23 ቀናት ሞላ
የፌደራል መጅሊስ ፕሬዚዳንት
ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ከዶክተር ሳሙኤል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደተነጋገሩና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በኒቃባቸው ምክንያት ሳይሳቀቁ እንዲማሩ እንደሚያደርጉ ከ23 ቀናት በፊት በአዲስ አበባ መጅሊስ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ገልፀው ነበር። ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ተወካዮች ከመጅሊሱ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ጋር የዚያኑ ቀን ውይይት ያደረጉ ሲሆን መጅሊሱ መመሪያው ይስተካከል ዘንድ የሚጠይቅ ደብዳቤ እንዲያስገባ፤ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የመብት ጥሰት የፈፀሙ የዩኒቨርስቲው አካላትን ሊከስ፤ ከዩኒቨርስቲው ጋር ለዘላቂው መፍትሔ ውይይት ሊደረግ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጨረሻ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ ከተቋቋመው 17 ኮሚቴ ጋር ተማሪዎች በቅርበት እንዲሰሩ ከስምምነት ተደርሶ ነበር።
ቃል በተገባ ማግስት ጀምሮ የመብት ጥሰቶቹ የቀጠሉ እና መመሪያውም ያልተሻሻለ ቢሆንም ባለፉት 23 ቀናት ውስጥ ከተጠቀሱት አራት ነጥቦች ውስጥ ወደ ተግባር የተለወጠ አንድም ነጥብ የለም። መጅሊስ የሙስሊሙን መብት ሊያስጠብቅ የሚገባ ግንባር ቀደም ተቋም እንደመሆኑ በዚህ ሁሉ ቀናት ውስጥ ትኩረት ተሰጥቶ ቁርጠኛ የሆነ አቋም ተወስዶ መፍትሔ አለመምጣቱ በተማሪው ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል።
ጥያቄያችን መብቶቻችን በመመሪያ ተፅፈው እና በሕግ ፀንተው እንዲመለሱልን ነው። ነፃነታችንን ገፍፎ ሙስሊም ጠልነቱን ሲያንፀባርቅ እና በደል ሲፈፅም የነበረ ሁሉ በሕግ አግባብ ይጠየቅ ዘንድም ግድ ነው።
ጥያቄ አለን እንላለን። ቢሮ ውስጥም በአደባባይም _ በሚዲያም በአካልም _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!
@aaumsu

🔥15❤5👍2💔2
It is not a joke !
It is not for fun !
በመብቱ የሚቀልድም ሆነ ለቀልድ መብቱን የሚጠይቅ ተማሪ የለም። ክላስ ቀጥተው፤ ካፌ እያለፋቸው፤ ታክሲ ሲጠፋ ኪሎ ሜትሮችን በእግራቸው እየተጓዙ ከቢሮ ቢሮ የሰው ፊት እየገረፋቸው ስለመብታቸው ሲጠይቁ የነበረው ለቀልድ አይደለም። ያ ሁሉ ተማሪ ያንን ሁሉ ቀናት በፅናት ሲራወጥ የነበረውም ለቀልድ አይደለም። ደከመኝ ሳይሉ የለፉት፤ ሳይፈሩ ሁሉንም አካል የተጋፈጡት የመብታቸውን ዋጋ ስለተረዱ ነው። ያላቸውን ሁሉ የሰጡትም ሊሰጥ የሚገባውን ስላወቁ ነው።
ዛሬ ከትላንት የተሻለ ይሆን ዘንድ የተከፈለውን ታሪክ ስለተነገራቸው ነው። ነገ ልጆቻቸው በሙሉ ነፃነት ይማሩ፣ ይሰሩ፣ ሀገራቸውን ያገለግሉ እና ይመሩ ዘንድ መከፈል ያለበትን ስለተረዱ ነው።
እንደዚያ ስለሆነም እንደ ቀልድ የምናልፈው ነገር አይኖርም። መጠየቅ ባለብን መንገድ ሁሉ መብታችን ይከበር ዘንድ እንጠይቃለን።
የመንገዱ ባህሪ ነውና!

🔥35❤5💯5
በሐጂ አደም ሳዶ ሀገር ባሌ የሚገኘው መዳ ወላቡ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች "Niqaaba ni uffanna barnootas ni baranna - ኒቃቧን እንደለበሰች ትማራለች።" - በማለት መልዕክታቸውን አድርሰዋል። "Justice for AAU Muslim Students!" - ሲሉም ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ጥያቄው የሁሉም ሙስሊም ተማሪ ነው። ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው። ጥያቄያችን በመመሪያ የተጣሰው መብታችን በመመሪ ይፅና ነው። ኒቃብ መልበስ መብት ነው። ኒቃብን መከልከል እስልምናን መንካት፤ ሙስሊሞችን ከትምህርት ማገድ ነው። ሙስሊም ደግሞ እስልምናው ሲነካ ዝም ብሎ አያይም። በሁሉም መንገድ ስለመብቶቻችን መጠየቃችን ግድ ነው። ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!

🔥25🥰4❤2😍1
ድምፄ እስኪሰማ...
እርቃንሽን ካልሆንሽ አትማሪም አሉኝ
"ኒቃብሽን አውልቂ" ብለዉ ተናገሩኝ
ክብሬን ስለጠበኩ መማር ከለከሉኝ
አናስገባም ብለው በሮቹን ዘጉብኝ
"ማንስ ፈቀደልሽ ከቶ ልትማሪ
እዚህ እንዳመጪ እዛዉ ቤትሽ ቅሪ"
ብለዉ አባረሩኝ ከእዉቀት ገበታዬ
ሗላ ላይ እንድቀር ካለማወቅ ቀዬ
በዘዴ ሊገፉኝ ከእዉቀት ማማዬ
አላህ ነዉ "አንብቢ!" "ኢቅራዕ!" ሲል ያዘዘኝ
ግን እነዚህ ሰዎች መማር ከለከሉኝ
ፊትሽን ካላየን አትምጪብን አሉኝ
መፅሃፍ እና ኒቃብ፣ የኔ ሆነዉ ሳለ
"አንዱን ምረጪ አለኝ"፣ መብቴን ከለከለ።
ሌሎቹ ሲማሩ መብታቸው ተከብሮ
እኔ ግን ተገለልኩ መብቴ ተገፍትሮ
ሁሉን ተመልካቹ አሸናፊዉ ጌታ
የጭቁኖች ረዳት ያማኞች አለኝታ
ለምነትህ ያደርን ታዛዥ ባሮችህ ነን
በበደለኞች ላይ ድልን አጎናፅፈን
ጭቆናዉ ቢበዛም ግፋ እንግልቱ
በሩን ቢዘጉትም ሊገፋኝ ከ'ዉቀቱ
መብቴ እሰኪከበር ድምፄን ማሰማቱ
ዛሬም ይቀጥላል ልክ እንደ ትናንቱ
እስኪሰማ ድረስ የፍትህ ብስራቱ
ጭቆና ተቀብሮ እስኪመጣ እዉነቱ!!!
ከአንድ ወንድማችን
©️Sefereselam muslim students jeme'a
@aaumsu
እርቃንሽን ካልሆንሽ አትማሪም አሉኝ
"ኒቃብሽን አውልቂ" ብለዉ ተናገሩኝ
ክብሬን ስለጠበኩ መማር ከለከሉኝ
አናስገባም ብለው በሮቹን ዘጉብኝ
"ማንስ ፈቀደልሽ ከቶ ልትማሪ
እዚህ እንዳመጪ እዛዉ ቤትሽ ቅሪ"
ብለዉ አባረሩኝ ከእዉቀት ገበታዬ
ሗላ ላይ እንድቀር ካለማወቅ ቀዬ
በዘዴ ሊገፉኝ ከእዉቀት ማማዬ
አላህ ነዉ "አንብቢ!" "ኢቅራዕ!" ሲል ያዘዘኝ
ግን እነዚህ ሰዎች መማር ከለከሉኝ
ፊትሽን ካላየን አትምጪብን አሉኝ
መፅሃፍ እና ኒቃብ፣ የኔ ሆነዉ ሳለ
"አንዱን ምረጪ አለኝ"፣ መብቴን ከለከለ።
ሌሎቹ ሲማሩ መብታቸው ተከብሮ
እኔ ግን ተገለልኩ መብቴ ተገፍትሮ
ሁሉን ተመልካቹ አሸናፊዉ ጌታ
የጭቁኖች ረዳት ያማኞች አለኝታ
ለምነትህ ያደርን ታዛዥ ባሮችህ ነን
በበደለኞች ላይ ድልን አጎናፅፈን
ጭቆናዉ ቢበዛም ግፋ እንግልቱ
በሩን ቢዘጉትም ሊገፋኝ ከ'ዉቀቱ
መብቴ እሰኪከበር ድምፄን ማሰማቱ
ዛሬም ይቀጥላል ልክ እንደ ትናንቱ
እስኪሰማ ድረስ የፍትህ ብስራቱ
ጭቆና ተቀብሮ እስኪመጣ እዉነቱ!!!
ከአንድ ወንድማችን
©️Sefereselam muslim students jeme'a
@aaumsu
👍18❤10👌1
ታድለን ቢሆን . . .
የሙስሊሙን ተማሪ መብት ማስከበር የሙስሊሙ ተማሪ ሀላፊነት ብቻ አልነበረም። ታድለን ቢሆን የተማሪዎቹን መብት አክብሮ ማስተማር የዩኒቨርስቲው ሀላፊነት ነበር። ግን አልሆነም! ታድለን ቢሆን ዩኒቨርስቲው መብታችንን ሲጥሱ መብታችንን የማስከበሩ ሀላፊነት የትምህርት ሚኒስቴር ነበር። ግን አልሆነም! ታድለን ቢሆን መብታችን ሲጣስ የማስከበሩ ሀላፊነት የሰላም ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ነበር። ግን አልሆነም! ታድለን ቢሆን እንደ ሙስሊም መብቶቻችንን የማስከበር ሀላፊነቱ የመጅሊስ ነበር። ግን አልሆነም!
አልሆነምና ተስፋ ቁረጡ የሚሉም አልጠፉም። ለሁሉም ግን አላህ በቅዱስ ቃሉ ያስቀመጠውን ድንቅ አንቀፅ አንብቡላቸው።
" الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ
እነዚያ ሰዎቹ ለእነርሱ፡- «ሰዎች ለእናንተ (ጦርን) አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» ይሉዋቸውና (ይህም) እምነትን የጨመረላቸው «በቂያችንም አላህ ነው ምን ያምርም መጠጊያ!» ያሉ ናቸው፡፡" [3:173]
ለሁሉም በቂ የሆነው አላህ መጠጊያችን ነው። ከእርሱ ወጪስ መጠጊያ አለን? ምንኛ ያማረ መጠጊያ ነው።

🔥21❤10⚡2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 2 ሶስት ቀን ኒቃብ አይከለከልም ቢል መፍትሔ መጣ አንልም። ምን ማለት ነው? እኛ የምንፈልገው በመመሪያ የፀና መብት ነው። ነገ የት ነው የምታስጮሁን ብለን ልንጠይቅ ነው?!" -
@aaumsu
@aaumsu
🔥24💯2
አልሐምዱሊላህ __ ታድለናል !
ገና ባልጠና ጉልበታችን፥ የብዙዎች ያልተሰራ የቤት ሥራ በጫንቃችን ላይ ተጣለብን።
ታድለን ...
የትውልድን ክብር በመጠበቅ ላይ ኃላፊነት ወሰድን።
ታድለን...
የእህታቸው ክብር እየተነካ፥ በሰላም ተኝተው የማያድሩ ዓይኖች ተሰጡን።
ታድለን...
ፍትሕ ስትቀበር «በእኔን ከተመቸኝ ይሁንታ» የማይቀበል አዕምሮ ተሰጠን።
ታድለን...
ቀን እስኪያልፍ የሚጎድልን ክብር የማይታገስ ልብ ተቸርን።
ታድለን...
ሌሎች የፈሩበትን ነገር በድፍረት የመጋፈጥ ወኔ ተሰጠን።
ታድለን...
«አዳኝ» እስኪመጣ ሳንጠብቅ፥ ኃላፊነታችንን የምንወጣበት ተቆርቋሪነት ተሰጠን።
እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ታድለን...
ፍትሕ መጓደል አመመን።
የመብታችን መጣስ ቆረቆረን።
ጭቆና አንገሸገሸን።
ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ታድለንማ'ኮ...
ታሪክ "ካላጎነበሱት" መካከል መዘገበን።
መስዋዕትነት ከገባቸው፤
ትውልዳቸውን ለመታደግ ቁርጠኛ ከሆኑት መሃል መዘገበን።
ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ታድለንማ'ኮ...
በአላህ ላይ ከሚመኩት፣
ለመንገዱ ከሚታመኑት፤
ድልንም ከርሱ ብቻ ከሚጠብቁት ሰራዊቶቹ መሃል አደረገን።
ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ለኛ የተሰጠው ለማን ተሰጥቷል?! - ዙሪያችሁን አትመለከቱምን?!
በህይወታችን ካየናቸው ብዙ ብዙ ብቸኝነቶች ውስጥ፥ በዚህ የትግል መንገድ ላይ ያለ ብቸኝነትን ያህል ዋጋ ያለው ብቸኝነት የት እናገኛለን?!
አላህ የሚያየው፣ የሚመሰክርለት ብቸኝነት!
ወደ ድል እንጂ የማይደርስ፣ ውድቀት የሌለበት ብቸኝነት!!
ትርጉሙ ጥልቅ፣ ክፍያው ብዙ ብቸኝነት!!!
ይህ እንደዋዛ 'ሚገኝ ነው እንዴ 'ሚመስለን?! በፍጹም።
ለዚህ ብቸኝነት መመረጥ ያሻዋል።
ይህ'ኮ ታላቅ ጸጋ እንጂ ሌላ አይደለም።
አልሐምዱሊላህ!!!
ሐስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል!!!

🔥34❤8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይህ ዛሬ 6 ሰዓት ከ50 ላይ በአምስት ኪሎ በር ላይ የተከሰተ ነው!
ኒቃቢስት ተማሪዎችን ኒቃባችሁን ካላወለቃችሁ አትገቡም በማለት መልሰዋል። መታዎቂያ አሳይተን እንግባ ቢሉም እምቢ ተብለው ተከልክለዋል።
መብታችንን በግልፅ የሚጥስ መመሪያ አወጡ፤ ኒቃቢስቶችን የሚያገል እና ምቹ ያልሆነ የቴክኖሎጂ ስርዓት ዘረጉ፤ ይህ ግልፅ የሆነ መዋቅራዊ ጭቆና ነው። ያሉበትን መዋቅር ሙስሊም ጠል ለሆነው አስተሳሰባቸው ማስፈፀሚያ እያደረጉት ነው።
የዚህ ሁሉ ምንጭ ለሐይማኖት ነፃነት መብታችን እውቅና መንፈግ ነውና በሁሉም መንገድ ልንጠይቃቸው ግድ ነው። በጋራ ሀገር በጋራ ሀብት በገነባነው ተቋም ውስጥ እኛን ያገለለ መመሪያ እና ስርዓት ለምን እንዳወጡ ልንጠይቃቸው ግድ ነው። በመመሪያ የጣሱትን መብት በመመሪያ ከለላ እስኪሰጡት፤ ለፈፀሙብን በደል በሕግ አግባብ እስኪጠየቁ ድረስ ልንታገላቸው ግድ ነው።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! !

😡60❤2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Sarbama mirgaafii cunqursa barattoota yuniversitii Finfinnee irra gahaa jiru, afaan niqaabistoota irraa. Dhaggeeffadhaa, hunduu akka dhagahuufis tamsaasaa.
Gaaffii qabna_ deebiin haqaa hanga kennamutti !
@aaumsu
Gaaffii qabna_ deebiin haqaa hanga kennamutti !
@aaumsu
🔥16❤3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበበ ዩምበረስቲ በኒቃቢስት ደረሳሶ ኢጄጅ ናረይ ምካት ተገግኒሙ ቲሰሙይ። አጥናቡይ! ለበለ ሰብ ኢጄጃምነኮ አሱይ
ሱል አለነ_ ኣዲል ጀዋብ ኢመጫን ጃንጎ!!!
@aaumsu
ሱል አለነ_ ኣዲል ጀዋብ ኢመጫን ጃንጎ!!!
@aaumsu
🔥19❤5😭5👌1
"ዝምታው ይሰበር!
ጭቆናው ይብቃ!" - ወንድም ሙራድ ታደሰ
የሚከተለውን መልዕክትም አስተላልፏል፦
"መንግስት አለ» በምንልበት፣ የሀገሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ፣ 4 ኪሎ እና 6 ኪሎ
(AAU) ላይ የሙስሊም እህቶቻችንን መብት ማስከበር ካልቻልን፤ የመንግስት አማጺ እና ጽንፈኛ በነገሰበት አክሱም ከተማ ላይ ሙስሊሙ መብት ያገኛል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው! ይህ በዋና ከተማችን፣ በመንግስት አፍንጫ ስር እየሆነ ያለ ግልጽ መዋቅራዊ ጭቆና ነው! በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ሴቶችን ክብር እና መብት ማስከበር ያቃተው ኡማ፣ አክሱም ላይ ሄዶ መብት አስከብራለሁ ቢል ቀልድ ነው።"
ኢንሻአላህ _ መብቶቻችንን ለምነን ሳይሆን ታግለን እናስከብራለን። ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !

🔥19❤9👌6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
في جامعة أديس أبابا، تعرضت الطالبات المنتقبات لانتهاكات تمس حقوقهن. يجب أن يصل هذا الأمر للجميع، ويجب اتخاذ خطوات لتحقيق العدالة.
استمعوا لرسالتهن وانشروها أمانةً لوجه الله، وسنستمر في طرح السؤال حتى نصل إلى إجابة عادلة.

🔥17💔13❤5👍4
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ
ሙስሊም ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው እያደረሰ ያለውን የመብት ጥሰት በመግለፅ መፍትሔ ያመጣ ዘንድ ለቦርዱ ደብዳቤ ይዘው የሄዱት ከወራት በፊት ነበር። ደብዳቤውን ለማስገባት ለሄዱት ተወካዮች "ቦርድ የዩኒቨርስቲው የመጨረሻ አካል ስለሆነ እስከዛሬ የሄዳችሁበትን መንገድ በደንብ በሚገልፅ መልኩ፤ ለተቋማት ሁሉ ያስገባችሗቸውን ደብዳቤ እንዲሁም የሰጡትን ምላሽ አጠናቅራችሁ አምጡ።" - የሚልን ምላሽ ሰጠ። መስፈርታቸውን በመቀበልም በብዙ ቀናት ዶክመንቶች ተዘጋጅተው ካለቁ ቡሃላ ተወካዮች ደብዳቤውን ከእነ ዶክመንቶቹ ለማስገባት ሲሄዱ "እኛ ከእናንተ ደብዳቤ አንቀበልም!" - በማለት መልሰዋል።
የዩኒቨርስቲው አመራሮችየተማሪዎችን ጥያቄ በማፈን እና መብታቸውን በመጣስ የጀመሩት የቁልቁለት ጉዞ ከቦርድ መድረሱ በጣም የሚያሳዝን ነው። ጥያቄያችንን በደብዳቤ ስናስገባ መቀበል፤ ችግሮቻችንን በውይይት እንፈታ ዘንድ ስንጠይቅም ማስተናገድ ግዴታም ስልጣኔም ቢሆንም አሻፈረኝ እንዳሉ ነው።
ያም ሆነ ይህ ግን መብቶቻችን መከበራቸው አይቀሬ ነው። በሁሉም መንገድ ጠይቀን የነጠቁንን መብት እናስከብራለን፤ በደል የፈፀሙብን አካላትም ተጠያቂ ይሆናሉ።
"ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው (ተባሉም)፡፡" [2:214]

🔥18❤5
🔥26🥰5❤2😍1
የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው!
ፍትህን ለማስፈንና መብቶቻችንን ለማስከበር በምናደርገው ጉዞ ውስጥ የሚገጥሙን መሰናክሎች የጥንካሬያችን መለኪያ እንጂ የውድቀታችን ምልክቶች አይደሉም። ጨለማው በጣም የሚበረታው ሊነጋ ሲል እንደሆነ ሁሉ፣ ፈተናውም የሚከብደው ድሉ ሊመጣ ሲቃረብ ነው።
ታላቁ ጌታችን በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል፦
ይህ የጽናት ጊዜ ነው። ይህ የተወኩል ወቅት ነው። የሐቅ መንገድ መቼም ቢሆን ቢጠነክር እንጂ አይበጠስም። በጌታችን በአላህ ቃል ኪዳን ላይ ሙሉ እምነት አለን፤ እርሱ ፍትሃዊ ነውና የተገፉትን አይጥልም፣ የደጋጎችንም ስራ አያጠፋም።
📌 ጥንካሬያችን የሚመነጨው ከልባችን እምነት እንጂ ከሁኔታዎች መለዋወጥ አይደለም።
📌 እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ በዱዓ ተጠናክረን ወደፊት እንጓዛለን።
📌 ትዕግስት የድል ሁሉ ቁልፍ ናት።
📌 ለእውነት የቆመ ማንም ይሁን ማን፣ መጨረሻው ስኬት ነው። እውነትና ፍትህ አሸናፊ መሆናቸው የማይቀር ሃቅ ነው።
ጌታችን ሆይ! በጽናት አጽናን፤ ድልህንም ቅርብ አድርግልን።

"የአላህ እርዳታ መቼ ነው? ይሉ ዘንድ (ተጨነቁ)። ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው።" (አል-በቀራህ፡ 214)
ይህ የጽናት ጊዜ ነው። ይህ የተወኩል ወቅት ነው። የሐቅ መንገድ መቼም ቢሆን ቢጠነክር እንጂ አይበጠስም። በጌታችን በአላህ ቃል ኪዳን ላይ ሙሉ እምነት አለን፤ እርሱ ፍትሃዊ ነውና የተገፉትን አይጥልም፣ የደጋጎችንም ስራ አያጠፋም።
📌 ጥንካሬያችን የሚመነጨው ከልባችን እምነት እንጂ ከሁኔታዎች መለዋወጥ አይደለም።
📌 እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ በዱዓ ተጠናክረን ወደፊት እንጓዛለን።
📌 ትዕግስት የድል ሁሉ ቁልፍ ናት።
📌 ለእውነት የቆመ ማንም ይሁን ማን፣ መጨረሻው ስኬት ነው። እውነትና ፍትህ አሸናፊ መሆናቸው የማይቀር ሃቅ ነው።
ጌታችን ሆይ! በጽናት አጽናን፤ ድልህንም ቅርብ አድርግልን።
@aaumsu
❤15🔥5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ለእኛ አጀንዳ ሰጥተው ከትምህርት ያዘናጉን አካላት ቀጣዩን ትውልድ፤ የእኛን ልጆች፤ የእኛን ወንድም እህቶች በተመሳሳይ ጥያቄ ከትምህርት እንዲያዘናጓቸው አንፈልግም። እኛ እየተሳቀቅን የኖርንበትን፤ እኛ እየተሳቀቅን የተማርንበትን፤ ማንም አካል በክብራችን እየተረማመደ ያለበትን ሁኔታ በእኛ ልጆች ላይ እንዲደገም አንፈቅድም።"
@aaumsu
@aaumsu
🔥17💯6❤3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"አሁን አሸባሪ እንደዚህ ሆኖ ቢገባና ጉዳት ቢያደርስ ራሳችሁን አይጸጽታችሁም?"
ኒቃብ የለበሱ ተማሪዎችን ላይብረሪ አትገቡም ብሎ ከልክሎ ምክንያቱን ሲያብራራ ከተናገረው ነው። ሙስሊም ጠልነታቸው በዚህ ልክ አግጥጦ ነው የሚታየው። እነዚህን አካላት ደፍሮ ከመጠየቅ፣ ከመታገል እና በሕግ ተጠያቂ ከማድረግ ውጪ አማራጭ የለንም።
By any means necessary መብታችን ሊከበር ግድ ነው። በመመሪያ የከለከሉትን መብት በመመሪያ ከለላ እስኪሰጡት መጠየቅ ግድ ነው። መብታችንን የጣሱ አካላት ተጠያቂ ሊደረጉ ግድ ነው።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !

😡22🔥2💔2❤1
አላሁ አክበር!!! አላሁ አክበር!!!
ከ19 ወራት በላይ፤ ከ620 ቀናት በላይ ጥያቄ አለን! ሲሉ የነበሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ለጥያቄ መልስ እንፈልጋለን! በማለት በአሁኑ ሰዓት ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤቱ ጋር ይገኛሉ!!

🔥45❤5⚡1👏1👌1