🔥41💯8🥰1🫡1
የመጨረሻ ጥሪ!!
ለተመራቂ ተማሪዎች ከዚህን በጀመዓ በኩል የተዘጋጀ ሪቫንና ባይንደር እንዳለ ያሳወቅናቹ ሲሆን አሁን ላይ ሁሉም ነገር ተጠናቆ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የሚደርስ ሲሆን ማዘዝ ፈልጋቹ እስካሁን ያላዘዛቹ እህትና ወንድሞች ስማችሁን ከነ አባት ስም ጋር፣ ካምፓሳችሁን እና ስልክ ቁጥራቹን በቴሌግራም ቦታችን @Niqab_issueBot በመላክ በፍጥነት ተመዝግባቹ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ጊዜው ከማለፉ በፊት ይፍጠኑ
@aaumsu

🤝14👏4❤3🥰3🔥1🤩1
ግብርና የሀገር ምሰሶ እንጂ ውርደት እና ቅጣት አይደለም።
ማረስ ክብር ነው።
እማራለሁ ... አርሳለሁ ... ስለመብቴም እጠይቃለሁ።
ሰላማዊ ትግል !
የተቀናጀ አካሄድ ! !
የማያፈገፍግ ትውልድ ! ! !
@aaumsu
ማረስ ክብር ነው።
እማራለሁ ... አርሳለሁ ... ስለመብቴም እጠይቃለሁ።
ሰላማዊ ትግል !
የተቀናጀ አካሄድ ! !
የማያፈገፍግ ትውልድ ! ! !
@aaumsu
🔥39❤11👌6💯3
በእውነቱ የዩኒቨርሲቲያችን አስተዳደር ሁሉንም የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አካታች የሆኑ፣ የተማሪዎችን ሁለንተናዊ አቅም የሚያሳድጉ እና ጠቃሚ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት እንዲሁም የተማሪዎችን መብት ማክበርና ማስከበር ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ፤ እንዲህ ባሉ የሙዚቃና የጭፈራ ድግሶች ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መገኘቱ በእጅጉ ያሳዝናል።
ውድ የግቢያችን ሙስሊም ተማሪዎች (በተለይም ተመራቂዎች)፤ እኛ ሙስሊሞች ነን! በእስልምናችን ደግሞ ከእንዲህ ያሉ አላህ ከማይወደዳቸው፣ ለጊዜያዊ ስሜት ተብለው ኢማንን ከሚያዳክሙና የጭፈራ ስፍራዎች ራሳችንን እንድንጠብቅ ታዘናል። ለአመታት የደከማችሁበትን እና የለፋችሁበትን ይህንን ታላቅ የምርቃት ስኬት በአላህ እገዛ እዚህ ስላደረሳችሁ ልታመሰግኑትና በሀላል መንገድ ልታከብሩት ይገባል እንጂ፤ ስኬታችሁን በወንጀልና በጭፈራ ማክበር የለባችሁም።
ስለሆነም ማንም ሙስሊም ተማሪ በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ እንዳይገኝና ራሱን ከእንዲህ አይነት ቦታዎች እንዲያርቅ እናሳስባለን። በምትኩ ጊዜያችንን ጠቃሚ በሆኑ ነገሮች እና ለቀጣዩ ህይወታችን ዱዓእ በማድረግ እናሳልፍ።

🫡23❤11👍10👏4
እስክርቢቶውን የጣለ እስክርቢቶ ተሸለመ ! ! !
ከ39 ቀናት በፊት ... በጁምዓ ቀን ... ሙስሊም ተማሪዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ጥያቄያቸውን የሚሰማ አካል ካለ በማለት ተሰባስበው ነበር። አቤት የሚል ጠፍቶ ባለበት ፀሐይ ለምሽት ቦታዋን ለቀቀች። የፌደራል ፖሊሶችም ተማሪዎች ከቦታው ተነስተው እንዲገቡ ግፊት ማድረግ ጀመሩ። ማስፈራሪያዎች እና ዛቻዎችም ቀጠሉ። በዚህ መሐል በአምስት ኪሎ ፍሬሽማን ተማሪ የነበረ "እስክርቢቶ የጣለ አለ?!" - ሲል ጠየቀ። ተማሪውም በዝምታ ውስጥ "ሊያስጥሉኝ ይሞክራሉ፤ ግን አልጣልኩም፤ አልጥልምም።" - የሚልን መልዕክት ካለበት በፅናት በመቆም አስመሰከረ።
በዚያን ሰዓት ይህንን ጥልቅ መልዕክት ያስተላለፈውን ተማሪ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት እና በሕብረቱ የ5ኪሎ ጀመዓ እስክርቢቶ እና ሁለት መፅሐፍ ሸልመውታል።
እስክርቢቶ የጣለ አለ?!
እስክርቢቷችንን አንጥልም።

🔥42❤13✍8👏7🫡1
አመስግኑት እንጂ አታምፁት
ለምርቃት መድረስ ከአላህ ፀጋዎች ነው። እርሱ ለዋለላችሁ ፀጋ አመፅን ማስከተል ትክክል አይደለም። ስለፀጋዎቹ አመስግኑት። የአላህን መንገድ ባልሳተ መልኩ። በተለይም ከሀራም ምሽቶች እና ድግሶች ራቁ። ለእናንተም አይጠቅምም። ሙስሊም ደስታዎን ክለብ በማምሸት አያከብርም። ሙስሊም ደስታውን በጭፈራ አያከብርም። ሙስሊም ደስታውን በኸምር አያከብርም። ውለታ የዋለላችሁን አምላክ አታምፁት። አመስግኑት። እርሱ በሚወደው መልክ፤ በዕርሱ መንገድ ደስታችሁን አክብር።
አላህ ምርቃታችሁን ለኸይር በር ያድርገው።

👍50❤11🥰3👏2
═══════ ✥.❖.✥ ═══════
🌷ِسْمِ اللّٰـهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ🌷
═══════ ✥.❖.✥ ═══════
ምስጋና የአለማት ጌታ ለሆነው አላህ የተገባ ነው፤ እናመሰግነዋለን፣ እርዳታውንና ምህረቱንም እንጠይቃለን፣ በእርሱም ላይ ብቻ እንመካለን። የአላህ ሰላምና እዝነት በነብያችን ሙሐመድ ﷺ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እና እስከ ቂያማ ቀን ድረስ የኢስላምን ቀጥተኛ መንገድ በተከተሉት ላይ ሁሉ ይሁን። ላለፈው አንድ አመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ውስጥ በሀላፍትና በአላህ ውሳኔና በታሪክ አጋጣሚ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶን ቆይቷል። የተጣለብንን አደራ ሁሉንም በብቃት ባንወጣውና የተሰጡንን የቤት ስራዎች በሙሉ ባንተገብርም፣ ጊዜ ማናችንንም አይጠብቅምና የኛም መውጫ ሰዓት ደርሶ ኃላፊነታችንን ለቀጣዩ ትውልድ አስረክበናል። ይህ መልእክቴ ለሀላፍትና ስንብት ሳይሆን፣ በልቤ ውስጥ ያለውን እረፍት የነሳኝን ታላቅ አማና በዱዓ በእንባ ለተገነባው የዩኒቨርሲቲው ሙስሊም ማህበረሰብ፣ ለጀመዓ መሪዎችና በየካምፓሱ የእስልምናን ባንዲራ ከፍ አድርገው ለሚያነሱት ጀግኖች በሙሉ የማስተላልፍበት የታሪክ ምስክርና የስንብት ስጦታዬ ነው።
አላህ ለዚህ ኡማ ከሰጣቸው ታላላቅና ውድ ፀጋዎች መካከል ተነጥሎ ሳይሆን እንደ አንድ አካልና በጀመዓ የመኖርን መለኮታዊ መመሪያ ነው። ጀመዓ ደካሞችን ያጠናክራል፣ የተሳሳቱትን ያስተካክላል፣ ታጋዩን ያነሳል፣ አማኙንም ከመጥመም ይጠብቃል። የነብያችን ﷺ “የአላህ እጅ ከጀማዓ ጋር ነው” የሚለው ንግግርና ተኩላ የሚበላው ብቸኛዋን በግ እንደሆነ ያስተማሩን ጥበብ ከመነጠልና ከመዳከም ሊጠብቀን የሚገባ የህይወት መመሪያችን ነው። ስለዚህም በውስጣችሁ ያለውን ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንደ አንድ ጠንካራ ህንፃ ጡቦች አጥብቃችሁ ያዙ። በመካከላችሁ ያለው ፍቅር፣ መተሳሰብና ቅንነት ከማንኛውም ምድራዊ ፈተና በላይ ሊያሻግራችሁ የሚችል የኢማን ምሰሶ ነውና በጀመዓው ጥላ ስር የምታሳዩት አንድነት የመንፈሳዊ ጥንካሬያችሁ ዋነኛ መገለጫ ይሁን።
ይህ ኡማ ከፍ የሚለውና ክብሩ የሚመለሰው ወጣቶቹ ከመዝናኛ ይልቅ መማርን፣ ከባዶ መፈክሮች ይልቅ ተግባርን ሲያስቀድሙ ብቻ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል። ያለ እውቀት የሚሰራ ሰው ከሚያስተካከለው ይልቅ የሚያበላሸው እንደሚበልጥ ከሰለፎች የተወረሰ ሀቅ ነውና፣ የእያንዳንዳችሁ መሰረት አላህን በመፍራት፣ እውቀትን በመፈለግ ከዚያም ባወቁት በመስራት ሊሆን ይገባል። ራሳችሁን በሁለንተናዊ መልኩ በትምህርታዊም ሆነ በዲናዊ እውቀቶች በሚገባ አጠናክሩ። ቂራአትን፣ ቁርኣንን፣ ሐዲስንና ፊቅህን የጀመዓችሁ ማዕከላዊ ምሰሶ በማድረግ፣ እውቀትን ለኩራት ወይም ለማህበራዊ ደረጃ ሳይሆን ራሳችሁን ከጥመት ለመጠበቅና ማህበረሰባችሁን ወደ እስልምና ብርሃን ለመምራት ተጠቀሙበት።
በዚህ በተጠናቀቀው የስራ ዘመናችን ውስጥ በእምነታችንና በማንነታችን ላይ የተቃጡ ዘርፈ ብዙ ፈተናዎችንና የመብት ጥሰቶችን በጋራ ለመጋፈጥ ሞክረናል። መብትን ጠንቅቆ ማወቅና ጥያቄዎችን በሰለጠነ፣ በህግና በስርዓት በተመራ መንገድ ማቅረብ የመነቃቃታችን ምልክት ነው። ፍትህ የጠቅላላው Universe መረጋጊያ ምሰሶ እንደመሆኑ መጠን፣ በደልን አሚን ብሎ መቀበል ወይም ዙልምን መሸከም በእስልምናችን ዘንድ ፈጽሞ ቦታ የለውም። ማንነታችንና መብታችን ሲነካ በተገቢው ጊዜና ቦታ የሚሰጥ የተደራጀ፣ ሰላማዊና ጽኑ ምላሽ ማሳየት ታሪካዊና ህሊናዊ ኃላፊነታችን ነው። ባለፉት ወራት የጀመርናቸው ህጋዊ ትግሎችና የተደረጉ በርካታ የመብት እንቅስቃሴዎች ገና ዘላቂ መፍትሔ አላገኙም። ስለሆነም ይህንን የመብት ጥያቄ የማስቀጠል፣ የጀመርናቸውን ስራዎች የመከታተልና ወደፊት የመግፋት ከባድ አደራ አሁን በግቢው ውስጥ ባላችሁ መሪዎችና መላው ተማሪዎች ጫንቃ ላይ የወደቀ የትውልድ ዕዳ ነው። ለአላህ ብላችሁ በቅንነት ስትቆሙና ሰዎችን ሳይሆን አላህን ለማስደሰት ስትተጉ፣ የሚመጣው ጫናና ማስፈራሪያ ሁሉ የእምነታችሁ መፈተኛ እንጂ የውርደታችሁ ምክንያት ሊሆን አይችልም።
ይህን ስል ይህ የታሪክ አደራ በግቢው ውስጥ በሚቀሩት ላይ ብቻ የተጣለ አይደለም፤ ይልቁንም የግቢውን ህይወት አጠናቃችሁ ወደ ቀጣዩ የህይወት ምዕራፍ ለምትሸጋገሩ ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠው አደራ የላቀ ነው። የግቢን ህይወት እንጂ እስልምናንና ማህበረሰባዊ ግዴታችሁን እየጨረሳችሁ እንዳልሆነ ልታውቁ ይገባል። ሃላፊነታችሁ እስከ ሞት ደጅ ድረስ የሚቀጥል ነውና፣ አሁን ላይ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እየተደረገ ያለውን ፍትሃዊና ህጋዊ የመብት ጥያቄ ባላችሁበት ቦታ ሁሉ ሆናችሁ በዕውቀታችሁ፣ በንብረታችሁና በሞራላችሁ እንድትደግፉ፣ የጀመዓውን ንቅናቄ ከውጭ ሆናችሁ እንድታግዙ አደራዬ የጸና ነው። የትም ብትሄዱ የኢስላም እውነተኛ ወኪል በመሆን ማህበረሰባችሁን ማገልገልንና ለእሴቶቻችሁ መቆምን አትተው።
በመጨረሻም፣ የቱንም ያህል ለመልካም ስራ ብንጥር የሰው ልጆች ከመሆናችን አንጻር በስራችን ውስጥ ጉድለትና ስህተት አይጠፋምና፣ ሁላችሁም የጌታችንን "ይቅርታም ያድርጉ፤ ጥፋተኞቹን ይለፉም፣ አላህ ለናንተ ሊምር አትወዱምን" (22:24) የሚለውን ቃል አስታውሳችሁ አውፍ ትሉኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ። በቃልም ሆነ በድርጊት የበደልኩትና ያስከፋሁትና ሀቁን ያለ አግባብ የወሰድኩበት አካል ካለ ለማስተካከልና ለመካስ ዝግጁ ከመሆኔ ጋር አፍዉ እንድትሉኝ እየገለጽኩ፣ ይህንን የትውልድ አማና አደራ ለማለት እወዳለው። አላህ ከእነዚያ ከሚፈሩትና መልካም ከሚሰሩት ጋር ነውና ስኬትና ድል ሁልጊዜም ከእናንተ ጋር ይሁን። አውፍ በሉኝ፣ እኔም አውፍ ብያለሁ፤
والسلام عليكم ورحمة الله وبركاته
✍ ወንድማችሁ ዘይድ ሷዲቅ

❤34😢4✍3🥰2
ከዛሬ ለሊት ጀምሮ የአሹራ ቀን ነው ነገ መፆም እንዳይረሳ
عَنْ أَبِي قَتَادَةَ رضي الله عنه أن النبي ﷺ قال : «... وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ، أَحْتَسِبُ عَلَى اللهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ» رواه مسلم
ከአቢ ቀታዳ (ረ.ዐ) ተይዞ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
«... የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አንደ አመት ያስምራል ብዬ ከአላህ እከጅላለው» ሙስሊም ዘግበውታል

🤝7🫡3❤1
ከዚህን በፊት በህብረታችን በኩል ሪቫንና ባይንደር እንዳዘጋጀን ገልፀንላቹ እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ ተሰርቶ ስለተጠናቀቀ ኢንሻአላህ አዛቹ ለከፈላቹ እህትና ወንድሞች ነገ በየግቢዎቻቹ እንዲደርሳችሁ የምናደርግ ይሆናል። በተጨማሪም ለመውሰድ ተመዝግባቹ ክፍያ ላልከፈላቹ እህትና ወንድሞች ክፍያውን አጠናቃቹ እንድትወስዱ ለማስታወስ እንወዳለን።
በተጨማሪ አሁንም መውሰድ የምትፈልጉ እህትና ወንድሞች የተዘጋጀው ባይንደርና ሪቫን በእለቱ ደምቀንና እሴቶቻችንን የምናሳይበት ልዩ ሪቫንና ባይንደር ስለሆነ ስማችሁን ከነ አባት ስም ጋር፣ ካምፓሳችሁን እና ስልክ ቁጥራቹን በቴሌግራም ቦታችን @Niqab_issueBot በመላክ በምንልክላቹ አካውንት ክፍያ ፈፅማቹ መቀበል እንደምትችሉ በደስታ ለማሳወቅ እንወዳለን።

❤7🥰1
📢 ልዩ የፓነል ውይይት በቲክቶክ ! ! ! 📢
ድምፃችንን ከፍ አድርገን የምናሰማባቸውን መድረኮች አብዝቶ ለፈጠረው አምላክ ምስጋና የተገባው ይሁንና በዕለተ እሁድ ሰኔ 7፣ 2017 ዓ.ል የመሰብሰብ እና የመወያየት መብታችንን በመነፈጋችን ምክንያት፣ በሰፊው ተደራሽ ወደ ሆነው የቲክቶክ መድረክ ያዞርነውን ታሪካዊ የፓናል ውይይት ዝርዝር መረጃ ይዘን መጥተናል!
📌 ርዕስ፡- "በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙስሊም ተማሪዎች መብት"
🎙 በዚህ አንገብጋቢ እና ወቅታዊ ርዕስ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሚሰጡን እና ውይይት የሚያደርጉልን ልዩ የክብር እንግዶች ጋብዘናል... እንግዶቻችን ማን ይሆኑ? 🤔 በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል፤ ዝግጅታችንን ይጠብቁ!
🗓 ቀን፡ ሰኞ፣ ሰኔ 22 (Monday, 29 June)
⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት
✨ "እውቀትን መፈለግ መብት ነው፤ እምነትንም በክብር መተግበር እንዲሁ!"
በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያላችሁ ተማሪዎች እና መላው ሕዝበ ሙስሊም በያላችሁበት ሆናችሁ በቲክቶክ ገፃችን ላይ እንድትታደሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እስከዚያው ይህን መልዕክት ለሁሉም በማጋራት የድምፃችን አካል ይሁኑ! የቲክቶክ ገፃችንን Follow በማድረግ ዝግጅቱን ይጠብቁ፦
https://www.tiktok.com/@aaumsu
✊ እወቅ፤ ጠይቅ፤ አስከብር።

🔥33👏8❤6👌1
"ፍትሕ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች!" - በሰመራ ዩኒቨርስቲ የዋንጫ ተሸላሚ የሆነው ዶክተር ሙሐመድ ሐሰን
በሰመራ ዩኒቨርስቲ የወርቅ ሜዳልያ እና ዋንጫ ተሸላሚ ሆኖ የተመረቀው ዶክተር ሙሐመድ ሐሰን በሐይማኖታቸው ምክንያት በደል እየደረሰባቸው ላሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች እና ለአክሱም ሙስሊሞች በምርቃቱ ቀን ድምፁን አሰምቷል። "ኒቃብ ፀጉርን እንጂ አዕምሮን አይፈንም!" - የሚልን መልዕክት ያስተላለፈው የዋንጫ ተሸላሚው ዶክተር ሙሐመድ ሙስሊም ተማሪዎችን የማያገል፤ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚያስተዳድር፤ ፍትሕን የሚያሰፍን መመሪያ እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል። በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጀምሮ እየደረሱ ያሉ የመብት ጥሰቶች ቆመው ፍትሕ ይሰፍን ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !
©️ EHEMSU

🔥36❤13👏4🥰2🫡1
በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል የትም ብንሆን አንረሳውም።
ተማሪ ሆነን አንረሳውም!
ተመራቂ ሆነን አንረሳውም!!
ወላጅ ሆነን አንረሳውም!!!
ከስራ ገብተን አንረሳውም!!!
በዳዮች ሁለንታናዊ እድገታችንን ለማቀጨጭ ሲሉ እየበደሉን ባለበት ሰዓት ልንዘናጋ የምንችልበት ምክንያት የለም።
ደስታ ውስጥ ሆነን አንረሳውም!
ሐዘን ውስጥም ሆነን አንረሳውም!!
የትላንቱ፣ የዛሬው፣ ብሎም የነገው ትውልድ አማና ነውና ባለንበት ቦታም ሆነ ባለንበት ሁኔታ ውስጥ ሆነን ጥያቄ አለን እንላለን። ስለ ሰብዓዊ መብታችን _ ስለሐይማኖታዊ መብታችን _ ስለመማር መብታችን _ ስለዜግነት መብታችን --- ጥያቄ አለን እንላለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

🔥29❤4👍1👌1
በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)። በዚህም ምክንያት ይደሰቱ። እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» (ዩኑስ 58) 📖✨
CONGRATULATIONS TO OUR GRADUATING BROTHERS AND SISTERS 🎉🎉🎉🎆🎆🎆🎆🎆🎉🎉🎉
ከብዙ ልፋትና ጥረት፣ ከስንት የእንቅልፍ ማጣት ሌሊቶች እና ከሐሳብና ጭንቀት ዓመታት በኋላ፣ ለዚህች በናፍቆት ስትጠብቋት ለነበረችው የድል ቀን የደረሳችሁ ውድ ተመራቂ የጀመዓችን አባላት ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ! 🎓🎉
የአመታት ልፋታችሁ ፍሬ አፍርቶ በነገው ዕለት በራሳችሁ የምትኮሩበት፣ ለዚህ ስላበቃችሁም አላህን የምታመሰግኑበት ታላቅ ቀን ነው። ይህ የጉዟቹ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻው እንዳልሆነ አውቃችሁ፣ የሙስሊሙን ዑማ ችግሮች ለመፍታትና በየሙያችሁ ለመታገል በበለጠ ወኔና ጥንካሬ እንደምትጓዙ ባለሙሉ ተስፋ ነን። 💪🌟
ዲናችን ምሉዕ ነውና በደስታም ሆነ በችሮታ ጊዜ እንዴት መሆን እንዳለብን ግልጽ መመሪያዎችን አስቀምጦልናል። እናም አደራ፣ በዚች የልፋታችሁን ፍሬ በምታዩባት የደስታ ቀን አላህን ከማመጽ እንጠንቀቅ። 🤲 እህቶች አለባበሳችሁን በመጠበቅና ከወንዶች ጋር ባለመቀላቀል፣ ወንድሞችም እይታን በመስበርና ለአንተ ተገቢ ካልሆነች ሴት ጋር ባለመገኘት እንዲሁም አላስፈላጊ ከሆኑ ስብስቦች በመራቅና በሰላተል-ጀማዓህ ላይ ሁላችሁም አደራችሁን እንድትወጡና የአላህን ድንበሮች እንድትጠብቁ እናሳስባለን። 🕌✨
ምርቃታችሁ የኸይር በር መክፈቻ ቁልፍ፣ ቀጣዩ የሕይወት ምዕራፋችሁም የተሳካና የሰመረ እንዲሆን ከልብ የመነጨ ዱዓችን ነው፤ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! 🎆
የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፍ የምትፈልጉ የጀመዓችን አባላት በ @Aaumuslimstudentsunion1 በኩል ላኩልን።
@aaumsu🌟✨

🎉28❤6👌1
በመጀመሪያ ለሀሉም ተመራቂ ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ እንኳን ደስ አላችሁ
መብሩክ ለሁላችሁም
በመቀጠል
ለ 6 ኪሎ ዳዕዋና ቂርአት ሴክተር ተመራቂ ወንድሞች በተለይም ለወንድሜ ለአቡበክር እንኳን ደስ አለህ
በመሰለስም ለ 4 kilo ጀመዓ ተመራቂ አሚሮች
እና ለሁሉም Information Systems(IS) ተመራቂ ወንድምና እህቶች እንኳን ደስ አላችሁ
ወንድማችሁ ሙሐመድ ዑመር
የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፍ የምትፈልጉ የጀመዓችን አባላት በ @Aaumuslimstudentsunion1 በኩል ላኩልን።
@aaumsu
መብሩክ ለሁላችሁም
በመቀጠል
ለ 6 ኪሎ ዳዕዋና ቂርአት ሴክተር ተመራቂ ወንድሞች በተለይም ለወንድሜ ለአቡበክር እንኳን ደስ አለህ
በመሰለስም ለ 4 kilo ጀመዓ ተመራቂ አሚሮች
እና ለሁሉም Information Systems(IS) ተመራቂ ወንድምና እህቶች እንኳን ደስ አላችሁ
ወንድማችሁ ሙሐመድ ዑመር
የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፍ የምትፈልጉ የጀመዓችን አባላት በ @Aaumuslimstudentsunion1 በኩል ላኩልን።
@aaumsu
❤11⚡2🔥1👏1
بِـــسْمِ اللّٰـهِ الرَّحْـمَنِ الرَّحِيــمِ
ለመላው የአዲስአበባ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ለዚህ ቀን በመድረሳችሁ እንኳን ደስስ አላችሁ ፤በእውነቱ ከ4 እስከ 7 አመት ተምሮ የተለያዩ ነገሮችን አሳልፎ ለዚህ መብቃት ትልቅ ነገር ነው።
በመቀጠልም በሁለት አመት የአአዩ ቆይታዬ ዪንቨረስቲውን እንድለምድ፣የጀመዓህ ስራ ላይ እንድሳተፍ እንዲሁም ውብ በሆኑ ምክሮች የተለያዪ መንገዶችን ስትጠቁምኝ ለነበራችሁ ወንድሞች የእንኳን አደረሳችሁ መልክቴን ማስተላለፍ እወዳለው።
በመጀመርያ አመት የስድስት ኪሎ ካምፓስ ቆይታዬ መስጂድ ከማሳየት ጀምሮ ብዙ ነገሮችን ያስተማራችሁኝ ወንድሞቼ አቡበክር፣አብዱልሀሚድ፣ሰይፈዲን፣መህይዲን፣ሙከረም እና ሙከሚል እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ።ከእንግዲህ ያለውን የህይወት ምዕራፍ አላህ እንዲያገራላችሁ ከልቤ እለምነዋለው።
በሁለተኛ አመት የአራት ኪሎ ካምፓስ ቆይታዬ ወቅት ካገኘዋቸው ወንድሞች ወስጥ፦
የቀድሞ የአአዩሙተህ ፀሃፊ ዘይድ ሷዲቅን ጀመዓህ ምን ማለት እንደሆን ከማስተማር ጀምሮ፤ ጀመዓው ውስጥ ያሉ እና የሚከናወኑ ተግባራትን እስከማስለመድ ለዋልክልኝ ውለታ ሁሉ አላህ ኸይር ጀዛኡን ይክፈልህ።እዚህ ደረሰህ በማየቴ እጅጉኑ ከሚደሰቱብህ ወንድሞችህ ወስጥ ነኝ። እንኳን ደስ አለህ!!!
እንዲሁም በአራት ኪሎ ካምፓስ የደዓዋና ቂራዓት ሴክተር አሚር የነበረው ፉኣድ ፈድሉ በአራት ኪሎ ካምፓስ ካገኘዋቸው ውድ ወንድሞች ውስጥ አንዱ ነህ፤ ብዙ ነገረን አስተምረኸኛል።ለጀመዓውም ትልቅ እና ግዜ ማይጥለው አስተዋፆ እንዳበረከትክ መስካሪ ነኝ።እንኳን ደስ አለህ!!
በመጨረሻም ለቀድሞ የአአዩሙተህ ፕሬዝዳንት መህፉዝ ነጋሽ የእንኳን ደስ አለህ መልክቴን እያስተላለፍኩ ግቢ ወስጥ ብዙ ነገሮችን ካንተ ተምሬያለሁ፤አላህ መልካምን ምንዳ ይመንዳህ።
በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስኳችሁ ወንድሞች እንዲሁም ስማችሁን ያልጠቀስኳችሁ ወንድምና እህቶች በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!!
መልካም ሌላ የህይወት እርከን👋👋
✍️أخوكم عبد الله

❤18
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ድምፃችን አይታፈንም!
በመጪው ሰኞ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት የቲክቶክ ገፅ ( https://www.tiktok.com/@aaumsu ) ላይ Live እንገናኝ። ድምፃችንን ለማፈን መድረክ ቢነፍጉንም ስለመብቶቻችን ለመወያየት፤ ከምሁራን አንደበት እውቀትን ለመቅሰም በበይነመረብ ቀጠሮ ይዘናል። ቀጠሯችንን ቀጠሯችሁ አድርጉ። ለሌሎችም አሰራጩ።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !
@aaumsu
በመጪው ሰኞ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት የቲክቶክ ገፅ ( https://www.tiktok.com/@aaumsu ) ላይ Live እንገናኝ። ድምፃችንን ለማፈን መድረክ ቢነፍጉንም ስለመብቶቻችን ለመወያየት፤ ከምሁራን አንደበት እውቀትን ለመቅሰም በበይነመረብ ቀጠሮ ይዘናል። ቀጠሯችንን ቀጠሯችሁ አድርጉ። ለሌሎችም አሰራጩ።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !
@aaumsu
🔥25👏7🫡3❤2
رسالة تهنئة لخريجي جامعة أديس أبابا المسلمين - دفعة 2026
بسم الله الرحمن الرحيم
إخواني وأخواتي، خريجي جامعة أديس أبابا المسلمين، أبناء الحبشة الغالية، أرض الإسلام الأولى،
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته،
أبارك لكم من أعماق قلبي بمناسبة تخرجكم في العام 2026، هذا الإنجاز العظيم الذي كان ثمرة جهدٍ وتعبٍ وسهرٍ طويل. أنتم اليوم تحصدون ما زرعتم، وتثبتون أن الإرادة والعزيمة تصنع المستحيل.
ولكنني لا أستطيع أن أمرَّ دون أن أُحيي فيكم شيئاً أعظم من الشهادة الجامعية، ألا وهو صبركم وثباتكم على دينكم وهويتكم في وجه كل التحديات، في بلدنا الحبيب إثيوبيا التي عرفت الإسلام منذ فجر الدعوة، واستقبلت الصحابة الكرام في أول هجرة في التاريخ الإسلامي. خاصةً أخواتنا المتنقبات اللواتي واجهنَّ نظرات التهميش والمعاملة الجائرة، ومع ذلك مضينَ قدماً، لم يلتفتنَ خلفهن، بل حملنَ نقابهنَّ كتاجٍ فوق رؤوسهنَّ، وخرجنَ من رحم المحنة أقوى وأعزَّ.
أنتنَّ يا صاحبات النقاب، أسطورة هذا الجيل، وقصة كفاح تستحق أن تُروى في تاريخ الحبشة المجيد. لم يمنعكنَّ ظلمٌ ولا تضييقٌ من مواصلة الطريق، بل كان نقابكنَّ درعاً، وإيمانكنَّ سلاحاً، ونجاحكنَّ اليوم هو الرد الأبلغ على كل من شكّ فيكنَّ.
قال الله تعالى في كتابه العزيز:
{وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَنتُمُ الْأَعْلَوْنَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ}
[آل عمران: 139]
وقال رسول الله ﷺ:
«عَجَبًا لِأَمْرِ الْمُؤْمِنِ، إِنَّ أَمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وَلَيْسَ ذَاكَ لِأَحَدٍ إِلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إِنْ أَصَابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ فَكَانَ خَيْرًا لَهُ، وَإِنْ أَصَابَتْهُ ضَرَّاءُ صَبَرَ فَكَانَ خَيْرًا لَهُ»
[رواه مسلم]
أقول لكم جميعاً: هذا التخرج ليس نهاية الطريق، بل بداية مرحلة جديدة من العطاء. كونوا سفراء للإسلام في مجتمعاتنا الحبشية، واحملوا علمكم وأخلاقكم أينما ذهبتم، واثبتوا أن المسلم القوي يُحدث الفرق حيثما حلّ.
أسأل الله أن يبارك لكم في شهادتكم، وأن يجعلها سبباً لخير الدنيا والآخرة، وأن يوفقكم في مستقبلكم، ويعينكم على كل صعوبات الحياة، وأن يحفظ بلدنا إثيوبيا وينصر أهلها على كل سوء.
تهانئي لكم، وأفتخر بكم جميعاً. والسلام عليكم ورحمة الله وبركاته.🤗
اختكم بنت أبرار🥰

🔥13❤5🫡1
መብሩክክክ!
አልፍፍፍ መብሩክክክ!!
Congradulations !!!!
እንኳን ደስ አላችሁ !!!
ዩኒቨርሲቲ ከሚሰጠን የማይተካ ፀጋዎች መካከል በየትኛውም አጋጣሚ ልናገኛቸው የማንችላቸውን ከተለያየ ቦታ የተለያየ ልምድ፣ እውቀት ማንነት እና እይታ ያላቸውን ወንድም እህቶችን ነው። የዩኒቨርስቲ ጀመዓ ደግሞ ይህንን የተለያዬ ቋንቋ፣ መነሻ እና ቀለም ያለውን ስብስብ ለአንድ አላማ፣ በአንድ ቤት በአላህ መንገድ ላይ ያስተሳስራል። በዚህ የተቀደሰ መንገድ ውስጥ ያገኘሗችሁ ወንድሞቼ፣ እህቶቼ፣ ተማሪዎቼ --- የዛሬው ደስታችሁ ደስታዬ ነውና እንኳን ደስ አላችሁ። 🎉🎉🎉🎉🎉 Congradulations ! ! !
መሕፉዝ ነጋሽ--- የሕብረታችን ፕሬዚዳንት ... በመንገዱ ውስጥ በአቋም መፅናትን ከአንተ ተምሬያለሁ። እንኳን ደስ አለህ! ዘይድ ሷዲቅ--- የሕብረታችን ፀሐፊ ... ለመንገዱ መስዋዕት መሆንን በተግባር አሳይተኸናል። ለጀመዓችን ጠንካራነት አስተዋፅዖህ ትልቅ ነው። Congrats ! አብዱልሐሚድ አሕመድ--- የሕብረታችን ም/ፕሬዚዳንት ... ግቢ ከገባህበት ጊዜ አንስቶ በኡስታዝነት ከማገልገል ጀምሮ የነበረህ አስተዋፅዖ ጉልህ ነበር። እንኳንም ለዚህ በቃህ። አረፋት ሙሐመድ--- የልደታ ካምፓስ ጀመዓ አሚር ... እርጋታህ፣ ሐሳቦችህ፣ ተስፋህ ትምህርትም ብርታትም ነበሩ። የዳሩልአርቀም የመሪነት ፕሮጀክትን በማስፈፀም ሂደት አሻራህ ከፍ ያለ ነበር። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እንደምትሆን አልጠራጠርም። እንኳን ደስ አለህ።
አብዱረህማን (የሰፈረሰላም ጀመዓ አሚር)፣ ሰይፈዲን (6ኪሎ)፣ ሙሐመድ ሙሐመድበሺር፣ አቡበክር (የ6ኪሎ ጀመዓ ም/አሚር)፣ ሰዒድ ሙሐመድ (ፖለቲካል ሳይንስ)፣ አንዋር (5ኪሎ)፣ አንዋር (ኮሜርስ)፣ ፉአድ ፈድሉ፣ ይስሐቅ አምሳሉ፣ ሁሴን (ሸዋሮቢት)፣ አሚር (ኮቻ)፣ ተማም ዳኜ፣ ገና ዱሬሳ፣ በረንቱ፣ ሙሕዲን (ቡታጅራ)፣ አይመን (ቻይንስ / ኒሃው) እንዲሁም ሌሎች በስም ያልጠቀስኳችሁ ወንድሞቼ፤ ስለደስታችሁ ደስስ ብሎኛልና እንኳን ደስ አላችሁሁሁ።
ረውዳ አህመድ፣ ነብያት ሰዒድ፣ ኢክራም ሙሐመድ፣ ነጃት ሁልጫፎ፣ ኢክራም ሱለይማን፣ ሀሊ ዑመር፣ መኪያ ዒሳ፣ ኢክራም ሰዒድ፣ ሀናን ሙሐመድ፣ ሲሐም ባርቀዳ፣ ነዒማ (Law)፣ ሀያት ሙሐመድ፣ ያስሚን ሙሐመድ፣ ተምኪን (psychology)፣ ዛሕራ ነስሮ፣ ሶብሪን ጀማል፣ ነጃት (ፖለቲካል ሳይንስ)፣ ኢንቲሳር ቃሲም፣ ደስኒያ እንዲሁም ሌሎች እህቶቼ ስለስኬታችሁ ደስስስ ብሎኛልና 🎉🎉🎉🎉🎉🎉 Congradulations ! ! !
ምርቃታችሁን ለትልቁ ሀላፊነት የሽኝት ፕሮግራም እንደሆነ አስቡት። ኡማው፤ ሀገራችን ከእናንተ ብዙ ትጠብቃለች። ከፍ ያለውን ተልማችሁ በትልቁ እንደምታገለግሉ አልጠራጠርም። አላህ በትልቁ ስኬት ያገናኘን። Congradulations! እንኳን ደስ አላችሁሁ!!! መብሩክክክክ!!!! አልፍ ወሚልዮን መብሩክክክ!!!!
ሙሐመድአሚን ካሳው

🥰17🎉12😍5❤4👏3🔥1