AAU - Muslim Students Union
6.44K subscribers
2.68K photos
149 videos
51 files
765 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
We never stop talking about palestine.

From the river to the sea Palestine will be free. 🇵🇸

@aaumsu
33👍6
ዝሆንና ዳክዬ ይለያያሉ !

እንማር ዘንድ ከሰማሁት አጭር ታሪክ ላጋራችሁ (የእንስሳት ስለሆነ እውነትነቱ ያጠራጥራል¡):-

   ከእለታት አንድ ቀን ቀበሮ ወደ ዝሆን በመምጣት "ዝሆን ሆይ! ዳክዬ ከጀርባህ ስላንተ መጥፎ ነገሮችን እያወራች ነው:: ስላንተ ካንተ ያልሆነን ውሸት እየፈጣጠረች ማሰራጨቱን ተያይዛዋለች:: በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው:: መቀጣጫ አድርጋት::" አለች :: ዝሆኑም በመኮሳተር "ትምህርት አደርጋታለሁ :: ያላትን አጥንት በሙሉ እሰባብርላታለሁ :: ሁሉንም ለእኔ ተይውና ወደ መኝታሽ ተመለሺ::" አላት ::

   በቀጣዩ ቀን ቀበሮዋ ወደ ዝሆኑ በመመለስ "ቃል የገባኸውን ቅጣት በዳክዬዋ ላይ አላሳረፍክም:: ይህኮ ቀላል ጉዳይ አይደለም:: ዳክዬዋ አሁንም በአንተ ላይ መቅጠፏን አላቆመችም:: ዝም ማለቱን አቁመህ የሚገባትን ስጣት::" አለች :: ዝሆኑም በማጉረምረም  "ትክክል ነሽ! የማትረሳውን ቅጣት የምቀጣበት ሰዓቱ አሁን ነው:: አንቺ ሂጂ:: እኔ እወጣዋለሁ::" አላት ::

   በ3ኛውም ቀን ቀበሮዋ ዝሆኑን ዳግም በመጠጋት "በጣም እየታገስክ ነው:: እመነኝ ዳክዬዋ ስላንተ የምታወራው ነገር በጣም መጥፎ ነው:: ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስተምራት::" አለች:: ዝሆኑም ትንሽ አሰብ አድርጎ ቀበሮዋን "ይሁን! ሄጄ መቅጣት ግዴታዬ ነው:: ግን መቁረጫ መፍለጫና አካፋ ስለሚያስፈልገኝ አምጪልኝ :: ቆራርጨ በመግደል መቅበር አለብኝ ::" አለ :: ቀበሮዋም ፈጥና በመሄድ የታዘዘችውን ይዛ በመምጣት ለዝሆኑ አቀበለች:: ዝሆኑ ግን ወደ ዳክዬዋ በመሄድ ፋንታ መሳሪያዎቹን ይዞ ወደ እርሻ ማሳው አመራ :: ቀበሮዋም በመገረም "ሄደህ ዳክዬዋን እንደምትቀጣ ከነገርከኝ ቡሃላ ምን እየሰራህ እንዳለህ ገብቶሃል?" አለችው ::

   ዝሆኑም ፈገግ በማለት "እኔ በስራዬ ቢዚ ነኝ:: ስራዋ ማውራትና ጫጫታ መፍጠር ለሆነባት ዳክዬ የምጨነቅበት ጊዜ የለኝም:: እኔ ጥንካሬንና ጥበብን የምገልፅ የአላህ ድንቅ ፍጥረት ነኝ:: በወረኛነትና ግርታ በመፍጠር ለሚታወቅ ፍጥረት ምላሽ በመስጠት ወደሗላ የምልበት ምክንያት የለኝም:: ስለዚህ ስራዬን እንድሰራ ተይኝ:: መሳሪያዎችሽን ስጨርስ እመልሳለሁ ::" በማለት ድንቅ ምላሽ ሰጣት ::

ትምህርት:- በህይዎት ውስጥ ምስለ ዳክዬ የሆኑ ብዙ ሰዎች ከጀርባችሁ ሆነው ሀሜትን ያሰራጫሉ :: ውሸትን ከመፍጠር ጀምረው እናንተን የሚጠሉ ሰዎች እስከ መመልመልም ይደርሳሉ :: ነገር ግን የሚፈልጉትን ትኩረት ልትሰጣቸው አይገባም :: በጥንካሬና በጥበብ እንደተሞላው ዝሆን ሁኑ :: በራሳችሁ ህይዎት ቢዚ በመሆን የእነሱን ሀሜት ከመጋፈጥ ራቁ :: ራሳችሁን ማጠናከርን የራሳችሁ የመጀመሪያ ፕሮጀክት አድርጉ :: ዝሆን ከዳክዬ እንደሚለይ በመረዳትም ለዳክዬ ጥቃት በቀበሮ ምክር ሳይሆን የዝሆንን መንገድ በመከተል ምላሽ ስጡ ::

@MohammadamminKassaw
👍14🔥3
🥀 Daily Reminder 89🥀

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱبۡتَغُوٓاْ إِلَيۡهِ ٱلۡوَسِيلَةَ وَجَٰهِدُواْ فِي سَبِيلِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ(35)

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ወደርሱም መቃረቢያን (መልካም ሥራን) ፈልጉ፡፡ ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ፡፡"

Surah Al-Ma'idah; 35

@aaumsu
🥰2
4 Unbreakable Promises from Allah !

@aaumsu
15
One place, billions love !

@aaumsu
21
Be careful who you marry. The biggest prison is a home without peace.

@aaumsu
🥰9👏3👌1
📂| ‏قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله :

حلاوة الإيمان: أن تتلذذ بالطاعات، فإذا وجدت نفسك تتلذذ بالصلاة، بالصيام، بالجهاد في سبيل الله، تتلذذ بالطاعة، هذه حلاوة الإيمان، وأما إذا أتى العبد بالعبادة، وهو لا يتلذذ بها، فهذا فاقد لحلاوة الإيمان .

📓 شرح كتاب الإيمان صـ ٥٦
👍21
"ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም"  ጧሀ : 52

      አብሽር አላህ አይረሳም

ያፈሰስካትን እንባ
የጠገንከውን ልብ
ያፅናናሀውን ነፍስ
ያነሳሀውን የሙዝ ልጣጭ
የቀረሀውን ቁርዐን
የቀሰምከውን ዕውቀት
የሰገድከውን ሰላት
የፆምካቸውን ቀናት
እረሱን ያስታወስክበትን ገዜያት
ይቅር ያልካቸውን በደል
የዋጥከውን ቁጭት
ለሱ የተውከውን በቀል
ችለህ የተቆጠብከውን ወንጀል
ያመሰገንከው ፀጋ በሙሉ
.
.
.

ፈጣሪህ አላህ ስለማይረሳ
አንተም ራስህን መገምገሙን አትርሳ
13👍6
ዳቦ ግዛልኝ ለሚልህ ካለህ ግዛለት :: ጠማኝ ያለህን አጠጣ :: ብር ብሎ ለጠየቀህ ካለህ ላይ ስጠው :: ከአንተ ከጅሎ ሲመጣ አመጣጡ አንተን ለማስቸገር ሳይሆን ከአንተ ወንጀል ሊቀንስ እንደሆነ አስብ ::

@aaumsu
🥰24👌75👍1
በሳውዲ መማር ለምትፈልጉ!

በተለያዩ ዘርፎች ለባችለር ዲግሪ እና ከዛ በላይ የሳውዲ ስኮላርሺፕ ለማግኘት በሚከተለው ኦፊሴሊያዊ ድረገፅ https://studyinsaudi.moe.gov.sa
ላይ ማመልከት የምትችሉ ሲሆን፤ የማመልከቻ ግዜው ከአፕሪል 21 እስከ 28 / 2024 ድረስ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ እንመክራለን።

አላህ ይወፍቃችሁ

@aaumsu
👍9
🥀 Daily Reminder 90🥀

فَلَا تَخۡشَوُاْ ٱلنَّاسَ وَٱخۡشَوۡنِ(44)

"ሰዎችንም አትፍሩ፡ (እኔን)ፍሩኝም!!"


Surah Al-Ma'idah; 44

@aaumsu
👍11
የMedicine,Dental medicine,Pharmacyና የሕግ መግቢያ ፈተና የምትወስዱ እህት ወንድሞቻችን:-

    አላህ ያግዛችሁ ዘንድ ዱዓችን ነው:: ጥሩ ሰርታችሁ የሚጠቅማችሁንና ኡማውን የምትጠቅሙበትን የምታገኙ ያድርጋችሁ:: ከዚያ ውጭ በተለያየ ምክንያት እየፈለጋችሁ ለፈተናው ብቁ ያልሆናችሁም አላህ የተሻለውን ለእናንተ ያውቃልና የተሻለውን ይስጣችሁ:: ባላችሁበት ስኬታማ የምትሆኑና ለሁሉም የኡማውን ክፍተት የምትሞሉ ያድርጋችሁ::

   መልካም ፈተና!
   መልካም እድል!

ሙሐመድአሚን ካሳው(የአአዩሙተህ አሚር)

@aaumsu
24👍2
Obbolewwan Qormaata seensa Medicine,Dental medicine,Pharmacy fi Seeraa fudhataniif,

Rabbiin isiin haa gargaarun du'aai teenya. Gaarii dalagdani Damee barnooraa kan isiin fayyaduu fi kan hawaasa Muslimaa itti fayyaddan warra argattan isiin haa taasisu. Kanaan alatti sababa garaagaraan warra qormaata kanarratti hirmaachu hin danda'iniif Rabbin wanta isiniif caaluu waan beekuuf waan caaluu isiniif haa laatu. Bakka jirtaniin warra milkooftani fi qaawwa hawaasa Muslimaa warra guuttan Rabbi isiin haa godhu.

Qormaata Gaarii !
Carraa Gaarii !


Muhaammadamiin kaasaawu(Amiira GBMUF)

@aaumsu
6👍4
በፌሚኒዝም ልክፍት የተለከፉ ሰዎችን ማከም የምዕራቡ ዓለም ከድህረ ቅኝ-ግዛት ቡሃላ የከፈተውን የጭንቅላት ጦርነት ከመዋጋት ነው ::

@aaumsu
👌9👍3
"ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ " አል ቀሰስ ፡ 24

ነብዩላህ ሙሳ ይህችን ንግግር የተናገሩ እለት ቤት ፣ ቤተሰብ ፣ ስራና ሚስት አግኝተው አደሩ።

አላህ ውስጥህን ስለሚያውቀው አትዋሸውምና አትዋሸው።ችግርና ስሞታህን ንገረው። ግንባርህን ደፍተህ ጠይቀው።

እንደ ሙሳ ሊሰጥህ
እንደ ዩኑስ ከችግር ማህፀን ሊያወጣህ
እንደ ኢብራሂም መከራን ሰላም ሊያደርግልህ
እንደ ሙሳ ባህሩን ሊከፍትልህ ይችላልና

በሮች ሁሉ ሲዘጉብህ የርሱን በር አንኳኳ።እሱን ልብህ ውስጥ አስገብተህ የልብህን በር ቆልፈው።
ይበቃሀልና።
5👍5
አንተ ኖሮህ የሌላቸው እንድትሰጣቸው ሲጠይቁህ ያለህን የሰጠህና ሁልጊዜም ቢሆን ጉዳዮችህን ይዘህ የምትቀርብለት ጌታ ባሮቹን እንዴት እንደምታስተናግድ እየፈተነህ እንደሆነ እወቅ !!

@aaumsu
👍113
ፈተናህን ስላቀለለው አብዝተህ አመስግነው !

    ነቢ አደም (ዐለይሂ ሰላም) ከእናታችን ሐዋ (ዐለይሃ ሰላም) ጋር ሆነው ልጃቸው ቃቢል ልጃቸው ሀቢልን የመግደሉን እውነታ በመቋቋም የተፈተኑት ፈተና የአንተ እንዳይሆን በማድረግ ፈተናህን ስላቀለለው ጌታህን አብዝተህ አመስግን :: ነቢ ኑሕ (ዐለይሂ ሰላም) ልጃቸው መርከቧን አሻፈረኝ ብሎ የአላህ ቅጣት በሆነው ማዕበል ተወስዶ ሲሄድ በማዬት የተፈተኑት ፈተና የአንተ እንዳይሆን በማድረግ ፈተናህን ያቀለለውን ጌታ አመስግነው :: ነቢ ኢብራሒም (ዐለይሂ ሰላም) በስተርጅና የተገኘውን ነቢ ኢስማኢል (ዐለይሂ ሰላም) ህፃን ሳለ ምድረ-በዳ ላይ ጥለው እንዲሄዱ ሲያድግ ደግሞ እንዲያርዱት በመጠየቅ ውስጥ የተፈተኑትን ፈተና ለአንተ ባለማድረግ ፈተናህን ያቀለለውን ጌታ አብዝተህ አመስግነው :: ነቢ የዕቁብ (ዐለይሂ ሰላም) የአይን ማረፊያቸው የሆነውን ነቢ ዩሱፍ(ዐለይሂ ሰላም) በራሳቸው ልጆች በመነጠቅ ውስጥ ያሳለፉትን ፈተና የአንተ ባለማድረግ ፈተናህን ያቀለለውን ጌታ አብዝተህ አመስግነው :: ሀቢቢ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሳይወለዱ አባታቸውን በማጣት : ህፃን ሆነው እናታቸውን ሲቀጥል አያታቸውን በማጣት : ጎልምሰው አጎታቸውን ሲቀጥልም 6 ልጆቻቸውን በመቅበር ውስጥ የተፈተኑትን ፈተና የአንተ ባለማድረግ ፈተናህን ያቀለለውን ጌታ አብዝተህ አመስግነው ::

    ስለ ሁሉም አልሃምዱሊላህ !

@aaumsu
🥰12👍6
አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ6 ኪሎ ጀመዓ እግር ኳስ ውድድር ምዝገባ መከፈቱን ስንገልጽ በደስታ ነው!
በ6 ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የሶሻል ሴክተር የተዘጋጀው ይህ የእግር ኳስ ውድድር በጤናማ የውድድር መንፈስ ደስታን ለመፍጠር እና በሙስሊም ወንድማማቾች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር ጥሩ አጋጣሚ ነው።

እንዴት መሳተፍ ይቻላል?
1- 16 አባላት ያሉት ቡድን በመመስረት እና የአባላቱን ስም በመጻፍ በpdf ወይም doc ፋይል አዘጋጁ። ቡድኑን እንደፈለጋችሁት/እንደምትቀራረቡት መመስረት ትችላላችሁ።
2- የቡድን መሪ ምረጡ።
3- ለቡድናችሁ ኢስላማዊ የሆነ ስም አውጡ(optional)።
4- ከታች ባለው link ምዝገባውን ያከናውኑ።

https://forms.gle/BuF6suXSKotNncrn7

NB: ውድድሩ ላይ መሳተፍ የሚችለው የ Main ወይም FBE ተማሪ/ነዋሪ የሆነ ብቻ ነው !

@AAU6KiloJemea
🔥51👍1😡1
Assalaamu Alaykum Waraahmatullaahi Wabarakaatuh

Dorgommii kubbaa miilaa Jama'aa 6 kiiloo yeroo dheeraa eegamaa turef galmeen eegaluu isaa yoo ibsinu gammachuu guddaadhaani!
Seektara hawaasummaa Jama'aa Barattoota Musliimaa 6 Kiilootiin kan qophaa'e dorgommiin kubbaa miilaa kun miira dorgommii fayya qabeessa ta'een gammachuu uumuu fi walitti dhufeenya obbolaawwan Muslimaa gidduu jiru cimsuuf carraa gaarii dha.

Akkamitti hirmaachuu dandeenya?
1- Garee miseensota 16 qabu ijaaruun maqaa miseensotaa barreessuudhaan faayila pdf ykn doc qopheessaa. Garee sana akka barbaaddanitti/akka itti dhihaattanitti ijaaruu dandeessu.
2- Dursaa garee filadhaa.
3- Garee keessaniif maqaa Islaamawaa ta'e filadhaa (optional...dhiisunis ni danda'ama).
4- Liinkii armaan gadiitti argamuun galmee taasisa.

https://forms.gle/BuF6suXSKotNncrn7

NB: Dorgommii kanarratti hirmaachu kan danda'u barataa/jiraataa kaampaasii Main ykn FBE kan tahe qofaa !

@AAU6KiloJemea
🔥2
ልቡ ውስጥ የአኼራ ቤቱን አሳምሮ እየገነባ ያለን ጀግና የዱንያ ቤቱን ቢያፈርሱበት ምን ሊጎድልበት ? ምንም !

@MohammadamminKassaw
32👍4🫡2🔥1👏1
🥀 Daily Reminder 91🥀

فَٱسۡتَبِقُواْ ٱلۡخَيۡرَٰتِۚ إِلَى ٱللَّهِ مَرۡجِعُكُمۡ جَمِيعٗا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ(48)

"በጎ ሥራዎችንም (ለመሥራት) ተሽቀዳደሙ፤ መመለሻችሁ በጠቅላላ ወደ አላህ ነው፡፡ በእርሱም ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር ይነግራችኋል!!"

Surah Al-Ma'idah; 48

@aaumsu
8👍3