AAU - Muslim Students Union
6.45K subscribers
2.68K photos
149 videos
51 files
765 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው!

ፍትህን ለማስፈንና መብቶቻችንን ለማስከበር በምናደርገው ጉዞ ውስጥ የሚገጥሙን መሰናክሎች የጥንካሬያችን መለኪያ እንጂ የውድቀታችን ምልክቶች አይደሉም። ጨለማው በጣም የሚበረታው ሊነጋ ሲል እንደሆነ ሁሉ፣ ፈተናውም የሚከብደው ድሉ ሊመጣ ሲቃረብ ነው።

ታላቁ ጌታችን በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል፦
"የአላህ እርዳታ መቼ ነው? ይሉ ዘንድ (ተጨነቁ)። ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው።" (አል-በቀራህ፡ 214)


ይህ የጽናት ጊዜ ነው። ይህ የተወኩል ወቅት ነው። የሐቅ መንገድ መቼም ቢሆን ቢጠነክር እንጂ አይበጠስም። በጌታችን በአላህ ቃል ኪዳን ላይ ሙሉ እምነት አለን፤ እርሱ ፍትሃዊ ነውና የተገፉትን አይጥልም፣ የደጋጎችንም ስራ አያጠፋም።

📌 ጥንካሬያችን የሚመነጨው ከልባችን እምነት እንጂ ከሁኔታዎች መለዋወጥ አይደለም።
📌 እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ በዱዓ ተጠናክረን ወደፊት እንጓዛለን።
📌 ትዕግስት የድል ሁሉ ቁልፍ ናት።
📌 ለእውነት የቆመ ማንም ይሁን ማን፣ መጨረሻው ስኬት ነው። እውነትና ፍትህ አሸናፊ መሆናቸው የማይቀር ሃቅ ነው።

ጌታችን ሆይ! በጽናት አጽናን፤ ድልህንም ቅርብ አድርግልን።

@aaumsu
15🔥5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ለእኛ አጀንዳ ሰጥተው ከትምህርት ያዘናጉን አካላት ቀጣዩን ትውልድ፤ የእኛን ልጆች፤ የእኛን ወንድም እህቶች በተመሳሳይ ጥያቄ ከትምህርት እንዲያዘናጓቸው አንፈልግም። እኛ እየተሳቀቅን የኖርንበትን፤ እኛ እየተሳቀቅን የተማርንበትን፤ ማንም አካል በክብራችን እየተረማመደ ያለበትን ሁኔታ በእኛ ልጆች ላይ እንዲደገም አንፈቅድም።"

@aaumsu
🔥17💯63
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"አሁን አሸባሪ እንደዚህ ሆኖ ቢገባና ጉዳት ቢያደርስ ራሳችሁን አይጸጽታችሁም?"

ኒቃብ የለበሱ ተማሪዎችን ላይብረሪ አትገቡም ብሎ ከልክሎ ምክንያቱን ሲያብራራ ከተናገረው ነው። ሙስሊም ጠልነታቸው በዚህ ልክ አግጥጦ ነው የሚታየው። እነዚህን አካላት ደፍሮ ከመጠየቅ፣ ከመታገል እና በሕግ ተጠያቂ ከማድረግ ውጪ አማራጭ የለንም።

By any means necessary መብታችን ሊከበር ግድ ነው። በመመሪያ የከለከሉትን መብት በመመሪያ ከለላ እስኪሰጡት መጠየቅ ግድ ነው። መብታችንን የጣሱ አካላት ተጠያቂ ሊደረጉ ግድ ነው።

ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !

@aaumsu
😡22🔥2💔21
አላሁ አክበር!!! አላሁ አክበር!!!

ከ19 ወራት በላይ፤ ከ620 ቀናት በላይ ጥያቄ አለን! ሲሉ የነበሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ለጥያቄ መልስ እንፈልጋለን! በማለት በአሁኑ ሰዓት ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤቱ ጋር ይገኛሉ!!

@aaumsu
🔥4551👏1👌1
ፕሬዝዳንቱ ሳይመጡ የትም አንሄድም! ጥያቄያችን ምላሽ ሳያገኝ ወደኃላ ማለት የለም ያሉት የግቢያችን ሙስሊም ተማሪዎች በአሁን ሰዓት በፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት በገፍ ተሰባሰበዋል!

@aaumsu
28🔥18💯21👌1
መብቱን አሳልፎ የማይሰጥ ትውልድ! መብቱን ለማስከበር መሄድ ያለበትን ሁሉ የሚሄድ ትውልድ እንደሆነ አላወቁም!

@aaumsu
🫡23🔥154🥰3👏2💯21👌1
ጥያቄያችን ግልጽ ነው! ጥያቄያችን የፍትህ የእኩልነት፤ የመብት ነው። ከማንም ውለታን አንፈልግም፤ የኛ የሆነውን መብታችንን ነው!

ጥያቄ አለን! መልስም እንፈልጋለን!

@aaumsu
16🔥41