እኛን ሊያስሩን ይችላሉ ... ጥያቄዎቻችንን ግን ሊያስሩ አይችሉም ... ወንድሞቻችንን ሊያስሩ ይችላሉ ... ወደሗላ እንድንተዋቸው ግን ሊያደርጉን አይችሉም ... በአንድነት በአንድ ድምፅ ወንድማችንን እንዳስፈታነው በጋራ በሕብረት በአንድነት ጥያቄያችንም ይፈታል።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu
🔥113❤25💯12🏆6
🔥97💯14❤8👍4👏1👌1
በዚህ ምሽት የተማሪውን ቁርጠኝነት ያስተዋለ ማንም ሰው ተማሪው ስለመብቱ ያለውን ግንዛቤ፤ ለመብቱ ሊከፍለው የሚችለውን መስዋዕትነት፤ እስኪያስከብር ድረስ ሊሄድ የሚችልበትን ርቀት ይረዳል። ተማሪው እየተራበ፣ ብርድ እየመታው፣ እንደበድብሃለን እየተባለ ነበር የቆየው። ሆኖም ሁሉም ማስፈራሪያ ምንም ነበር። ይባስ ብሎም ከውጪ የነበረው ተማሪ ካልተቀላቀልን፣ አብረን ካልሆን ብሎ እየታገለ ነበር። ነገሩ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ (ረድየላሁ ዐንህ) "እናንተ ሞትን የምትሸሹትን ያክል የእኔ ወታደሮች ይፈልጉታል።" - እንዳለው ነው። እንደ ድንገት ሳይደርሱ የቀሩት ተማሪዎች ቁጭት እና መልዕክት ደግሞ "ምነው ከእናንተ ጋር በሆንን!" - የሚል ነበር።
ጥንካሬያችንም ይኼው ነው። ብርታታችንም ይኼው ነው። የተማሪው ቁጭት፣ ግንዛቤ፣ ቆራጥነት እና መስዋዕትነት ማለት ነው።
ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu
ጥንካሬያችንም ይኼው ነው። ብርታታችንም ይኼው ነው። የተማሪው ቁጭት፣ ግንዛቤ፣ ቆራጥነት እና መስዋዕትነት ማለት ነው።
ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu
🔥127❤18👏7🥰4💯3👍1
Forwarded from AAU - Muslim Students Union
አልሐምዱሊላህ __ ታድለናል !
ገና ባልጠና ጉልበታችን፥ የብዙዎች ያልተሰራ የቤት ሥራ በጫንቃችን ላይ ተጣለብን።
ታድለን ...
የትውልድን ክብር በመጠበቅ ላይ ኃላፊነት ወሰድን።
ታድለን...
የእህታቸው ክብር እየተነካ፥ በሰላም ተኝተው የማያድሩ ዓይኖች ተሰጡን።
ታድለን...
ፍትሕ ስትቀበር «በእኔን ከተመቸኝ ይሁንታ» የማይቀበል አዕምሮ ተሰጠን።
ታድለን...
ቀን እስኪያልፍ የሚጎድልን ክብር የማይታገስ ልብ ተቸርን።
ታድለን...
ሌሎች የፈሩበትን ነገር በድፍረት የመጋፈጥ ወኔ ተሰጠን።
ታድለን...
«አዳኝ» እስኪመጣ ሳንጠብቅ፥ ኃላፊነታችንን የምንወጣበት ተቆርቋሪነት ተሰጠን።
እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ታድለን...
ፍትሕ መጓደል አመመን።
የመብታችን መጣስ ቆረቆረን።
ጭቆና አንገሸገሸን።
ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ታድለንማ'ኮ...
ታሪክ "ካላጎነበሱት" መካከል መዘገበን።
መስዋዕትነት ከገባቸው፤
ትውልዳቸውን ለመታደግ ቁርጠኛ ከሆኑት መሃል መዘገበን።
ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ታድለንማ'ኮ...
በአላህ ላይ ከሚመኩት፣
ለመንገዱ ከሚታመኑት፤
ድልንም ከርሱ ብቻ ከሚጠብቁት ሰራዊቶቹ መሃል አደረገን።
ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ለኛ የተሰጠው ለማን ተሰጥቷል?! - ዙሪያችሁን አትመለከቱምን?!
በህይወታችን ካየናቸው ብዙ ብዙ ብቸኝነቶች ውስጥ፥ በዚህ የትግል መንገድ ላይ ያለ ብቸኝነትን ያህል ዋጋ ያለው ብቸኝነት የት እናገኛለን?!
አላህ የሚያየው፣ የሚመሰክርለት ብቸኝነት!
ወደ ድል እንጂ የማይደርስ፣ ውድቀት የሌለበት ብቸኝነት!!
ትርጉሙ ጥልቅ፣ ክፍያው ብዙ ብቸኝነት!!!
ይህ እንደዋዛ 'ሚገኝ ነው እንዴ 'ሚመስለን?! በፍጹም።
ለዚህ ብቸኝነት መመረጥ ያሻዋል።
ይህ'ኮ ታላቅ ጸጋ እንጂ ሌላ አይደለም።
አልሐምዱሊላህ!!!
ሐስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል!!!

🔥131❤36🥰10🫡7👌4👏1
በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተከሰተውን ክስተት አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የወጣ መግለጫ
“መብት በልመና አይገኝም!”
ይህ በታላቅ ትዕግስትና ፅናት ያለፉትን 19 ወራት (ከ620 ቀናት በላይ) መዋቅራዊ በደልና ማግለል የተጋፈጠው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ድምፅ ነው ። ህገ-መንግስታዊ መብትን በሚጥስና በተለይም የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ሂጃብና ኒቃብ በግቢው ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሚከለክል አድሏዊ መመሪያ ምክንያት እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በየቀኑ ሲንገላቱ፣ አካዳሚያዊና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ሲፈጸምባቸው ኑረዋል ። ትናንት ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ል. በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሰላማዊ መንገድ በመሰባሰብ፣ በብርድ፣ በጨለማና በረሃብ ውስጥ ሆነው የታየው የመቶዎች ፅናት ይህ ትውልድ ማንነቱን፣ እምነቱንና ክብሩን ለምንም አሳልፎ የማይሰጥ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠበት ታሪካዊ ክስተት ነው ። ከሃይማኖት መሪዎቻችን (መጅሊስ) ጋር በተደረገው ስምምነትና በተሰጠው ቃል መሠረት ጉዳዩን በኃላፊነት እንዲይዙት ሌሊት ላይ ተማሪው ወደ ማደሪያው ቢበተንም ፣ ይህ ትግሉ ተጠናቀቀ ማለት ሳይሆን መመሪያው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሻሻል የተሰጠ የጊዜ ገደብ ነው ። መብታችን በግልፅ ተረጋግጦ፣ የታተመ የመመሪያ ለውጥ በይፋ እስካልመጣ ድረስ ሰላማዊ ትግላችን በበለጠ ስፋትና ጉልበት ይቀጥላል! መላው ፍትህ ፈላጊ ማህበረሰብም ከተበደሉ ተማሪዎች ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ። በዱዓ፣ በንቃትና በአንድነት ቆመን የመጨረሻውን ፍሬ እናያለን!
“ጥያቄ አለን! መልስም እንፈልጋለን!”

👏126🔥21❤18🫡5🥰4👌4🏆3👍1
AAU - Muslim Students Union
© ለፈገግታ 😁 ትዝ የሚለው ካለ ፅናትን፣ ጥንካሬንና ከአቋም አለማፈግፈግን ያየንበት አጋጣሚ!! @aaumsu
እስኪርቢቶ የጣለ?
ፍትህ እንደራበኝ እንደተጠማሁኝ ፣
ጁሙዐን ሰግጄ ቶሎ አሰላመትኩኝ ፣
ሀጃ አለብኝ እና... በፍጥነት ወጣሁኝ ፤
መንገዱን ተጉዤ ጫፍ እንደደረስኩኝ ፣
መብቴን ለመጠየቅ ከቢሯቸዉ ቆምኩኝ ::
የእህቴን ስቃይ እንግልት አይቼ፣
ህመሟ ተሰምቶኝ ግፉን ተመልክቼ ::
ነፃነትን ሽቼ... ከስኬት ለመድረስ ፣
ስለ ፍትህ ቆምኩኝ መብቷን ለማስመለስ::
ታዲያ በቆምኩበት እዛው ስብሰለሰል ፣
ላቤ ግጥም አለ ጭንቀቱ ነው መሰል ?
ግራ ተጋባሁኝ 'ምን ሆኘ ነው ዛሬ?'
የውሸት ነው እንዴ ቢላህ መመስከሬ ?
ነብዩን መውደዴ ኢስላምን ማፍቀሬ ?
በጭራሽ አይሆንም! የምን ጥርጣሬ ፣
በላብ ያጠመቀኝ... ያውና ሚስጥሬ ...
ለካስ ፀሀዩ ነው መጨነቄ አይደለም፣
ትንሽ ሞቆኝ እንጂ ያሳሰበኝ የለም ::
ጠራራው በረደ ፀሀይም ጠለቀች ፣
መግሪብ ተሰገደ ልቤም ተፈተነች::
ፊትለፊቴ ቁሞ ግብዳው ፌደራል ፣
ጥቁር ጎማ ይዞ ሲዝት ይሰማኛል ፤
ታዲያ ሰውነቴ መንቀጥቀጡን ያዘው ፣
እኔም ግራ ገባኝ 'እንዴ! ምን ሆኜ ነው?'::
እውነት አልነበረም ለአሏህ መስገዴ ?
መቆም መቀመጤ ማጎንበስ መውረዴ ?
አካሌ ሲከዳኝ እንዲሁ መፍቀዴ ...
በፍፁም አይደለም! ላስረዳችሁ አንዴ ::
ለካስ ነፋሱ ነው የአመሻሽ ብርዱ ፣
ፈርቸ አልነበረም የነቢ ልጅ ወንዱ ፤
"አንዴ ሁላችሁም ሶለዋት አውርዱ"
ንቅንቅ አላልኳትም አገዘኝ ሶመዱ ::
በዚህ ሁኔታ ላይ እዛው ተቀምጬ፣
ሳወርድ ሳወጣ በሀሳብ ተውጬ::
መጋፋት ጀመሩ... ፌደራል ፖሊሱ ፣
ከበው አስፈራሩ "ተበተን" "ተነሱ"
ጭንቀቴ አገረሸ ጀግንነት ተረሳ ፣
ያኛው "ግደሉን" ሲል ለነብሱ ሳይሳሳ ፤
ያንኛው ሲቀመጥ... ያንኛው ሲነሳ ፣
ግራ ተጋባሁኝ 'አወይ የኔ አበሳ!'::
በዛ መሀል ነበር ይች ቃል ተሰማች ፣
"እስኪርቢቶ የጣለ...?" ሰኪናን አመጣች ፤
አንዱ ወንድማችን ይህን ከማለቱ ፣
ብዙ መልክት አለው ሁሉም በመስማቱ ፤
የጣለውን እቃ ይውሰድ ባለ ሀቁ ፣
ምንም አያመጡ በፅናት ጠይቁ ፣
አብሽሩ ማለት ነው አትጨናነቁ ፣
ወዳው ሲገባቸው ወንድሞችም ሳቁ ፤
እንደማንመለስ እነሱም አወቁ ::
እኔ ግን የቆጨኝ... በራሴ መፍረዴ ፣
ያችን ጥቁር ዱላ ሳልቀምሳት መሄዴ፣
ኡስታዝን አምኜ... ለጊዜው መውደዴ ፣
መፍትሄው ሊርቀኝ ጥያቄ መስደዴ፣
ዘላቂ እንደማይሆነ እያወቀው ሆዴ ::
"ሽርጡን የጣለ"... ይህ ነው ጨርቄ ማቄ፣
ለምን ነበር ታዲያ ምሽጌን መልቀቄ ፣
"መስገጃ የጣለ"... በቂ ነበር ስንቄ ፤
ቅር አለኝ በእውነት... ውይ አለማወቄ ::
©Sefere Selam Muslum Students Jeme'a
@aaumsu
ፍትህ እንደራበኝ እንደተጠማሁኝ ፣
ጁሙዐን ሰግጄ ቶሎ አሰላመትኩኝ ፣
ሀጃ አለብኝ እና... በፍጥነት ወጣሁኝ ፤
መንገዱን ተጉዤ ጫፍ እንደደረስኩኝ ፣
መብቴን ለመጠየቅ ከቢሯቸዉ ቆምኩኝ ::
የእህቴን ስቃይ እንግልት አይቼ፣
ህመሟ ተሰምቶኝ ግፉን ተመልክቼ ::
ነፃነትን ሽቼ... ከስኬት ለመድረስ ፣
ስለ ፍትህ ቆምኩኝ መብቷን ለማስመለስ::
ታዲያ በቆምኩበት እዛው ስብሰለሰል ፣
ላቤ ግጥም አለ ጭንቀቱ ነው መሰል ?
ግራ ተጋባሁኝ 'ምን ሆኘ ነው ዛሬ?'
የውሸት ነው እንዴ ቢላህ መመስከሬ ?
ነብዩን መውደዴ ኢስላምን ማፍቀሬ ?
በጭራሽ አይሆንም! የምን ጥርጣሬ ፣
በላብ ያጠመቀኝ... ያውና ሚስጥሬ ...
ለካስ ፀሀዩ ነው መጨነቄ አይደለም፣
ትንሽ ሞቆኝ እንጂ ያሳሰበኝ የለም ::
ጠራራው በረደ ፀሀይም ጠለቀች ፣
መግሪብ ተሰገደ ልቤም ተፈተነች::
ፊትለፊቴ ቁሞ ግብዳው ፌደራል ፣
ጥቁር ጎማ ይዞ ሲዝት ይሰማኛል ፤
ታዲያ ሰውነቴ መንቀጥቀጡን ያዘው ፣
እኔም ግራ ገባኝ 'እንዴ! ምን ሆኜ ነው?'::
እውነት አልነበረም ለአሏህ መስገዴ ?
መቆም መቀመጤ ማጎንበስ መውረዴ ?
አካሌ ሲከዳኝ እንዲሁ መፍቀዴ ...
በፍፁም አይደለም! ላስረዳችሁ አንዴ ::
ለካስ ነፋሱ ነው የአመሻሽ ብርዱ ፣
ፈርቸ አልነበረም የነቢ ልጅ ወንዱ ፤
"አንዴ ሁላችሁም ሶለዋት አውርዱ"
ንቅንቅ አላልኳትም አገዘኝ ሶመዱ ::
በዚህ ሁኔታ ላይ እዛው ተቀምጬ፣
ሳወርድ ሳወጣ በሀሳብ ተውጬ::
መጋፋት ጀመሩ... ፌደራል ፖሊሱ ፣
ከበው አስፈራሩ "ተበተን" "ተነሱ"
ጭንቀቴ አገረሸ ጀግንነት ተረሳ ፣
ያኛው "ግደሉን" ሲል ለነብሱ ሳይሳሳ ፤
ያንኛው ሲቀመጥ... ያንኛው ሲነሳ ፣
ግራ ተጋባሁኝ 'አወይ የኔ አበሳ!'::
በዛ መሀል ነበር ይች ቃል ተሰማች ፣
"እስኪርቢቶ የጣለ...?" ሰኪናን አመጣች ፤
አንዱ ወንድማችን ይህን ከማለቱ ፣
ብዙ መልክት አለው ሁሉም በመስማቱ ፤
የጣለውን እቃ ይውሰድ ባለ ሀቁ ፣
ምንም አያመጡ በፅናት ጠይቁ ፣
አብሽሩ ማለት ነው አትጨናነቁ ፣
ወዳው ሲገባቸው ወንድሞችም ሳቁ ፤
እንደማንመለስ እነሱም አወቁ ::
እኔ ግን የቆጨኝ... በራሴ መፍረዴ ፣
ያችን ጥቁር ዱላ ሳልቀምሳት መሄዴ፣
ኡስታዝን አምኜ... ለጊዜው መውደዴ ፣
መፍትሄው ሊርቀኝ ጥያቄ መስደዴ፣
ዘላቂ እንደማይሆነ እያወቀው ሆዴ ::
"ሽርጡን የጣለ"... ይህ ነው ጨርቄ ማቄ፣
ለምን ነበር ታዲያ ምሽጌን መልቀቄ ፣
"መስገጃ የጣለ"... በቂ ነበር ስንቄ ፤
ቅር አለኝ በእውነት... ውይ አለማወቄ ::
©Sefere Selam Muslum Students Jeme'a
@aaumsu
❤95🥰20🔥10👏9🏆9👌7😭3👍1😍1
እስክርቢቶ የጣለ?
ሊያስጥሉኝ ያስባሉ። ሊያስጥሉኝም እየሞከሩ ነው። ግን አልጣልኩም፤ አልጥልምም።
ፌደራሎች እያስፈራሩ፤ ተማሪውን እየገፈታተሩ፤ ተማሪው የፈራ የተጨነቀ በመሰላቸው ሰዓት ከአንድ ወንድም ጮክ ብላ የተሰማች ንግግር ነበረች። መልዕክቱ ጥልቅ ነበር። የእኛ ትኩረት ሊነጥቁን፣ ሊወስዱብን፣ ሊያሳጡን እየሞከሩ ያሉትን ብዕር በፅናት መያዝ ላይ እንደሆነ ያመለክታል። ከፊት ለፊታችን የነበረው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የሴራው ጠንሳሽ ሲሆን፤ እኛ ደግሞ ብዕራችንን እንደያዝን ለሴራው ሳንበገር ከዚያው ቆመን ነበር።
በአላህ ፈቃድ መብታችን በመመሪያ እስኪፀና፤ ብዕራችንን ለመንጠቅ የሚሞክሩ ሰዎች በሕግ ፊት ተጠያቂ እስኪሆኑ ድረስ እንደፀናን እንቆያለን።
መብት በትግል እንጂ በልመና አይገኝምና!

🔥40❤10👌3👍1
Update!
በትላንትናው ዕለት ቅዳሜ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ተወካዮች ከመጅሊስ ተወካዮች ጋር ረጅም ሰዓታት የፈጀ፣ የችግሩን አሳሳቢነትና የእህቶቻችንን ስቃይ በዝርዝር ያቀረብንበትን ውይይት አድርገናል። በዚሁ መሠረት፣ ይህንን ውይይት ይበልጥ በተጠናከረና ውጤት ተኮር በሆነ መልኩ ነገ ሰኞ ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
ነገር ግን ላለፉት 19 ወራት የተመገብናቸው የውሸት ተስፋዎችና የተሰበሩ ቃላቶች በልባችን ላይ የፈጠሩት ቁስልና ቁጣ አሁንም ትኩስ ነው! እነዚህ ውይይቶች የተማሪውን ቁጣ ለማብረድ፣ ጊዜ ለመግዛትና ድምፃችንን ለማጥፋት የሚደረግ ሌላው የተለመደ "የማደንዘዣ" እና የማስታገሻ ሙከራ እንዳልሆነ የምናምንበት ምንም ምክንያት የለንም። እኛ በውይይት ሰበብ የምንታለል ትውልድ አይደለንም፤ እኛ በወረቀት ላይ የሰፈረና የታተመ ውጤት የምንፈልግ ትውልድ ነን!
በዚህ ጉዳይ ላይ እጃችሁን ላስገባችሁ አካላት ሁሉ፡ ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ለመንግስት ተቋማትም ሆነ ለመጅሊስ የምናስተላልፈው መልዕክት አጭርና ግልጽ ነው፦
ለተማሪዎቻችን፦
ንቃታችሁ ይባስ እንጂ ፈፅሞ አይቀንስ። በዱዓ እና በንቃት ቁሙ። ነገ ሰኞ የሚመጣውን ውጤት በንቃት እንጠብቃለን፤ ያ ውጤት ግን የታተመና የተፈረመ የፖሊሲ ለውጥ የሚያመጣ አቅጣጫ ካልሆነ፣ ትላንት በፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት ፊት ለፊት የነበረው ማዕበል በበለጠ ጉልበትና ስፋት የማይመለስበት ምንም ምክንያት የለም!
አሁንም ጥያቄ አለን! መልስም እንፈልጋለን!

“ህጉን አስተካክሉ (መመሪያውን ቀይሩ) እንጂ ሰላማዊ ተማሪዎችን ለማታለልና ጊዜ ለመግዛት አትሞክሩ!” መብቱን የጠየቀን፣ ንፁህ እና ሰላማዊ ተማሪ በቢሮክራሲ ማድረቅና ማሸማቀቅ አይቻልም። ፍትህ በውይይት ቀጠሮዎች አይተካም!
ለተማሪዎቻችን፦
ንቃታችሁ ይባስ እንጂ ፈፅሞ አይቀንስ። በዱዓ እና በንቃት ቁሙ። ነገ ሰኞ የሚመጣውን ውጤት በንቃት እንጠብቃለን፤ ያ ውጤት ግን የታተመና የተፈረመ የፖሊሲ ለውጥ የሚያመጣ አቅጣጫ ካልሆነ፣ ትላንት በፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት ፊት ለፊት የነበረው ማዕበል በበለጠ ጉልበትና ስፋት የማይመለስበት ምንም ምክንያት የለም!
አሁንም ጥያቄ አለን! መልስም እንፈልጋለን!
@aaumsu
🔥118💯26😡11❤10👏7🫡7👌2
أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَأْتِكُم مَّثَلُ الَّذِينَ خَلَوْا مِن قَبْلِكُم ۖ مَّسَّتْهُمُ الْبَأْسَاءُ وَالضَّرَّاءُ وَزُلْزِلُوا حَتَّىٰ يَقُولَ الرَّسُولُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ مَتَىٰ نَصْرُ اللَّهِ ۗ أَلَا إِنَّ نَصْرَ اللَّهِ قَرِيبٌ.
@aaumsu
@aaumsu
🔥60❤14🥰4👍2
الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ.
@aaumsu
@aaumsu
🔥68🥰27👍2❤1
የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ የዚህ ትውልድ ሀላፊነት ነው። By any means necessary መብቶቻችን እስኪከበሩ እንጠይቃለን። ድንበር አልፈው ክብራችንን የሚነኩ አካላትንም ተጠያቂ እናደርጋለን።
@aaumsu
@aaumsu
🔥61❤8👌4💯3
🔥48❤22💯9🥰1
የዙልሒጃ ጨረቃ ዛሬ ታይታለች። ዱንያ ላይ ካሉ ቀናቶች መካከል አስሩ አንድ ብለው ጀመሩ ማለት ነው። በዚህም ዒደል- አድሃ ግንቦት 19 ረቡዕ ቀን የሚውል ይሆናል።
አላህ በእነዚህ በላጭ በሆኑ ቀናት በላጭ የሆኑ ስራዎችን የምንሰራ ያድርገን። መብቶቻችን ተከብረው፤ የእህቶቻችን ስቃይ ቆሞ፤ በዳዮችም ተጠይቀው ፍትሕን የምናሰፍንበትን ብርታት ይስጠን። አሚን!
ኢንሻ አላህ ይሳካል ! ! !
@aaumsu
አላህ በእነዚህ በላጭ በሆኑ ቀናት በላጭ የሆኑ ስራዎችን የምንሰራ ያድርገን። መብቶቻችን ተከብረው፤ የእህቶቻችን ስቃይ ቆሞ፤ በዳዮችም ተጠይቀው ፍትሕን የምናሰፍንበትን ብርታት ይስጠን። አሚን!
ኢንሻ አላህ ይሳካል ! ! !
@aaumsu
❤41🔥14⚡1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘህረዲን የኒቃብ ክልከላን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።
"አሚና ኒቃብ ለብሼ ልግባ ስትል በቀለች በአንቺ ትቀናና ሌላ ነገር ታመጣለች አይባልም። ካመጣች ሐይማኖቶ ከሆነ ለምንድን ነው የማይፈቀድላት? ይህ ሀገር እኮ የሐይማኖተኞች ሐገር ነው። ሐይማኖተኞች መከበር አለባቸው። ጥቁር ለበሰች ነጭ ለበሰች ለትምህርት ጎድቶት አይደለም። እኔ አስተማሪ ነበርኩ። አዕምሮን አይደል የምትለውጡት? እንደ ምሁራን ተሰባስባችሁ መልበስ ይጠቅማል አይጠቅምም ተብሎ ሊወራ አይገባም።"

🔥80💯17❤7👏6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በስልጤ ዞን የዳሎቻ ወረዳ ማህበረሰብ ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu
ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu
❤120🔥27👏7😭7👌6😍1
#ዘመቻ_ዙልሒጃ!
ትግላችን ወደቀጣይ እርምጃ የሚሸጋገርበት አዲስ ነገር ••• !!!
አላህ (ሱ.ወ) ከዱንያ ቀናት ሁሉ ያከበራቸው እነዚህ ቀናት፥ የተከበረ የሆነውን የርሱን ሃይማኖት ለመጠበቅ አመቺ ዕድሎች ናቸው።... መንገዱ በነዚህ የዙልሒጃ ቀናት ይበልጥ ትርጉሙን ያገኛል።... አጅሩም በዚያው ልክ እጥፍ ድርብ ይሆናል!!! - እኛን ሊያከብር ኃላፊነት ያሸከመንና በተለያዩ አጋጣሚዎች ምንዳችንን የሚያበዛው እንዲሁም ድልን ሊያቀዳጀን ቃልኪዳኑ የሆነው ጌታችን ምስጋና ይገባው። አልሐምዱሊላህ።
ከምንም በላይ ለድላችን መፋጠን ሰበብ በሚሆኑ መልካም ስራዎች፥ በተለይ በዱዓ በመበርታት ላይ ሁላችሁንም አደራ እንላለን።
የጭቆና ውድቀት የሚጀምረው፥ ሰዎች ሁኔታውን በግልጽ የተረዱበት ጊዜ ላይ ነው።... እኛም አሁን ላይ ገብቶናል። በሕገ-ወጥ መመሪያ ሽፋን የሚፈጸምን በደል እንረዳለን። የእስልምናና የሙስሊሞች ጥላቻ ያለባቸው አካላት የሚመርጡትን ሂደት እናውቀዋለን።... እኛ ወደ ድል እንደምንጓዝም ጭምር።
የተነካው የአላህ (ሱ.ወ) ዲን፣ የረሱሉ (ሰ.ዐ.ወ) መንገድ፣ የምዕመናን ባጠቃላይ ክብር ነውና፥ ወደኋላ ለመመለስ የሚያስችለን ሁኔታ የለም። ከጅምሩ ወደኋላ ለመመለስ የሚያስበው ለቀለለ ነገር የሚታገል እንጂ ሌላ ማን ነው?!... ይህንን ዓለም የሚሻገር የገዘፈ ዓላማ ባለቤት የሆነ፣ ወደ ድል እንጂ ወዴትም እንደማይሄድ ያረጋገጠ ሰው እንዴት ብሎ ወደኋላ ስለመሄድ ያስባል?! - መንገዳችንማ ወደፊት ብቻ ነው!!!
የርሱ ባሪያዎች አድርጎ፥ ፍርሃትን በኛ ላይ ጉልበት ያሳጣው ጌታችን ምስጋና የተገባው ይሁን።
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ፦
በነዚህ የመስዋዕትነት አየር ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ በሙእሚኖች ልብ ላይ በሚነፍስበት ወቅት፥ የኢስማዒልን (ዐ.ሰ) አላህን የመታዘዝና፥ በመንገዱ ላይም ራስን ለመስዋዕትነት የማዘጋጀት ጉዞ በጋራ እንጓዝ ዘንድ ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ?!
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ፦
ጌታችን በነጻነት የማይመለክበት ቦታ ላይ እንደመቀመጥ የሚቆረቁር ነገር አለን?! - ታዲያ ነገ በአላህ ፊት የምትጠየቅ ነፍሳችን፥ ትመልሰው ቃል እንዳታጣ የሚያደርጋትን ተግባር ለማከናወን ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ?!
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ፦
ወደኋላ መመለሳችን፥ ከፊት ከሚጠብቁን ፈተናዎች በላይ አስፈሪ በሆነበትና መመለስ በማይታሰብበት በዚህ ጊዜ... ከባዱን ግን አስተማማኙን የድል መንገድ ለመምረጥ ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ?!
••• ይኼኛውን ዒድ ከብዙ ትርጉሞች ጋር የምናከብረው ስንሆን (በአላህ ፈቃድ) •••

🔥49❤18👌5🫡5💯2