AAU - Muslim Students Union
7.95K subscribers
2.95K photos
186 videos
57 files
842 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
የፓናል ውይይት ስለ መብቶቻችን
- የዚህ ታላቅ ታሪካዊ ዝግጅት አካል እንሁን

ነገ እሁድ ጠዋት 2:30 ወደ ጦር ሀይሎች (ረያን መስጅድ)
- ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል !

@aaumsu
🔥18❤9👍3
እጅግ አስቸኳይ መረጃ!
የነገው ፕሮግራም እንዲሰረዝ ተደርጓል!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በረያን መስጂድ በነገው እለት ሊያዘጋጀው የነበረው የፓናል ውይይት እንዲሰረዝ ተደርጓል። ለዚህም በዋነኝነት የተሰጠው ምክንያት "የመንግስት አካላት ፕሮግራሙ እንዳይካሄድ ክልከላ አድርገዋል" የሚል ነው። ህብረታችንም ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚወክለው መጅሊስ እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት የዜጎችን ህገ-መንግስታዊ እና ተፈጥሯዊ መብት ከማስከበር አኳያ ከጎናችን በመቆም መፍትሄ ያመጣሉ ብለን ተስፋ አድርገን የነበረ ቢሆንም፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ተገቢውን ከለላ፣ ድጋፍ እና መፍትሄ ማግኘት አልተቻለም።

ፕሮግራሙን ለመታደም ከተለያየ ዩኒቨርስቲ መጥታችሁ አዲስ አበባ ያደራችሁ የጀመዓ አሚሮች፤ አላህ (ሱ.ወ) ጥረታችሁን በጀነት ይመንዳችሁ። ጁምዓ በየመስጂዱ ጥሪ ሲደረግ በእምባ ታጅባችሁ ዱዓ በማድረግ ጭምር እንደምትመጡ የነገራችሁን እናት አባቶች፤ አላህ ዱዓችሁን ይቀበልልን። ከተለያየ ሀይስኩል፣ ኮሌጅ እና መድረሳዎች ለመምጣት የተሰናዳችሁ እህት ወንድሞቻችን፣ የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት የተሰናዳችሁ ቲቪዎች፣ ኡስታዞች፣ መሻይኾች እና የክብር እንግዶቻችን፤ ኒያችሁን አላህ ያሳምርላችሁ።

መስጂድ የሁሉም ሙስሊም የጋራ ቤት ነው። በሰላማዊ መንገድ መሰባሰብ እና ስለጋራ ጉዳያችን መወያየት በማንም ሊገፈፍ የማይችል ሕገ-መንግስታዊ መብታችን ነው። የሚዳፈንም ሆነ ወደኋላ የሚጎተት ጥያቄ የለንም። መብታችንን ለማስከበር የምናደርገው ጉዞ በህግ፣ በስርአት እና በኢስላማዊ አዳብ የታነፀ ሆኖ ይቀጥላል።

ይህ መልእክት በጊዜው ያልደረሳቸው እና ለፕሮግራሙ በነገው እለት ወደ መስጂዱ የሚመጡ በርካታ ወንድም እና እህቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ፤ ይህንን ፕሮግራም ያገዳችሁ አካላት፣ ቢያንስ እንኳን ይህን አላዋቂ እንግዳ በእንግድነቱ ልክ በክብር በማስተናገድ እና በጥሩ ቃል በመመለስ ከሚጠበቅባችሁ ትንሹን እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ቀጣዩን አቅጣጫችንን በቅርቡ እስከምናሳውቅ ድረስ በዱዓ፣ በሰብር እና በፅናት ጠብቁን።

"በእርግጥም የአላህ እርዳታ ሁሌም ቅርብ ነው።" (አል-በቀራህ 214)

@aaumsu
😡131💔64😭17🤬8❤7👌1🫡1
ሀሳብን መፍራት የውድቀት መጀመሪያ ነው!

ምክንያታዊነት ሲጎድል እና አሳማኝ መከራከሪያ ሲጠፋ፣ ብቸኛው መሸሸጊያ መንገድ ሀሳብን በጉልበት ማፈን ይሆናል። ይሁን እንጂ የሀሳብን ልእልና የሚፈሩ እና እውነትን የሚሸሹ አካላት ውድቀታቸው እጅግ የፈጠነ ነው። ብርሃንን በመጋረድ ጨለማን ማንገስ አይቻልም።

@aaumsu
💯69🔥17👌7❤6👍3
አልሐምዱሊላህ __ ታድለናል !

‎ገና ባልጠና ጉልበታችን፥ የብዙዎች ያልተሰራ የቤት ሥራ በጫንቃችን ላይ ተጣለብን።
‎
‎ታድለን ...
‎የትውልድን ክብር በመጠበቅ ላይ ኃላፊነት ወሰድን።
‎
‎ታድለን...
‎የእህታቸው ክብር እየተነካ፥ በሰላም ተኝተው የማያድሩ ዓይኖች ተሰጡን።
‎
‎ታድለን...
‎ፍትሕ ስትቀበር «በእኔን ከተመቸኝ ይሁንታ» የማይቀበል አዕምሮ ተሰጠን።
‎
‎ታድለን...
‎ቀን እስኪያልፍ የሚጎድልን ክብር የማይታገስ ልብ ተቸርን።
‎
‎ታድለን...
‎ሌሎች የፈሩበትን ነገር በድፍረት የመጋፈጥ ወኔ ተሰጠን።
‎
‎ታድለን...
‎«አዳኝ» እስኪመጣ ሳንጠብቅ፥ ኃላፊነታችንን የምንወጣበት ተቆርቋሪነት ተሰጠን።
‎
እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
‎
‎ታድለን...
‎ፍትሕ መጓደል አመመን።
‎የመብታችን መጣስ ቆረቆረን።
‎ጭቆና አንገሸገሸን።
‎
‎ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
‎
‎ታድለንማ'ኮ...
‎ታሪክ "ካላጎነበሱት" መካከል መዘገበን።
‎መስዋዕትነት ከገባቸው፤
‎ትውልዳቸውን ለመታደግ ቁርጠኛ ከሆኑት መሃል መዘገበን።
‎
‎ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
‎
‎ታድለንማ'ኮ...
‎በአላህ ላይ ከሚመኩት፣
‎ለመንገዱ ከሚታመኑት፤
‎ድልንም ከርሱ ብቻ ከሚጠብቁት ሰራዊቶቹ መሃል አደረገን።
‎
‎ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
‎ለኛ የተሰጠው ለማን ተሰጥቷል?! - ዙሪያችሁን አትመለከቱምን?!
‎
‎በህይወታችን ካየናቸው ብዙ ብዙ ብቸኝነቶች ውስጥ፥ በዚህ የትግል መንገድ ላይ ያለ ብቸኝነትን ያህል ዋጋ ያለው ብቸኝነት የት እናገኛለን?!
‎አላህ የሚያየው፣ የሚመሰክርለት ብቸኝነት!
‎ወደ ድል እንጂ የማይደርስ፣ ውድቀት የሌለበት ብቸኝነት!!
‎ትርጉሙ ጥልቅ፣ ክፍያው ብዙ ብቸኝነት!!!
‎
‎ይህ እንደዋዛ 'ሚገኝ ነው እንዴ 'ሚመስለን?! ‎በፍጹም።
‎ለዚህ ብቸኝነት መመረጥ ያሻዋል።
‎
‎ይህ'ኮ ታላቅ ጸጋ እንጂ ሌላ አይደለም።
‎አልሐምዱሊላህ!!!
‎

‎ሐስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል!!!

@aaumsu
🔥64🥰12👍7❤5⚡2👌1
አንድ ወር ሞላው

ግንቦት ሰባት ላይ ነበር። ሙስሊም ተማሪዎች የደረሰባቸው የመብት ጥሰት ይቋጭ ዘንድ ጥያቄ አለን በማለት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ተሰባሰቡ። የቀኑ ፀሐይ እና የምሽቱ ብርድ ሳይበግራቸው እስከ ምሽት 4:30 ተቀመጡ። ለአመራሮች ችላ ባይነት እና ለፌደራሎች ማስፈራሪያ ሳይበገሩም በዝምታ ውስጥ ትልቅ መልዕክትን አስተላለፉ። በሰላም እና ፀጥታ፤ በስነ-ምግባር እና ቁርጠኝነት መልዕክታቸውን አስተላለፉ።

ዛሬ ሰኔ ሰባት ሆኗል። ያ ታሪካዊው ውሎ እና ምሽት አንድ ወር ደፍኗል። ሆኖም በዚያ ምሽት ከሰላም ሚኒስቴር፤ ከዩኒቨርስቲው፤ ከሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ፤ ከፀጥታ ክፍል፤ ከመጅሊስ ወዘተ... በመምጣት በተማሪው ፊት ዘላቂ መፍትሔን ለማምጣት ቃል ገብተዎ ቢመለሱም ለመፍትሔ የሚሆንን ነገር ሳያደርጉ ጥያቄ አለን የሚለው ቃል ደምቆ እንዲቀጥል ሆኗል።

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
ጥያቄ አለን _ መብቶቻችን ተከብረው መማር እስክንችል!!
ጥያቄ አለን _ መብታችን ሳይነፈግ በመስጂዶቻችን መሳበሳብ እስክንችል!!!

@aaumsu
🔥41❤10🤬5😭4💔3👌1
በዛሬው እለት በረያን መስጂድ ልናዘጋጀው የነበረው የፓናል ውይይት እንዲሰረዝ መደረጉን ባለመስማት ከቦታው ደርሳችሁ የተመለሳችሁ እህት ወንድሞች፣ እናት አባቶች እና የክብር እንግዶቻችን ሁሉ አላህ ንያችሁን ተቀብሎ እና ልፋታችሁን ቆጥሮ ለሙስሊሙ መብት መከበር ሰበብ የምትሆኑ ያድርግላችሁ። ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም ከከምባታ፣ ሀረማያ፣ ሰላሌ፣ ወራቤ እና ከተለያየ ዩኒቨርስቲ ጀመዓዎች አዲስ አበባ ድረስ መጥታችሁ አድራችሁ የተመለሳችሁ ወንድሞቻችን አላህ የተሻሉ ለውጦችን ማምጣት የምትችሉበትን ብርታት ይስጣችሁ፤ ልፋታችሁንም ይቁጠር።

በአላህ ፈቃድ ለተሻለው ይሆናል። እንድንጠነክር አድርጓል። ለመልካም ለውጥ ሰበብ ይሆናል። ለተሻለ ነገ መሠረት ይሆናል።

የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄዎች ከዚህ ትውልድ አይሻገሩም። ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ጥያቄ አለን።

@aaumsu
🔥46❤18😭8💔7
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት የሚተላለፉ መልዕክቶች እና አቅጣጫዎች ይደርሳችሁ ዘንድ በቴሌግራም @aaumsu ፤ በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@aaumsu?_r=1&_t=ZS-97D9UHuTcGO እንዲሁም በዩቲዩብ https://youtube.com/@aaumsu ተከታተሉ። ለሌሎች ይደርስም ዘንድ አሰራጩት።

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

@aaumsu
🫡19🔥8❤4
AAU - Muslim Students Union
ክቡራን የ2018 ዓ.ል የAAU ሙስሊም ተመራቂ ተማሪዎች፤ ቀደም ሲል ያሳወቅናችሁ የልዩ የምረቃ ሪቫን ምዝገባ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥሎ የሚገኝ መሆኑን እያበሰርን፣ ካባችሁን በባዶ አንገት ከመልበስ ይልቅ ከሪቫኑ ጋር አብሮ የተዘጋጀውን ውብ ባይንደር (Binder) ጨምረው ማዘዝ እንደሚችሉ እናስታውሳለን። ምዝገባው ከመጠናቀቁ በፊት ዕድሉን በመጠቀም ስምዎን ከነ አባት ስም ጋር፣ ካምፓስዎን እና ስልክ…
ለተመራቂ ተማሪዎች ከዚህን በፊት እንዳሳወቅነው በህብረታችን በኩል የተዘጋጀ ሪቫንና ባይንደር እንዳለ ያሳወቅናቹ እንደነበር ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ብዙዎች በመመዝገብ ላይ ይገኛሉ።

እስከአሁን ድረስ ያልተመዘገባቹ እህትና ወንድሞች ያለው ጊዜ የተወሰነ በመሆኑ ከወዲሁ ምዝገባው ሳይጠናቀቅ ሙሉ ስማችሁን ግቢያችሁን እና ስልክ ቁጥራችሁን በዚህኛው @Niqab_issueBot ቦት ላይ በማስቀመጥ እንድትመዘገቡ ለማስታወስ እንወዳለን።

@aaumsu
❤19
ሰላማዊ ትግል !
የተቀናጀ አካሄድ ! !
የማያፈገፍግ ትውልድ ! ! !


@aaumsu
🔥57⚡6❤3
ታላቅ የፓናል ውይይት ... በቲክቶክ መድረክ ! ! !

ድምፃችንን ከፍ አድርገን የምናሰማባቸውን መድረኮች አብዝቶ ለፈጠረው አምላክ ምስጋና ይገባ። ታሪካዊውን የፓናል ውይይት በመስጂድ ልናከናውን ቀጠሮ የያዝን ቢሆንም የመሰብሰብ እና የመወያየት መብታችንን በመንፈግ እንደተከለከልን የሚታወስ ነው። ሆኖም እነርሱ ከለከሉን ማለት ዝም ብለን እንቀመጣለን ማለት አይደለም። በሰፊው፣ ሁሉም በያለበት ሆኖ ይታደም ዘንድ በተመቻቸ ሁኔታ፤ ርዕሶቹም ሰፋ ብለው፤ በቅርቡ በቲክቶክ ታላቅ የፓናል ውይይት የሚኖረን ይሆናል።

የክብር እንግዶቻችን እንዳሉ ሆነው፤ መምጣት ሳይችሉ ቀርተው ሲቆጩ የነበሩት ባሉበት ሆነው እንዲሳተፉ በሚያስችል መድረክ፤ በውጭ ሀገርም ሆነው በሀገር ውስጥ ያሉ ተማሪዎች እና መላው ሕዝበ ሙስሊም የሚሳተፍ ይሆናል።

እስከዚያው መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ። የቲክቶክ ገፃችንን https://www.tiktok.com/@aaumsu?_r=1&_t=ZS-97D9UHuTcGO በመግባት Follow አድርጉ።

የሚታፈን ድምፅ የለም ! ለበዳዮች እጁን የሚሰጥ ትውልድም አይኖርም !!

ጥያቄ አለን ... ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

@aaumsu
🔥70👏11❤7🫡2🥰1
Seeking knowledge is a right, and so practicing your faith with dignity.

@aaumsu
🔥37💯22❤7🥰2
በጎ ፈቃደኞች ይፈለጋሉና በቶሎ ተመዝገቡ ... እማራለሁ፤ ስለመብቴ እጠይቃለሁ፤ አርሳለሁም!
ጥያቄ አለን ... ክረምቱን ስለመብቴ !!

የበጋ ትምህርት ተዘግቶ ክረምቱ ስለገባ ጥያቄያችን ይቆማል ማለት አይደለም። ይልቁንስ "በጥያቄያችሁ ከገፋችሁ ከትምህርት አባርሬ እንድታርሱ ነው የማደርገው።" - ያሉንን አካላት ማረስ ክብር እንደሆነ፤ እንደምንማር እንደምናርስ፤ እየተማርንም እያረስንም ጥያቄያችንን እንደምንቀጥል ማስመስከር አለብን።

ስለሆነም በክረምቱ መርሐግብር በያላችሁበት ሆናችሁ እያረሳችሁ (ከግብርና ውጪም እየሰራችሁ) በአንድ ልብ በመሆን ጥያቄያችን ሳይደበዝዝ ሰላማዊ፣ ሕጋዊ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ አስተዋፅዖ ማድረግ የምትፈልጉ ተማሪዎች ትመዘገቡ ዘንድ ጥሪያችን ነው።

ለመመዝገብ፦ https://forms.gle/EuFEGNEockRxRp5DA ይጠቀሙ።

እማራለሁ፣ አርሳለሁ፤ ስለ መብቴም እጠይቃለሁ !

እኔ የጥያቄ አለን ትውልድ አካል ነኝ !

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

@aaumsu
🔥49🫡17❤12
ክረምቱን ስለመብቴ !

በጋ ተቋጭቶ ክረምት ገባ ማለት ጥያቄያችን ተቋጨ ማለት አይደለም። በያለንበት፣ በሁሉም መንገድ ጥያቄ አለን ማለት የጥያቄ አለኝ ትውልድ መለያ ባህሪ ነው። በጋውን ፀሐይ ሳንፈራ ቢሮ ለቢሮ፤ በየሚዲያው ስንዞር ነበር። በጋውን ካፌ ውስጥ፤ ቢሮ ውስጥ፤ በአደባባይ ጥያቄ አለን ስንል ነበር።

"በክረምትስ ምን እናድርግ?" - ለሚለው ምላሽ የሚሰጥ መድረክም ተመቻችቷል። በዚህ ውስጥ የዚህ ታሪካዊ እንቅስቃሴ አካል ለመሆን በተቀመጠው ፎርም ተመዝገቡ። በያላችሁበት የሚጠበቅባችሁን ጥቂት ነገር በማድረግ ስለመብታችሁ ትልቅን ነገር አበርክቱ።

ለመመዝገብ https://forms.gle/EuFEGNEockRxRp5DA ይጠቀሙ።

እማራለሁ፣ አርሳለሁ፤ ስለ መብቴም እጠይቃለሁ !

እኔ የጥያቄ አለን ትውልድ አካል ነኝ !

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

@aaumsu
🔥45❤7👌3🥰1🫡1
እማራለሁ!
አርሳለሁ!!
ስለመብቴም እጠይቃለሁ!!!


ያልተመዘገበ አለ ወይ? "ክረምቱን ለመብቴ!" - ንቅናቄ ውስጥ ለመሳተፍ ብዙዎች ተመዝግበዋል። ከበጋ አልፎ ለክረምት የሚተርፍ አላማን ለሰጠን አምላክ ምስጋናን እያደረስን በአንድ ልብ ለአንድ አላማ በአንድ መንገድ ለመቆም ተዘጋጅተናል። ለዚህ ዓላማ ጊዜያችሁን በመስጠት የአላህን ዲን ለመኻደም የምትፈልጉ ሁሉ https://forms.gle/EuFEGNEockRxRp5DA ተመዝገቡ። በአላህ ፈቃድ በአንድነት በአብሮነት የበዳዮች በደል ታሪክ ይሆናል።

እማራለሁ፣ አርሳለሁ፤ ስለ መብቴም እጠይቃለሁ !

እኔ የጥያቄ አለን ትውልድ አካል ነኝ !

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

@aaumsu
🔥23👍5
I WILL LEARN
I WILL FARM
I WILL DEMAND MY RIGHTS !!!

@aaumsu
🔥25❤5
"የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ከዚህ ትውልድ አይሻገርም።" - መፈክር ብቻ አይደለም፤ ይህ ትውልድ ስለመብቱ የገባው ቃልኪዳንም ጭምር እንጂ። ቃላችንን ደግሞ አናጥፍም፤ ሳንሞላውም አናርፍም።

@aaumsu
❤31🔥19💯10🫡3👌2👏1
የአንድ ተማሪ ዋጋው ስንት ነው?

የማያፈገፍግ ትውልድ ! ! !

@aaumsu
🔥49❤15👏7
እስክሪቢቶ የጣለ?

እምነቴን መደራደሪያ አድርገው ሊያስጥሉኝ እየሞከሩ ነው፤ በፅናት ቆሜ አልጣልኩም፤ እንደፀናሁ ቆሜም አልጥልም።

ሰላማዊ ትግል፤ የተቀናጀ አካሄድ፤ የማያፈገፍግ ትውልድ ! ! !

@aaumsu
🔥61👍16🫡7❤6
It is not a joke !
It is not for fun !

  በመብቱ የሚቀልድም ሆነ ለቀልድ መብቱን የሚጠይቅ ተማሪ የለም።

@aaumsu
🔥41💯8🥰1🫡1
የመጨረሻ ጥሪ!!

ለተመራቂ ተማሪዎች ከዚህን በጀመዓ በኩል የተዘጋጀ ሪቫንና ባይንደር እንዳለ ያሳወቅናቹ ሲሆን አሁን ላይ ሁሉም ነገር ተጠናቆ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የሚደርስ ሲሆን ማዘዝ ፈልጋቹ እስካሁን ያላዘዛቹ እህትና ወንድሞች ስማችሁን ከነ አባት ስም ጋር፣ ካምፓሳችሁን እና ስልክ ቁጥራቹን በቴሌግራም ቦታችን @Niqab_issueBot በመላክ በፍጥነት ተመዝግባቹ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ጊዜው ከማለፉ በፊት ይፍጠኑ

@aaumsu
🤝14👏4❤3🥰3🔥1🤩1