AAU - Muslim Students Union
6.48K subscribers
2.76K photos
151 videos
51 files
767 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
ነገ ሐሙስ ነው!

የቻላችሁ ፁሙ!

ፆም ጋሻ ከመሆኑም ባሻገር በጀነት ውስጥ ረያን የባለቤቶቹ መግቢያ በር መሆኑ ሽልማቱን ያልቀዋል::

@aaumsu
👍8
ዛሬ የላብ-አደሮች ቀን ነው!

ግን ከእኛ አይደለም:: አናከብረውምም:: ነገርግን ወደሗላ ተመልሼ ከዚህ ቀን ጋር ተያይዞ የተፈጠረን ክስተት ላጋራችሁ:-

ከ2 አመታት በፊት ዩኒቨርሲቲያችን AAU ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ከዒድ ቀን ጋር በተመሳሳይ ቀን ጥሪ አቀረበ:: ይህንን በመቃወም የአአዩሙተህ አሚር አህመዲን : ሱልጣን ሙሐመድንና ሙሐመድአሚንን ተወካይ አድርጎ ላከ:: ጉዳዩን በመጀመሪያ ወደ ሬጅስትራር አቀረቡ:: በሰዓቱ የተቀበለቻቸው ሴት "ምን ችግር አለው? ካለንደሩኮ ነው:: እዚህ ሲደርሱ ያከብሩታል::" አለች:: እነሱም "ካለንደሩ ከሰማይ የወረደ አይደለም:: ጥያቄያችን እንዴት ካላንደር እያለ ዩኒቨርሲቲው ከሙስሊሞች በዓል ጋር በተመሳሳይ ቀን ያደርጋል ነው:: ወይስ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች የሉም?" አሏት:: ከዚያ በፊት ከተሐጁድና ከጎንደር ሙስሊሞችጋ ተያይዞ ተቃውሞወችና ሰልፎች ተደርገው ስለነበር ደንገጥ ብላ "ልትቃወሙ ነው እንዴ?" አለች:: "እሱን እናያለን!" ብለዋት ወጡ:: በአንድ ሰዓት ውስጥ ጥያቄያችንን ተቀብለው በቲክቫህ በኩል ሙስሊም ተማሪዎች በዓሉን ቤተሰብጋ አክብረው ከረቡዕ እስከ ጁምዓ መግባት እንደሚችሉ አስነገረ (ዒዱ ሰኞ ነበር:: ግቢውም ግቡ ያለው ሰኞና ማክሰኞ ነበር)::

ነገርግን ሰኞ ቀን ዒድ ቢሆንም ሰራተኞች ስራ ገብተው የመጡ የሌላ እምነት ተከታዮችን ከመናሃሪያ ተቀበሉ:: ሐሙስ ሲደርስ ደግሞ የላባደሮች ቀን ነውና ስራ አንገባም የሚል አምባጓሮ ተፈጠረ:: አሁንም "እንዴት በዒዱ ሰርተው የላባደሮች ቀን በሚል ሙስሊሞችን ማስተናገድ ያቆማሉ?" የሚል ጥያቄ ተነሳ:: ከብዙ ጭቅጭቅ ቡሃላም በአላህ ፈቃድ ተመለሰ:: አልሃምዱሊላህ!!

@aaumsu
👍18
አቡ ሁረይራ (رضي الله عنه) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል:-

"የዲናር፣የዲርሀምና የውብ አልባሳት ባሪያ ከሰረ። ሲያገኝ ይደሰታል። ሲያጣ ይከፋዋል።"።  (ቡኻሪ )

@MohammadamminKassaw
👍9
"Success is not about the competition, but the collaboration." - Unknown

@aaumsu
👌6👍2



"" ወንጀል መዘዙ ብዙ ነው። በወንጀላችን ምክንያት ሳናውቅ ብዙ እየተቀጣን ነው። ምናልባት እኛ በግልፅ ስላላየነው ምንም ላይመስለን ይችላል። ግን ወላሂ በወንጀል በወንጀላችን ምክንያት የዒባዳን ጥፍጥና አጠትናል፣ ከጌታችን ርቀናል፣ ቁርዓን ከብዶናል፣ የተማርነውን እውቀት በረካውን ተነስተናል፣ ትልቁና አስፈሪው ደግሞ አኼራችንን እያበላሸን ነው።

በወንጀል ሲሳይ ይጠባል፣ ህይወት ትጠባለች፣ ቀልብ ይደርቃል፣ ለአላህ ቁጣ ሰበብ ይሆናል፣ ልባችን ስክነት እርጋታ ይርቀዋል፣ ነገሮች ይወሳሰባሉ፣ ጉዳዮቻችን መፈታት ይከብዳቸዋል።

ወንጀል ሙሉ ህይወታችንን ያበላሻልና ከወንጀል እንራቅ። ለሰራነው አላህን ምህረት እንጠይቅ!!!!

والله اعلم

👍12
🥀 Daily Reminder 105🥀

وَإِذَا فَعَلُواْ فَٰحِشَةٗ قَالُواْ وَجَدۡنَا عَلَيۡهَآ ءَابَآءَنَا وَٱللَّهُ أَمَرَنَا بِهَاۗ قُلۡ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَأۡمُرُ بِٱلۡفَحۡشَآءِۖ أَتَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ(28)

"መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን አላህም በእርሷ አዞናል ይላሉ፡፡ «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን??» በላቸው!!"

Surah Al-A'raf; 28

@aaumsu
👍7
የአላህ timing እጅጉኑ ይገርመኛል። በሁሉም የህይወት መልክህ ውስጥ የሚያስፈልግህን በመስጠት ምርጥ ሆኖ ታገኘዋለህ። በርካታ የህይወት ጥያቄዎችህን የሚፈታው እንደአስሓቡል ካህፍ  በአንዲት ሌሊት የመኝታ ሰዓትህ ሊሆንም ይችላል።  ጌታህ ከሰመጥክበት የሀዘን ዓለም ሊያወጣህ የማይፈልግ "ታጋሾችን አበስራቸው" የሚል ቃልአባይ ይመስልሃል?  መንገዱ መሀል ላይማ… እንደዩሱፍ ለባርነት መሸጥ አለ፣ እንደ የዕቁብ የማያባራ ለቅሶ አለ፣ እንደ  ኢብራሂም ግራ መጋባት አለ፣ እንደ ነብይህ ሙሀመድ መሰደድም አለ…  አምላካዊ ጥበቡን የምትረዳው  ነገሮች ዘግይተው ዘግይተው…  ላንተ ትክክለኛውን ሰዓት ጠብቀው ሲመጡ ስታይ ነው። እርሱ…  እጅጉኑ ጠቢብ ነው።

@aaumsu
👍191
"እያንዳንዱ ፋሽስት ሀገር ይወድቃል!" - የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

   በሀገረ አሜሪካ ስለ ፍልስጤም ብቻ ድምፅ በመሆናቸው የታሰሩ ተማሪዎች ቁጥር 1700ን እንዳለፈ ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል:: ዲሞክራሲን መለያዋ አድርጋ ስለ ዲሞክራሲ ሀገራትን ያፈራረሰችው ፋሽስታዊቷ አሜሪካ ትክክለኛ መልኳ ለሚያይ ሁሉ እንደ ቀትር ፀሐይ ወገግ ብሎ እየታዬ ነው:: ፕሬዚዳንቷን በአደባባይ መዝለፍና መቃወም መብት እንደሆነ በFreedom of speech አልፋቤቷ መጀመሪያ ላይ ያስቆጠረችን ሀገር ስለ ፍልስጤማውያን መጮህን ለእስር እንደሚዳርግ በተግባር እያሳያች ነው::

   ቆዳቸው የእባብ እንደነበር ታይቷል:: ምላሳቸው እንደ እባብ እንደሆነ ተገልፇል:: ነገርግን አይችሉም:: እውነትን ማሸነፍ አይችሉም:: ፊርዓውን ነቢ ሙሳን የለመነበት ታሪክ ሲደገም እናያለን:: አምባገነኖች ሲንኮታኮቱ እናያለን:: ፍልስጤም ነፃ ስትሆን እናያለን::

አሁንም FREE FREE PALESTINE እንላለን!
From the river to the sea Palestine will be free!!

@MohammadamminKassaw
🥰13👍3👏3🔥2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Civil defense teams reached him while he was performing the Fajr (dawn) prayer under the rubble of his house after it was bombed by the occupation.

Where are you O those who neglect the Fajr prayer whilst being safe in your homes!
😭161
Arrogance, pride, and self-amazement are the negative traits that destroys a seeker of knowledge.

Keep your feet on the ground.

@MohammadamminKassaw
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ በሀገረ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ነው:: ተማሪዎች የአሜሪካና እስራኤልን ጄኖሳይድ በመቃወም የሰሩትን ድንኳን የአሜሪካ ፖሊሶች ለማፈራረስ ሲሞክሩና ተማሪዎችን ሲያስሩ ያሳያል::

አላህ ውድቀቷን እስከ አወዳደቋ ያሳዬን!

@aaumsu
😭10🥰4👍2
The 6 Kilo Jemea Football Cup heated up today with a thrilling showdown between Nejashi and Rayyan!

After a setback in their previous match, Nejashi roared back with an impressive 6-3 triumph over Rayyan. Nejashi's goal scorers were on fire, with Osman Ahmed leading the charge with two brilliant goals. Haile Aseffa, Seyfedin Abdulmejid, Naik Girma, and Mujib Husen also joined the scoring frenzy, each contributing a goal to secure Nejashi's victory.

Despite Rayyan's valiant efforts, including goals from Said Abdu, Adil Muhammad, and Mubarak Hashim, they couldn't contain the relentless attack from Nejashi.

With the tournament now in full swing, every match brings new excitement and surprises. Stay tuned for more thrilling action in the 6 Kilo Jemea Football Cup!

@aau6kilojemea
@aau6kilojemea
👍6
ጁምዓ ነው!

📌 ከህፍን አንብቡ !
📌 በረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ አብዝታችሁ ሰለዋት አውርዱ !
📌 ንፅህናችሁን ጠብቁ !
📌 በሁሉም ቦታ ያሉ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችሁን በዱዓችሁ አስታውሱ !

መልካም ጁምዓ !

@aaumsu
👍14
"Allah is enough for me."

(Qur'an 9: 129)

@aaumsu
👍115
አቡ ሁረይራ (رضي الله عنه) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል።

"ሰውዬው በጓደኛው(በወዳጁ)ዲን ላይ ነው፡ እናም ከእናንተ አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት(ያስብበት/ያጢነው)።"

(አቡ ዳዉድ)

@aaumsu
👍9
'Niqab' means - to hide your precious beauty, from the gaze of the inappropriate person, for the appropriate person.

@aaumsu
9👍2
"በል 'እርሱ አላህ አንድ ነው:: አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው:: አልወለደም : አልተወለደምም:: ለእርሱም አንድም ቢጤ የለውም::' " - ሱረቱል ኢኽላስ 1-4

@aaumsu
👍12
"And [for] their saying, "Indeed, we have killed the Messiah, Jesus the son of Mary, the messenger of Allāh." And they did not kill him, nor did they crucify him; but [another] was made to resemble him to them. And indeed, those who differ over it are in doubt about it. They have no knowledge of it except the following of assumption. And they did not kill him, for certain." - 4:157

@aaumsu
👍8
وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ

አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡

@aaumsu
👍13
🥀 Daily Reminder 106🥀

وَكُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ وَلَا تُسۡرِفُوٓاْۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡرِفِينَ(31)

"ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና!!"

Surah Al-A'raf; 31

@aaumsu
🥰6👍2
" ድንኳኖቹን በቶሎ አስወግዷቸው:: አክራሪዎቹን ድል አድርጉ:: ካምፓሶቻችንን መማር ለሚፈልጉ ጤነኛ ተማሪዎች ዳግም ምቹ አድርጉ:: እነዚህ ዘገምተኛ እብዶች ናቸው::" - ዶናልድ ትራምፕ

   በጋዛ ላይ የተከፈተው ፍጅት 210ኛ ቀኑን አስቆጥሯል:: እስካሁን 35ሺህ ጋዛውያን መስዋዕት ሲሆኑ  78ሺህ ቁስለኛ ሆነዋል:: ሬሳቸው ከፍርስራሽ ስር ሆኖ ለመቀበር ያልታደሉ ሺዎች እንዳሉም ተመላክቷል::

  አምባገነኖች በእብሪት ተሞልተው ጭካኔውን ሲፈፅሙ ማዬት የተሳናቸው የምዕራቡ አለም ተማሪዎች ሁለ ነገራቸውን መስዋዕት አድርገው በካምፓሶች ዙሪያ ተቃውሞ ከጀመሩ ቀናቶች ተቆጥረዋል:: እስካሁን ከ2200 በላይ ተማሪዎች የታሰሩ ሲሆን የተለያየ አይነት እንግልትም እየደረሰባቸው ነው::

  ግን አሁንም ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው:: ከተማሪዎች አንደበት የወጣው የነፃነት ድምፅ አያስተኛ ያላቸው የዋይት ሀውስ ሰዎች ፀጥታውን ሰብረዋል:: የአሁኑ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን "ሀገራችን አምባገነናዊ ስላልሆነች ድምፆችን አታፍንም:: ተማሪዎች የመናገር መብት ቢኖራቸውም ለአመፅ ማነሳሳት አይችሉም:: ይህ ከህገ-መንግስታችን ውጭ ነው:: የእነሱ ተቃውሞ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ያላትን ፖሊስ አያስቀይርም::" ሲሉ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ተማሪዎች "ዘገምተኛ እብዶች!" ብለው በመዝለፍና ፖሊሶች እየወሰዱት ያሉትን የሀይል እርምጃ በማበረታታት ዳግም ጠበቅ ያለ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል::

  የዲሞክራሲ ጭምብል ሲገለጥ የሚታዬው እብሪትና አምባገነንነት ግልፅ ሆኗል:: አላህ ውርደታቸውን ያቅርብ:: የፍልስጤማውያንን ድል ያቅርብ:: የዳውድ ጌታ የዳውድን ጥበብ ለፍልስጤማውያን ሰጥቶ በጎልያድ ላይ የተቀዳጀውን ድል በምዕራባውያን ላይ ይስጣቸው::

   የተማሪዎቹ መፈክር የእኛም ነው:: የፍልስጤማውያን ነፃነት የእኛም ነው::

  UP UP WITH LIBERATION!
  DOWN DOWN WITH OCCUPATION!
  DOWN DOWN WITH OPPRESSION!
 
FREE FREE PALESTINE!
FROM THE RIVER TO THE SEA PALESTINE WILL BE FREE!


@MohammadamminKassaw
👍20