AAU - Muslim Students Union
6.45K subscribers
2.69K photos
149 videos
51 files
766 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
🥀 Daily Reminder 91🥀

فَٱسۡتَبِقُواْ ٱلۡخَيۡرَٰتِۚ إِلَى ٱللَّهِ مَرۡجِعُكُمۡ جَمِيعٗا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ(48)

"በጎ ሥራዎችንም (ለመሥራት) ተሽቀዳደሙ፤ መመለሻችሁ በጠቅላላ ወደ አላህ ነው፡፡ በእርሱም ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር ይነግራችኋል!!"

Surah Al-Ma'idah; 48

@aaumsu
8👍3
ምድር ላይ መጥተህ መልካም ነገር መጨመር ካልቻልክ አንተ ጭማሪ ሸክም ነህ !

@aaumsu
👍15👌4
ህፃናት የወደፊት ህልማቸውን በነፃነት እንዳያልሙ የሚያደርገው አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ !
   ከፌስቡክ መንደር ያገኘሁት!

ትላንት የሆነ ቦታ በአጋጣሚ አንዲት ደስ የምትል የ10 ዓመት ልጅ ከእናቷ ጋር ሆና አጠገቤ ተቀምጠዋሉ። ሙስሊም ናቸው። ልጅቷ በጣም ቀልጣፋ ነች። አይን አይኔን ስታየኝ ወሬ ጀመርኩ።

'ትምህርት እንዴት ነው ?' ስላት ፣ በትምህርቷ ጎበዝ እንደሆነች'ና እስከአሁን አንደኛ ብቻ እየወጣች እንደሆነ ነገረቺኝ። እናቷ በፈገግታ የምናወራውን ትሰማለች። 'እና ስታድጊ ምን መሆን ነው የምትፈልጊው ?' ስላት ፣ ድንገት እናቷ ፊቷ ቅይርይር አለ። ልጅቷ ላይ ተኮሰታተረችባት። ግራ ገባኝ።

ልጅቷም እያፈራረቀችን በፍርሃት ውስጥ ሆና እኔ'ና እናቷን ታየን ጀመር። 'ምነው ?' አልኳት ለህፃኗ ቀስ ብዬ። 'እናቴ እኔ መሆን የምፈልገውን ነገር አትደግፈኝም...' አለቺኝ ለንቦጯን እየጣለች።

የልጅቷ አይን በእንባ ሲሞላ 'ችግር የለውም ንገሪው በቃ እኔኮ ለአንቺው ብዬ ነው...' አለች እናቷን የግዷን ፈገግ ለማለት እየሞከረች።

'እኔ ሳድግ ፓይለት ወይም ሆስተስ መሆን ነው የምፈልገው...' አለች ህፃኗ ፍንድቅድቅ እያለች። ያልጠበኩት ነገር ስለነበር እኔም ወደ እናቷ እየዞርኩ 'አሪፍ ነገር እኮ ነው የተመኘችው። እኔኮ እንደማንኛውም ህፃን የማይሆን ነገር እየጠራች አስቸግራችሁ መስሎኝ ነበር...' ስላት ፣ 'እኔም ሆንን አባቷ እኮ የምትፈልገው ብትሆን ደስታችን ነበር። ግን ደግሞ ከአሁኑ ተስፋ አድርጋ አድጋ ወደፊት ፓይለትም ሆነ ሆስተስ ለመሆን በአየር መንገዱ ሂጃብሽን ካላወለቅሽ ፣ ሱሪ ወይም አጭር ቀሚስ ካለበስሽ አይሆንም ስትባል ምን ልትሆን ነው ብለን ስለምናስብ ነው ከአሁን የምንከለክላት....' አለቺኝ የንዴት ሳቅ እየሳቀች !

ከዚህ በፊት በብዙ ሙስሊም እህቶቻችን ይሄ ቅሬታ ሲነሳ ብሰማም እንደዚህ ግን ተረብሼ አላውቅም። ቁጭ ብዬ የአንዲት ጎበዝ ተማሪ ሙስሊም ህፃን መብቷ ሲነፈግ ፣ ምኞቷን ገና ከአሁኑ ስትነጠቅ ማየት ያናዳል። ያሳዝናል። ልብ ያደማል።

ሴኩላር ነው በሚባል ሀገር ላይ ሙስሊም እህቶቻችንን በአለባበሳቸው ብቻ መቀጠር የማይችሉበት አየር መንገድ የሚያህል ትልቅ ተቋም መኖሩ ያሳፍራል። አውሮፕላን ውስጥ ለማስተናገድ በየቱ አስገዳጅ ምክንያት ነው ፀጉር መልቀቅ ግዴታ ሆኖ ሂጃብ ማድረግ ሊያስከለክል የቻለው ? ሱሪና አጭር ቀሚስ ተፈቅዶ ረዥምም ቀሚስ የተከለከለው ተሳፋሪው ላይ ምን እንዳይጎልበት ነው ?

አየር መንገዱ እንደ ገላ ሻጭ በሆስተሶቹ ሰውነት'ና ፀጉር መራቆት ምንድን ነው የተለየ የሚያገኘው ጥቅም ?

የሙስሊሙም ጭምር የህዝብ ተቋም የሆነው አየር መንገድ ውስጥ ተቀጥሮ ለመስራት እህቶቻችን መማር እንጂ ሰውነታቸውን አጋልጠው ማሳየት ግዴታ ሊሆንባቸው አይገባም !

በአሁን ሰዓት ሙስሊሙ ህብረተሰብም ሆነ እስላማዊ ተቋማቶች ከምንም በላይ ጊዜ ሳንሰጥ ልንታገለው የሚገባ አድሎዊ ተቋም ይሄንኑ አየር መንገድ ይመስለኛል። ይሄ ተቋም በማይረባ ቢሮክራሲው ትላንት የብዙ እህቶቻችንን ተስፋ መቀማቱ ሳያንሰው ዛሬም የልጆቻችንን ህልም ጭምር እየነጠቀ ነው።

ይሄን የተቋሙ አግላይ የሆነ አካሄድ በጊዜ በቃ ልንለው ይገባል። እኛ ታግለን መብታችንን ባለማስከበራችን ልጆቻችን ስርአት ባለው ሃይማኖታዊ አለባበሳቸው ሊያፍሩ'ና ሊሸማቀቁ አይገባም !

ሂጃብ ፣ እንዲሁም ያላጠረ'ና ያልተወጠረ ቀሚስ ያደረገች ሙስሊም ሴት ፓይለትም ሆነ ሆስተስ የመሆን መብት አላት ! ትሆናለችም !

©ሙስተጃብ ነኝ

@MohammadamminKassaw
👍17😡7👌3
"መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወግዳሉ" ሁድ :114

ወንጀል ማቆም ከተሳነህ በጥሩ ስራዎች አጨናንቃት ዋጣት

የትኛውም አይነት ወንጀል ላይ ስትወድቅ አንድ ዙር ውጊያውን እንጂ ጦርነቱን እንዳልተሸነፍክ እውቅ።ተስፋ አትቁረጥ።በልብስ ተጠቅልለህ ከጉዞህ አትቁም።ጥሩ ስራዎችን በእጥፍ አሳድጋቸው ።ወንጀሉን በዉዱእ እጠበውና በሁለት ረክዐዎች እንደ አዲስ ታደስ።

ወንጀል በሰሩ ጣቶቾህ አላህን አስታውሰው
ሀራም በተመለከቱ አይኖችህ ቁርዐንን እይበት በምላስህ ቁርዐንን አንብብበት ምህረቱን ጠይቅበት
ወደ መጥፎ ቀዬ የመሩህ እግሮችህን ወደ መስጅድ ምራቸው

አል ገፉር፣አል አፉው ፣ አል ገፋር እና መሰል የአዛኙ ጌታችን ስሞች አንተን ካልሆነ ማንን እየተጣሩ ይመስለሀል?
👍62
መግዛት ባልችል ገዢና ተገዢን ለመመልከት !

"ገዢው ማነው? ተገዢውስ?" የሚሉት ጥያቄዎች የአዲሳባ መፅሐፍ ሻጮች እንደ ከተማዋ የታክሲ ሰልፈኛ ወደተደረደሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመፅሐፍ አውደ-ርዕይና ሽያጭ ማዕከል እየገፉ ወሰዱኝ:: እንደደረስኩም "የኢቅረዕ ትውልድ የት ናቸው?" ለሚል ጥያቄ መልስ ይሆነኝ ዘንድ ወዳ ወዲህ ማማተር ጀመርኩ:: አውቄው አሰላሙአለይኩም ያልኩት ሰው ግን አልነበረም :: መፅሐፎቹን ስመለከት ሁሉም በሚባል ደረጃ ከፀሐይ መግቢያ በኩል የመጡ ወይም መጥተው በሀገርኛ ቋንቋ የተተረጎሙ ነበሩ :: ይህንን ሳስብ "ከፀሐይ መግቢያ የፀሐይ ብርሃን ነው ብዬ የማስበው መፅሐፍ መምጣቱ የቂያማ ምልክት ይሆን?" አልኩኝ :: ምክንያቱም ፀሐይ ከምዕራብ የምትወጣው ቂያማ ሲቆም ነውና ::

ይህንን ጥያቄ በማለፍ ቅኝቴን ስቀጥል የሀገሬ ደራሲዎች የፃፏቸውም መፅሐፍቶች ከኢቅረዕ ትውልድ መሠረት ውጭ ሆነው አገኘሗቸው:: እየተገረምኩ ሳልፍ ግን ለናሙና ቢሆንም "ሶባሐል ኸይር!" የሚለውን የABX መፅሐፍት አገኘሁ :: አለፍ ስል "የተረሳው ኢስላማዊ ታሪካችን!" የሚለውን የአቡ ቢላል ሙፅሐፍ : Vocabularies of The Holy Quran እንዲሁም ተፍሲሩል ቁርዓነል ከሪም የሚሉ መፅሐፍትን ተመለከትኩ :: አንድ አማኝ ለሺ ካፊር በሚል ማባባያም ተስፋዬን አለምልሜ ድንኳኑን ጥዬ ወጣሁ ::

መልዕክት:- እናንብብ! እንፃፍ! እናብብ!

@aaumsu
👍123🫡1
🥀 Daily Reminder 92🥀

وَقُل رَّبِّ زِدۡنِي عِلۡمٗا(114)

"ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ» በል!!"


Qur'an 20; 114


@aaumsu
👍10
ፀሐይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጭ የሆነ ቀን ነው :: በእርሱ ውስጥ አደም (ዐለይሂ ሰላም) ተፈጥሯል:: የሰው ልጅ ታሪክ አንድ ብሎ ጀምሯል ማለት ነው :: ማንኛችን ኸይርን እንደምንሰራ ልንፈተን ተፈጠርን ማለት ነው :: ይህ ቀን ጁምዓ ነው :: ይህ ቀን ዛሬ ነው :: አላህ በላጭ ያድርገን ::

መልካም ጁምዓ !

@aaumsu
👍101
"አላህ ለባሪያው መልካምን ከከጀለ ምላሱን በነቢ ሙሐመድ ላይ ሰለዋት ለማውረድ ያገራለታል!" ኢብነል-ጀውዚ (ረህመቱላሂ ዐለይህ)

فيا ربي صل وسلم على حبيبي وحبيبك محمد وعلى آله وصحبه عدد ما كان وما يكون وما لم يكن وما لا يكون.

وأسألك يا مولاي أن تجمعني به كما وعدتنا بلسانه أنك تجمع المحب مع من أحب.

@aaumsu
8🥰2👍1
አይን ጆሮ ሆኖ አይሰማም :: ጆሮም አይን ሆኖ ሊያይ አይችልም :: ምላስ መናገሪያ እንጅ መራመጃ እግር አይደለም :: ሆድ ሊበላ እንጅ ሊያስብ ሀይል የለውም ::

  ሁሉም የተገራው ለተፈጠረበት አላማና ቦታ ነው :: ቦታውን ለቆ ከሌላ ቦታ ከተገኘ እሱም ሳይሰራ የሌሎችንም እያደናቀፈ በድንግዝግዝ መስመር ላይ እስኪበሰብስ ይኖራል:: ለአንተም ተመሳሳይ ነው:: ሚናህን ካለየህ ትጠፋለህ :: ያለ ሚናህ ከገባህ ታጠፋለህ ::

    ስለዚህ እንደ ህፃን ያየኸውን ሁሉ አትመኝ :: ሚናህን ለይተህ የሚጠበቅብህን አድርግ :: ስኬትህም እርሱ እርሱ ነው ::

@aaumsu
14👍4
"ይህ የአላህ ፍጡር ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ?" - ሉቅማን : 11

እየጠየቀ ያለው ሰማያትን ያለ ምሰሶ የፈጠረው አምላክ ነው:: እየጠየቀ ያለው መሬትን እንዳታረገርግ ተራራዎችን የጣለው አምላክ ነው:: እየጠየቀ ያለው ከሰማይ ውሃን አውርዶ አዝዕርትን ያበቀለው አምላክ ነው:: እየጠየቀ ያለው የእኔ የአንቺ የአንተ የሁላችን አምላክ የሆነው አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ነው ::

እስቲ ከእርሱ ውጭ ያሉት የፈጠሩትን ያምጡ! ጌታዬ አይችሉም! አንተ አንድና አሸናፊ ነህ! አንተ ሁሉን ፈጣሪና አድራጊ ነህ! አንተ አዛኝና መሐሪ ነው! ላጠፋነው ይቅር በለን! አይችሉም! አንችልም!

@MohammadamminKassaw
👍17
Forwarded from Ibnu Ahmed


بسم الله الرحمن الرحيم

ቁርዓን! የተከበረው የአላህ ቃል!!!!

ቁርዓን የህየወታቾን መርህ ነው። አጠቃላይ የህይወት ኮምፓስ ነው። ቁርዓን ክስረት የሌለበት ትርፋማ ንግድ ነው። ቁርዓንን ይዞ የከሰረ የለም። ከአላህ ጋር ነግዶ ንግዱ የተበላሸ የለም። ቁርዓንን አንብቦ የተገበረ በርግጥም ማይበጠስ አስተማማኝ ገመድን ጨብጧል። አላህ ይህንን እንዲህ ሲል በቁርዓኑ ይነግረናል

"እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱ፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በምስጢርም ኾነ በግልጽ የለገሱ፣ በፍጹም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡" ፋጢር:29

ህይወቱን ከቁርዓን ጋር ያደረገ ሁሌም የበላይ ነው። በዱንያም በአኼራም ከሰዎች ሁሉ በላጩ እርሱ ነው። ሰዎች በብዙ ነገር ሊበላለጡ ይችላሉ። በሃብት በዝና አሌሎች የበለጡ የታወቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ቁርዓንን ተምሮ ካስተማረ በላይ በላጭ ሰዉ የለም። አላህ ዘንድ የተከበሩት እነርሱ ናቸው። የአላህ አህልም ናቸው። ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ሲሉ ይገልፃሉ

"" ከናንተ በላጩ ቁርዓንን ተምሮ ያስተማረ ነው።"
" የቁርዓን ሰዎች የአላህ ቤተሰቦች ናቸው።" ረሱል ሰ.ዐ.ወ

በቁርዓን ሁሉም ይገራል ።የከበደው ይቀላል፣ የራቀው ይቀርባል ፣ ቁርዓንን ማንበብ የልብ ብርሃን ነው። ሰለፎች እንዲህ ሲሉ ይመክሩ ነበር" ቁርዓንን ቅሩ እርሱን መቅራት አትተው። ቁርዓንን በቀራቹ ልክ ሌላው ጉዳያቹ ይገራል።"

ቁርዓን ማንበብ ለሁሉም ነገር መዳኒት ነው ።የሁለት ሀገር ስኬት ዋስትና ነው። ቁርዓንን በማንበብ ልብ ይሰፋል፣ አዕምሮ ይመጥቃል ፣ አካል ይጠነክራል። ቁርዓን ለልብ ብርሃን: መድሃኒት ለአዕምሮ ምግብ ነው።

ኢብኑ ተይሚያህ አንዲህ ይላሉ "" ቁርዓንን ደጋገሞ ከማየት በላይ ለአዕምሮና ሩህ ምግብ ፣ አካልን ጠባቂ  ለሁለት ሀገር ስኬት ዋስትና የሆነ ነገር አላየሁም ።"

አደራ!!ከቁርዓን ጋር ያለንን ግኑኝነት አናቋርጥ!!!

والله اعلم

@to2success
@to2success

👍5
Be busy as bee, your result will be as sweet as honey!!

@aaumsu
26👍3
When you find yourself in a position to help someone, be happy because Allah is answering that persons prayer through you.

@aaumsu
👍11🥰2
🥀 Daily Reminder 93🥀

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ جَنَّٰتُ ٱلنَّعِيمِ(8)

"እነዚያ ያመኑና መልካሞችንም የሠሩ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው!!"

Surah Luqman;8

@aaumsu
👍4
Ya Allah,

Bless us with someone who is good for us, for our life, for our livelihood, for our deen, for our akhirah. The one who would strengthen our imaan, make us closer to you and walk beside us in Jannah.

@aaumsu
11
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ!

መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ!

መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!

ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ

@MohammadamminKassaw
🔥8👍41
አፋርና ሶማሌ !

በአፋርና ሶማሌ ህዝቦች መካከል የነበረውን የወንድማማቾች ደም መፍሰስ ለማቆም በኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ፍሬ አፍርቶ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰምተናል :: ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው ::

አላህ የኡማውን አንድነት ያጠናክር!

@aaumsu
🔥5👍4🥰41👏1



بسم الله الرحمن الرحيم

""በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ(1)።
መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ(2)።
ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ(3)፡፡
ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ(4)፡፡
በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)(5)፡፡
ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ(6)፡፡
ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ(7)፡፡
ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ(8)፡፡""
سورة التكاثر

ወላሂ! ነፍሴ በእጁ በሆነቸው ጌታ እምላለሁ!! እንደ ቁርዓን መካሪ የለም!!!!

والله اعلم

@to2success
@to2success

👍7
የዛሬ 50 አመት በዛሬዋ ቀን !

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አፄ ሀ/ስላሴ "ይህ ሁሉ እስላም በሀገሬ አለ እንዴ?" በማለት ፍዝዝ እስኪሉ ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ሰላማዊ ሰልፍ በመሐል አዲስ አበባ አካሂደዋል :: "በኢትዮጵያ የሚኖሩ እስላሞች ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ተብለን እንጠራ!" የሚልን መፈክር ይዘው ድል አድርገዋል :: የኢድ በዓላት ሀገራዊ በዓል እንዲሆኑ ጠይቀው ስኬትን አምጥተዋል :: "የክርስቲያን ደሴት!" ተብላ ትጠራ የነበረችውን ኢትዮጵያ ከንጉሱ መውረድ ጋር ስርዓተ - ቀብሯን ፈፅመዋል :: ትልቅን ድል በትልቅነት ውስጥ ለትውልድ አሻግረዋል ::

     አደራቸውን የምንጠብቅ ያድርገን !

@aaumsu
👍36😭32🥰1
ክብራችሁ እንደ መድሃኒት ነው። ሕፃናት ከማይደርሱበት ቦታ አርቃችሁ አስቀምጡት።

ABX

@aaumsu
👌14🫡4👍3🔥1
በAAU 6ኪሎ ካምፓስ የተከፈተው የመፅሐፍ አውደ ርዕይ ነገ እሁድ ይዘጋል :: ያልሸመታችሁ ወይም ዳግም ለመሸመት ያቀዳችሁ እድሉን ተጠቀሙበት ::

  እናንብብ! እናብብ!!

@aaumsu
👍7