AAU - Muslim Students Union
6.48K subscribers
2.76K photos
151 videos
51 files
767 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
🥀 Daily Reminder 106🥀

وَكُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ وَلَا تُسۡرِفُوٓاْۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡرِفِينَ(31)

"ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና!!"

Surah Al-A'raf; 31

@aaumsu
🥰6👍2
" ድንኳኖቹን በቶሎ አስወግዷቸው:: አክራሪዎቹን ድል አድርጉ:: ካምፓሶቻችንን መማር ለሚፈልጉ ጤነኛ ተማሪዎች ዳግም ምቹ አድርጉ:: እነዚህ ዘገምተኛ እብዶች ናቸው::" - ዶናልድ ትራምፕ

   በጋዛ ላይ የተከፈተው ፍጅት 210ኛ ቀኑን አስቆጥሯል:: እስካሁን 35ሺህ ጋዛውያን መስዋዕት ሲሆኑ  78ሺህ ቁስለኛ ሆነዋል:: ሬሳቸው ከፍርስራሽ ስር ሆኖ ለመቀበር ያልታደሉ ሺዎች እንዳሉም ተመላክቷል::

  አምባገነኖች በእብሪት ተሞልተው ጭካኔውን ሲፈፅሙ ማዬት የተሳናቸው የምዕራቡ አለም ተማሪዎች ሁለ ነገራቸውን መስዋዕት አድርገው በካምፓሶች ዙሪያ ተቃውሞ ከጀመሩ ቀናቶች ተቆጥረዋል:: እስካሁን ከ2200 በላይ ተማሪዎች የታሰሩ ሲሆን የተለያየ አይነት እንግልትም እየደረሰባቸው ነው::

  ግን አሁንም ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው:: ከተማሪዎች አንደበት የወጣው የነፃነት ድምፅ አያስተኛ ያላቸው የዋይት ሀውስ ሰዎች ፀጥታውን ሰብረዋል:: የአሁኑ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን "ሀገራችን አምባገነናዊ ስላልሆነች ድምፆችን አታፍንም:: ተማሪዎች የመናገር መብት ቢኖራቸውም ለአመፅ ማነሳሳት አይችሉም:: ይህ ከህገ-መንግስታችን ውጭ ነው:: የእነሱ ተቃውሞ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ያላትን ፖሊስ አያስቀይርም::" ሲሉ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ተማሪዎች "ዘገምተኛ እብዶች!" ብለው በመዝለፍና ፖሊሶች እየወሰዱት ያሉትን የሀይል እርምጃ በማበረታታት ዳግም ጠበቅ ያለ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል::

  የዲሞክራሲ ጭምብል ሲገለጥ የሚታዬው እብሪትና አምባገነንነት ግልፅ ሆኗል:: አላህ ውርደታቸውን ያቅርብ:: የፍልስጤማውያንን ድል ያቅርብ:: የዳውድ ጌታ የዳውድን ጥበብ ለፍልስጤማውያን ሰጥቶ በጎልያድ ላይ የተቀዳጀውን ድል በምዕራባውያን ላይ ይስጣቸው::

   የተማሪዎቹ መፈክር የእኛም ነው:: የፍልስጤማውያን ነፃነት የእኛም ነው::

  UP UP WITH LIBERATION!
  DOWN DOWN WITH OCCUPATION!
  DOWN DOWN WITH OPPRESSION!
 
FREE FREE PALESTINE!
FROM THE RIVER TO THE SEA PALESTINE WILL BE FREE!


@MohammadamminKassaw
👍20
📌እድሜው ሙስሊሙ ተማሪ ተቋማት ውስጥ መብቱን መጠየቅ ከጀመረበት ጊዜ አንድ ብሎ ይጀምራል ::

📌 ከውስጡ ለኢትዮጵያ ሙስሊም እንቁ የሆኑ ስብዕናዎች ወጥተዋል ::

📌ከኡማው ጋር እኩል እየተፈተነ ለ35 አመታት ተማሪዎችን በማነፅ ሌሎችን በማነቃቃትና ሞደል በመሆን ዛሬን ደርሷል ::

   🔺ይህ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ነው :: ስለ ህብረቱ ሙሉ መረጃ ለማግኘትና በጉዞው ውስጥ አብሮ ለመሆን ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ የህብረቱን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ ::

   @aaumsu
   @aaumsu
   @aaumsu

ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድርጉ ::
👍9
📌Umriin isaa yeroo barattoonni Muslimaa mirgaa ofii gaafachuu jalqaban irraa eegala.

📌 Isa keessaa ummata Muslima Itoophiyaatiif haallii fi ammalli gaariin hedduun burqee jira.

📌 Ummata waliin walqixa dararamaa umrii 35 oliif  barattoota bocaa, kaka'uumsa fi hidhannoo (model) ta'aaf har'a gahee jira.

🔺 Innis Gamtaa barattoota Muslimaa Yunivarsiitii Finfinneeti. Hubannoo waa'ee gamtichaa guutuu isaa argachuu fi imala isaa waliin ta'uuf sarara armaan gadii cuqaasuun(tuquun) Telegiraama gamtichaatti makamaa
@aaumsu
@aaumsu
@aaumsu

Hiriyoota keessaniif share godhaa!
👍42
📌 It's stepping stone was planted  when Muslim students begin demanding their rights within educational institutions.

📌 From among it's students, there emerged valuable figures for Ethiopian Muslims and the country.

📌 It was tested on a same footing with the Ummah during its 35 years journey.

📌 It encouraged its students, served as an inspirational entity to others, and has had an examplery and outstanding history.
        {📌 📌 📌📌 }
This 👆👆👆👆 is Addis Ababa University Muslim Students Union.To get comprehensive, timely and updated information about the Union as well as to travel with AAU-MSU to the CLIMAX, join its Telegram channel
using the link below.
👇👇👇
@aaumsu
@aaumsu
@aaumsu
🔥61😡1
Students council-union election.pdf
1.6 MB
ለተማሪዎች ካውንስል መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ attached ከተደረገው file መረጃዎችን ወስዳችሁ ከወዲሁ ራሳችሁን አዘጋጁ:: ምርጫው ግንቦት 16 እንደሚደረግ ተገልፇል::

@aaumsu
👍6
ሱፍያን አሰውሪ (رحمه الله) እንዲህ ይሉ ነበር፦

﴿إذا عرفتَ نفسَك لم يضرَّكَ ما قيلَ لَكَ،﴾

“አንተ ስለራስህ የምታውቅ ከሆነ፤ ስላንተ የሚባለው የሰዎች ንግግር አይጎዳህም።”

@aaumsu
👍84👌3🥰1
May Allah remove our sadness !

@aaumsu
14👌5👍4🥰3😭2
Quran will tell you the solution for all your problems!

@aaumsu
16🥰5👍2
🥀 Daily Reminder 107🥀

فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓۚ(37)

"በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው??"

Surah Al-A'raf; 37

@aaumsu
👍12
“O you who believe, Take care of your soul.”

[Qur'an-5:105]

@aaumsu
3👍2
ሟቹ "ጌታ!"
~
ወሎ ውስጥ ነው። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ  ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል።
·
* ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ።
–  "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት።
·
ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ።
·
ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው።

* "እሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ።
·
አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል።
·
* "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው።
– "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት።

* "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ።
– "አዎ" አሉት።
·
ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:–
"እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!!"

የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው።

መወለድ፣ ማደግ፣ መሞት ለፈጣሪ የማይመጥኑ የደካማ ፍጡሮች መታወቂያ ናቸው። እባካችሁ ያገሬ ሰዎች ቆም ብላችሁ አስቡ። "ፍፁም ሰው፣ ፍፁም አምላክ" እያሉ "ተጨፈኑ እናሙኛችሁ" ሲሉ እጅ አትስጡ። "ሁሉን ምርምሩ። መልካሙን ያዙ።" በአባቶች የውርስ ጋቢ ተጠቅልላችሁ፣ በይሉኝታ ጆሯችሁን ደፍናችሁ፣ በምስጢረ ሥላሴ ትብታብ ታስራችሁ እንጂ ህሊናችሁን ፋታ ሰጥታችሁ በእርጋታ ብታዳምጡት የሚነግራችሁ ሐቅ አለ።
"ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ ይነግርሀል አንዳች እውነት" ይላል ገጣሚው።
·
ዳሰሳ ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 12 ቁ 29 እስከ 34።
----------
"ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። #ከትእዛዛቱ_ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ #ጌታ_አምላካችን #አንድ_ጌታ ነው፥" (የማርቆስ ወንጌል 12:29)
·
ማነው ይህን ያለው? እየሱስ እራሱ!! "ጌታ አምላካችን" ማለቱን አስምርበት። እየሱስ ፍጡር እንጂ ጌታ እንዳልሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ጥቅስ ነው። ይሄ ቀዳሚ ትእዛዝ ግን በክርስቲያኖች ተገፍቷል። እንቀጥል።

"አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።" (የማርቆስ ወንጌል 12:30)
·
ልብ በል! በዚህ መልኩ "ጌታህን ውደድ" እያለ የሚያስተምረው እየሱስ እራሱ ነው። ይህም እሱ አስተማሪ እንጂ ጌታ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው። እንቀጥል።

"ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።

ጻፊውም። መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ #አንድ_ነው#ከእርሱም_በቀር_ሌላ_የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ፤" (ማርቆስ 12:31–32)

እያስተዋልክ ነው?!
እውነት የምትፈልግ ከሆንክ "አምላክ አንድ ነው። ከርሱ በቀር ምንም የለም" ብለህ በልብህ ዝከር። በምላስህ አስተጋባ። በተግባር ኑር። ይሄ በኢስላም "ላ ኢላሀ ኢለላህ" ("ከአላህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ የለም") ከሚለው ምስክርነት ጋር መሳ ነው። እንቀጥል።

"በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው።" (ማርቆስ 12:33)

ይህን ነው የምልህ። ስላሴ፣ ቅብጥርሴ የሚባለውን ወደ ኋላህ አሽቀንጥረህ ጣልና ለመፅሐፋዊ መልእክቱ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም አእምሮህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ እደር። ሥላሴ ልብ ወለድ እንጂ እውነታ አይደለም። ሥላሴ ጤነኛ ጭንቅላት የማይፈታው እንቆቅልሽ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም። "ያልገባህ መንፈስ ቅዱስ ስላላደረብህ ነው" እያሉ አይሸውዱህ። ይሄ ምእመኑ እንዳይመረምር የሚያስተኙበት የእንቅልፍ ክኒን ነው። በክኒኑ እራሳቸውን ያስተኙበት። አንተ ግን ንቃ። ይህን ስታደርግ፣ ወደ አእምሮህ ስትመለስ "ለመንግስተ ሰማያት" ትቀርባለህ። አብረን እናንብብ።

"ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ። አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።" (ማርቆስ 12:34)

ኢብኑ ሙነወር

@aaumsu
👍12
We often hear: "life is short, enjoy it." But often forget: "Eternity is long, prepare for it."

@MohammadamminKassaw
👍10🥰4👌2
Forwarded from Ibnu Ahmed


بسم الله الرحمن الرحيم

🌸እውቀትን ከመማር በፊት አደብን ተማር

ኢማሙ ማሊክ ረሂመሁሏህ ከቁረይሽ ለሆነ ወጣት እንዲህ አሉት:-

🔘የወንድሜ ልጅ ሆይ!አደብን ተማር።እውቀት ከመማርህ  ከመቅሰምህ በፊት  አሉት
الحلية ٦/٣٣٠

🔘አዎ አደብ ከሌለህ ትክክለኛና ጠቃሚ እውቀትን ማግኘት አትችልም።

🔘ከተማሪዎች ከመሻይኾች፣ከኡስታዞችህ  ጋ አደብ ከሌለህ እንዴት ጠቃሚ እውቀት መቅሰም ትችለላህ?

🔘አደብ  ከሌለህ  ከጓደኞች ጋር መኗኗር ይከብዳል ።

🔘አደብ  ከሌለህ  ከማህበረሰብም ጋር  መኗኗር ይከብዳል ።

🔘 አደብ  ከሌለህ እውቀትን የምታስቀምጥበት ቦታ ሰው አታገኝም ፡፡

ሰዎች መጀመሪያ የሚመለከቱት  አህላቅህን አደብህን ነው።

🔘ሰለፎች ያን ሁሉ እውቀት ያገኙት አደብ ስለነበራቸው ነው።

ለሸይኾቻቸው እንዴት እንደሚተናነሱ ታሪካቸውን ብናነብ የኛ ሁኔታ ግርም ይለን ነበር።

الله المستعان
አሏህ ይዘንልን።


Copied

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
👍82
«መልካምና ጥሩ ሐሳብ ያለው ሰው ከሰዎች ነውር የራሱ ነውር ያሳስበዋል። ልክ በሽተኛ ከሰዎች ይልቅ የራሱ በሽታ እንደሚያሳስበው።»
.
©ኢማም አሽ-ሻፊዒይ (ረህመቱላሂ ዐለይህ)

@aaumsu
🥰8👍5👌3
Don't risk Jennah for this world!

@aaumsu
🥰13👍6
"AF ዳቦ ቤት!" - አድራሻቸው ከየካቲት 12 ሆስፒታል ወደ 4ኪሎ በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ላይ ወይም ወደ አይነ-ስውራን ማህበር ቢሮ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኝ ሲሆን አብዱልከሪምና ፈይዱ በሚባሉ የ2ኛ አመት ተማሪዎች በሆኑ ወንድሞቻችን የተከፈተ ነው::

ገና እየጀመሩ ነውና ሄዳችሁ ከፍላችሁ በመቅመስ በመብላትና ለሌሎች በማስተዋወቅ አበረታቷቸው:: ቦታው ከጠፋባችሁ ከላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል አናግሯቸው::

የሚሰሩ እጆች ይባረኩ!
አላህ ትርፋማ ያድርጋቸው!!

"መብሩክ!" ብለናል!!

@aaumsu
👍14👏5
ሰበር ዜና!

በዛሬው እለት የአአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የምክክር ካውንስል(SHURA' COUNCIL) ባደረገው አስቸኳይ ምክክር  የህብረቱ ፕሬዚዳንት ሙሐመድአሚን ካሳው በሥራ መደራረብ ምክንያት: በራሱ ፈቃድ ከሀላፊነት እራሱን ማግለሉን ሰምቷል :: ይህም በ ሹራ አባላቱ  ተቀባይነት በማግኘቱ: በእርሱ ቦታ : የቀድሞ የፋይናንስ ሴክተር አሚር የነበረው: ወንድም አሚር አህመዲንን ፕሬዚዳንት በማድረግ ወደ ሀላፊነት አምጥቷል::

Breaking‼️‼️‼️
Today, in the urgent consultation of the AAU Muslim Students' Union SHURA' COUNCIL), it was reported that the President of the Union, his excellency Muhammad Amin Kasaw, has voluntarily resigned from the position due to the overlapping work environment. And this resignation of him was accepted by the members of the council.
Accordingly,  based on the succession principle of our Union, the former Amir of the financial sector, brother Amir Ahmedin, was brought into charge and nominated as The New President of AAMSU.

@aaumsu
😭16👍7🫡1😡1
A message from Amir Ahmedin ( The newly elected president of AAUMSU)

Bismillah-ir-Rahman-ir-Rahim!

Assalamu Alaikum Warahmatullahi Wabarakatuh,
My beloved brothers and sisters in Islam,
I am deeply honored and humbled to stand before you as the newly elected President of our prestigious Muslim Students Union at Addis Ababa University. This responsibility is not just a title but a sacred trust bestowed upon me by Allah and entrusted to all of us as a community.
Our union's mission is not merely about holding positions but about embodying the teachings of Islam and working together to achieve our university's goals and vision. It is a responsibility that touches my heart, knowing that each action we take reflects our commitment to our faith and community.
As we embark on this journey together, let us draw inspiration from the noble teachings of the Quran and the Sunnah of our beloved Prophet Muhammad (peace be upon him).
Allah says in the Quran:
                    وَقُلِ اعْمَلُوا فَسَيَرَى اللَّهُ عَمَلَكُمْ وَرَسُولُهُ وَالْمُؤْمِنُونَ (Surat At-Tawbah 9:105)
This verse, "And say, 'Do [as you will], for Allah will see your deeds, and [so, will] His Messenger and the believers,'" encourages us to take action with sincerity and righteousness. Our actions are not hidden from Allah; He sees and knows everything. This verse highlights the importance of accountability in our deeds, reminding us that our efforts and intentions are observed by Allah, His Messenger, and the believers.
Let us also reflect on the words of our beloved Prophet Muhammad (peace be upon him) who said:
"إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ بِتَوَاصُّلِهِمْ وَتَرَاحُمِهِمْ وَتَعَاطُفِهِمْ كَمَا الْجَسَدِ إِذَا اشْتَكَى مِنْهُ عُضْوٌ تَدَاعَى لَهُ سَائِرُ جَسَدِهِ بِالسَّهَرِ وَالْحُمَّىٰ" (Sahih Muslim)
"The believers, in their mutual kindness, compassion, and sympathy, are like one body; when any part of it suffers, the whole body responds with sleeplessness and fever." (Sahih Muslim)
This hadith emphasizes the concept of unity and empathy within the Muslim community. It reminds us that our strength lies in our solidarity and our ability to support and uplift one another in times of need.

Fellow students, our Jemeah has a rich history of academic excellence and contributions to society, especially within the Ethiopian Muslim community. We stand on the shoulders of giants—those who have come before us and made lasting impacts through their dedication, knowledge, and service.
Let us also recognize the present students who are actively engaged in making positive changes and contributions within our university and beyond. Each one of us has a role to play in continuing this legacy of excellence and service.
Together, let us commit ourselves to promoting academic excellence, fostering unity and brotherhood/sisterhood, and being ambassadors of Islam. Let us work tirelessly to contribute positively to our university Jemeah and society, guided by the principles of our faith and the values of our community.
I urge each one of you to actively participate, collaborate, and support our initiatives and programs. Let us harness the power of our collective efforts to make a meaningful and lasting impact, insha'Allah.

May Allah bless our endeavors, guide us on the right path, and make us a source of goodness for our university and community.
Jazakum Allahu Khairan. Wassalamu Alaikum Warahmatullahi Wabarakatuh.

@aaumsu
👍14🔥3
AAU - Muslim Students Union
A message from Amir Ahmedin ( The newly elected president of AAUMSU) Bismillah-ir-Rahman-ir-Rahim! Assalamu Alaikum Warahmatullahi Wabarakatuh, My beloved brothers and sisters in Islam, I am deeply honored and humbled to stand before you as the newly elected…
መልዕክት- ከአሚር አህመዲን (ከአዲሱ የአአዩሙተህ አሚር)

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!
የተወደዳችሁ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ:-

በመጀመሪያ የታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ተደርጌ በመመረጤ የተሰማኝን ክብር ለመግለፅ እወዳለሁ:: ይህ ሀላፊነት ማዕረግ ብቻ ሳይሆን ለእኔም ሆነ ለእናንተ እንደ ማህበረሰብ ከአምላካችን አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በኩል የተሰጠን ቅዱስ አደራ ነው:: የህብረታችን ዋና አላማ ስም መያዝ ብቻ ሳይሆን ራዕያችንንና ተልዕኳችንን ለማሳካት በዩኒቨርሲቲያችን ውስጥ ለሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ተገቢ የሆነውን አገልግሎት መስጠት ነው:: በዚህ ውስጥ የምንሰራቸው ስራዎች ሁሉ ለሀይማኖታችንና ለማህበረሰባችን የሚኖረንን ቀናዒነት እንድናንፀባርቅ ማድረጋቸው ልዩ የሆነ ስሜት ይሰጠኛል::

በመቀጠል መንገዳችንን ስንጀምር መንገዳችን የኢስላም ነውና መሰረታችንን ከቁርዓንና ከሐዲስ ማድረግ እንዳለብን ማሳሰብ እወዳለሁ:: አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በቁርዓኑ:- "በላቸውም ሥሩ አላህ በእርግጥ ስራችሁን ያያልና:: መልዕክተኛውና ምዕምናንም (እንደዚሁ ያያሉ)" ሲል ስራችንን በትክክል እንድንሰራ ያዛል:: ሁሉን ተመልካች አዋቂ ነውና ከእርሱ ምንም እንደማይደበቅ ያስጠነቅቃል:: በዚህ ውስጥ በስራችን ውስጥ አላህ ዘንድም ሆነ አማኞች ዘንድ ተጠያቂነት እንደሚኖር ልብ እንድንል ያደርጋል:: የእኛ ዘላለማዊ አርዓያ የሆኑት ነብይም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም):- "አማኞች እርስ በዕርስ ባላቸው መልካምነት መተዛዘንና አንዱ የሌላውን ሀዘን በመካፈል ልክ እንደ አንድ አካል ናቸው:: ከእርሱ አንዱ ክፍል ሲታመም ሌላው እንቅልፍ በማጣትና በትኩሳት እንደሚጣራው::" ሲሉ ሙስሊሞች እርስ በዕርስ በመተዛዘንና አንድ በመሆን ምን ያክል መጓዝ እንዳለባቸው ያሳስባሉ:: ጥንካሬያችን የሚታየው አንዱ ለሌላው ባስፈለገው ሰዓት በሚያሳየው ድጋፍ እንደሆነ ያመላክታሉ::

ወንድም እህቶቼ:- ጀመዓችን ለሙስሊሙ ማህበረሰብም ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባደረገው አበርክቶ ትልቅ የሆነ ታሪክ እንዳለው ይታወቃል:: እኛም በትላንት አባቶቻችን ጠንካራ ትከሻ ላይ ሆነን ታሪክ የማይሽረው መልካም አሻራ አሳርፈን ማለፍ አለብን:: በዚህ ውስጥ አንዱ ለሌላው እውቅና በመስጠት ሊያበረክተው የሚችለው አስተዋፅዖ እንዳለ ልብ ሊባል ይገባል:: በህብረት ክንዳችንን በአንድ ላይ አድርገን በትምህርት ዘርፉም ሆነ ሀይማኖታችንን በመማርና በማስተማር ውስጥ የኢስላም አምባሳደር እንደመሆናችን ጥንካሬያችንን ልናሳይ ግድ ይለናል:: ሁላችሁም ተሳተፉ:: እንተባበር:: እንተጋገዝ:: ፕሮግራሞቻችንን እውን እናድርግ:: የህብረታችንን ፍሬ ዘመን በማይሽራቸው ተፅዕኖዎች ውስጥ እንመልከት::

አላህ በጥረቶቻችን ላይ በረካን ይጨምር:: ወደ ቀጥተኛው መንገድ ሁሌም ይምራን:: ለመልካም ነገር ምንጭ ያድርገን:: ጀዛኩሙላሁ ኸይረን!!

ወሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!!

@aaumsu
9🔥2👍1
AAU - Muslim Students Union
ሰበር ዜና! በዛሬው እለት የአአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የምክክር ካውንስል(SHURA' COUNCIL) ባደረገው አስቸኳይ ምክክር  የህብረቱ ፕሬዚዳንት ሙሐመድአሚን ካሳው በሥራ መደራረብ ምክንያት: በራሱ ፈቃድ ከሀላፊነት እራሱን ማግለሉን ሰምቷል :: ይህም በ ሹራ አባላቱ  ተቀባይነት በማግኘቱ: በእርሱ ቦታ : የቀድሞ የፋይናንስ ሴክተር አሚር የነበረው: ወንድም አሚር አህመዲንን ፕሬዚዳንት በማድረግ…
መልዕክት - ከቀድሞው የአአዩሙተህ ፕሬዚዳንት ሙሐመድአሚን ካሳው!

መልዕክቴን በዚህ ትልቅ ታሪክና አሻራ ባለው ህብረት ውስጥ ለ3 የትምህርት አመታት በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ እንዳገለግል ፈቃዱ በሆነው አምላካችን አላህ ስም እጀምራለሁ:: ከጀመዓ ወዳጆቼ ጋር ይህንን ረጅም ጊዜ እንዳሳልፍ በማድረግ ላከበረኝ አምላካችን አላህ በክብሩ ልክ ምስጋና ይድረስ:: "የአላህ እጅ ከጀመዓ ጋር ነው::" የሚልን አስተምህሮ በማስተማር በወንድም እህትማማችነት መንፈስ እንድንሰባሰብ መሰረቱን በጣሉልን አርዓያችን መሪያችንና ነብያችን ላይ የአላህ ሰላምና ውዳሴ ይስፈን::

ጀመዓ በተለይም የዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ በብዙ ትግልና ውጣ ውረድ ውስጥ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ ቅርፁን የሚሰራ መሆኑ ይታወቃል:: በዚህም ሂደት ውስጥ እንደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ባሉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጉልህ ሚና ኖሮት ዘመናትን የተሻገረውን የአአዩሙተህ በአላህ ችሮታ ለአመታት በመሪነት ቦታ ላይ ሆኜ አገልግያለሁ:: መሪነት ትልቅ ሀላፊነት ከመሆኑም ባሻገር በብዙ ስራዎች ውስጥ የሚያልፍና ከብዙ አካላትን ሸክም ይዞ ወደፊት አብሮ ለመራመድ የሚደረግ ትንቅንቅ ነው:: በዚህ ሂደት ውስጥ የተሰሩ ብዙ ስራዎች ቢኖሩም ያልተሰሩት እንደሚልቁ እሙን ነው:: የተደፈኑ ቀዳዳዎች ቢኖሩም ያልተደፈኑ ብሎም የተከፈቱ ክፍተቶች መኖራቸው አይቀሬ ነው:: በዚያ ሂደት ውስጥ በሁሉም ውስጥ የሁላችንም ድርሻ መኖሩ አይቀሬ ነውና በስራዎች ውስጥ በእኔ በኩል ለነበሩ ክፍተቶችና ጉድለቶች ሁላችሁንም አውፍታ እጠይቃለሁ:: እናንተም ያጎደላችሁት ካለ አውፍ ብያለሁ::

ከዚያ በመቀጠል አሁንም ቢሆን ጀመዓችን እንደ ሀገር ለሙስሊሙ ማህበረሰብም ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ አዎንታዊ ለውጦችን በማምጣት ረገድ በሚያደርገው እንቅስቃሴ በወንድሜ አሚር አህመዲን መሪነት በሚሰራቸው ተግባራት ላይ በንቃት ትሳተፉ ዘንድ ወንድማዊ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ:: ትላንት አባቶቻችን በትልቅ መስዋዕትነት ያስረከቡንን የዛሬ እውነታ ይበልጥ አሻሽለን ለነገው ትውልድ የማስረከብ ሀላፊነት አለብንና የትም ሆንን የት ለታሪካዊ ተልዕኳችን የሚጠበቅብንን የማድረግ ግዴታ አለብን::

መልካም የስራ ጊዜን ለወንድሜ አሚር አህመዲን (አሚሬ) ተመኘሁ:: አላህ ያግዝህ ያ አኺ! የተሻለ ያማረ ጊዜን ለጀመዓችን ለመላው የኢትዮጵያ ሙስሊምም ሆነ የአለም ሙስሊም እንዲያመጣ ዱዓዬ ነው::

ወሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!!

@aaumsu
12👏3👍2😭1