AAU - Muslim Students Union
6.45K subscribers
2.69K photos
149 videos
51 files
766 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
Ya Allah,

Bless us with someone who is good for us, for our life, for our livelihood, for our deen, for our akhirah. The one who would strengthen our imaan, make us closer to you and walk beside us in Jannah.

@aaumsu
11
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ!

መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ!

መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!

ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ

@MohammadamminKassaw
🔥8👍41
አፋርና ሶማሌ !

በአፋርና ሶማሌ ህዝቦች መካከል የነበረውን የወንድማማቾች ደም መፍሰስ ለማቆም በኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ፍሬ አፍርቶ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰምተናል :: ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው ::

አላህ የኡማውን አንድነት ያጠናክር!

@aaumsu
🔥5👍4🥰41👏1



بسم الله الرحمن الرحيم

""በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ(1)።
መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ(2)።
ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ(3)፡፡
ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ(4)፡፡
በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)(5)፡፡
ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ(6)፡፡
ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ(7)፡፡
ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ(8)፡፡""
سورة التكاثر

ወላሂ! ነፍሴ በእጁ በሆነቸው ጌታ እምላለሁ!! እንደ ቁርዓን መካሪ የለም!!!!

والله اعلم

@to2success
@to2success

👍7
የዛሬ 50 አመት በዛሬዋ ቀን !

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አፄ ሀ/ስላሴ "ይህ ሁሉ እስላም በሀገሬ አለ እንዴ?" በማለት ፍዝዝ እስኪሉ ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመሐል አዲስ አበባ አካሂደዋል :: "በኢትዮጵያ የሚኖሩ እስላሞች ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ተብለን እንጠራ!" የሚልን መፈክር ይዘው ድል አድርገዋል :: የኢድ በዓላት ሀገራዊ በዓል እንዲሆኑ ጠይቀው ስኬትን አምጥተዋል :: "የክርስቲያን ደሴት!" ተብላ ትጠራ የነበረችውን ኢትዮጵያ ከንጉሱ መውረድ ጋር ስርዓተ - ቀብሯን ፈፅመዋል :: ትልቅን ድል በትልቅነት ውስጥ ለትውልድ አሻግረዋል ::

     አደራቸውን የምንጠብቅ ያድርገን !

@aaumsu
👍36😭32🥰1
ክብራችሁ እንደ መድሃኒት ነው። ሕፃናት ከማይደርሱበት ቦታ አርቃችሁ አስቀምጡት።

ABX

@aaumsu
👌14🫡4👍3🔥1
በAAU 6ኪሎ ካምፓስ የተከፈተው የመፅሐፍ አውደ ርዕይ ነገ እሁድ ይዘጋል :: ያልሸመታችሁ ወይም ዳግም ለመሸመት ያቀዳችሁ እድሉን ተጠቀሙበት ::

  እናንብብ! እናብብ!!

@aaumsu
👍7
🥀 Daily Reminder 94🥀

وَمَا لَنَآ أَلَّا نَتَوَكَّلَ عَلَى ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنَا سُبُلَنَاۚ وَلَنَصۡبِرَنَّ عَلَىٰ مَآ ءَاذَيۡتُمُونَاۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ(12)

"መንገዳችንንም በእርግጥ የመራን ሲኾን በአላህ ላይ የማንመካ ለእኛ ምን አለን? በማሰቃየታችሁም ላይ በእርግጥ እንታገሳለን፡፡ በአላህም ላይ ተመኪዎች ሁሉ ይመኩ!!"

Surah Ibrahim; 12

@aaumsu
👍7
ደስታችሁን ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ አታውሩ። ምቀኝነት ሰምቶ ከእንቅልፉ ይነሳል።

ABX

@aaumsu
👍18
ዑቅባ ኢብን ዓምር አል-አንሷሪ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) በዘገበው ሓዲስ የአላህ መልእክተኛ( ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ። “ ‘ሓያእ ካላደረግክ የፈለከውን ስራ’ የሚለው ንግግር ሰዎች ከደረሱበት የመጀመርያ የነብያት ንግግር ነው።”

ሓዲሱን ቡኻሪ ዘግበውታል።
👍7
Forwarded from Ibnu Ahmed


بسم الله الرحمن الرحيم
👉ሁሉም ያልፋል !!!!

" አዚህች ዓለም ላይ ሁሉም ያልፋል። ቋሚና ዘውታሪ  ኃያሉ ጌታ አላህ ብቻ ነው። ይህንን እውነታ አላህ በቃሉ እንዲህ ሲል ገልፃታል።

كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ

በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡

وَيَبْقَىٰ وَجْهُ رَبِّكَ ذُو الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ

የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡

እሩቅ የሚመስል ሁሉ ቅርብ ነው። አይመጣም ተብሎ የሚታሰብ ሁሉ መምጣቱ አይቀሬ ነው። ሰዎች ብዙ ነገሮችን እሩቅ አድርገው ይመለከቷቸዋል። በተለይ ሞትና ቂያማን እሩቅ አድርገው ይጠብቋቸዋል። የሚገርመው ደግሞ አላህ ዘንድ በጣም የቀረቡ ናቸው ። ሰዎች በቂያማ ዕለት ምን በህይወት ዘመናቸው ምን ያክል እንደቆዩ ይጠያየቃሉ።ቆይታቸው አንድ ቀን ወይም ከቀን የሆነን ያክል ሰዓት ብቻ እንደሆነ አድርገው ይመልሳሉ።አላህ እንዲህ ይላል

إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا

እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡

وَنَرَاهُ قَرِيبًا

እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡

ታዲያ ዛሬ ላይ ብዙ እሩቅ አድርገን ስንመለከታቸው የነበሩ ነገሮች መጥተው አልፈዋል ፣ አይከሰቱም ብለን ስናስባቸው የነበሩ ነገሮች ተከስተው አልፈዋል ። ወደፊትም እንዲሁ ነው።  ይሀው በቅርቡ እንኳንን እሩቅ ስንጠብቀው የነበረው የረመዳን ወር ዛሬ ላይ አልፎ እንደ ትዝታ ማስታወሳችን ጠቋሚ አይደለምን?። ህይወታችንም እንዲህ ናት የሆነ ቀን ያለፈ ትዝታ መሆኗ አይቀሬ ነው። በቃ ዱንያ ስትባል ባህሪዋ ይሄው ነው አንድ ቀን  ትጠፋለች። ቀጠሯን እየጠበቀች እንጂ ጓዟን ጠቅልላ መሰናበቷ አይቀርም። አላህ የዱንያን ህይወት ምሳሌ እንዲህ ሲል ይነግረናል


إِنَّمَا مَثَلُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا كَمَاءٍ أَنزَلْنَاهُ مِنَ السَّمَاءِ فَاخْتَلَطَ بِهِ نَبَاتُ الْأَرْضِ مِمَّا يَأْكُلُ النَّاسُ وَالْأَنْعَامُ حَتَّىٰ إِذَا أَخَذَتِ الْأَرْضُ زُخْرُفَهَا وَازَّيَّنَتْ وَظَنَّ أَهْلُهَا أَنَّهُمْ قَادِرُونَ عَلَيْهَا أَتَاهَا أَمْرُنَا لَيْلًا أَوْ نَهَارًا فَجَعَلْنَاهَا حَصِيدًا كَأَن لَّمْ تَغْنَ بِالْأَمْسِ ۚ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

የቅርቢቱ ሕይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ፣ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት (እንደ ፋፋ) ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋም በርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው፡፡ እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡

ምሳሌዋ እንዲህ ነው አለች ስትባል የምትጠፋ አታላይ ሀገር ናት። ታዲያ ጠፊና አታላይ በሆነችው ዱንያ መሸወድ ደግሞ ሞኝነት ነው።አዋቂና ብልጥ ማለት ለዚህች ጠፊ ዱንያ ሳይንበረከክ ለመጪው ዓለም የሚሰነቅ ሰው ነው። ረሱል እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል።

"አዋቂ ማለት እራሱን የተሳሰበና ከሞት ቡኋላ ላለው የሰራ ነው።"

አህባቢ ይሀው ረመዳን መጥቶ አለፈ በረመዳን የተጠቀመም ያልተጠቀመም ሁለቱም አሉ። ልዩነቱ ግን ሁለቱም በውስጡ ከዘሩት ጋር በቀጣዩ ዓለም ይገናኛሉ። ህይትም እንዲህ ናት። አንድ ቀን መሞታችን አይቀርም። ግን ምንን አሳልፈን ነው የሚለው ነገር ልናስብበት ይገባል። ረመዳን ቢያልፍም ህይወት ትቀጥላለች። ታዲያ ትላንት በረመዳን ያገኘናትን ብርሃን እንድትፋፋ መልካም ስራ ላይ እንዞትር። ከመስጂድ መራቅ ሳይሆን ወደ መስጂድ እንቅረብ። ከጌታችን ሸሽተን ምንጠለልበት አንድም ቦታ የለንምና ።ወደ ጌታችን ብንሸሽ ከርሱ ጋር ብንታረቅ ሁለት ሀገራችን ያምራል።

ስለዚህ ወንድሞቼ አላህን የሚያመልኩ ወደርሱ የሚሸሹ እውነተኛ የአላህ ባሮች እንጅ የረመዳን  አገልጋዮች እንዳንባል ከወዲሁ ልናስብበትና አላህ ባዘዘን ነገሮች ላይ ልንፀና ክልከላወቹንም ልንርቅ ይገባል እያልኩኝ በዚሁ እቋጫለሁ።

والله اعلم

@to2success
@to2success
👍10
አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "ሀብት ማለት የገንዘብ ብዛት ሳይሆን የነፍስ(የውስጥ)  መብቃቃት ና መረጋጋት ነው።"    (ቡኻሪ ና ሙስሊም)

@aaumsu
👍101
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዌስት ባንክ ከእርሻ ማሳ ላይ የፍልስጤምን ባንዲራ ለማውረድ የሞከረ እስራኤላዊ ከባንዲራውጋ በተጠመደ ፈንጅ ቆስሏል ::

ነጃሳ እግራቸውን ለማሳረፍ በሚሞክሩበት ቦታ ሁሉ ውርደትን ይስጣቸው :: መቁሰልን ይሸልማቸው :: ይበቀላቸው ::

@aaumsu
👍23
በሀዲያ ዞን አንሊሙ ወረዳ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ተፈፀመ!
...
(ሀሩን ሚድያ ደቡብ ስቱዲዮ፦ ሚያዚያ 13/2016)
...
በሀዲያ ዞን አንሊሙ ወረዳ ምዕራብ አናሌሞና ምስራቅ አናሌሞ ቀበሌ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት የደረሰ ሲሆን በጥቃቱም የሱመያ መስጂድ ኡስታዝ ሳዲቅ ሸምሰዲንን ጨምሮ ሌላ ተጨመሪ 3 ሙስሊሞችን ጨምሮ በድምሩ 4 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
...
የጥቃቱ መንሴኤም በምዕራብ አንሌሞ ቀበሌ 140 ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አራሊዶ መስጂድ እና በምስራቅ አናሌሞ ቀበሌ ሱመያ መስጂዶች መኃል ላይ ቤተክርስቲያን ለመገንባት አሸዋና ድንጋይ አራግፈው ግንባታ ሲያስጀምሩ የግንባታው ቦታ ከመስጂድ መራቅ አለበት አግባብ አይደለም ባሉ ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት መከፈቱን ያነጋገርናቸው የአይን እማኝ የነገሩን ሲሆን
...
ከዚህ ቀደም ለቀበሌውም አስተዳዳር እንዲሁም ለወረዳው አስተዳደር አመልክተው የመንግስት አካላት ግንባታውን አስቁመው ለቤተክርስቲያን መገንቢያ ቦታ የሰጧቸው ቢሆንም ያን ቦታ ትተው በመስጂዶቹ መኃል ካልገነባን ብለው አቁም ስንላቸው ጥቃት ፈጽመውብናል በማለት ከስራፍራው ያነጋገርናቸው የአይን እማኛ ለሀሩን ሚዲያ ገልጸውልናል።
...
እንደ አይን እማኞቹ ገለጻ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት የወረዳው አስተዳደር ለነገ ማለትም ለዕለተ ሰኞ ቀጠሮ ይዟል በማለት የገለጹልን ሲሆን ጥቃቱን ያደረሱ አካልት ግን እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ በህግ ቁጥጥር ስር አልዋሉም በማለት ጉዳት የደረሰባቸው ሙስሊሞች ህክምና እይውተደረገላቸው መሆኑኑንም ገልጸውልናል።
...
©ሀሩን ሚዲያ

@aaumsu
😡11👍3🔥1
ምን አይነት ተዓምረኛ ትውልድ ናቸው ?

ጋዛውያንን ማለቴ ነው :: "በዛሬው እለት በጋዛ በስተ-ምዕራብ በአንድ ት/ቤት ተጠልለው ከነበሩት መካከል 100 ተማሪዎች በቁርዓን ሂፍዝ ተመረቁ::" የሚል ዜና አነበብኩ :: አጂብ ! በዚያች ሚጥጥዬ ከተማ ውስጥ ከሀገራት የተውጣጣ ቦንብ እየዘነበባቸው እንኳ ፀንተው ቆመዋል :: አላጎነበሱም :: ቀጥ ብለው እንዳሉ ናቸው ::

እነዚህ የቁርዓን ትውልዶች በቴልአቪቭ ተሰባስበው በድል ተክቢራ የሚደምቁበትን ቀን ቅርብ ያድርግ! የምዕራባውያንን ውድቀት ያቅርብ!

From the river to the sea Palestine will be free !

@MohammadamminKassaw
27👍4👏2
ነገር አሳባቂ (ወሬ አመላላሽ)  ና በጣም ዋሾ የሆነ ሰው ሳሒር(ድግምተኛ) በዓመት የማያበላሸውን እሱ በሰዓት  ያበላሸዋል። "

የሕያ ኢብኑ አቢ ከሲር (ረሒመሁሏህ)

copied

@aaumsu
👍6
🥀 Daily Reminder 95🥀

قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ(1)

በል "እርሱ አላህ አንድ ነው"!!"

Surah Al-Ikhlas; 1

@aaumsu
👍15
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ثلاثةٌ حقٌّ على اللهِ عونُهم: المجاهِدُ في سَبيلِ اللهِ، والمكاتَبُ الَّذي يريدُ الأداءَ، والنّاكِحُ الَّذي يُريدُ العفافَ﴾

“ሶስት አይነት ሰዎች አላህ እገዛ ሊያደርግላቸው የተገቡ ናቸው። በአላህ መንገድ ላይ የሚታገል ሙጃሂድ፣ እዳውን ለመክፈል ጥረት የሚያደርግ፣ ከዝሙት ለመጠበቅ ትዳር የሚመሰርት (ኒካህ የሚያስር) ናቸው።”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል፡ 1655

@aaumsu
👍112