ይህ ትላንት የሆነ ነው!!!
ለውይይት የተገባው ቃል 4 ቀን ካለፈው በኋላ ማለት ነው።
"አንቺ ለምንድን ነው ያስገባሻት? አልሸባብ ብትሆንም አሸባሪ ብትሆንም እንደዚህ ነው የምታስገቢያት? ምን ማለት ነው?" -
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ለ20 ወራት ሲያካሂድ የነበረውን የመብት ጥሰት በውይይት ለመፍታት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ግንቦት 7 / 2018 ዓ.ል ከዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ ጠይቀን ነበር። ውይይትን የተጠየፉት የዩኒቨርስቲው አመራሮች ለተማሪዎች ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ምሽት አራት ሰዓት ሲያልፍ ከሰላም ሚኒስቴር፤ ከኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ፤ ከፌደራል እና አዲስ አበባ መጅሊስ የመጡ አመራሮች ባሉበት ቅዳሜ ውይይት ተደርጎ ዘላቂ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ እንደሚሰራ ተገልፆ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በማግስቱ ቅዳሜ እንዲሁም ሰኞ እለት ከመጅሊስ አመራሮች ጋር ጥልቅ እና ፍሬያማ ውይይት የተደረገ ሲሆን የመንግስት አካላት በዚህ ሳምንት የውይይት መድረኮችን ሊያዘጋጁ ቃል እንደገቡ ተገልፆ ነበር።
ሆኖም ይህ በእንዲህ ባለበት በዛሬው እለት በ6ኪሎ የሚገኙ ጥበቆች በኒቃቢስት ተማሪዎች ላይ እላፊ ንግግሮችን ሲናገሩ እና ተማሪዎች ላይ እንግልት ሲፈፅሙ ነበር። ጥበቃዎቹ ኒቃቢስት ተማሪዎችን እንዳይገቡ ሲከለክሉ አንዲት እህት እርሷ በከፈተችው በር እንዲገቡ ማድረጓን ተከትሎ "አንቺ ለምንድን ነው ያስገባሻት? አልሸባብ ብትሆንም አሸባሪ ብትሆንም እንደዚህ ነው የምታስገቢያት? ምን ማለት ነው?" - እያሉ ሲወርፏት ተስተውሏል።
ይህ ፍፁም አግባብነት የሌለው፤ ዩኒፎርምን ከለበሰ የጥበቃ አካል የማይጠበቅ ድርጊት ነው። መሠል ሕገ- ወጥ ተግባራት እየተፈፀሙ ያሉት ዩኒቨርስቲው ባፀደቀው ሕገ- ወጥ መመሪያ ምክንያት ነውና ችግሩ በውይይት እንደሚፈታ ቃል የገቡ የመንግስት አካላት ውይይቱን በቶሎ አድርገው ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመጡ እንጠይቃለን።
ለተማሪዎቻችን፦ ስነ-ምግባር የጎደለው እና ፀያፍ ንግግርን ለሚናገሩ የዩኒቨርስቲው አካላት ምላሽ አትሰጡ። በአላህ ፈቃድ በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲሆኑ የምናደርግ ይሆናል።
ለሰላም ሚኒስቴር፤ የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ እና ለሚመለከታቸው በሙሉ፦ ተማሪው በአደባባይ የወጣው ለ20 ወራት ያክል ከቢሮ ቢሮ ተንከራቶ ፍትሕን ስለተነፈገ ነው። በዚያ ምሽት ከተማሪ ፊት የገባችሁትን ቃል በመፈፀም ሀገር የጣለችባችሁን ሀላፊነት ትወጡ ዘንድ ጥሪያችን ነው።
@aaumsu

የ6ኪሎ ጥበቃ

😡100❤10💯7🤬5
ለዩኒቨርስቲ ጀመዓዎች፤ ለኸጢቦች፤ ለኢማሞች፤ ለኡስታዞች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕናዎች፦
ባለፈው ጁምዓ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች በኒቃብ ምክንያት እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰት እና እንግልት አቤት ለማለት ከዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ቢገኙም ጥሪያቸውን የሚሰማ ጠፍቶ እስከ ምሽት 4:30 ብርድ እና ፀሐይ ከፌደራል ማስፈራሪያ ጋር እየተፈራረቀባቸው መቆየታቸው የሚታወስ ነው። መጨረሻ አካባቢ ለማናገር የመጡ ኡስታዞች፣ የሰላም ሚኒስቴር ሰዎች፣ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ አመራሮች ወዘተ ... መጥተው ውይይት ለካሂዶ ዘላቂ መፍትሔ እንደሚመጣ ቢገልፁም እስካሁን ባለው የተባለው ውይይት አልተካሄደም። የዩኒቨርስቲው አካላትም በጀመሩት የመብት ጥሰት እንደቀጠሉ ናቸው።
ስለሆነም በመጪው ጁምዓ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላሉ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችሁ ዱዓ እንድታደርጉ፤ እየደረሰባቸው ስላለው ነገር በኹጥባዎቻችሁ እንድታደርሱ እንዲሁም አጋርነታችሁን እንድታሳዩ እንጠይቃለን።

❤81🔥22🫡10💔4👏2👌2
🌟 ታላቅ የዳዕዋ እና የሽኝት ፕሮግራም! 🌟
⭐️ Grand Da'wa and Well Go Program ⭐️
በአላህ ﷻ ፈቃድ ልቦች ለአላህ ሲሉ የሚገናኙበትና ፈጽሞ ሊያመልጥዎት የማይገባ ታላቅ የዳዕዋ እና የሽኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል።
በተከበሩ እንግዶቻችን መገኘት የምንማርበትና የምንነቃቃበት፣ እንዲሁም ለዓመታት የህብረታችን አካልና የጉዟችን አጋር የነበሩትን ውድ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶቻችንን በታላቅ ክብርና ፍቅር የምንሸኝበት ልዩ ዕለት ነው።
ይህ ፕሮግራም መጪው እሑድ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ል (May 24, 2026) በአል-አቅሷ መስጂድ የሚካሄድ ሲሆን፣ በአላህ ፈቃድ ከጠዋቱ 2፡30 (08:30 AM) ሰዓት ላይ የሚጀምር ይሆናል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ ለመማር፣ ለማስተንተንና መንፈስን ለማደስ በዚህ ፕሮግራም ላይ እንድትገኙ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
✨ @aaumsu ✨

😭21❤11👍7🥰3💯1🫡1
የጊዜ ገደቡ ተጠናቋል፤ ሰበቦቹ ግን ቀጥለዋል!
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የመንግስት አካላት እና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች አፋጣኝ የውይይት መድረክ እንደሚያዘጋጁ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። እኛም የተገባውን ቃል በማክበር ይህንን ሳምንት እንደ የመጨረሻ የትዕግስት ጊዜ ሰጥተን ነበር። ነገር ግን ዛሬ ጁምዓ (ግንቦት 14) ቢደርስም፣ ከተማሪዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ ውይይት እስካሁን አልተካሄደም።
በውይይት ጠረጴዛ ዙሪያ ከመቀመጥ ይልቅ፣ የሚመለከታቸው አካላት አሁንም የተለያዩ ሰበቦችን እየደረደሩ ይገኛሉ።
አቋማችን አሁንም የፀና ነው፤ መብቱን የጠየቀን ንፁህ እና ሰላማዊ ተማሪ በቢሮክራሲ ማድረቅና ማሸማቀቅ አይቻልም።
ለሚመለከታችሁ አካላት ሁሉ የምናስተላልፈው መልዕክት አጭርና ግልጽ ነው፦ ህጉን አስተካክሉ እንጂ መፍትሔን አታዘግዩ!
ለተማሪዎቻችን:- የሰጠነው የጊዜ ገደብ አብቅቷልና ንቃታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እናሳስባለን። ከዚህ በኋላ ለሚፈጠረው ማናቸውም ነገር ኃላፊነቱን የሚወስዱት ቃላቸውን ያጠፉት አካላት ናቸው። ቀጣዩን አቅጣጫ እና የትግል እርምጃ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል!
አሁንም ጥያቄ አለን! ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!

❤50🫡37🔥10💯3
"እኛ አፋሮች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና በአክሱም ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን በደል እንቃወማለን። ኒቃቧንም ትለብሳለች፤ ትምህርቷንም ትማራለች።"
በአፋር ካሉ ሙስሊም ወንድሞች አመሻሹን የተላከ የአብሮነት መልዕክት ነው። ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው። ከአፋር ጀምሮ እስከ ሶማሌ፤ ከባሌ ጀምሮ እስከ ደሴ ያለውን ሙስሊም ይመለከታል። የእምነት፣ የማንነት፣ የክብር ጉዳይ ነውና።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !

🔥61❤22💯7🥰5👌3👍2👏1
🌟 1 ቀን ብቻ ቀረው🌟
ታላቅ የዳዕዋ እና የሽኝት ፕሮግራም!
ነገ ጠዋት 2:30 እግሮች ሁሉ ወደ አቅሷ መስጂድ ያመራሉ!!
📌 ታላላቅ እንግዶች የሚታደሙበት፤
📌 ለአመታት አብረዉን የቆዩ የጊቢያችንን ሙስሊም ተማሪዎችና የህብረታችን ልጆች የምንሸኝበት፤ እና
📌የተለያዩ ቁም-ነገር አዘል ትምህርቶችን የምንቀስምበት ፕሮግራማችን እነሆ ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል
ታላቁ የዳዕዋ እና የሽኝት ፕሮግራም የአንድ ቀን እድሜ ብቻ ቀርቶታል!
🕔 ታላቅ ፕሮግራም በታላቁ አል-አቅሷ መስጂድ፣ ነገ ከጠዋቱ 02፡30 ጀምሮ!
ሁሉም የአአዩ ተማሪዎች እንዲታደሙ ተጋብዘዋል!

❤16👍4🥰2
በአሁን ሰዓት በታላቁ አል-አቅሷ መስጅድ!
በአካል መገኘት ያልቻችላሁ፡
https://www.youtube.com/live/hc6cMuGnHjI?si=g0q3bAtLkOZvVwPu

❤8🔥3