ እያሳየው ወደ ውስጥ ልገባ ስል "ነይ ነይ ፊትሽን ክፈቺ እንጂ!!" አሉኝ የቆሙት ጥበቆች አሷ ትፈትሸኝ ለሷ አሳያለው አልኩኝ ወደ ሴቷ ጥበቃ እየጠቆምኩኝ በጣም እየተባባሰባቸውም ስለሆነ ሊሰሙኝ አልቻሉም፣ ረጅም ሰዓት ቆሜ ተከራከርኩ ግን ከማመናጨቅ ውጪ ሊያስገቡኝ ፍቃደኛ አልነበሩም። በጣም ደክሞኝም ስለነበር ማስኩን ከፍቼ አሳየዋቸው እና አለፍኩ።ወደ ውስጥ እየገባሁ ማስኬን ሳስተካክል አይቶኝ በድጋሚ ጠርቶ "ጭራሽ አውልቂ አይቻልም ስልሽ ትለብሺያለሽ እንዴ!!" አለ በቁጣ ••"የምን ማስክ! የምን ፊት መሸፈን ነው! አደለም ማስክሽን ከ አንገት በላይ ራሱ መከፈት አለብሽ ... " እያለ ስለጅልባቤ እንኳ ሳይቀር ለመስማት በሚሰቀጥጥ መልኩ ሲያወራ አልቻልኩም እና ምግቡን እንደያዝኩ ቀጥታ ወጥቼ ወደ መስጅድ ነበር የሄድኩት፣ እዛ እናንተን ሳይ ደሞ ብላ አሁንም መንሰቅሰቅ ጀመረች።

"እናንተ ኒቃቡን አናወልቅም ብላችሁ ለሱ ስትታገሉ እኔ ግን ማስኬን ዝቅ አደረኩኝ, ጭራሽ ማስኬን ዝቅ ሳረግላቸው ደሞ ጸጉርሽን አንገትሽን አሉኝ!!!"
በአሏህ አውፍ በሉኝ••

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
🍂ሁሉም ስለምንታገልለት እስልምና እና ስለ ትግሉ በደምብ እስከተረዳ ድረስ!
🍂የ አንዱ ህመም ሌላውን እስከተሰማው ድረስ!
🍂ጠላት ፊት በ 1 እስከቆምን ድረስ
በ ጥንካሬ እስከጸናን ድረስ፣ በ አላህ እስከተመካን እና እስከታገልን ድረስ የ አሸናፊዎች መንገድ ላይ ነን!!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሕያው ምስክር ~ 1 ~ በ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ስለተደረገው ታሪካዊ የ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል ሙሉ ሁኔታ ሚዳሰስበት ልዩ መድረክ!

🗓 (ነሐሴ, 15) ጁምዐ ምሽት 3:00LT
በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል
@aaumsu

@aaumsu
😭28😡167🤬3💔1
🔥ለ ሱመያ ልጆች የተዘጋጀ ታላቅ መድረክ!
🔥ለ ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራህም አል ጋዚ ልጆች የተዘጋጀ ታላቅ መድረክ!

" የ ጥያቄ አለን ትውልድ ሚዘነጋው ትግል የለም!"

የ ትግስት፣ የ ታማኝነት፣ የ ጽናት፣ የ ጥንካሬ፣ የ አንድነት ምሳሌ ሆነው ስላለፉ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!! በ ሕያው ምስክር 1!

🗓ነገ(ጁምዐ) ከ ምሽቱ 3:00 በዚው ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን!


@aaumsu
🔥163👍2👌1🏆1
🗯ድምጽ አልባው እምባ!

🔥ከዛው ከዲላ ከሙተነቂቦች መንደር..ነፃነት'ን በልመና

'በመንገዱ' ላይ ላላችሁ ሁሉ ያጠነክራችሁ ዘንድ ዛሬ የ አንዷን እህቴ ታሪክ ፈተና ላጋራችሁ ወደድኩ...
ትላለች••

ከመስጂድ መልስ ቁርስ ሰአት ሲደርስ ሁሌም በምንገባበት የጀርባ በር ሄድኩ። እንደሁሌውም ተረኛ ጠባቂው ማን ይሆን ..¿ እያልኩ ። ኡፍ ያቺ ሴት ከሆነች በቃ አታስገባኝም !! ሳልወድ በግዴ ጠዋት ወደ መስጂድ ስወጣ << ሰላም አደራቹ ለ2 ወር ብቻ >> ብዬ የምለማመጣቸው ነገር ትዝ አለኝ። ክላስ ልንጨርስ 2 ወር ነበር የቀረን። እስከዛው ድረስ ነጻነት'ን በልመና !¡
እንደፈራሁት አትገቢም አለኝ። <<እንዲ ለብሶ መግባት አይቻልም !! ከላይ የተሰጠን ትእዛዝ ነው። ከዚ ቡሃላ በዚ በር እንዳትመጪ>>አለኝ። በፊት በር ሄድኩ። የዋናው በር ጋር ስደርስ የተወሰኑ ሰዎች ሰብሰብ ብለው ስለነበር ልብ አላሉኝም። አልሃምዱሊላህ id አሳይቼ ብቻ ገባሁ።

በሰላም በመግባቴ ደስ እንዳለኝ ክላስ እንዳላረፍድ እየተሯሯጥኩ ወደ ካፌ ሄድኩ። ያለ ወትሮ ከካፌ ውጪ በሩ ላይ ዳቦ እየሰጡ ነበርና ተጠግቼ ሚልካርዴን ሰጠሁት።

<<ይሄን ለብሳችሁ አትምጡ አልተባላቹም!! አይሰሙምኮ>> እያለ አምባረቀብኝ። እንዴት ክው እንዳልኩ: ጸጥ አልኩት። መልስ ከምመላለስ ብዬ ትቼው መንገድ ስጀምር <<ነይ!! ነይ!! >>አለኝ ።
ስመለስ አይዲሽን አምጪ ሲለኝ ሁሌም እንደምለው ID አልያዝኩም ብዬ ሚል ካርዴን ሰጠሁት።
"ያለ id መስጂድ መሄድ አይታሰብም" እያልኩ በ ውስጤ።
"አይዲሽን ስታመጪ ሚልካርዱ ይመለሳል!" አለኝ። 

ከእህቶች ጋር ባወራም መፍትሄ አላገኘሁም። ካፌ ሳልደርስ ሳምንታት አለፉ ምግብ መግዣ ብርም አለቀብኝ። ከበፊትም ቤተሰቦቼን ብር መጠየቅ አልወድም ነበር። አሁን ግን ግድ ሆነብኝ።ሳገኝ እየበላው ብዙውን ጊዜ በ ባዶ እያሳለፍኩ ቀስ በ ቀስ እየደከምኩ በመጨረሻ ታምሜ ሆስፒታል የሄድኩበትን ጊዜ አልረሳም።
እጄ ላይ ካኑላ እንደተደረገ ወደ ካፌ ስሄድ ያለ ሚልካርድ አናስገባም ብለው አባረሩኝ፣ ውጪ ያገኘውት ጥላ ስር ቁጭ ብዬ ሳለቅስ <<እዚህ ጋር እንዲ ለብሶ መቀመጥ አይቻልም !!ልጆች ይደነግጣሉ !!>> ያሉኝን ቀን መቼም አረሳውም ።

ታድያ ምን ይሻላል?!?
ከዶርምሜቴ ጋር እያውጠነጠንን 1 አስደናቂ ሃሳብ ጓደኛዬ ፈለቀላት። የሚገርመው እስልምናን ምታከብር ክርስቲያን ነበረች።

ያኔ የሚሰጠን ሚል ካርድ ወረቀት ነበርና ቲክ ተደርጎ ሲያልቅ ሌላ ይተካል። የሷ ወረቀት ስላለቀ ሳታስረክብ አዲስ ወረቀት ተቀበለች። ያለቀውን ሚልካርድ ስም በውሃ አነካክተን አስለቀቅነው።በቦታው የኔን ስም ጽፈንበት ሚልካርድ ወደ ሚቀየርበት ቢሮ ሄደን አስቀየርን። ከዛ በዛ አድርጌ ካፌ መግባት ጀመርኩ።
አቤት ዱዓ፣ ጭንቀት .. ለምን ኒቃብ ለበሽ ብቻ !!"


ብዙ ያልተነኩና የልተዳሰሱ አሻራዎች ያሉበት መንገድ!
ሕያው ምስክር ~ 1 ~ ዲላ ዩኒቨርስቲ የነፃነት ትግል!!

🗓ነገ(ጁምዐ) ከ ምሽቱ 3:00 እንገናኝ!


@aaumsu
💔22😢108😡4😭1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎉ደርሷሷልል

🔥 ሕያው ምስክር ~ 1 ~
🔥

ዘመናትን ሲሸጋገር የቆየው የ ጭቆና ብትር በ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ!!

እነሆ ታሪካዊው መድረካችን 1 ብሎ ለ ዛሬ ቀጠሮውን ይዟል! እውነታዎችን በማስተንተን ማንነትን በ አግባቡ መገንባት ላይ ያተኮረው "የሕያው ምስክር" መድረክ በ ታሪክ ገጽ ደምቆ የሰፈረወን የ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል ሊያስቃኛቹ ዝግጅቱን አጠናቋል !!

🗯የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የነፃነት ጉዞ ምን ይመስል ነበር !?

🗯አምስቱ ዋና ጥያቄዎቻቸው ምን ምን ነበሩ ?!

🗯እጅግ ፈታኝና ተስፋ አስቆራጭ የነበረው ትግል በምን መልኩ መፍትሄ ሊያገኝ ቻለ ?!


በ ሙስሊምነታቸው ሲደርስባቸው የነበረውን መራራ በደል "ከሙተነቂቦች መንደር" በ ጥቂቱ ልናስቃኛችሁ ሞክረናል፣ በ ዛሬው ምሽት በ 2017 ስለ ተደረገው የተቀናጀ እና ብዙዎችን ስላስደመመው፣ ጠይቆ ታግሎ ማንነትን እና መብትን በማስከበር ረገድ ትልቅ ተምሳሌት ሆኖ ስላለፈው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ትግል በ ጥልቅ እንዳስሳለን።

ከ ሃይስኮል እስከ ኮሌጅ
ከ ዩኒቨርሲቲ እስከ ሥራው ዓለም ድረስ
ስለ ችግሮቻችን ያሰሰበው ሁሉ፣ ለተጨነቀ እና ለመፍትሄው ለተብሰለሰል ሁሉ ለመንገዳችን ትልቅ ስንቅ ምንሰንቅበት ልዪ መድረክ ነው!

🗓ዛሬ(ጁምዐ) ማታ 3:00 በቀጠሯችን እንገናኝ!

@aaumsu
🫡187🤝3
ሰዓታት ብቻ ይቀሩታል!

ምስሉን ፕሮፋይል እናድርግ

በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ
ቻናል እና ግሩፕ ያላችሁ መልዕክቱን በዚያ በኩል አድርሱ
ኢንቦክስ በመግባትም ለምናውቃቸው ሁሉ እንላክ!

ዛሬ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንገናኝ !

@aaumsu
🔥12👍21
1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ብቻ ቀረው!

ዝግጁ?


@aaumsu
🫡15💯4
Live stream scheduled for
Live stream started
ኔትዎርክ እያስቸገራችሁ ያላችሁ ልጆች leave ብላችሁ ደግማችሁ ግቡ!

@aaumsu
👍131
"ዩኒቨርሲቲው ውስጥ የነበሩ አካላት ወደ ረብሻ እና ብጥብጥ እንድንገባ ብዙ ጥረቶችን ሲያደርጉ ነበር።"

@aaumsu
👌106🫡2💯1😭1
"ምንም ነገር ቢፈጠር ወደኃላ አንመለስም። ትምህርታችንንም አንተውም"

- በጊዜው በዲላ ዩኒቨርሲቲ የነበሩ ሙስሊም ተማሪዎች

@aaumsu
🫡2152🥰2
"በሰላማዊ መንገድ መጓዝን ምርጫችን አድርገን እየተንቀሳቀሰን ሳለ እነሱ ግን ወደ ማስፈራራት፤ መረበሽ፤ ልጆችን አትመረቁም በማለት፣ ቤተሰብን በመጥቀስ ለማስፈራራት ሞክረዋል።"

@aaumsu
🔥181
«ኢማን ባይሆን! የአኺራ ጉዳይ ባይሆን ኖሮ ለማለፍ አስቸጋሪ ነበር!»

ሊከለክሉን የሞከሩት ሰዎች ያልገባቸውና እኛ ብቻ የሚገባን ቁልፍ ነገር ይህ ነው።

ሁሉ የሆነው ለዚያ ነው። ... ኢማን ስለሆነ!!!

@aaumsu
🔥20👌74💯2🤗2
"የእናንተ ክብር ማለት የኡማ ክብር ነው!"

- የዲላ ዩኒቨርሲቲ ወንድ ሙስሊም ተማሪዎች

@aaumsu
🔥28👌5🥰32👍2🏆1