AAU - Muslim Students Union
6.44K subscribers
2.68K photos
149 videos
51 files
765 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
በረሃብ፤ በብርድ ውስጥ ሆኖ ተማሪው አሁንም እንደጸና ነው!

@aaumsu
🔥39👏8👌21👍1
ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ከተሰባሰብን 5 ሰዓታት አልፈዋል። ጀምበር አዘቅዝቃም ምሽት ገብቷል። እኛ መቶዎችን ሆነን ለጥያቄያችን መልስ ስጡን እያልን ባለበት ሰዓት ፕሬዚዳንቱ ልደታ ካምፓስ ዶርም እያስመረቁ ነበር። አሁን ደግሞ ምግብ አታስገቡም ብለው በሆድ ሊደልልን፣ ከውጪ ያሉትን ደግሞ እንገባለን ካላችሁ እንደበድባችሗለን በማለት እያስፈራሩ ነው።

ዳግም ለማስቀመጥ ያክል፦

ጥያቄያችን ሰላማዊ ነው። ሰላማዊ ነው ማለት ግን በሆድ ወይንም በዱላ ይሸጣል ማለት አይደለም። ለጥያቄያችን መልስ እስክናገኝ ድረስ እናድራለን፣ እንውላለን፣ እንራባለን፤ መስዋዕትነትም እንከፍላለን።

መጅሊስ እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፦ ሰላማዊው ጥያቄያችን በፍትሐዊ መንገድ ይመለስ ዘንድ ስሩ። ሴት ልጅ ብርድ ላይ አትደር፤ ተማሪዎች እንቅልፍ አጥተው ሜዳ ላይ አይደሩ። ስለፍትሕ ቁሙ! ታሪክ እየተፃፈ ነው!!

@aaumsu
👏6915🔥9👍6💯31👌1
"እናንተም የበላዮች ስትኾኑ ምእመናን እንደኾናችሁ አትስነፉ፤ አትዘኑም፡፡" (ኣሊ-ዒምራን 139)

@aaumsu
55🔥6👌3💯2👏1
እናት አባቶች ዱዓችሁ መሳሪያችን ነውና በዱዓ አስታውሱን። ይህ የትውልድ አማና ነው። ሁሉም በያለበት በሚችለው ማገዝ ግዴታው ነው። ኡስታዞች፣ የመጅሊስ አካላት፣ የሚዲያ ሰዎች፣ የመንግስት አካላት ሀላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ ጥያቄያችን ነው።

አደራ ! አደራራራ!!

@aaumsu
80👍11💯4🔥2👌21🥰1
የዚህ ትውልድ አካል መሆን ከክብርም ክብር ነው!

@aaumsu
🔥77💯2414👏4👌32
ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ አሁን ምሽት 2:40 ሰዓት ድረስ፣ ተማሪዎቻችን በብርዱና በጨለማው ውስጥ ቁጭ ብለው ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እየጠበቁ ይገኛሉ። መብትንና ክብርን ለማስከበር የሚደረግ ጉዞ መራራና ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም፣ የእነዚህ ወጣቶች ጽናት ግን የፍትሃዊነታቸው ትልቁ ማረጋገጫ ነው።

📌 ለተማሪዎቻችን በዚህ ብርድ በበዛበት ምሽት እያሳያችሁት ያለው ተስፋ አለመቁረጥና ቁርጠኝነት ታሪክ የማይረሳው ታላቅ የጽናት መዝገብ ነው። ቅስናችሁ አይሰበር፣ ሞራላችሁ አይውረድ። በዚህ አስቸጋሪ ሰዓት የምታሳዩት ትዕግስት (ሰብር) እና አንድነት ለነገው ድላችሁ መሰረት ነው። አላህ እውነተኞችንና መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ የሚጠይቁትን መቼም ቢሆን አይጥልም።

📌 ለሚዲያ አካላት እነዚህ ወጣቶች የነገዋ ሀገር ተስፋዎች እንጂ የሁከት አራማጆች አይደሉም። ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ህጋዊና ሰብአዊ መብቶቻቸውን ይዘው መልስ ፍለጋ በብርድ ላይ ተቀምጠዋል። ለነዚህ ተማሪዎች ድምጽ በመሆን ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።

📌 ለዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ላነሷቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ፣ ግልጽና ፍትሃዊ ምላሽ መስጠት የሀላፊነት ሁሉ መጀመሪያ ነው። ጉዳዩን በቸልተኝነት መመልከት ወይንም ማዘግየት መፍትሄ አይሆንም። አሁንም ጥያቄያችን ግልጽ ነው! ከምላሹ መሸሽ አይቻልም!

📌 ለመጅሊስ፦ የናንተ የመጀመሪያ ኃላፊነት የሙስሊሙን መብት ማስጠበቅ ነው። ሰላማዊው ጥያቄያችን በፍትሐዊ መንገድ ይመለስ ዘንድ ስሩ። ሴት ልጅ ብርድ ላይ አትደር፤ ተማሪዎች እንቅልፍ አጥተው ሜዳ ላይ አይደሩ። ስለፍትሕ ቁሙ! ታሪክ እየተፃፈ ነው!!

📌 ለሙስሊም ማህበረሰብ እነዚህን በብርድና በጨለማ ውስጥ ያሉ ልጆቻችሁን በዱዓና በሞራል ከጎናቸው ቁሙ።

@aaumsu
👏9716😭13🔥8👌4🫡21🏆1💔1
"ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው።" (አል-በቀራህ 214)

@aaumsu
👍6117💯15🔥4
ድል የሚገኘው ከትዕግስት ጋር ነው። እፎይታ የሚገኝው ከጭንቅ በኋላ ነው። በርግጥም ከችግር በኋላ ምቾት አለ!።” - ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

@aaumsu
💯6527🔥3
በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና የአዲስ አበባ መጅሊስ ጸሐፊ ኡስታዝ ሺሃቡዲን ሸይኽ ኑራ ወደግቢው እየመጡ ይገኛሉ።

የዩኒቨርሲቲውም ፕሬዝዳንት እዚያው ግቢ ውስጥ ይገኛል።

አሁንም ቢሆን ለጥያቄያችን ፍትኃዊ ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ የትም አንቀሳቀስም!

@aaumsu
🔥10420👌16👏9👍2🏆2
መፍትሄ እንጂ ቀጠሮ አንቀበልም!

@aaumsu
106👏28👌13💯7🫡5🔥4🏆4💔3😭32
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"አንድ ሰው እናግኝና ጭፍልቅ ነው የምናደርጋችሁ!" - ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት

ከነዚህ አካላት ጋር ንግግርም ቀጠሮም አንቀበልም! መብታችን ሳይከበር፤ ጥያቄያችን ሳይመለስ ወዴትም አንቀሳቀስም!

@aaumsu
😭67😡5011🤬7💔5👌3
በአሁን ሰዓት ኡስታዝ አቡበከር የደረሰ ሲሆን ከተማሪዎች ጋር እየተነጋገሩ ነው።

@aaumsu
62👏25👌13🔥9