AAU - Muslim Students Union
6.45K subscribers
2.68K photos
149 videos
51 files
765 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
ለተመራቂ ተማሪዎች !

   በመጀመሪያ ለዚህ ላበቃችሁ አላህ ላቅ ያለ ምስጋና ይድረስ :: ስኬታችሁንም ከሚጠበቀው በላይ ያደርግ ዘንድ ዱዓችን ነው :: በመቀጠል ጀመዓችን የአአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ያቋቋመው የAAUMSU GC ኮሚቴ ወደተግባር መግባቱን ስናበስር ከታላቅ ደስታ ጋር ነው። ስለሆነም ስለፕሮግራሞቹ አጠቃላይ ይዘት የሚገልፅና አጠቃላይ ሂደቱን የሚያብራራ የመወያያ ግሩፕ ተከፍቷል። እናንተም ግሩፑን በመቀላቀል ያዘጋጀናቸው ፕሮግራሞች ተሳታፊና ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛችሗል። ለዚህም ሲባል የተዘጋጀውን google form ይሙሉ።

            የአአዩሙተህ GC ኮሚቴ !

https://surveyheart.com/form/661ac020f1f407073283db81
👍5
Forwarded from Ibnu Ahmed


بسم الله الرحمن الرحيم

" የውስጥ ሰላም በአላህ ብቻ ነው። ሰዎች ወደ ፈጠራቸው ጌታ አላህ በተቃረቡ ቁጥር ውስጣቸው ሰላም ያገኛል፣ ይረጋጋል፣ ልባቸው ትሰክናለች። ያለ አላህ ሱ.ወ ደስታን ማግኘት የማይታሰብ ነው። የሰው ልጅ ምንም እንኳ ውጫዊ ገፅታው ያማረ የተዋበ ቢሆንም ከፈጣሪው ጋር ያለው ግንኙነት የላላ ከሆነ ሰላም ሊያገኝ አይችልም። ጭንቀት፣ ጥበት፣ ሃሳብ ይወረዋል። ጥርሱ ፈገግ ቢልም ደስታ ግን ይርቀዋል።

የአላህን ትዕዛዝ ከመፈፀም በላይ ወንጀልን ከመራቅ በላይ ልብን የሚያበራ ህይወትን የሚያስተካክል ነገር የለም። ሰዎች ከጌታቸው ጋር ያላቸውን ግኑኘነት ማስተካከል ከቻሉ ሌላው ነገር ሁሉ ይገራል፣ ቀላል ይሆናል፣ ነገሮች ይሳካሉ። ግኑኝነቱ ሲላላ ግን ነገሮች ይከብዳሉ ፣ ከኛ ይርቃሉ፣ ቀላል የነበሩ ነገሮች ይወሳሰባሉ። የነገሮች ሁሉ መገራት በአላህ ብቻ ነው።

ከውስጥ ሰላም በላይ ደግሞ ሰላም የለም። ምንም እንኳ ውጩ ሰላም ሆኖ ከራሳችን ጋር ያለን ግኑኝነት ሰላም ካልሆነ ሰላም ልናገኝ አንችልም። ሰላም የሚጀምረው ከውስጥ ነው። ይህ ሰላም የሚገኘው ደግሞ ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው። ከአላህ ጋር ያለንን ግኑኝነት ትዕዛዙን በመፈፀም እና ከወንጀል በመራቅ እናጠንክረው።

والله اعلم

@to2success
@to2success

👍42
🥀 Daily Reminder 87🥀

أَوَلَمۡ يَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ(52)

"አላህ ሲሳዩን ለሚሻው ሰው የሚያሰፋ የሚያጠብም መኾኑን አያውቁምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑት ሕዝቦች ግሣጼዎች አሉበት!!"

Surah Az-Zumer; 52

@aaumsu
👍31
ምሽቱን ለጋዛውያን ኢድ ነበር !

"ከጉልበተኛም በላይ ጉልበተኛ አለ!" እንደሚባለው ኢራን የበቀል እርምጃዋን በ100ዎች የሚቆጠሩ ድሮኖችን : ሮኬቶችንና ሚሳኢሎችን ወደ እስራኤል በማስወንጨፍ ጀምራለች :: ይህንንም ተከትሎ ከ6 ወራት ቡሃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጋዛ ሰማይ ቦንብ ከሚያዘንቡ ዲሞክራት ፓይለቶች ፀድቶ አድሯል :: ጋዛውያንም አርፈው ተራው ለእስራኤል ህዝቦች ሆኖ ነበር ::

ከኢራን የበቀል እርምጃ መልስ አሜሪካ እስራኤልን ዳግም እንዳታጠቃና ጦርነቱ አድማሱን እንዳያሰፋ አስጠንቅቃለች:: ኢራንም ለሚኖሩ ማንኛውም ምላሾች እጥፍ ድርብ አድርጋ ለመመለስ መዘጋጀቷን አስታውቃለች ::

ጋዛውያን እረፍታችሁ ደስታችን ነው !
ምዕራባውያን ከልጃችሁ እስራኤልጋ ውርደታችሁ ደስታችን ነው !

አላህ ሆይ:- ድሉን አቅርብ !!!

@MohammadamminKassaw
🔥21👍1
“If you are tempted by Satan, then seek refuge with Allah. Surely He is All-Hearing, All-Knowing.”

@aaumsu
👍4
ለኻሊድ ኢብኑ ወሊድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) "የሆነ ሰው እየሰደባችሁ ነው!" የሚል ስሞታ ደረሳቸው :: እሳቸውም "የስራ መዝገቡ የራሱ ነው:: በፈለገው ይሙላው::" ሲሉ መለሱ ::

@MohammadamminKassaw
👍9🥰31👌1
ለእስራኤል ዱዓ አድርጉ!

  ዱዓ አድርጉላት ! በፍልስጤማዊያን ላይ ያደረሰችው ግፍ ምን እንደሚመስል ሙሉ ለሙሉ በራሷ ላይ ደርሶ ታየው ዘንድ ዱዓ አድርጉ!

@aaumsu
👍17🫡2
ዓመታዊው የመፃህፍት ዓውደ ርእይ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ አዘጋጅነት የሚቀርበው 16ኛው ዓመታዊ የመፃህፍት ዓውደ ርእይ ከነገ ሰኞ ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ጀምሮ ለ አንድ ሳምንት በስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ ይካሄዳል።

መፅሐፍ የመግዛት እቅድ ያላችሁ ዋጋው ቅናሽ ነውና እድሉን ተጠቀሙት !

@aaumsu
🔥3👍1
You're not obligated to set yourself on fire to keep others warm.  Set boundaries, value your time and protect your energy.

@aaumsu
🥰9👍86👌2🫡1
ስለሰው ለአንተ የሚነግርህ ስላንተ ለሰው ይናገራል :: የሚወደውን ነገር ስታደርግለት በውሸት ሊያስወድድህ የሚሞከር የሚጠላውን ነገር ስታደርግ በውሸት እንድትጠላ ለማድረግ መሞከሩ አይቀርም ::

@aaumsu
👍112👌2
በህይዎት እያለን የእስራኤልን መጥፋትና የምዕራባውያንን ውርደት ያሳዬን !

@aaumsu
45👍7🥰5👌3
🥀 Daily Reminder 88🥀

فَٱذۡكُرُونِيٓ أَذۡكُرۡكُمۡ وَٱشۡكُرُواْ لِي وَلَا تَكۡفُرُونِ(152)

"አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና ለኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም!!"

Surah Al-Baqarah; 152

@aaumsu
👍3
Your children learn from you.
You’re nice, they are nice.
You’re nasty, they are too.
You’re happy, they are happy.
You’re sad, they are sad.
Your kids copy you, this is not
genetic - its learned.
They’re taught by you.
Think about it.
Be a better person to create better people......
It starts with You.

@aaumsu
👍13👌3
AAU - Muslim Students Union pinned «For graduating students! First of all, All praises are be to Allah, the one that allowed you to reach here. It is our prayer that your success will exceed your expectations. Next, it is with a great pleasure that we announce you the launching of the AAUMSU…»
What comes easy, will not always last. And what will last, will not always come easy.

@aaumsu
6🔥2👍1
May we witness Free Palestine soon !

@aaumsu
15👍2🥰2🫡1
قال الامام أحمد بن حنبل رحمه الله

ما رأيت أحدا أتبع للأثر من الشافعي .

سير أعلام النبلاء

""አንድም ሰው ከ ኢማሙ ሻፊዒዪ(ረ) በላይ የረሱልን ሱና የሚከተል አላየሁም።"

ኢማሙ አህመድ(ረ)
👍61
" አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና"አል በቀራ:152

በየትኛው ይበልጥ እንደሰት በምክኒያቱ አልያም በውጤቱ እርሱን በማውሳቱ ወይስ ስናወሳው እኛን በማውሳቱ......

አላህን መታዘዝህ ከችሮታው እንጂ ከምንም አይደለም።እንድታወሳው መርጦህ ፈቅዶልህ እንጂ ለፍተህ ከሌሎች በልጠህም አይደለም።

አስበኀዋል ግን በተወሰኑ ሆሂያት ምላስህን በማላወስ አላህን ስታወሳ ማውሳትህ ምንም የማይጨምርለት የተብቃቃው ልዕለ ሀያሉ ፈጣሪህ ከአንት በተሻለ መልኩ ሲያወሳህ

ምን አይነት ማዕረግና መመረጥ ነው በአላህ

አላህን ማውሳቱ በራሱ ያለውን የልብ መረጋጋት የቀመሰው እንጂ ሌላው አይገባውም። እንዲገባን እንጀርበው እስኪ።አላህ እናስታውሰው ያስታውሰናልና
👍112
Prophet Nüh lived in a house made of wool for 950 years.

The Prophet Muḥammad (PBUH) lived in a house was built of mud.

'Umar ibn al-Khattab's clothes had twelve patches.

This is because they understood that this world is a bridge and a bridge should not be taken as a home.

Beware of being afflicted with the disease of loving the dunyā.

Cure yourself by seeking knowledge, and contemplating the biographies of the wise scholars.

This is the only way.

@aaumsu
👍21
We never stop talking about palestine.

From the river to the sea Palestine will be free. 🇵🇸

@aaumsu
33👍6
ዝሆንና ዳክዬ ይለያያሉ !

እንማር ዘንድ ከሰማሁት አጭር ታሪክ ላጋራችሁ (የእንስሳት ስለሆነ እውነትነቱ ያጠራጥራል¡):-

   ከእለታት አንድ ቀን ቀበሮ ወደ ዝሆን በመምጣት "ዝሆን ሆይ! ዳክዬ ከጀርባህ ስላንተ መጥፎ ነገሮችን እያወራች ነው:: ስላንተ ካንተ ያልሆነን ውሸት እየፈጣጠረች ማሰራጨቱን ተያይዛዋለች:: በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው:: መቀጣጫ አድርጋት::" አለች :: ዝሆኑም በመኮሳተር "ትምህርት አደርጋታለሁ :: ያላትን አጥንት በሙሉ እሰባብርላታለሁ :: ሁሉንም ለእኔ ተይውና ወደ መኝታሽ ተመለሺ::" አላት ::

   በቀጣዩ ቀን ቀበሮዋ ወደ ዝሆኑ በመመለስ "ቃል የገባኸውን ቅጣት በዳክዬዋ ላይ አላሳረፍክም:: ይህኮ ቀላል ጉዳይ አይደለም:: ዳክዬዋ አሁንም በአንተ ላይ መቅጠፏን አላቆመችም:: ዝም ማለቱን አቁመህ የሚገባትን ስጣት::" አለች :: ዝሆኑም በማጉረምረም  "ትክክል ነሽ! የማትረሳውን ቅጣት የምቀጣበት ሰዓቱ አሁን ነው:: አንቺ ሂጂ:: እኔ እወጣዋለሁ::" አላት ::

   በ3ኛውም ቀን ቀበሮዋ ዝሆኑን ዳግም በመጠጋት "በጣም እየታገስክ ነው:: እመነኝ ዳክዬዋ ስላንተ የምታወራው ነገር በጣም መጥፎ ነው:: ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስተምራት::" አለች:: ዝሆኑም ትንሽ አሰብ አድርጎ ቀበሮዋን "ይሁን! ሄጄ መቅጣት ግዴታዬ ነው:: ግን መቁረጫ መፍለጫና አካፋ ስለሚያስፈልገኝ አምጪልኝ :: ቆራርጨ በመግደል መቅበር አለብኝ ::" አለ :: ቀበሮዋም ፈጥና በመሄድ የታዘዘችውን ይዛ በመምጣት ለዝሆኑ አቀበለች:: ዝሆኑ ግን ወደ ዳክዬዋ በመሄድ ፋንታ መሳሪያዎቹን ይዞ ወደ እርሻ ማሳው አመራ :: ቀበሮዋም በመገረም "ሄደህ ዳክዬዋን እንደምትቀጣ ከነገርከኝ ቡሃላ ምን እየሰራህ እንዳለህ ገብቶሃል?" አለችው ::

   ዝሆኑም ፈገግ በማለት "እኔ በስራዬ ቢዚ ነኝ:: ስራዋ ማውራትና ጫጫታ መፍጠር ለሆነባት ዳክዬ የምጨነቅበት ጊዜ የለኝም:: እኔ ጥንካሬንና ጥበብን የምገልፅ የአላህ ድንቅ ፍጥረት ነኝ:: በወረኛነትና ግርታ በመፍጠር ለሚታወቅ ፍጥረት ምላሽ በመስጠት ወደሗላ የምልበት ምክንያት የለኝም:: ስለዚህ ስራዬን እንድሰራ ተይኝ:: መሳሪያዎችሽን ስጨርስ እመልሳለሁ ::" በማለት ድንቅ ምላሽ ሰጣት ::

ትምህርት:- በህይዎት ውስጥ ምስለ ዳክዬ የሆኑ ብዙ ሰዎች ከጀርባችሁ ሆነው ሀሜትን ያሰራጫሉ :: ውሸትን ከመፍጠር ጀምረው እናንተን የሚጠሉ ሰዎች እስከ መመልመልም ይደርሳሉ :: ነገር ግን የሚፈልጉትን ትኩረት ልትሰጣቸው አይገባም :: በጥንካሬና በጥበብ እንደተሞላው ዝሆን ሁኑ :: በራሳችሁ ህይዎት ቢዚ በመሆን የእነሱን ሀሜት ከመጋፈጥ ራቁ :: ራሳችሁን ማጠናከርን የራሳችሁ የመጀመሪያ ፕሮጀክት አድርጉ :: ዝሆን ከዳክዬ እንደሚለይ በመረዳትም ለዳክዬ ጥቃት በቀበሮ ምክር ሳይሆን የዝሆንን መንገድ በመከተል ምላሽ ስጡ ::

@MohammadamminKassaw
👍14🔥3