AAU - Muslim Students Union
7.94K subscribers
2.95K photos
186 videos
57 files
842 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
በጎ ፈቃደኞች ይፈለጋሉና በቶሎ ተመዝገቡ ... እማራለሁ፤ ስለመብቴ እጠይቃለሁ፤ አርሳለሁም!
ጥያቄ አለን ... ክረምቱን ስለመብቴ !!

የበጋ ትምህርት ተዘግቶ ክረምቱ ስለገባ ጥያቄያችን ይቆማል ማለት አይደለም። ይልቁንስ "በጥያቄያችሁ ከገፋችሁ ከትምህርት አባርሬ እንድታርሱ ነው የማደርገው።" - ያሉንን አካላት ማረስ ክብር እንደሆነ፤ እንደምንማር እንደምናርስ፤ እየተማርንም እያረስንም ጥያቄያችንን እንደምንቀጥል ማስመስከር አለብን።

ስለሆነም በክረምቱ መርሐግብር በያላችሁበት ሆናችሁ እያረሳችሁ (ከግብርና ውጪም እየሰራችሁ) በአንድ ልብ በመሆን ጥያቄያችን ሳይደበዝዝ ሰላማዊ፣ ሕጋዊ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ አስተዋፅዖ ማድረግ የምትፈልጉ ተማሪዎች ትመዘገቡ ዘንድ ጥሪያችን ነው።

ለመመዝገብ፦ https://forms.gle/EuFEGNEockRxRp5DA ይጠቀሙ።

እማራለሁ፣ አርሳለሁ፤ ስለ መብቴም እጠይቃለሁ !

እኔ የጥያቄ አለን ትውልድ አካል ነኝ !

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

@aaumsu
🔥49🫡17❤12
ክረምቱን ስለመብቴ !

በጋ ተቋጭቶ ክረምት ገባ ማለት ጥያቄያችን ተቋጨ ማለት አይደለም። በያለንበት፣ በሁሉም መንገድ ጥያቄ አለን ማለት የጥያቄ አለኝ ትውልድ መለያ ባህሪ ነው። በጋውን ፀሐይ ሳንፈራ ቢሮ ለቢሮ፤ በየሚዲያው ስንዞር ነበር። በጋውን ካፌ ውስጥ፤ ቢሮ ውስጥ፤ በአደባባይ ጥያቄ አለን ስንል ነበር።

"በክረምትስ ምን እናድርግ?" - ለሚለው ምላሽ የሚሰጥ መድረክም ተመቻችቷል። በዚህ ውስጥ የዚህ ታሪካዊ እንቅስቃሴ አካል ለመሆን በተቀመጠው ፎርም ተመዝገቡ። በያላችሁበት የሚጠበቅባችሁን ጥቂት ነገር በማድረግ ስለመብታችሁ ትልቅን ነገር አበርክቱ።

ለመመዝገብ https://forms.gle/EuFEGNEockRxRp5DA ይጠቀሙ።

እማራለሁ፣ አርሳለሁ፤ ስለ መብቴም እጠይቃለሁ !

እኔ የጥያቄ አለን ትውልድ አካል ነኝ !

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

@aaumsu
🔥45❤7👌3🥰1🫡1
እማራለሁ!
አርሳለሁ!!
ስለመብቴም እጠይቃለሁ!!!


ያልተመዘገበ አለ ወይ? "ክረምቱን ለመብቴ!" - ንቅናቄ ውስጥ ለመሳተፍ ብዙዎች ተመዝግበዋል። ከበጋ አልፎ ለክረምት የሚተርፍ አላማን ለሰጠን አምላክ ምስጋናን እያደረስን በአንድ ልብ ለአንድ አላማ በአንድ መንገድ ለመቆም ተዘጋጅተናል። ለዚህ ዓላማ ጊዜያችሁን በመስጠት የአላህን ዲን ለመኻደም የምትፈልጉ ሁሉ https://forms.gle/EuFEGNEockRxRp5DA ተመዝገቡ። በአላህ ፈቃድ በአንድነት በአብሮነት የበዳዮች በደል ታሪክ ይሆናል።

እማራለሁ፣ አርሳለሁ፤ ስለ መብቴም እጠይቃለሁ !

እኔ የጥያቄ አለን ትውልድ አካል ነኝ !

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

@aaumsu
🔥23👍5
I WILL LEARN
I WILL FARM
I WILL DEMAND MY RIGHTS !!!

@aaumsu
🔥25❤5
"የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ከዚህ ትውልድ አይሻገርም።" - መፈክር ብቻ አይደለም፤ ይህ ትውልድ ስለመብቱ የገባው ቃልኪዳንም ጭምር እንጂ። ቃላችንን ደግሞ አናጥፍም፤ ሳንሞላውም አናርፍም።

@aaumsu
❤31🔥19💯10🫡3👌2👏1
የአንድ ተማሪ ዋጋው ስንት ነው?

የማያፈገፍግ ትውልድ ! ! !

@aaumsu
🔥49❤15👏7
እስክሪቢቶ የጣለ?

እምነቴን መደራደሪያ አድርገው ሊያስጥሉኝ እየሞከሩ ነው፤ በፅናት ቆሜ አልጣልኩም፤ እንደፀናሁ ቆሜም አልጥልም።

ሰላማዊ ትግል፤ የተቀናጀ አካሄድ፤ የማያፈገፍግ ትውልድ ! ! !

@aaumsu
🔥61👍16🫡7❤6
It is not a joke !
It is not for fun !

  በመብቱ የሚቀልድም ሆነ ለቀልድ መብቱን የሚጠይቅ ተማሪ የለም።

@aaumsu
🔥41💯8🥰1🫡1
የመጨረሻ ጥሪ!!

ለተመራቂ ተማሪዎች ከዚህን በጀመዓ በኩል የተዘጋጀ ሪቫንና ባይንደር እንዳለ ያሳወቅናቹ ሲሆን አሁን ላይ ሁሉም ነገር ተጠናቆ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የሚደርስ ሲሆን ማዘዝ ፈልጋቹ እስካሁን ያላዘዛቹ እህትና ወንድሞች ስማችሁን ከነ አባት ስም ጋር፣ ካምፓሳችሁን እና ስልክ ቁጥራቹን በቴሌግራም ቦታችን @Niqab_issueBot በመላክ በፍጥነት ተመዝግባቹ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ጊዜው ከማለፉ በፊት ይፍጠኑ

@aaumsu
🤝14👏4❤3🥰3🔥1🤩1
ግብርና የሀገር ምሰሶ እንጂ ውርደት እና ቅጣት አይደለም።

ማረስ ክብር ነው።
እማራለሁ ... አርሳለሁ ... ስለመብቴም እጠይቃለሁ።

ሰላማዊ ትግል !
የተቀናጀ አካሄድ ! !
የማያፈገፍግ ትውልድ ! ! !

@aaumsu
🔥39❤11👌6💯3
በእውነቱ የዩኒቨርሲቲያችን አስተዳደር ሁሉንም የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አካታች የሆኑ፣ የተማሪዎችን ሁለንተናዊ አቅም የሚያሳድጉ እና ጠቃሚ  ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት እንዲሁም የተማሪዎችን መብት ማክበርና ማስከበር  ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ፤ እንዲህ ባሉ የሙዚቃና የጭፈራ ድግሶች ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መገኘቱ በእጅጉ ያሳዝናል።

​ውድ የግቢያችን ሙስሊም ተማሪዎች (በተለይም ተመራቂዎች)፤ ​እኛ ሙስሊሞች ነን! በእስልምናችን ደግሞ ከእንዲህ ያሉ አላህ ከማይወደዳቸው፣ ለጊዜያዊ ስሜት ተብለው ኢማንን ከሚያዳክሙና የጭፈራ ስፍራዎች ራሳችንን እንድንጠብቅ ታዘናል። ለአመታት የደከማችሁበትን እና የለፋችሁበትን ይህንን ታላቅ የምርቃት ስኬት በአላህ እገዛ እዚህ ስላደረሳችሁ ልታመሰግኑትና በሀላል መንገድ ልታከብሩት ይገባል እንጂ፤ ስኬታችሁን በወንጀልና በጭፈራ ማክበር የለባችሁም።

​ስለሆነም ማንም ሙስሊም ተማሪ በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ እንዳይገኝና ራሱን ከእንዲህ አይነት ቦታዎች እንዲያርቅ እናሳስባለን። በምትኩ ጊዜያችንን ጠቃሚ በሆኑ ነገሮች እና ለቀጣዩ ህይወታችን ዱዓእ በማድረግ እናሳልፍ።

@aaumsu
🫡23❤11👍10👏4
እስክርቢቶውን የጣለ እስክርቢቶ ተሸለመ ! ! !

ከ39 ቀናት በፊት ... በጁምዓ ቀን ... ሙስሊም ተማሪዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ጥያቄያቸውን የሚሰማ አካል ካለ በማለት ተሰባስበው ነበር። አቤት የሚል ጠፍቶ ባለበት ፀሐይ ለምሽት ቦታዋን ለቀቀች። የፌደራል ፖሊሶችም ተማሪዎች ከቦታው ተነስተው እንዲገቡ ግፊት ማድረግ ጀመሩ። ማስፈራሪያዎች እና ዛቻዎችም ቀጠሉ። በዚህ መሐል በአምስት ኪሎ ፍሬሽማን ተማሪ የነበረ "እስክርቢቶ የጣለ አለ?!" - ሲል ጠየቀ። ተማሪውም በዝምታ ውስጥ "ሊያስጥሉኝ ይሞክራሉ፤ ግን አልጣልኩም፤ አልጥልምም።" - የሚልን መልዕክት ካለበት በፅናት በመቆም አስመሰከረ።

በዚያን ሰዓት ይህንን ጥልቅ መልዕክት ያስተላለፈውን ተማሪ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት እና በሕብረቱ የ5ኪሎ ጀመዓ እስክርቢቶ እና ሁለት መፅሐፍ ሸልመውታል።

እስክርቢቶ የጣለ አለ?!
እስክርቢቷችንን አንጥልም።

@aaumsu
🔥42❤13✍8👏7🫡1
አመስግኑት እንጂ አታምፁት
  ለምርቃት መድረስ ከአላህ ፀጋዎች ነው። እርሱ ለዋለላችሁ ፀጋ አመፅን ማስከተል ትክክል አይደለም። ስለፀጋዎቹ አመስግኑት። የአላህን መንገድ ባልሳተ መልኩ። በተለይም ከሀራም ምሽቶች እና ድግሶች ራቁ። ለእናንተም አይጠቅምም። ሙስሊም ደስታዎን ክለብ በማምሸት አያከብርም። ሙስሊም ደስታውን በጭፈራ አያከብርም። ሙስሊም ደስታውን በኸምር አያከብርም። ውለታ የዋለላችሁን አምላክ አታምፁት። አመስግኑት። እርሱ በሚወደው መልክ፤ በዕርሱ መንገድ ደስታችሁን አክብር።

አላህ ምርቃታችሁን ለኸይር በር ያድርገው።

@aaumsu
👍50❤11🥰3👏2
═══════ ✥.❖.✥ ═══════
🌷ِسْمِ اللّٰـهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ🌷
═══════ ✥.❖.✥ ═══════

ምስጋና የአለማት ጌታ ለሆነው አላህ የተገባ ነው፤ እናመሰግነዋለን፣ እርዳታውንና ምህረቱንም እንጠይቃለን፣ በእርሱም ላይ ብቻ እንመካለን። የአላህ ሰላምና እዝነት በነብያችን ሙሐመድ ﷺ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እና እስከ ቂያማ ቀን ድረስ የኢስላምን ቀጥተኛ መንገድ በተከተሉት ላይ ሁሉ ይሁን። ላለፈው አንድ አመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ውስጥ በሀላፍትና በአላህ ውሳኔና በታሪክ አጋጣሚ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶን ቆይቷል። የተጣለብንን አደራ ሁሉንም በብቃት ባንወጣውና የተሰጡንን የቤት ስራዎች በሙሉ ባንተገብርም፣ ጊዜ ማናችንንም አይጠብቅምና የኛም መውጫ ሰዓት ደርሶ ኃላፊነታችንን ለቀጣዩ ትውልድ አስረክበናል። ይህ መልእክቴ ለሀላፍትና ስንብት ሳይሆን፣ በልቤ ውስጥ ያለውን እረፍት የነሳኝን ታላቅ አማና በዱዓ በእንባ ለተገነባው የዩኒቨርሲቲው ሙስሊም ማህበረሰብ፣ ለጀመዓ መሪዎችና በየካምፓሱ የእስልምናን ባንዲራ ከፍ አድርገው ለሚያነሱት ጀግኖች በሙሉ የማስተላልፍበት የታሪክ ምስክርና የስንብት ስጦታዬ ነው።

አላህ ለዚህ ኡማ ከሰጣቸው ታላላቅና ውድ ፀጋዎች መካከል ተነጥሎ ሳይሆን እንደ አንድ አካልና በጀመዓ የመኖርን መለኮታዊ መመሪያ ነው። ጀመዓ ደካሞችን ያጠናክራል፣ የተሳሳቱትን ያስተካክላል፣ ታጋዩን ያነሳል፣ አማኙንም ከመጥመም ይጠብቃል። የነብያችን ﷺ “የአላህ እጅ ከጀማዓ ጋር ነው” የሚለው ንግግርና ተኩላ የሚበላው ብቸኛዋን በግ እንደሆነ ያስተማሩን ጥበብ ከመነጠልና ከመዳከም ሊጠብቀን የሚገባ የህይወት መመሪያችን ነው። ስለዚህም በውስጣችሁ ያለውን ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንደ አንድ ጠንካራ ህንፃ ጡቦች አጥብቃችሁ ያዙ። በመካከላችሁ ያለው ፍቅር፣ መተሳሰብና ቅንነት ከማንኛውም ምድራዊ ፈተና በላይ ሊያሻግራችሁ የሚችል የኢማን ምሰሶ ነውና በጀመዓው ጥላ ስር የምታሳዩት አንድነት የመንፈሳዊ ጥንካሬያችሁ ዋነኛ መገለጫ ይሁን።

ይህ ኡማ ከፍ የሚለውና ክብሩ የሚመለሰው ወጣቶቹ ከመዝናኛ ይልቅ መማርን፣ ከባዶ መፈክሮች ይልቅ ተግባርን ሲያስቀድሙ ብቻ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል። ያለ እውቀት የሚሰራ ሰው ከሚያስተካከለው ይልቅ የሚያበላሸው እንደሚበልጥ ከሰለፎች የተወረሰ ሀቅ ነውና፣ የእያንዳንዳችሁ መሰረት አላህን በመፍራት፣ እውቀትን በመፈለግ ከዚያም ባወቁት በመስራት ሊሆን ይገባል። ራሳችሁን በሁለንተናዊ መልኩ በትምህርታዊም ሆነ በዲናዊ እውቀቶች በሚገባ አጠናክሩ። ቂራአትን፣ ቁርኣንን፣ ሐዲስንና ፊቅህን የጀመዓችሁ ማዕከላዊ ምሰሶ በማድረግ፣ እውቀትን ለኩራት ወይም ለማህበራዊ ደረጃ ሳይሆን ራሳችሁን ከጥመት ለመጠበቅና ማህበረሰባችሁን ወደ እስልምና ብርሃን ለመምራት ተጠቀሙበት።

በዚህ በተጠናቀቀው የስራ ዘመናችን ውስጥ በእምነታችንና በማንነታችን ላይ የተቃጡ ዘርፈ ብዙ ፈተናዎችንና የመብት ጥሰቶችን በጋራ ለመጋፈጥ ሞክረናል። መብትን ጠንቅቆ ማወቅና ጥያቄዎችን በሰለጠነ፣ በህግና በስርዓት በተመራ መንገድ ማቅረብ የመነቃቃታችን ምልክት ነው። ፍትህ የጠቅላላው Universe መረጋጊያ ምሰሶ እንደመሆኑ መጠን፣ በደልን አሚን ብሎ መቀበል ወይም ዙልምን መሸከም በእስልምናችን ዘንድ ፈጽሞ ቦታ የለውም። ማንነታችንና መብታችን ሲነካ በተገቢው ጊዜና ቦታ የሚሰጥ የተደራጀ፣ ሰላማዊና ጽኑ ምላሽ ማሳየት ታሪካዊና ህሊናዊ ኃላፊነታችን ነው። ባለፉት ወራት የጀመርናቸው ህጋዊ ትግሎችና የተደረጉ በርካታ የመብት እንቅስቃሴዎች ገና ዘላቂ መፍትሔ አላገኙም። ስለሆነም ይህንን የመብት ጥያቄ የማስቀጠል፣ የጀመርናቸውን ስራዎች የመከታተልና ወደፊት የመግፋት ከባድ አደራ አሁን በግቢው ውስጥ ባላችሁ መሪዎችና መላው ተማሪዎች ጫንቃ ላይ የወደቀ የትውልድ ዕዳ ነው። ለአላህ ብላችሁ በቅንነት ስትቆሙና ሰዎችን ሳይሆን አላህን ለማስደሰት ስትተጉ፣ የሚመጣው ጫናና ማስፈራሪያ ሁሉ የእምነታችሁ መፈተኛ እንጂ የውርደታችሁ ምክንያት ሊሆን አይችልም።

ይህን ስል ይህ የታሪክ አደራ በግቢው ውስጥ በሚቀሩት ላይ ብቻ የተጣለ አይደለም፤ ይልቁንም የግቢውን ህይወት አጠናቃችሁ ወደ ቀጣዩ የህይወት ምዕራፍ ለምትሸጋገሩ ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጠው አደራ የላቀ ነው። የግቢን ህይወት እንጂ እስልምናንና ማህበረሰባዊ ግዴታችሁን እየጨረሳችሁ እንዳልሆነ ልታውቁ ይገባል። ሃላፊነታችሁ እስከ ሞት ደጅ ድረስ የሚቀጥል ነውና፣ አሁን ላይ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እየተደረገ ያለውን ፍትሃዊና ህጋዊ የመብት ጥያቄ ባላችሁበት ቦታ ሁሉ ሆናችሁ በዕውቀታችሁ፣ በንብረታችሁና በሞራላችሁ እንድትደግፉ፣ የጀመዓውን ንቅናቄ ከውጭ ሆናችሁ እንድታግዙ አደራዬ የጸና ነው። የትም ብትሄዱ የኢስላም እውነተኛ ወኪል በመሆን ማህበረሰባችሁን ማገልገልንና ለእሴቶቻችሁ መቆምን አትተው።

በመጨረሻም፣ የቱንም ያህል ለመልካም ስራ ብንጥር የሰው ልጆች ከመሆናችን አንጻር በስራችን ውስጥ ጉድለትና ስህተት አይጠፋምና፣ ሁላችሁም የጌታችንን "ይቅርታም ያድርጉ፤ ጥፋተኞቹን ይለፉም፣ አላህ ለናንተ ሊምር አትወዱምን" (22:24) የሚለውን ቃል አስታውሳችሁ አውፍ ትሉኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ። በቃልም ሆነ በድርጊት የበደልኩትና ያስከፋሁትና ሀቁን ያለ አግባብ የወሰድኩበት አካል ካለ ለማስተካከልና ለመካስ ዝግጁ ከመሆኔ ጋር አፍዉ እንድትሉኝ እየገለጽኩ፣ ይህንን የትውልድ አማና አደራ ለማለት እወዳለው። አላህ ከእነዚያ ከሚፈሩትና መልካም ከሚሰሩት ጋር ነውና ስኬትና ድል ሁልጊዜም ከእናንተ ጋር ይሁን። አውፍ በሉኝ፣ እኔም አውፍ ብያለሁ፤

والسلام عليكم ورحمة الله وبركاته

✍ ወንድማችሁ ዘይድ ሷዲቅ
@aaumsu
❤34😢4✍3🥰2
ከዛሬ ለሊት ጀምሮ የአሹራ ቀን ነው ነገ መፆም እንዳይረሳ

عَنْ أَبِي قَتَادَةَ رضي الله عنه أن النبي ﷺ قال : «... وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ، أَحْتَسِبُ عَلَى اللهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ» رواه مسلم

ከአቢ ቀታዳ (ረ.ዐ) ተይዞ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
«... የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አንደ አመት ያስምራል ብዬ ከአላህ እከጅላለው» ሙስሊም ዘግበውታል

@aaumsu
🤝7🫡3❤1
ከዚህን በፊት በህብረታችን በኩል ሪቫንና ባይንደር እንዳዘጋጀን ገልፀንላቹ እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ ተሰርቶ ስለተጠናቀቀ ኢንሻአላህ አዛቹ ለከፈላቹ እህትና ወንድሞች ነገ በየግቢዎቻቹ እንዲደርሳችሁ የምናደርግ ይሆናል። በተጨማሪም ለመውሰድ ተመዝግባቹ ክፍያ ላልከፈላቹ እህትና ወንድሞች ክፍያውን አጠናቃቹ እንድትወስዱ ለማስታወስ እንወዳለን።

በተጨማሪ አሁንም መውሰድ የምትፈልጉ እህትና ወንድሞች የተዘጋጀው ባይንደርና ሪቫን በእለቱ ደምቀንና እሴቶቻችንን የምናሳይበት ልዩ ሪቫንና ባይንደር ስለሆነ ስማችሁን ከነ አባት ስም ጋር፣ ካምፓሳችሁን እና ስልክ ቁጥራቹን በቴሌግራም ቦታችን @Niqab_issueBot በመላክ በምንልክላቹ አካውንት ክፍያ ፈፅማቹ መቀበል እንደምትችሉ በደስታ ለማሳወቅ እንወዳለን።

@aaumsu
❤7🥰1
📢 ልዩ የፓነል ውይይት በቲክቶክ ! ! ! 📢

ድምፃችንን ከፍ አድርገን የምናሰማባቸውን መድረኮች አብዝቶ ለፈጠረው አምላክ ምስጋና የተገባው ይሁንና በዕለተ እሁድ ሰኔ 7፣ 2017 ዓ.ል የመሰብሰብ እና የመወያየት መብታችንን በመነፈጋችን ምክንያት፣ በሰፊው ተደራሽ ወደ ሆነው የቲክቶክ መድረክ ያዞርነውን ታሪካዊ የፓናል ውይይት ዝርዝር መረጃ ይዘን መጥተናል!

📌 ርዕስ፡- "በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙስሊም ተማሪዎች መብት"

🎙 በዚህ አንገብጋቢ እና ወቅታዊ ርዕስ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሚሰጡን እና ውይይት የሚያደርጉልን ልዩ የክብር እንግዶች ጋብዘናል... እንግዶቻችን ማን ይሆኑ? 🤔 በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል፤ ዝግጅታችንን ይጠብቁ!

🗓 ቀን፡ ሰኞ፣ ሰኔ 22 (Monday, 29 June)
⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት

✨ "እውቀትን መፈለግ መብት ነው፤ እምነትንም በክብር መተግበር እንዲሁ!"

በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያላችሁ ተማሪዎች እና መላው ሕዝበ ሙስሊም በያላችሁበት ሆናችሁ በቲክቶክ ገፃችን ላይ እንድትታደሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እስከዚያው ይህን መልዕክት ለሁሉም በማጋራት የድምፃችን አካል ይሁኑ! የቲክቶክ ገፃችንን Follow በማድረግ ዝግጅቱን ይጠብቁ፦

https://www.tiktok.com/@aaumsu

✊ እወቅ፤ ጠይቅ፤ አስከብር።

@aaumsu
🔥33👏8❤6👌1
"ፍትሕ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች!" - በሰመራ ዩኒቨርስቲ የዋንጫ ተሸላሚ የሆነው ዶክተር ሙሐመድ ሐሰን

በሰመራ ዩኒቨርስቲ የወርቅ ሜዳልያ እና ዋንጫ ተሸላሚ ሆኖ የተመረቀው ዶክተር ሙሐመድ ሐሰን በሐይማኖታቸው ምክንያት በደል እየደረሰባቸው ላሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች እና ለአክሱም ሙስሊሞች በምርቃቱ ቀን ድምፁን አሰምቷል። "ኒቃብ ፀጉርን እንጂ አዕምሮን አይፈንም!" - የሚልን መልዕክት ያስተላለፈው የዋንጫ ተሸላሚው ዶክተር ሙሐመድ ሙስሊም ተማሪዎችን የማያገል፤ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚያስተዳድር፤ ፍትሕን የሚያሰፍን መመሪያ እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል። በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጀምሮ እየደረሱ ያሉ የመብት ጥሰቶች ቆመው ፍትሕ ይሰፍን ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል።

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

©️ EHEMSU

@aaumsu
🔥36❤13👏4🥰2🫡1