AAU - Muslim Students Union
6.49K subscribers
2.76K photos
151 videos
51 files
767 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ስለ ፍልስጤማውያን ሲባል ተቃውሞዎች ተቀጣጥለዋል :: ተማሪዎች ዶርም በቃን ብለው ድንኳን ጥለዋል :: የአሜሪካ ፖሊሶችም በተቃዋሚ ተማሪዎች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ነው :: የዲሞክራሲ መምህር ነኝ የምትለዋ ሀገር ትክክለኛ ፊት እየታዬ ነው ::

ውርደትን ለአሜሪካ የግፍ አገዛዝ እንመኛለን :: ከMIT እስከ New York ዩኒቨርሲቲ ላሉ የነፃነት ቀንዲሎች ብርታትና ድልን እንዲያጎናፅፍ ዱዓ እናደርጋለን :: የፍልስጤምንም ነፃነት ከትናንሽ ወንዞች እስከ ትላልቅ ባህሮች እንዲያመጣ እንተጋለን ::

Palestine is within our heart.
Free Free Palestine.
From the river to the sea Palestine will be free!

@aaumsu
👍222
አብደላህ ኢብኑ ሺኺር (رضي الله عنه) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል:-

   የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) ዘንድ መጣሁ። ሰላት ውስጥ ነበሩ።ከለቅሷቸው የተነሳ እንደተጣደ ድስት የመንፈቅፈቅ ድምፅ ከሆዳቸው ይሰማል።
(አቡዳውድና ቲርሚዚይ)

@aaumsu
👍5😭5
"የጋዛ ልጆች : የፍልስጤም ህዝቦች አጋርነታችሁ ይሰማቸው ዘንድ መሬትን አንቀጥቅጧት ::" - ሙምያ አቡ-ጀማል (ጥቁሩ አብዮተኛ በኒውዮርክ የተማሪዎች ተቃውሞ ላይ የተናገረው)

በሀገረ-አሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞው ተቀጣጥሎ እንደቀጠለ ነው :: ከሎስአንጀለስ እስከ ኒውዮርክ : ከኦስቲን እስከ ቦስተን: ከቺካጎ እስከ አትላንታ ብሎም እስከ ነጩ ቤተ-መንግስት መቀመጫ ዲሲ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አሜሪካና እስራኤል የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ሆነው በፍልስጤማውያን ላይ እየፈፀሙት ያሉትን ጄኖሳይድ እየተቃወሙ ነው :: የዲሞክራሲ አባት የሆነችው አሜሪካ ፖሊሶችም የተማሪዎችን ድምፅ ለማፈን የቻሉትን እየሞከሩ ነው :: ግና እጅን ቢያስሩ ልብን ማሰር አይችሉም :: እግሩን ቢያስሩ ህሊናን ማሰር አይችሉም :: ስለ ነፃነት የሚተነፈስን አየር የግፍ ዱላ ሊያቆመው አይችልም ::

Shake the earth so that the people of Gaza, the people of Palestine, feel your solidarity with them.

We never stop talking about the freedom of Palestine and it's people.

Free free Palestine.
From the river to the sea Palestine will be free!

@MohammadamminKassaw
👍20
እውነትን ውደድ
ግን ለስህተት ይቅርታ በማድረግ ትምህርትን ውሰድ!


@aaumsu
👍13
"But perhaps you hate a thing and it is good for you; and perhaps you love a thing and it is bad for you. And Allah knows, while you know not." (Quran 2:216)

@aaumsu
👍6👌2
ከዱንያ የምትጠብቀው ነገር አለህን?

📌 ጨረቃን መሳዩ ዩሱፍ (ዐለይሂ ሰላም) በርካሽ ዋጋ ከተሸጠባት ዱንያ የምትጠብቀው ነገር አለህን?

📌  የነብያት አባት የሆነው ኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም) ወደ እሳት ከተወረወረባት ዱንያ የምትጠብቀው ነገር አለህን?

📌 የሙሳን (ዐለይሂ ሰላም) ተዓምር ድግምት ብለው ከጠሩባት ዱንያ የምትጠብቀው ነገር አለህን?

📌 ሀቢቢ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በድንጋይ ከተደበደቡባት : እብድ ጠንቋይ ከተባሉባት ዱንያ የምትጠብቀው ነገር አለህን ?

🔺ትከፍለኛለች ብለህ የምትጠብቀው ጥሩ ነገር ካለ ተሳስተሃል :: አኼራን ከፊትህ አስቀምጥ :: የዚያኔ ዱንያ ለጥቂት ዝቅ ልታደርግህ ብትሞክርም አኼራ ለዘለዓለሙ ከፍ ያደርግሃል ::

  
@aaumsu
👍9👌61
قال العلامة ابن عثيمين رحمه اللَّه

« الشرع لا يُقر الاختلاط بين الرجال
والنساء حتّى في مقام التعليم ».

‏ [ شرح صحيح البخاري ]

‏قال العلامة ابن عثيمين رحمه الله

‏ « المرأة⁩ إذا ذهب عنها الحياء، صارت كأنها رجل أو أردىٰ من الرجل، وذهاب الحياء له أسباب، منها : الاختلاط، ومنها : أنْ ترتَدي المرأة من صغرها ألبسَة بعيدة عن الحشمة وعن الحياء فتألَف هذا الشيء ».

‏ [ لقاء الباب المفتوح]
የለፋ ብቻ ያገኛል :: በማጣት ውስጥ ትልቁ ልፋት ታግሶ መቆዬት ነው :: ነቢ አዩብ (ዐለይሂ ሰላም) ከበሽታቸው ያገግሙ ዘንድ : የጠፋው ሀብት ይመለስ ዘንድ : የራቃቸው ዘመድ አዝማድ ይቀርባቸው ዘንድ እንደ አጠቃላይ ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ይሞላ ዘንድ 18 አመታትን ጠብቀዋል :: ነቢ ዩሱፍ ከአባት ወንድም ናፍቆት ይላቀቁ ዘንድ : ከባርነትና ከእስር ነፃ ይወጡ ዘንድ እንዲሁም ከተቀጠፈባቸው የሴራ ጉንጉን ተላቀው ንጉስ ይሆኑ ዘንድ አስርት አመታትን ጠብቀዋል :: ወደ የዕቁብም (ዐለይሂ ሰላም) የዩሱፍ ሽታ ይመለስ ዘንድ ያንን ያክል ጊዜ መጠበቁ ግዴታ ነበር :: ነቢ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ህዝባቸውን ከፊርዓውን የባርነት ቀንበር ያላቅቁ ዘንድ 40 አመታትን መታገስ ግዴታ ሆኖባቸው ነበር :: የእኔም ነብይ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፈትሁ መካን ይቀዳጁ ዘንድ በመጀመሪያ በመካ 13 የግፍ አመታትን በትዕግስት ማሳለፍ ነበረባቸው :: ከዚያም በመዲና ናፍቆትና ትግልን የቀላቀለ ትዕግስት ግዴታ ነበር ::
  
  ሁላቸውም የአላህ ነብያት ናቸው:: ሁላቸውም የሰው ልጆች ዘላለማዊ አርዓያዎች ናቸው:: አላህ ዝም አላላቸውም:: ለጥያቄያቸው መልስ ሰጠ:: የተሰበሩትን ጠገነ:: ያጡትን ሰጠ:: የናፈቁትን አገናኘ:: የጎደለውን ሞላ:: ከትዕግስት ቡሃላ ያለውን ጣፋጭ ፍሬ ለሁላቸውም ለገሰ:: የአዩብ : የሙሳ : የዩሱፍ : የየዕቁብና የሀቢቢ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጌታም የአንተ ጌታ ነው :: "እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ!" ብሎ ለጠየቀው ነቢ ኑሕ ሰማይና መሬትን የገለባበጠው ጌታ የአንተም ጌታ እንደሆነ አስታውስ:: ከራበህ ጠይቀው:: ካመመህ ጠይቀው:: ከጨነቀህ ጠይቀው:: ከተሰበርክ ጠይቀው:: ከወደክ ጠይቀው:: ግን ከትዕግስት ጋር ይሁን::

@aaumsu
9👍2🔥1🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሀገረ ካናዳ የሚገኘው McGill University ተማሪዎችም ስለ ፍልስጤማውያን ነፃነት በአሜሪካና አውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎች እየተቀጣጠለ ያለውን ተቃውሞ ተቀላቅለዋል:: "ነፃነት ለፍልስጤም!" የሚለውን ቃል በአንድነት እያስተጋቡት ነው::

የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው !!

@aaumsu
👍20
🥀 Daily Reminder 101🥀

إِن تَجۡتَنِبُواْ كَبَآئِرَ مَا تُنۡهَوۡنَ عَنۡهُ نُكَفِّرۡ عَنكُمۡ سَيِّـَٔاتِكُمۡ وَنُدۡخِلۡكُم مُّدۡخَلٗا كَرِيمٗا(31)

"ከእርሱ ከተከለከላችሁት ታላላቆቹን (ኀጢአቶች) ብትርቁ (ትናንሾቹን) ኀጢአቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን፡፡ የተከበረንም ስፍራ (ገነትን) እናገባችኋለን!!"

Surah Al-Nisa'; 31

@aaumsu
👍6
ታላቁ ዑመር(ረድየሏሁ አንሁ) የ ስምንት ክፍለ ሀገራት አሚር ስለአጥሚት አሰራር ሲያስተምሩ!

ሀዝም ኢብን ሂሻም ከአባቴ ሰምቸለሁ ብለው እንዳስተላለፉልን  "አንዴ ዑመር የሆነ ጉዞ ላይ ሳሉ አንድ አጥሚት የምትሰራ ሴትን ተመለከቱ። አሰራሯ አልጣማቸውም ነበርና ማስተካከያ ሊሰጧት ቀረቡ። እናም ምክራቸውን ሲጀምሩ፡ በመጀመርያ ዉሀው እስኪፈላ ምንም ነገር እንዳትጨምር በመንገር ሀሳባቸውን ጀመሩ፤ ከዚያም የዱቄት አጨማመሯ ጥቂት ጥቂት እየሆነ ሳታቋርጥ እንድታማስል ምክር ለግሰዋት አለፉ። ሴትዮዋም በሰማችው የወንድ ምክር ሳትደናገጥ ተገረመች።"

የዛኔ ዑምር እና ግዛታቸው ማለት በሀያልነት እንደ አሁኗ አሜሪካ እንደ ጆ ባይደን ማለት ነው። ትዝብቱን ለናንተ ትቸዋለሁ።

@aaumsu
👍11👌1
🎉 The 6 Kilo Jemea Football Cup kicked off today after Fajr prayer, setting the stage for an exhilarating display of football prowess!

In a thrilling display of skill and determination, Palestine FC emerged victorious with a stunning 6 - 3 win over Nejashi. The goal scorers for Palestine FC were Abdulahi Hassen 2x, Muhammad Kamal 2x, Abdurezak Usman 1x, and Muhammad Siyad 1x. On the opposing side, Nejashi showed their grit with goals from Osman Ahmed, Haile Aseffa, and Seyfedin.

Before the opening match kicked off, the tournament was blessed with a beautiful Qur'an recitation by brother Abdurehim Amin, setting a tone of tranquility and spirituality. Moreover, the significance of the competition was highlighted by the heartfelt speeches delivered by General Amir of the 6 Kilo Jemea, Ismael Abduro, and organizing committee member, brother Mu'min, emphasizing unity and brotherhood as the main purpose behind the tournament.

@aau6kilojemea
@aau6kilojemea
5👍3
"ተቃውሞውን ቀጥሉ :: ተቃውሞውን ቀጥሉ :: መቃወማችንን ከቀጠልን ጥፋታቸውን ያምናሉ::" - (በ1968 በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳለች የቬትናምን ወረራ የተቃወመች እናት ከ56 አመት ቡሃላ በተመሳሳይ ቦታ ስለ ፍልስጤም ያስተጋባችው)

ነፃነትን በልባቸው የቀረፁ ትውልዶች ምንም ሳይገዳቸው በየዩኒቨርሲቲዎች ፍልስጤም የሚለውን ቃል እያስተጋቡ ነው :: ከተማሪ እስከ አስተዳደር ሰራተኛ : ከሚስተር እስከ ፕሮፌሰር ሁሉም ተቃውሞውን ተቀላቅሏል :: ፖሊስ በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የነበሩ ፕሮፌሰርን ለምን ተቃዋሚዎችን ቀረፃችሁ በማለት ሲያንገላታ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚድያ መነጋገሪያ ሆኗል :: በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን ተማሪዎች ተመሳሳይ ተቃውሞ ካደረጉ የዲሲፕሊን እርምጃ እንደሚወስድ ቢገልፅም ካሳወቀ 1 ሰዓት ሳይሞላው ተቃውሞው ተቀጣጥሎ ቀጥሏል :: ሌሎች የአውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎችም "Free Palestine!" የሚልን የነፃነት ሀረግ ጧት ማታ እየሰሙት ነው ::

አሁንም FREE PALESTINE!
From the river to the sea Palestine will be free!

@aaumsu
🔥104👍1
ዝም በል !
  በቁጣ ሰዓት ዝም በል:: እውነታ ከሌለህ ዝም በል:: ቃላትህ ሌሎችን የሚሰብር ከሆነ ዝም በል:: ማዳመጥ ባለብህ ሰዓት ዝም በል:: ከተናገርክ ቡሃላ ሊፀፅትህ እንደሚችል ካሰብክ ዝም በል:: ሰዎች አዟዙረው ሊረዱትና ከመጠን በላይ ሊዟዟርባቸው እንደሚችል ካሰብክ ዝም በል:: ጉዳዩ የማይመለከትህ ከሆነ ዝም በል:: ከአፍህ የሚወጣው ውሸት ሊሆን እንደሚችል ካሰብክ ዝም በል:: የምላስህ ጫፍ የሌሎችን ክብር ሊነካ እንደሚችል ካሰብክ ዝም በል:: ንግግርህ ጓደኝነትን ሊያፈርስ እንደሚችል ካሰብክ ዝም በል:: እንደ አህያ ካልጮህክ መናገር የማትችል ከሆነ ዝም በል:: ቃላቶችህ የወዳጆችህን ስስ ጎን የሚያንፀባርቁ ከሆነ ዝም በል:: ሁለት ጊዜ የተናገርከው ነገር ከሆነ ዝም በል:: በወሬ ፋንታ ስራ ካለህ ዝም በል:: ዝምታ በሚበልጥበት ቦታ ሁሉ ዝም በል::

@MohammadamminKassaw
👍13🫡4
Forwarded from AAU MEREJA
Found ID
U can take it from FBE Librarian's
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
A Muslim student among the demonstrators at American universities was arrested, so he performed prayer while handcuffed.

@aaumsu
🥰16👍1
ማስጠንቀቂያ

ቴሌግራም ላይ ከማንኛውም ሰው በ cutt.ly or bit.ly የሚጀምር  ማንኛውም ሊንክ ተልኮላችሁ ስታገኙ እንዳትከፍቱት። ምክንያቱም ከቅርብ ግዜ ወዲህ የመጣ የሌላ ሰውን አካውንት ሀክ የሚያደርጉበት ዘዴ ነውና ተጠንቀቁ! የላኩላችሁ ሰዎች የናንተ የቅርብ ሰው ቢሆኑም እንዳትከፍቱት እነሱም ቢሆኑም ለምን እንደላኩት፣ መቼ እንደላኩት አያውቁትም።
ማንኛውንም አይነት ሊንክ ሳታጣሩ እንዳትነኩ!

በተጨማሪም ከሀከሮች አካውንታችሁን ለማዳን በምታስታውሱት Password Two-Step Verification On አድርጉ!

ምናልባት ባለመዋወቅ ከፍታችሁት ከሆነ ወደቴሌግራማችሁ Setting>>Devices በመሄድ terminate አድርጉት

@aaumsu
🫡7👍3
Forwarded from Happiness (سعادة)
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🖐🖐

🗣🗣 የማይቀርበት ሳምንታዊ የዳዕዋ ፕሮግራም

👉👉 በጀመዓችን የሚዘጋጀው ተጠባቂዉና ተወዳጁ ሳምንታዊ የዳዕዋ ፕሮግራማችን በዚህኛው ሳምንት ነገ ዕለተ ሰኞ በተወዳጁ ኡስታዛችን ኡ.ሻሚል ሙዘሚል የሚሰጥ ይሆናል።

👌 አላህ የሰጠንን ጊዜ በመልካም ላይ እናሳልፍ። ሁላችንም ከጓደኞቻችን ጋር በመሆን እንሳተፍ።

🕰 ሰዓት: ከመግሪብ-ኢሻ

🕌 ቦታ: 4ኪሎ ተማሪዎች መስጂድ


#4kMSJ
#AAU MSU

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
👍7
Hijab is the safeguard for every pious Muslimah
A Muslimah without Hijab is like a Pearl without shield.
Protect and safeguard yourself with Hijab, and make it a role model for your life.

@aaumsu
🥰14👌3👍1
لا شيء أنفع للقلب من قراءة القرآن بالتدبُّر والتفكُّر، فإنَّه جامع لجميع منازل السائرين وأحوال العالمين ومقامات العارفين .

‏ابن القيم رحمه الله
👍8
ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው "በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በነበረው ተቃውሞ ላይ ተሳታፊ ከነበሩ ተማሪዎች በ10 ቀናት ውስጥ 900 ተማሪዎች ታስረዋል:: ግን ተቃውሞው አሁንም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል::

From the river to the sea Palestine will be free!

@aaumsu
🥰21👍9🔥41