AAU - Muslim Students Union
6.45K subscribers
2.68K photos
149 videos
51 files
765 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አለማወቅ 2!

‎ተረት ተረት ...

‎አንዲት ጦጣ ሙዙን ሰርቃ
‎በጫካው ውስጥ ብትደበቅ፣
‎ሰው «ተይ» አለ በመልካም ቃል
‎የሀገር ሰላም ለመጠበቅ።

‎ጦጣ ሆዬ መቼ ሰምታ
‎ቢለሳለስ ሞኝ አለችው፣
‎ከዛፉ ላይ ተደብቃ
‎በማጮለቅ ታዘበችው።

‎አልታየችም በሷ ሃሳብ
‎ከፍ ማለት ከልሏታል፣
‎ፍትሕ ምሳር ሆኖ ሲገኝ
‎የሚምራት ይመስላታል?!

‎ከዛፉ ጋር አብሮ ጣላት
‎ተበዳዩ ጊዜው ደርሶ፣
‎ለጭቆናም መቋጫ አለው
‎የነቁ ቀን ጥርስን ነክሶ።

‎በሰው ክብር ተረማምዶ
‎መንጠላጠል የናፈቀው፣
‎ከዛፉ ጋር አንድ ላይ ነው
‎ተገንድሶ የሚወድቀው።

‎ገና መቼ?!

‎ገና መቼ ተቀጣጥሎ
‎ሊያስፈራራ ከምን በቃ፣
‎ልንለኩሰው ስንዘጋጅ
‎የሚሸሹን በደቂቃ?!

‎ገና'ኮ ነው።

‎እሳት ንቆ የከረመው
‎ፍንጣሪ ሸሸ ቢባል፥
‎ያየው እንጂ የማያውቀው
‎አሁን ይሄን እንዴት ያምናል?!

‎ገና መቼ?!

‎ከነግርማው ተሰይሞ
‎ከፊታችን ሰደድ እሳት፣
‎ምን ይባላል ለጨረፍታው
‎መንጠላጠል በር መዝጋት?!

‎ገና'ኮ ... መለኮሱ ነው ...
‎የነደደ መስሏቸው ነው?!

‎ወይ እሳቱን አለማወቅ!!!

#ዘመቻ_ዙልሒጃ!
#በሂደት_ላይ...
#አሁንም_ዝግጁ?!

ቪድዮ፦ ከተማሪ ፊት ለፊት መጥተው ምላሽ መስጠት የነበረባቸው የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሰዎች በመስኮት አጮልቀው ተማሪዎችን ሲመለከቱ።

@aaumsu
🔥5312🥰43
አለማወቅ... 3!

‎ዱላ አስከተለ አሉ
‎አልቻልህ ቢለው፥ በአፉ ዝም ማስባል፣
‎እንዴት በገዛ እጁ
‎ሰው ለራሱ መጥፊያ፥ ቃታውን ይስባል?!

‎አጃኢብ'ኮ ነው።

‎በምድራዊ ጉልበት
‎ሙእሚንን ሊረታ፥ ህልም የወጠነ 'ለት፣
‎ሽንፈቱን ጀምሯል
‎ያኔ ነው ውድቀቱ፥ ያን ጊዜ አበቃለት።

‎ትላንትን አያይም?!

‎የብርሃኑን ችቦ
‎ለማጥፋት አስቦ፥ እጁን የሰደደ፣
‎አቀጣጠለ እንጂ
‎መች እንደተመኘው፥ እሳት አበረደ?!

‎እሳቱ ተፈጥሮው
‎የመጥፋት ዘመኑ፥ ድሮ ስላለፈ፣
የነካካው ጊዜ
‎ከፊቱ የባሰ፥ አንድዶት አረፈ።

‎አጠፋለሁ ብሎ
‎የቆሰቆሰበት፥ ጸጸቱ ቢያውከው፣
‎ወላፈኑ ከብዷል
‎የሰደደውን እጅ፥ ዳግመኛ እንዳይልከው።

‎አርፈው ቢቀመጡ
‎ተቃጥሎ ከመውደም፥ በገዛ ሥራቸው፣
‎አላህን የያዘ
‎መጥፋት እንደማይችል፥ ማን በነገራቸው?!

‎አለማወቅ!!!
ይህን እሳት፥ አለማወቅ!!!

#ዘመቻ_ዙልሒጃ!
#በሂደት_ላይ...
#አሁንም_ዝግጁ?!

@aaumsu
🔥533👏32👍1👌1💯1
አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ

​ባለፈው ጁምዓ በፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ተሰባስባችሁ ከነበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች መካከል በምስሉ ላይ የሚታዩትን ፓወር ባንክ (Power Bank) እና መስገጃ የረሳችሁ (የጣላችሁ) ካላችሁ እቃዎቹን መውሰድ ትችሉ ዘንድ ከታች በተቀመጠው ቦት አማካኝነት ያናግሩን። 👇
@MediasectorFeedback_bot

ማሳሰቢያ፦ እቃዎቹ የእርስዎ መሆናቸውን እርግጠኛ ለመሆን በሚያናግሩን ወቅት ጥቂት ማብራሪያ (ለምሳሌ፦ የፓወር ባንኩን ብራንድ ወይም መስገጃው ያለበትን የተለየ ምልክት) ቢጠቅሱልን ኸይር ነው።


​እባክዎ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉት። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን!

©AAU6kilojemea

@aaumsu
👍327
ዩኒቨርስቲ አዕምሮን ማበልፀጊያ እንጅ ማንነትን መደፍጠጫ አይደለም።

ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንዲያስቡ፣ እንዲመራመሩ፣ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ፣ ሐይማኖታቸውን እንዲጠብቁ፣ መከባበርን እንዲያደብሩ ማገዝ አለበት እንጂ ጨፍላቂ መሆን የለበትም።

የሚወጡ ሕጎች መማር ማስተማሩን ሊያሻሽሉ ሲገባ የተማሪዎችን ማንነት ከጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ መሆን የለባቸውም።

@aaumsu
🔥36💯156👌1
አለማወቅ... 4!

‎ማስፈራሪያው የበገረው
‎ቃልኪዳኑን ያጓደለ፣
‎የድል ድርሳን መክተቢያውን
«እስክሪብቶ» ... የጣለ አለ?!

‎በዚያች ቦታ ...
‎የዚያን ጊዜ ...

‎ታሪክ ዝንቱን የማይረሳው
‎የሚዘከር ገድል ሲጻፍ፣
‎"ጸንቶ መቆም" ጎልቶ ጩኋል
‎"ሂዱ" ከሚል የጨቋኝ አፍ።

‎በዚያች ቦታ ...
‎የዚያን ጊዜ ...

‎"እስክሪብቶ የጣለ አለ"ን
‎"ተበተኑ" ካለው በላይ፣
‎እንደሰማን ማን ይንገረው
‎ያለመፍራት ልኩን እንዲያይ።

‎ለነገሩ... ማን ይፈርዳል?!

‎ሐቅን ይዞ 'ፍርሃት' ላይኖር
‎ከሙእሚን ልብ መዝገበ ቃል፣
‎'መፍራት' ቃሉን እንደማናውቅ
‎ይህን እርሱ በምን ያውቃል?!

‎ባወቀማ... ባልሞከራት!

‎እንድንፈራው ነበር መሰል
‎ዱላ ይዞ የከበበን፣
‎እሳት ዱላን ፈርቶ ሲቆም
‎የት እንዳየው በነገረን?!

‎አለማወቅ!

‎በነገ ገጽ የምንከትበው
‎'ክብርን ማውለቅ' ስለሌለው፣
‎ስለዚህ ነው ቢያስፈራሩን
‎እስክሪብቶ የማንጥለው።

‎ማስፈራሪያው የበገረው
‎ቃልኪዳኑን ያጓደለ፣
‎የድል ድርሳን መክተቢያውን
‎«እስክሪብቶ» ... የጣለ አለ?!

‎••• ከየት መጥቶ?!

#ዘመቻ_ዙልሒጃ!
#በሂደት_ላይ...
#አሁንም_ዝግጁ?!

@aaumsu
🔥41👌85💯3👏1😍1
የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የቀድሞ ኢንፎርሜሽን ሴክተር አሚር አቡበክር "ፍትሕ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች!" - ሲል መልዕክቱን አድርሶናል።

ጥያቄው የሁሉም ነው _ ፍትሕ እስኪመጣ በሁሉም መንገድ እንጠይቃለን _ በአደባባይም ቢሮ ውስጥም እንጠይቃለን _ በሚዲያም በአካልም እንጠይቃለን!

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !

@aaumsu
🔥45👍11👏64👌2🫡2💯1
‎Update !

‎እስከአሁኗ ሰዓት ሰዓት ድረስ ከዩኒቨርሲቲው በኩል ለውይይት የተከፈተ በር የለም!!! - ያንን ተከትሎም ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ሳምንት የቀሩትን ቀናት በመጠቀም ራሱን ለውይይት ብቁ እንዲያደርግ ለመጨረሻ ጊዜ ጥሪ እናቀርባለን። ያ ሳይሆን ቢቀር ግን የውይይት በር ሲዘጋ ለሚከፈቱት ሌሎች በሮች ሁሉ ዩኒቨርሲቲው ተጠያቂነቱን የሚወስድ ይሆናል።

እንደሚታወቀው ሰኞ ዕለት ከፌደራል መጅሊስ አመራሮች ጋር ከቅዳሜው የቀጠለ ውይይት ነበረን። ውይይቱ ፍሬያማ የነበረ ሲሆን፥ በዚህ ሳምንት ውስጥ የመንግስት አካላት የውይይት መድረክ አዘጋጅተው ዘላቂ መፍትሔ የሚመጣበት መንገድ እንደሚኖር ተገልጿል።

‎ውይይቱ ይካሄዳል የተባለው ጁምዓ ምሽት ከተማሪዎች ፊት ሆኖ ሳለ እስካሁንም መዘግየቱ ቅሬታ ፈጥሯል። አሁንም ቢሆን በተማሪው ፊት የተገባው ቃል ተግባራዊ ሆኖ ዘላቂ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ እንጠይቃለን።

‎በቀጠሮ የሚዘገይ ፍትሕ ሊኖር አይገባም። ጨቋኙ የዩኒቨርስቲው መመሪያ ይሻሻል። ድንበር አልፈው እምነታችንን ያንቋሸሹ እና ተማሪዎችን ያንገላቱ አካላት ተጠያቂ ይሁኑ።

ማስታወሻ፦

‎ይህንን ለማስተካከል የሰጠነው ጊዜ፥ ይሄኛው ሳምንት ብቻ ነው። እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ ባሉ የሥራ ቀናት፥ በተገባው ቃል መሰረት ከግቢው በኩል ምላሽ የማናገኝ ከሆነ ትግላችን ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

‎ተማሪዎቻችን፦

‎ይህንን ሳምንት በተመለከተ... ያሉ ሂደቶችንና ውጤቶቻቸውን በትዕግስት እንድትጠብቁና በተጠቀሱት ቀናት ምንም ውጤት የማይመጣ ከሆነ፥ ራሳችሁን ተደራሽነቱን ለሚያሰፋው ትግል እንድታዘጋጁ ስንል እንጠይቃለን።

‎ቀኑ መቁጠር ጀምሯል።

በሚነጉዱት ሰዓታት ፍጥነት ልክ ራሳችሁን እያዘጋጃችሁ ጠብቁ!

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !

@aaumsu
🔥84🫡2815👏4🤬2💯2
ይህ ትላንት የሆነ ነው!!!
‎ለውይይት የተገባው ቃል 4 ቀን ካለፈው በኋላ ማለት ነው።

"አንቺ ለምንድን ነው ያስገባሻት? አልሸባብ ብትሆንም አሸባሪ ብትሆንም እንደዚህ ነው የምታስገቢያት? ምን ማለት ነው?" - የ6ኪሎ ጥበቃ

‎   አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ለ20 ወራት ሲያካሂድ የነበረውን የመብት ጥሰት በውይይት ለመፍታት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ግንቦት 7 / 2018 ዓ.ል ከዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ ጠይቀን ነበር። ውይይትን የተጠየፉት የዩኒቨርስቲው አመራሮች ለተማሪዎች ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ምሽት አራት ሰዓት ሲያልፍ ከሰላም ሚኒስቴር፤ ከኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ፤ ከፌደራል እና አዲስ አበባ መጅሊስ የመጡ አመራሮች ባሉበት ቅዳሜ ውይይት ተደርጎ ዘላቂ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ እንደሚሰራ ተገልፆ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በማግስቱ ቅዳሜ እንዲሁም ሰኞ እለት ከመጅሊስ አመራሮች ጋር ጥልቅ እና ፍሬያማ ውይይት የተደረገ ሲሆን የመንግስት አካላት በዚህ ሳምንት የውይይት መድረኮችን ሊያዘጋጁ ቃል እንደገቡ ተገልፆ ነበር።

‎   ሆኖም ይህ በእንዲህ ባለበት በዛሬው እለት በ6ኪሎ የሚገኙ ጥበቆች በኒቃቢስት ተማሪዎች ላይ እላፊ ንግግሮችን ሲናገሩ እና ተማሪዎች ላይ እንግልት ሲፈፅሙ ነበር። ጥበቃዎቹ ኒቃቢስት ተማሪዎችን እንዳይገቡ ሲከለክሉ አንዲት እህት እርሷ በከፈተችው በር እንዲገቡ ማድረጓን ተከትሎ "አንቺ ለምንድን ነው ያስገባሻት? አልሸባብ ብትሆንም አሸባሪ ብትሆንም እንደዚህ ነው የምታስገቢያት? ምን ማለት ነው?" - እያሉ ሲወርፏት ተስተውሏል።

‎   ይህ ፍፁም አግባብነት የሌለው፤ ዩኒፎርምን ከለበሰ የጥበቃ አካል የማይጠበቅ ድርጊት ነው። መሠል ሕገ- ወጥ ተግባራት እየተፈፀሙ ያሉት ዩኒቨርስቲው ባፀደቀው ሕገ- ወጥ መመሪያ ምክንያት ነውና ችግሩ በውይይት እንደሚፈታ ቃል የገቡ የመንግስት አካላት ውይይቱን በቶሎ አድርገው ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመጡ እንጠይቃለን።

‎ለተማሪዎቻችን፦ ስነ-ምግባር የጎደለው እና ፀያፍ ንግግርን ለሚናገሩ የዩኒቨርስቲው አካላት ምላሽ አትሰጡ። በአላህ ፈቃድ በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲሆኑ የምናደርግ ይሆናል።

‎ለሰላም ሚኒስቴር፤ የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ እና ለሚመለከታቸው በሙሉ፦ ተማሪው በአደባባይ የወጣው ለ20 ወራት ያክል ከቢሮ ቢሮ ተንከራቶ ፍትሕን ስለተነፈገ ነው። በዚያ ምሽት ከተማሪ ፊት የገባችሁትን ቃል በመፈፀም ሀገር የጣለችባችሁን ሀላፊነት ትወጡ ዘንድ ጥሪያችን ነው።

@aaumsu
😡10010💯7🤬5
ለዩኒቨርስቲ ጀመዓዎች፤ ለኸጢቦች፤ ለኢማሞች፤ ለኡስታዞች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕናዎች፦

  ባለፈው ጁምዓ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች በኒቃብ ምክንያት እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰት እና እንግልት አቤት ለማለት ከዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ቢገኙም ጥሪያቸውን የሚሰማ ጠፍቶ እስከ ምሽት 4:30 ብርድ እና ፀሐይ ከፌደራል ማስፈራሪያ ጋር እየተፈራረቀባቸው መቆየታቸው የሚታወስ ነው። መጨረሻ አካባቢ ለማናገር የመጡ ኡስታዞች፣ የሰላም ሚኒስቴር ሰዎች፣ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ አመራሮች ወዘተ ... መጥተው ውይይት ለካሂዶ ዘላቂ መፍትሔ እንደሚመጣ ቢገልፁም እስካሁን ባለው የተባለው ውይይት አልተካሄደም። የዩኒቨርስቲው አካላትም በጀመሩት የመብት ጥሰት እንደቀጠሉ ናቸው።

  ስለሆነም በመጪው ጁምዓ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላሉ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችሁ ዱዓ እንድታደርጉ፤ እየደረሰባቸው ስላለው ነገር በኹጥባዎቻችሁ እንድታደርሱ እንዲሁም አጋርነታችሁን እንድታሳዩ እንጠይቃለን።

@aaumsu
81🔥22🫡10💔4👏2👌2
🌟 ታላቅ የዳዕዋ እና የሽኝት ፕሮግራም! 🌟

⭐️ Grand Da'wa and Well Go Program ⭐️


በአላህ ﷻ ፈቃድ ልቦች ለአላህ ሲሉ የሚገናኙበትና ፈጽሞ ሊያመልጥዎት የማይገባ ታላቅ የዳዕዋ እና የሽኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል።

በተከበሩ እንግዶቻችን መገኘት የምንማርበትና የምንነቃቃበት፣ እንዲሁም ለዓመታት የህብረታችን አካልና የጉዟችን አጋር የነበሩትን ውድ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶቻችንን በታላቅ ክብርና ፍቅር የምንሸኝበት ልዩ ዕለት ነው።

ይህ ፕሮግራም መጪው እሑድ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ል (May 24, 2026) በአል-አቅሷ መስጂድ የሚካሄድ ሲሆን፣ በአላህ ፈቃድ ከጠዋቱ 2፡30 (08:30 AM) ሰዓት ላይ የሚጀምር ይሆናል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ ለመማር፣ ለማስተንተንና መንፈስን ለማደስ በዚህ ፕሮግራም ላይ እንድትገኙ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
@aaumsu
😭2111👍7🥰3💯1🫡1
የጊዜ ገደቡ ተጠናቋል፤ ሰበቦቹ ግን ቀጥለዋል!

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የመንግስት አካላት እና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች አፋጣኝ የውይይት መድረክ እንደሚያዘጋጁ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። እኛም የተገባውን ቃል በማክበር ይህንን ሳምንት እንደ የመጨረሻ የትዕግስት ጊዜ ሰጥተን ነበር። ነገር ግን ዛሬ ጁምዓ (ግንቦት 14) ቢደርስም፣ ከተማሪዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ ውይይት እስካሁን አልተካሄደም።

በውይይት ጠረጴዛ ዙሪያ ከመቀመጥ ይልቅ፣ የሚመለከታቸው አካላት አሁንም የተለያዩ ሰበቦችን እየደረደሩ ይገኛሉ።
አቋማችን አሁንም የፀና ነው፤ መብቱን የጠየቀን ንፁህ እና ሰላማዊ ተማሪ በቢሮክራሲ ማድረቅና ማሸማቀቅ አይቻልም።

ለሚመለከታችሁ አካላት ሁሉ የምናስተላልፈው መልዕክት አጭርና ግልጽ ነው፦ ህጉን አስተካክሉ እንጂ መፍትሔን አታዘግዩ!

ለተማሪዎቻችን:- የሰጠነው የጊዜ ገደብ አብቅቷልና ንቃታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እናሳስባለን። ከዚህ በኋላ ለሚፈጠረው ማናቸውም ነገር ኃላፊነቱን የሚወስዱት ቃላቸውን ያጠፉት አካላት ናቸው። ቀጣዩን አቅጣጫ እና የትግል እርምጃ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል!

አሁንም ጥያቄ አለን! ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!

@aaumsu
50🫡37🔥10💯3
"እኛ አፋሮች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና በአክሱም ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን በደል እንቃወማለን። ኒቃቧንም ትለብሳለች፤ ትምህርቷንም ትማራለች።"

በአፋር ካሉ ሙስሊም ወንድሞች አመሻሹን የተላከ የአብሮነት መልዕክት ነው። ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው። ከአፋር ጀምሮ እስከ ሶማሌ፤ ከባሌ ጀምሮ እስከ ደሴ ያለውን ሙስሊም ይመለከታል። የእምነት፣ የማንነት፣ የክብር ጉዳይ ነውና።

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !

@aaumsu
🔥6122💯7🥰5👌3👍2👏1
🌟 1 ቀን ብቻ ቀረው🌟

ታላቅ የዳዕዋ እና የሽኝት ፕሮግራም!

ነገ ጠዋት 2:30 እግሮች ሁሉ ወደ አቅሷ መስጂድ ያመራሉ!!

📌 ታላላቅ እንግዶች የሚታደሙበት፤
📌  ለአመታት አብረዉን የቆዩ የጊቢያችንን ሙስሊም ተማሪዎችና የህብረታችን ልጆች የምንሸኝበት፤ እና
📌የተለያዩ ቁም-ነገር አዘል ትምህርቶችን የምንቀስምበት ፕሮግራማችን እነሆ ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል

ታላቁ የዳዕዋ እና የሽኝት ፕሮግራም የአንድ ቀን እድሜ ብቻ ቀርቶታል!

🕔 ታላቅ ፕሮግራም በታላቁ አል-አቅሷ መስጂድ፣ ነገ ከጠዋቱ 02፡30 ጀምሮ!

ሁሉም የአአዩ ተማሪዎች እንዲታደሙ ተጋብዘዋል!

@aaumsu
16👍4🥰2
🌟 የተወሰኑ ደቂቃዎች ብቻ 🌟

ታላቁ የዳዕዋ እና የሽኝት ፕሮግራማችን ሊጀምር የተወሰኑ ደቂቃዎች ቀርተዋል ሁላችንም እንገኝ!

@aaumsu
13💔1
ሸይኽ ሙሀመድ ፈረጅ በአሁኑ ሰዓት ስለወጣትነት ልክ ምክር እየለገሱን ይገኛሉ።

እስካሁን ያልተገኘን ቶሎ እንፍጠን

@aaumsu
🥰145💔1
በአሁን ሰዓት በታላቁ አል-አቅሷ መስጅድ!

በአካል መገኘት ያልቻችላሁ፡
https://www.youtube.com/live/hc6cMuGnHjI?si=g0q3bAtLkOZvVwPu

@aaumsu
10🔥3