ተለቋል!
እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች እየደረሰብን ያለውን የመብት ጥሰት በመታገል ረገድ አሁናዊ ሁኔታን በደንብ የሚገልፀው ፖድካስት ተለቋል።
ሊንክ https://youtu.be/OLd-8QipP2k?si=JhpcMx-4MoqCpmnE ነው። ለሌሎችም ያድርሱ።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu

🔥21❤1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን ቪድዮ እናሰራጭ። የተፈፀመውን ሁሉም ያውቅ ዘንድ። ማብራሪያ መስጠት ያለበት ማብራሪያ ይሰጥ ዘንድ። መጠየቅ ያለበትም ይጠየቅ ዘንድ።
ሊንኩ https://vt.tiktok.com/ZS9PMXMfg/ ነው። ግቡና ሪፖስት አድርጉ።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!

🔥29👍4😭4❤3🫡2
ነገ ጁምዓ ነው!
የዩኒቨርስቲ ጀመዓዎች በየመስጂዶቻችሁ እንዲሁም ኹጥባ የምታደርጉ ኡስታዞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን የመብት ጥሰት እንድታወግዙ፤ ሒጃብን/ኒቃብን የሚከለክለው መመሪያ ይሻሻል ዘንድ መልዕክት እንድታስተላልፉ፤ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች አጋርነታችሁን እንድታሳዩ ጥሪያችን ነው።
ጥያቄው የሁላችንም ነው!
ፍትሕ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ሙስሊም እንደ አንድ አካል ነው፤ ሙስሊም እንደ አንድ ግንብ ነው፤ ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው።
አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሙሐመድ !😍!

🫡27❤16👍3👌2
የወሎ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ከጁምዓ ቡሃላ "ፍትሕ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች!" - በማለት አስተጋብተዋል።
ሒጃብ ማንነት ነው። ማንነት ሊከለከል አይገባም!
መብቶቻችንን የነጠቁ አካላት በሕግ ይጠየቁ!
ጥያቄው የእኛም ነው!
ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው!
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!
ይህ ጅማሮው ነው _ ይቀጥላል 🔥
@aaumsu
ሒጃብ ማንነት ነው። ማንነት ሊከለከል አይገባም!
መብቶቻችንን የነጠቁ አካላት በሕግ ይጠየቁ!
ጥያቄው የእኛም ነው!
ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው!
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!
ይህ ጅማሮው ነው _ ይቀጥላል 🔥
@aaumsu
🔥45❤11👏5🥰2⚡1👍1
ይህ ከመቱ ሰማይ ስር ነው
የመቱ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ከጁምዓ ቡሃላ ጥያቄ አለን ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ጥያቄው የሕዝበ ሙስሊሙ ነው!
Gaaffii Qabna !
Qaamonni mirga keenya sarban seeraan haa gaafataman !
ፍትሕ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እንፈልጋለን _ ዘላቂ መፍትሔ እንፈልጋለን !

🔥42❤18👏3🥰2⚡1🫡1
የሰፈረሰላም ተማሪዎች ቅሬታቸውን በካምፓሱ ባሉ ሳጥኖች ውስጥ በፅሁፍ እያስገቡ ነው
"አለባበሴ በእምነቴ የታዘዝኩት ማንነቴ እና አውልቄ ልጥለው የማልችለው ነገር ከመሆኑ ጋር ዩኒቨርስቲው ይህንን አድርጌ እንዳልማር መከልከሉ ከትምህርቴ እና ማንነቴ እንድመርጥ የሚያስገድድ በመሆኑ ዩኒቨርስቲው መመሪያውን እንዲያሻሽል እጠይቃለሁ።"
"በአንቀፅ 6.6 ምክንያት ከቃላት ጀምሮ የተለያየ እንግትል እና የመብት ጥሰት እየደረሰብኝ ስለሆነ መመሪያው ይሻሻል ዘንድ እጠይቃለሁ።"
"A university should be a place of belonging where diversity is embraced and every student feels respected. But when we see our university it is isolating muslim students from the institution . I kindly urge the administration to reconsider article 6.6 and to restore our rughts."
ከገቡ መልዕክቶች መካከል ናቸው። ሁላችንም ወደ ቅሬታ ሳጥኖች እየሄድን ቅሬታዎቻችንን እናስገባ። ድምፃችንን በስነ- ስርዓት እናሰማ። ለቅሬታችን ምላሽ ይሰጡ ዘንድ እንጠይቅ።
ያስገባችሁትን ቅሬታ @Niqab_issueBot ላኩልን።

🔥28👏5👌1🫡1
6ኪሎዎች ሰፈረሰላምን ተከትለው ቅሬታቸውን ግቢው ውስጥ ካለው የቅሬታ ማስገቢያ አስፍረዋል። ከመልዕክቶቹ መካከል እነሆ፦
"የዩኒቨርስቲው ጨቋኝ መመሪያ ይነሳ! ኒቃቧ ለርሷ ሠብዓዊ መብት፤ የሐይማኖት እና መብት መገለጫ፤ የማንነቷ አካል ሲሆን ለተቀረነው ሙስሊሞች ደግሞ በፍፁም ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው። ይህንን መስመር ሊተላለፍ የሞከረ ሁሉ የሕዝበ ሙስሊሙን ክብር ተዳፍሯል። ኒቃብ ቀይ መስመራችን ነው! ጥያቄ አለን!! መልስ እንፈልጋለን!!!"
"በብዙ ትግል እና ጥንቀት ማትሪክን በብቃት ካለፍን ቡሃላ እንደ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የግቢውን ፈተናም አልፈን የገባን ተማሪዎች ነን። በዚህ ሁሉ አልፈን ገብተን ግን እንደ ተማሪ አልተቆጠርንም። መብታችን እየተጣሰ እና እየተገፈፈ ነው ያለው። ከማንነታችሁ እን ከትምህርታችሁ ምረጡ እየተባልን ነው ያለነው። ምርጫው ግን አንድ እና አንድ ብቻ ነው፤ እንደለበስን መማር። ግቢውም ይህንን ተረድቶ መመሪያውን ያሻሽል ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ።"
"ኒቃብ ስለለበስን ከግቢ በር ጀምሮ ላይብረሪ እና ካፌ ላይ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰብን ነው። ለዚህ ምክንያት የሆነው መመሪያ ተሻሽሎ መብታችን ይከበር ዘንድ እጠይቃለሁ።"
አንተስ? አንቺስ? ሌሎች ካምፓሶችስ? እንንቀሳቀስ። ጥያቄዎቻችንን በሁሉም መንገድ እናድርስ። ያስገባችሁትን ቅሬታ @Niqab_issueBot ላኩልን።

🔥18❤8👌4
ዳግም ጥሪ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየፈፀመ ያለው በደል እንደቀጠለ መሆኑ፤ ያወጣው ጨቋኝ መመሪያ አለመሻሻሉ እና አጥፊዎችም ተጠያቂ አለመደረጋቸው ይታወቃል። ሌሎችም እርሱን በመከተል ኒቃብን የሚከለክል መመሪያ እያወጡ እንደሆነ ተስተውሏል። ይህንን አጀንዳ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ካልተቻለ ክልከላው ከዩኒቨርስቲ ዩኒቨርስቲ መሸጋገሩ አይቀሬ ነው።
ስለሆነም በነገው እለት ሁሉም የዩኒቨርስቲ ጀመዓዎች፤ የመስጂድ ኢማሞች እና ኸጢቦች በኹጥባዎቻችሁ ውስጥ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኒቃብ ላይ ያደረገውን ክልከላ በማንሳት ታወግዙ ዘንድ፤ መልዕክት በማስተላለፍ እየደረሰ ስላለው ነገር ለማህበረሰብ ታደርሱ ዘንድ እንጠይቃለን።

🫡28
4_60262876053629905171_1.mp4
15.5 MB
ባለፈው ሳምንት _ በወሎ ዩኒቨርስቲ ከተደረገ የጁምዓ ኹጥባ !
"የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ፕሮጀክት ተመልከቱ። መራቆትን ባህል አድርገው እንደ ምዕራባውያን ካልሆናችሁ እያሉ ነው። ጉዳዩ የባህል ከሆነ ለምን የአፋር እና ሶማሌን ባህል አያከብሩም? ኒቃብ ለአፋር ባህሉ ነው። ኒቃብ ለሶማሌ ባህሉ ነው።"

🔥12💯4❤2
"የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ በሁሉም የሚደረስ ታዚያ መሆን የለበትም። በዚህ ዘመን በዚህ ትውልድ የሚቋጭ እንጂ።"
@aaumsu
@aaumsu
💯26❤8🔥6👌4⚡2
وَلَا تَهِنُوا(አትድከሙ/አትስነፉ)፦
የሰበሰባችሁት 1,141 ፊርማ በ "X" ሲሰረዝ፣ የተወካዮቻችሁ ድምፅ "አናውቃችሁም" ተብሎ ሲናቅ፣ በሩ ላይ ያሉት ጥበቆች መንገዱን ሲዘጉባችሁ... አትድከሙ! የእናንተ ጥንካሬ የሚለካው በሮች በመከፈታቸው ሳይሆን፣ በሮች ተዘግተውባችሁም ለቆማችሁለት አላማ ባለመደላደላችሁ (resilience) ነው።
وَلَا تَحْزَنُوا(አትዘኑ)፦
ርቦሽ ከካፌ ስትባረሪ፣ ታመሽ ከክሊኒክ ስትገፊ፣ ወይም መምህራን ማርክሽን ቀንሰው ሊያሸማቅቁሽ ሲጥሩ... አትዘኚ! ይህ የአጭር ጊዜ እንግልት ነው። እነሱ 'እየቀጣናችሁ ነው' ብለው ቢያስቡ፣ አላህ ግን በሰማይ ቤቱ ለአንቺ የክብር ማዕድ 🍱 እያዘጋጀ ነው። ውጤትሽን በወረቀት ላይ ቢቀንሱትም፣ በእርሱ ዘንድ ያለሽ ደረጃ ግን ከፍ ያለ ነው።
وَأَنتُمُ الْأَعْلَوْنَ(እናንተ የበላይ ናችሁ)፦
ሀቅ ነው! ኒቃብሽን እንደ "ስጋት" ለሚቆጥሩት፣ ክብራቸውን ለዲግሪ ለሸጡትና የሌላውን ጥላ ለሚከተሉት ሰዎች አትሸማቀቂ። "በጥላ ውስጥ የሚቆይ ሰው ጥላ የለውም!" እንደሚባለው፣ ማንነታቸውን ደብቀውና የሌላውን ቀለም ለብሰው የሚሄዱት እነርሱ እንጂ፣ በፀሐይ ተቃጥለሽም ቢሆን የራስሽን የፅናት ጥላ ይዘሽ የቆምሽው አንቺ የበላይ ነሽ! ዲግሪ ካንቺ በታች ነው፤ ኒቃብሽ ግን የፈጣሪሽ አደራ በመሆኑ ካንቺ ጋር ከፍ ያለ ነው።
ባርነት ወይስ ዕውቀት?
ዛሬ ላይ ባለመማር ሊቀጡሽ የወሰኑ አካላት አንድ ነገር ሊረዱ ይገባል፤ ጥያቄሽ አንድና ግልፅ ነው— "መማር እፈልጋለሁ!" ነገር ግን ስትማሪ ክብርሽን፣ ሞገስሽንና ኒቃብሽን ጠብቀሽ ነው። ያለ ዲንሽ ሕይወት የለሽም፤ ያለ ተቅዋ ትምህርት ትርጉም አይሰጥሽም። የታላቁ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) አደራ የሆነውን ዲን አጥፍተሽ የምታመጪው ዲግሪ ለቤትሽም ለሀገርሽም በረካ አይሆንም። አንገትሽን አስደፍተው፣ በራስሽ ማንነት እንድትሸማቀቂ አድርገው የሚሰጡሽ እውቀት እውቀት ሳይሆን 'ባርነት' ነው።
አብሽሪ! አንቺ አትሰበሪም!
ለካፌና ለክሊኒክ ስትከለከዪ፣ በሩ ላይ ስትገፊና ስትገለዪ "ተሰበረች" ብለው ለገመቱ ሁሉ የምንለው፤ ይሄ ጫና የሚጨምረው ጥንካሬሽን እንጂ ድካምሽን አይደለም። ዛሬ በሩን ቢዘጉብሽ፣ ተቅዋን በልብሽ ካኖርሽ..
ረቡና በውብ ንግግሩ እንዲህ ሲል አብሽር ይልሻል፦
وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا ۞ وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِب
...አንቺ ብቻ እኔን ፍሪ እንጂ ላለሽበት ጭንቀት እና ጫና መውጫን አደርግልሻለሁ፤ ምን እሱ ብቻ ባላሰብሽው በኩልም ሪዝቄን እረዝቅሻለሁ ይልሻል። አንገትሽን ሊያስደፉሽ በሞከሩ ሰዎች ፊት፣ በኩራት ቀና ብለሽ የምትሄጂበት ቀን ደግሞ እሩቅ አይደለም። Inshallah ❤️
.... أَلَا إِنَّ نَصْرَ اللَّهِ قَرِيبٌ
(እውቁ! የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው) ፦
የእርሱ እርዳታ በቢሮክራሲና በሰው ፍቃድ የታጠረ አይደለም። ለጊዜው ነገራቶችን እያየ ዝም ያለው አንቺ እንድትሰበሪ or ሊቀጣሽ ሳይሆን፣ በፅናትሽ ታሪክ ሰርተሽ ለድል እንድትበቂ ነው።
ሀስቡነላህ ወኒእመል ወኪል!
ሰዎች "ተከታታይ ክስ መስርተንባችኋል፣ አናውቃችሁም፣ ዲግሪ የላችሁም" ብለው ሊያስፈራሯችሁ ሲሞክሩ፣ ቁርአን የሚሰጣችሁ 'ወኔ' ግን ፍፁም የተለየ ነው ፦
الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ
Look... እነሱ 1,141 ፊርማን ሲንቁ፣ አንቺ ግን "አላህ በቂዬ ነው" ስትይ፣ ሰማይና ምድር ካንቺ ጋር ይቆማሉ። ዲግሪ ወረቀት ነው፤ ኒቃብሽ ግን 'ሞገስ' ነው። ዛሬ አንገትሽን ሊያስደፉሽ የሞከሩ ሁሉ፣ ነገ በፅናትሽ ብርሃን አይናቸው ሲታወር ታያለሽ።
አብሽሪ እህቴ! አንቺ የአላህ እንግዳ እንጂ የካምፓስ ስደተኛ አይደለሽም። ዛሬ በካፌው በር ብትከለከዪም፣ ነገ በጀነት በር 'ያለምንም ሂሳብ' የምትገቢው አንቺ ነሽ!
"ኒቃቧንም ትለብሳለች... ትምህርቷንም ትማራለች!"
©ከቁርአን አያህ
#AAUMuslimStudents #DignityOverEverything #KeQuranAyah #JusticeForNiqabis #Ethiopia

❤️🩹ከ ቁርአን አያህ...
©ከቁርአን አያህ
#AAUMuslimStudents #DignityOverEverything #KeQuranAyah #JusticeForNiqabis #Ethiopia
@aaumsu
❤59🥰5🏆2👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጥያቄ አለን ማለት ከጀመርን 624 ቀናት ሞላ። መመሪያው በረቂቅነት ደረጃ ሳለ በመስከረም 15, 2017 ዓ.ል ነበር ጥያቄ አለን በማለት በአምስት ኪሎ ግቢ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ያሰማነው። የዚያኔ ለጥያቄያችን ምላሽ ላለመስጠት መድረኩን ረግጠው ቢሄዱም ቢሯቸው ድረስ ተሰብስበን በመሄድ ደጋግመን ጠይቀናቸው ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለ20 ወራት እና 19 ቀናት ብንጠይቅም በውይይት አምኖ ለጥያቄያችን ምላሽ ለመስጠት ከጠረጴዛ በአግባቡ የተቀመጠ አካል የለም። ለጥያቄያችን የተነፈገው ትኩረት እና በሂደቱ የተሰጠው ግብረመልስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ያለውን ውይይት ጠል እና ሙስሊም ጠል አካሄዶችን የሚያሳይ ነው። ምንም ቢሆን ምን መብቶቻችንን በመጣሳቸው ፍትሕን ለመጠየቅ የጀመርነው ጉዞ አይቋጭም። በሰላማዊ መንገድ በአስቸኳይ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ ዳግም እንጠይቃለን።
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu
ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ !
@aaumsu
🔥20👍8💯6❤1
ሒጃቧ - ማንነቷ!
መገለጫዋ ነው
ማንነት ምስጢሩ፥ የተወጠነበት፣
የሴትነት ሀሁ
የተፈጥሮ ሚዛን፥ ጸንቶ የቆመበት።
እሷነት ነው ሒጃብ
ጥንት የተሰጠችው፥ የገጿ ላይ አርማ፣
በወቅት አይደበዝዝ
አረጀብኝ ብላ፥ እትጥለው ከርማ።
እቃዋም አይደለም
ሲያሻት የምትጥለው፥ ደግሞ 'ምታነሳው፥
የመኖር ምሷ ነው
ከራሷ ተገምዶ፥ እሷው የምትለብሰው።
ማንነት ነውና
ነፍስና ስጋዋን፥ ተዋሕዶ ያለ፣
እሷን ከሂጃቧ
የምትነጥልበት፥ ጉልበት ወዴት አለ?
©EHEMSU
@aaumsu
መገለጫዋ ነው
ማንነት ምስጢሩ፥ የተወጠነበት፣
የሴትነት ሀሁ
የተፈጥሮ ሚዛን፥ ጸንቶ የቆመበት።
እሷነት ነው ሒጃብ
ጥንት የተሰጠችው፥ የገጿ ላይ አርማ፣
በወቅት አይደበዝዝ
አረጀብኝ ብላ፥ እትጥለው ከርማ።
እቃዋም አይደለም
ሲያሻት የምትጥለው፥ ደግሞ 'ምታነሳው፥
የመኖር ምሷ ነው
ከራሷ ተገምዶ፥ እሷው የምትለብሰው።
ማንነት ነውና
ነፍስና ስጋዋን፥ ተዋሕዶ ያለ፣
እሷን ከሂጃቧ
የምትነጥልበት፥ ጉልበት ወዴት አለ?
©EHEMSU
@aaumsu
🔥20👏4❤2