ይህ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ድምፅ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያወጣውን ጨቋኝ መመሪያ አስመልክቶ ጥያቄ አለን በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል። ሙስሊሙ ተማሪ ከጫፍ እስከ ጫፍ በሚያሰማው ድምፅ ለጥያቄው መልስ ያገኛል።
መብቶቻችንን የሚጥሱ አካላት በሕግ ይጠየቁ!
Qaamonni mirga keenya sarban seeraan haa gaafataman!
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu

🔥25❤10👌1
አስራ አምስት ወራት አለፉ
ሰላም ሚኒስቴር
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያወጣው ጨቋኝ መመሪያ እያደረሰ ያለው የመብት ጥሰት በዝርዝር ተጠቅሶ የመፍትሔው አካል እንዲሆኑ በመግለፅ የመጀመሪያው ደብዳቤ ከገባላቸው አስራ አምስት ወራት አልፈዋል። በ2017 በነበረ አንድ ግንኙነት በጉዳዩ ላይ ከመጅሊስ አካላት ጋር ተወያይተው መፍትሔ እንደሚያመጡ ቢገልፁም መፍትሔው ሳይመጣ አመቱ ተጠናቀቀ። መመሪያውም ጭቆናውም በ2018 መቀጠላቸውን ተከትሎ ከ6 ወራት በፊት ዳግም ደብዳቤ ቢገባላቸውም ምንም አይነት ምላሽም ሆነ መፍትሔ ሳይሰጡ እስካሁን አሉ።
ሙስሊሙ ተማሪ ተቋሜ ብሎ በሄደበት ተቋም አገልግሎት ሊያገኝና መብቱን ሊያስጠብቁለት የተገባ ቢሆንም ፍሬው የታዬ ስራ ባለመሰራቱ መመሪያው ሳይሻሻል እስካሁን አለ። ይህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሙስሊሙ ተማሪ ጥያቄ የሰጠውን ቦታ የሚያሳይ እና በጥልቁ ቅሬታ የፈጠረ ተግባር ነው።
ሆኖም ግን በሁሉም መንገድ፣ የሚመለከተው ሁሉ ዘንድ በመሄድ ስንጠይቅ የነበረው ጥያቄ የእኛ ትውልድ ሀላፊነት ነውና የማስከበሩ ሀላፊነት የእኛው ነው። በአላህ ፈቃድ በትብብር፣ በቅንጅት፣ በመናበብ፣ ለአንድ አላማ በአንድነት በመቆም ስለመብታችን እንጠይቃለን፤ መብታችንም እስኪከበር ድረስ ጥያቄ አለን እንላለን።
ጥያቄ አለን እንላለን _ በሚዲያም በአካልም _ በቢሮም በአደባባይም _ በጋራ በአንድነት ጥያቄ አለን እንላለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !

🔥24❤4
በሁዳ መልቲሚዲያ
2000 ላይ ሒጃብን የሚከለክለው የመጀመሪያው መመሪያ ሲወጣ የነበረው ትንቅንቅ ተዳሷል። ከዚያ በፊት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ሲደርሱ የነበሩት፤ አሁን ላይ እየደረሰ ያለው ተጠቅሷል። የአዲስ የአበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰትም የተዳሰሰ ሲሆን ብቸኛ መፍትሔውም በዝርዝር ተቀምጧል።
ሊንኩ https://youtu.be/eM0omRXNjIM?si=lKtxA0iK3NW96kMO ነው። በደንብ ያዳምጡ። የቤት ስራዎንም ይውሰዱ። ለሌሎችም ያሰራጩ።

🔥17❤5🥰2👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኒቃቢስቷ፦ እምነቴን መተው አለብኝ?
የAAU ጥበቆች፦ እምነት ብሔር የሚባል ነገር የለም። እምነት በልብ ነው።
ይህ ኒቃቢስት እህት ላይ በር ያለች ጥበቃ አትገቢም ብላ ካቆመቻት ቡሃላ የተናገሩት ንግግር ነው። እዚህ እምነት የሚባል ነገር አይሰራም በማለት የእምነቷ ክፍል የሆነን አለባበስ ከበር ጥላ እንድትገባ ጠይቋታል። እርሷም "እና እምነቴን መተው አለብኝ?" - በማለት እየጠየቀች ነው። እምነቷን መተው አለባት? እምነታችንን መተው አለብን? ገብተን እንማር ዘንድ እስልምናችንን ከበር ጥለን መግባት አለብን? ይህ ድፍረትን የቀላቀለ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት የሚጥስ ንግግር ነው። እስልምና ከዩኒቨርስቲ በር ተጥሎ የሚገባ ሐይማኖት አይደለም።
ኒቃብን በመመሪያ በመከልከል መብታችን የሆነን አለባበስ ከመከልከል ጀምሮ ጥላቻ አዘል ንግግሮች እንዲደርሱብን እየሆነ ነው። ይህ ለምን እንደተፈለገ አሁንም ጥያቄ አለን። መመሪያው ይሻሻል ዘንድ በሁሉም መንገድ ስንጠይቅ እንደነበረውም መመሪያው ተሻሽሎ መብታችን ይጠበቅ ዘንድ በትብብር፣ በአንድነት፣ በጋራ እና በሕብረት ድምፃችንን ማሰማት፤ ስለመብታችን መጠየቅ፤ የእኛ ስለሆነውም መሞገት ግዴታችን ሆኗል። በአላህ ፈቃድ ይህ እሮሮ በእኛ ትውልድ ይቋጫል። መብታችን ተከብሮም ፍትሕ የሚሰፍን ይሆናል። ኢንሻ አላህ!

🔥10🤬8😭2❤1👌1😡1
ሒጃቧ - መብቷ!
እኩል ግብር ከፍሎ
እኩል ደሙን ሰጥቶ፥ ባጸናት ሐገሩ
ልጄን ላስተምር ሲል
አይሆንም ሲባል ግን፥ አለመታፈሩ?!
የነጻነት ምድር
ቀበርኩት ብትልም፥ ጭቆናን ምድሯ ላይ
አይኗ ተሸፍኗል
ልማር የምትላት፥ ልጇን ዞራ እንዳታይ።
ለስሙ እኩልነት
ሲሰበክ ቢውልም፥ መድረክ ተፈልጎ
የታለ እኩልነት
ያ'ገሪቷን ግማሽ፥ ወደ ጎን አድርጎ?!
ትዝብት እንጂ ትርፉ
ፍትሕ ስሟ ቀርቶ፥ ግብሯ ቢሆን ኦና፣
ሀገር አትሰራም
ከግለሰቦች ደጅ፥ መብት እየተጠና።
ሌሎች እኩዮቿን
መብት እንደሆናቸው፥ ትምህርትና ስራ፣
እሷም ትማራለች
(እሷም ትሰራለች)
እምነቷን አክብራ፥ መብቷን አስከብራ።
©️EHEMSU
@aaumsu
እኩል ግብር ከፍሎ
እኩል ደሙን ሰጥቶ፥ ባጸናት ሐገሩ
ልጄን ላስተምር ሲል
አይሆንም ሲባል ግን፥ አለመታፈሩ?!
የነጻነት ምድር
ቀበርኩት ብትልም፥ ጭቆናን ምድሯ ላይ
አይኗ ተሸፍኗል
ልማር የምትላት፥ ልጇን ዞራ እንዳታይ።
ለስሙ እኩልነት
ሲሰበክ ቢውልም፥ መድረክ ተፈልጎ
የታለ እኩልነት
ያ'ገሪቷን ግማሽ፥ ወደ ጎን አድርጎ?!
ትዝብት እንጂ ትርፉ
ፍትሕ ስሟ ቀርቶ፥ ግብሯ ቢሆን ኦና፣
ሀገር አትሰራም
ከግለሰቦች ደጅ፥ መብት እየተጠና።
ሌሎች እኩዮቿን
መብት እንደሆናቸው፥ ትምህርትና ስራ፣
እሷም ትማራለች
(እሷም ትሰራለች)
እምነቷን አክብራ፥ መብቷን አስከብራ።
©️EHEMSU
@aaumsu
🔥17❤3👌3
70 ቀናት ሞላ
ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት
አስቸኳይ የሆነ የፖለቲካ አመራር እና ውሳኔ በማሳለፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ስልታዊ የመብት ጥሰት እና ማግለል ያስቆም ዘንድ ለብልፅግና ጽ/ቤት ደብዳቤ ከገባ 70 ቀናት ሞልቷል። ሆኖም ግን እስካሁን ባለው ጊዜ ተማሪዎች ላስገቡት ደብዳቤ የተሰጠ ምላሽም ሆነ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የተወሰደ ቁርጠኛ እርምጃ አልታየም።
መሠል ምላሾች አግባብነት የሌላቸው እንደሆኑ እናምናለን። ተማሪዎች የደረሰባቸው በደል ተሰምቶ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ ሁሉንም አማራጭ ተጠቅመዋል። ቅሬታዎችን ሰምቶ አጥፊዎችን በመቅጣት መፍትሔ መስጠት የመንግስት ሀላፊነት ቢሆንም መፍትሔው ሳይመጣ እስካሁን አለ።
መመሪያው ይስተካከል ዘንድ ዳግም እንጠይቃለን። መመሪያው እስኪስተካከልም ጥያቄ አለን እንላለን። የደረሰብንን በደል አሳውቀን ምላሽ ላልሰጡን ስለምን ምላሽ እንዳልሰጡ ጥያቄ አለን። መፍትሔ እንደሚያመጡ ቀጠሮ ሰጥተው ቃላቸውን ላጠፉ አካላት ስለምን ቃላቸውን እንዳጠፉ ጥያቄ አለን። መመሪያውን ሳያሻሽሉ በደላቸውን ለቀጠሉ አካላት ስለምን በበዳይነታቸው ለመቀጠል እንደቆረጡ ጥያቄ አለን።
ጥያቄያችንንም ሳንሰለች ሳንደክም ሳንፈራ ሳናፍር በቢሮ ውስጥም ሆነ በአደባባይ እናቀርባለን። በሚዲያም ሆነ በአካል እናሰማለን። ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!

🔥15❤2👌2
🫡19❤3💯3
በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሙስሊሞች ይባል ነበር _ ቀደምቶቻችን በከፈሉት ዋጋ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ተባልን
ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ነች ይባል ነበር _ አባቶቻችን ባደረጉት ትግል ኢትዮጵያ የሁሉም የሆነች ሴኩላር ሀገር ነች እንዲባል ሆነ
በሁለቱ ዒዶች የመንግስት መስሪያ ቤት ክፍት ሆኖ ይውል፤ ትምህርት ቤትም ሆን ተብሎ የፈተና ቀን ይሆን ነበር _ ታሪካቸውን በወርቅ ብዕር ከትበው ባለፉ ትውልዶች ዒዶቻችን ብሔራዊ በዓል ሆኑ
ስለ እስልምና _ የሐይማኖት ነፃነት መብት በሕገ- መንግስት እንዲፀና _ የሐይማኖት እኩልነት መብት በሕግ እንዲቀመጥ ያልተከፈለ መስዋዕትነት የለም። ሆኖም በሕገ- መንግስት እንዲፀና የተደረገው መብት የትምህርት ሚኒስቴርን አጥር መሻገር ተስኖታል። ዋጋ ተከፍሎበት በሕግ እንዲፀና የሆነው መብት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን አጥር መሻገር ተስኖት በመመሪያ ተጥሷል።
ሆኖም ቀደምት አባት እናቶች ታግለው ያፀኑትን ታግሎ ማስከበሩ የእኔ፣ የአንተ የአንቺ፣ የሁላችን ሀላፊነት ሆኗል። ዋጋ ለተከፈለበት ዋጋ መክፈል ግድ ነው።

🔥20❤5💯3👍2
23 ቀናት ሞላ
የፌደራል መጅሊስ ፕሬዚዳንት
ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ከዶክተር ሳሙኤል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደተነጋገሩና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በኒቃባቸው ምክንያት ሳይሳቀቁ እንዲማሩ እንደሚያደርጉ ከ23 ቀናት በፊት በአዲስ አበባ መጅሊስ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ገልፀው ነበር። ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ተወካዮች ከመጅሊሱ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ጋር የዚያኑ ቀን ውይይት ያደረጉ ሲሆን መጅሊሱ መመሪያው ይስተካከል ዘንድ የሚጠይቅ ደብዳቤ እንዲያስገባ፤ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የመብት ጥሰት የፈፀሙ የዩኒቨርስቲው አካላትን ሊከስ፤ ከዩኒቨርስቲው ጋር ለዘላቂው መፍትሔ ውይይት ሊደረግ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጨረሻ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ ከተቋቋመው 17 ኮሚቴ ጋር ተማሪዎች በቅርበት እንዲሰሩ ከስምምነት ተደርሶ ነበር።
ቃል በተገባ ማግስት ጀምሮ የመብት ጥሰቶቹ የቀጠሉ እና መመሪያውም ያልተሻሻለ ቢሆንም ባለፉት 23 ቀናት ውስጥ ከተጠቀሱት አራት ነጥቦች ውስጥ ወደ ተግባር የተለወጠ አንድም ነጥብ የለም። መጅሊስ የሙስሊሙን መብት ሊያስጠብቅ የሚገባ ግንባር ቀደም ተቋም እንደመሆኑ በዚህ ሁሉ ቀናት ውስጥ ትኩረት ተሰጥቶ ቁርጠኛ የሆነ አቋም ተወስዶ መፍትሔ አለመምጣቱ በተማሪው ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል።
ጥያቄያችን መብቶቻችን በመመሪያ ተፅፈው እና በሕግ ፀንተው እንዲመለሱልን ነው። ነፃነታችንን ገፍፎ ሙስሊም ጠልነቱን ሲያንፀባርቅ እና በደል ሲፈፅም የነበረ ሁሉ በሕግ አግባብ ይጠየቅ ዘንድም ግድ ነው።
ጥያቄ አለን እንላለን። ቢሮ ውስጥም በአደባባይም _ በሚዲያም በአካልም _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!

🔥15❤5👍2💔2
It is not a joke !
It is not for fun !
በመብቱ የሚቀልድም ሆነ ለቀልድ መብቱን የሚጠይቅ ተማሪ የለም። ክላስ ቀጥተው፤ ካፌ እያለፋቸው፤ ታክሲ ሲጠፋ ኪሎ ሜትሮችን በእግራቸው እየተጓዙ ከቢሮ ቢሮ የሰው ፊት እየገረፋቸው ስለመብታቸው ሲጠይቁ የነበረው ለቀልድ አይደለም። ያ ሁሉ ተማሪ ያንን ሁሉ ቀናት በፅናት ሲራወጥ የነበረውም ለቀልድ አይደለም። ደከመኝ ሳይሉ የለፉት፤ ሳይፈሩ ሁሉንም አካል የተጋፈጡት የመብታቸውን ዋጋ ስለተረዱ ነው። ያላቸውን ሁሉ የሰጡትም ሊሰጥ የሚገባውን ስላወቁ ነው።
ዛሬ ከትላንት የተሻለ ይሆን ዘንድ የተከፈለውን ታሪክ ስለተነገራቸው ነው። ነገ ልጆቻቸው በሙሉ ነፃነት ይማሩ፣ ይሰሩ፣ ሀገራቸውን ያገለግሉ እና ይመሩ ዘንድ መከፈል ያለበትን ስለተረዱ ነው።
እንደዚያ ስለሆነም እንደ ቀልድ የምናልፈው ነገር አይኖርም። መጠየቅ ባለብን መንገድ ሁሉ መብታችን ይከበር ዘንድ እንጠይቃለን።
የመንገዱ ባህሪ ነውና!

🔥35❤5💯5
በሐጂ አደም ሳዶ ሀገር ባሌ የሚገኘው መዳ ወላቡ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች "Niqaaba ni uffanna barnootas ni baranna - ኒቃቧን እንደለበሰች ትማራለች።" - በማለት መልዕክታቸውን አድርሰዋል። "Justice for AAU Muslim Students!" - ሲሉም ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ጥያቄው የሁሉም ሙስሊም ተማሪ ነው። ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው። ጥያቄያችን በመመሪያ የተጣሰው መብታችን በመመሪ ይፅና ነው። ኒቃብ መልበስ መብት ነው። ኒቃብን መከልከል እስልምናን መንካት፤ ሙስሊሞችን ከትምህርት ማገድ ነው። ሙስሊም ደግሞ እስልምናው ሲነካ ዝም ብሎ አያይም። በሁሉም መንገድ ስለመብቶቻችን መጠየቃችን ግድ ነው። ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!

🔥25🥰4❤2😍1
ድምፄ እስኪሰማ...
እርቃንሽን ካልሆንሽ አትማሪም አሉኝ
"ኒቃብሽን አውልቂ" ብለዉ ተናገሩኝ
ክብሬን ስለጠበኩ መማር ከለከሉኝ
አናስገባም ብለው በሮቹን ዘጉብኝ
"ማንስ ፈቀደልሽ ከቶ ልትማሪ
እዚህ እንዳመጪ እዛዉ ቤትሽ ቅሪ"
ብለዉ አባረሩኝ ከእዉቀት ገበታዬ
ሗላ ላይ እንድቀር ካለማወቅ ቀዬ
በዘዴ ሊገፉኝ ከእዉቀት ማማዬ
አላህ ነዉ "አንብቢ!" "ኢቅራዕ!" ሲል ያዘዘኝ
ግን እነዚህ ሰዎች መማር ከለከሉኝ
ፊትሽን ካላየን አትምጪብን አሉኝ
መፅሃፍ እና ኒቃብ፣ የኔ ሆነዉ ሳለ
"አንዱን ምረጪ አለኝ"፣ መብቴን ከለከለ።
ሌሎቹ ሲማሩ መብታቸው ተከብሮ
እኔ ግን ተገለልኩ መብቴ ተገፍትሮ
ሁሉን ተመልካቹ አሸናፊዉ ጌታ
የጭቁኖች ረዳት ያማኞች አለኝታ
ለምነትህ ያደርን ታዛዥ ባሮችህ ነን
በበደለኞች ላይ ድልን አጎናፅፈን
ጭቆናዉ ቢበዛም ግፋ እንግልቱ
በሩን ቢዘጉትም ሊገፋኝ ከ'ዉቀቱ
መብቴ እሰኪከበር ድምፄን ማሰማቱ
ዛሬም ይቀጥላል ልክ እንደ ትናንቱ
እስኪሰማ ድረስ የፍትህ ብስራቱ
ጭቆና ተቀብሮ እስኪመጣ እዉነቱ!!!
ከአንድ ወንድማችን
©️Sefereselam muslim students jeme'a
@aaumsu
እርቃንሽን ካልሆንሽ አትማሪም አሉኝ
"ኒቃብሽን አውልቂ" ብለዉ ተናገሩኝ
ክብሬን ስለጠበኩ መማር ከለከሉኝ
አናስገባም ብለው በሮቹን ዘጉብኝ
"ማንስ ፈቀደልሽ ከቶ ልትማሪ
እዚህ እንዳመጪ እዛዉ ቤትሽ ቅሪ"
ብለዉ አባረሩኝ ከእዉቀት ገበታዬ
ሗላ ላይ እንድቀር ካለማወቅ ቀዬ
በዘዴ ሊገፉኝ ከእዉቀት ማማዬ
አላህ ነዉ "አንብቢ!" "ኢቅራዕ!" ሲል ያዘዘኝ
ግን እነዚህ ሰዎች መማር ከለከሉኝ
ፊትሽን ካላየን አትምጪብን አሉኝ
መፅሃፍ እና ኒቃብ፣ የኔ ሆነዉ ሳለ
"አንዱን ምረጪ አለኝ"፣ መብቴን ከለከለ።
ሌሎቹ ሲማሩ መብታቸው ተከብሮ
እኔ ግን ተገለልኩ መብቴ ተገፍትሮ
ሁሉን ተመልካቹ አሸናፊዉ ጌታ
የጭቁኖች ረዳት ያማኞች አለኝታ
ለምነትህ ያደርን ታዛዥ ባሮችህ ነን
በበደለኞች ላይ ድልን አጎናፅፈን
ጭቆናዉ ቢበዛም ግፋ እንግልቱ
በሩን ቢዘጉትም ሊገፋኝ ከ'ዉቀቱ
መብቴ እሰኪከበር ድምፄን ማሰማቱ
ዛሬም ይቀጥላል ልክ እንደ ትናንቱ
እስኪሰማ ድረስ የፍትህ ብስራቱ
ጭቆና ተቀብሮ እስኪመጣ እዉነቱ!!!
ከአንድ ወንድማችን
©️Sefereselam muslim students jeme'a
@aaumsu
👍18❤10👌1
ታድለን ቢሆን . . .
የሙስሊሙን ተማሪ መብት ማስከበር የሙስሊሙ ተማሪ ሀላፊነት ብቻ አልነበረም። ታድለን ቢሆን የተማሪዎቹን መብት አክብሮ ማስተማር የዩኒቨርስቲው ሀላፊነት ነበር። ግን አልሆነም! ታድለን ቢሆን ዩኒቨርስቲው መብታችንን ሲጥሱ መብታችንን የማስከበሩ ሀላፊነት የትምህርት ሚኒስቴር ነበር። ግን አልሆነም! ታድለን ቢሆን መብታችን ሲጣስ የማስከበሩ ሀላፊነት የሰላም ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ነበር። ግን አልሆነም! ታድለን ቢሆን እንደ ሙስሊም መብቶቻችንን የማስከበር ሀላፊነቱ የመጅሊስ ነበር። ግን አልሆነም!
አልሆነምና ተስፋ ቁረጡ የሚሉም አልጠፉም። ለሁሉም ግን አላህ በቅዱስ ቃሉ ያስቀመጠውን ድንቅ አንቀፅ አንብቡላቸው።
" الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ
እነዚያ ሰዎቹ ለእነርሱ፡- «ሰዎች ለእናንተ (ጦርን) አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» ይሉዋቸውና (ይህም) እምነትን የጨመረላቸው «በቂያችንም አላህ ነው ምን ያምርም መጠጊያ!» ያሉ ናቸው፡፡" [3:173]
ለሁሉም በቂ የሆነው አላህ መጠጊያችን ነው። ከእርሱ ወጪስ መጠጊያ አለን? ምንኛ ያማረ መጠጊያ ነው።

🔥21❤10⚡2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 2 ሶስት ቀን ኒቃብ አይከለከልም ቢል መፍትሔ መጣ አንልም። ምን ማለት ነው? እኛ የምንፈልገው በመመሪያ የፀና መብት ነው። ነገ የት ነው የምታስጮሁን ብለን ልንጠይቅ ነው?!" -
@aaumsu
@aaumsu
🔥24💯2
አልሐምዱሊላህ __ ታድለናል !
ገና ባልጠና ጉልበታችን፥ የብዙዎች ያልተሰራ የቤት ሥራ በጫንቃችን ላይ ተጣለብን።
ታድለን ...
የትውልድን ክብር በመጠበቅ ላይ ኃላፊነት ወሰድን።
ታድለን...
የእህታቸው ክብር እየተነካ፥ በሰላም ተኝተው የማያድሩ ዓይኖች ተሰጡን።
ታድለን...
ፍትሕ ስትቀበር «በእኔን ከተመቸኝ ይሁንታ» የማይቀበል አዕምሮ ተሰጠን።
ታድለን...
ቀን እስኪያልፍ የሚጎድልን ክብር የማይታገስ ልብ ተቸርን።
ታድለን...
ሌሎች የፈሩበትን ነገር በድፍረት የመጋፈጥ ወኔ ተሰጠን።
ታድለን...
«አዳኝ» እስኪመጣ ሳንጠብቅ፥ ኃላፊነታችንን የምንወጣበት ተቆርቋሪነት ተሰጠን።
እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ታድለን...
ፍትሕ መጓደል አመመን።
የመብታችን መጣስ ቆረቆረን።
ጭቆና አንገሸገሸን።
ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ታድለንማ'ኮ...
ታሪክ "ካላጎነበሱት" መካከል መዘገበን።
መስዋዕትነት ከገባቸው፤
ትውልዳቸውን ለመታደግ ቁርጠኛ ከሆኑት መሃል መዘገበን።
ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ታድለንማ'ኮ...
በአላህ ላይ ከሚመኩት፣
ለመንገዱ ከሚታመኑት፤
ድልንም ከርሱ ብቻ ከሚጠብቁት ሰራዊቶቹ መሃል አደረገን።
ደግሞ እንደኛ የታደለ አለ እንዴ?!
ለኛ የተሰጠው ለማን ተሰጥቷል?! - ዙሪያችሁን አትመለከቱምን?!
በህይወታችን ካየናቸው ብዙ ብዙ ብቸኝነቶች ውስጥ፥ በዚህ የትግል መንገድ ላይ ያለ ብቸኝነትን ያህል ዋጋ ያለው ብቸኝነት የት እናገኛለን?!
አላህ የሚያየው፣ የሚመሰክርለት ብቸኝነት!
ወደ ድል እንጂ የማይደርስ፣ ውድቀት የሌለበት ብቸኝነት!!
ትርጉሙ ጥልቅ፣ ክፍያው ብዙ ብቸኝነት!!!
ይህ እንደዋዛ 'ሚገኝ ነው እንዴ 'ሚመስለን?! በፍጹም።
ለዚህ ብቸኝነት መመረጥ ያሻዋል።
ይህ'ኮ ታላቅ ጸጋ እንጂ ሌላ አይደለም።
አልሐምዱሊላህ!!!
ሐስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል!!!

🔥34❤8