AAU - Muslim Students Union
Photo
ረመዷን2️⃣9️⃣
(ወደ ጽናት)⓶
፨፨፨
<<እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡>>[አ'ሹራ፡15]
፨፨፨
ጊዜ ይሄዳል፤ቀናት ተደማምረው ወራት ይተካሉ፤አላህ ድጋሚ ከሚያገኙት ያድርገንና ረመዷንም ተመልሶ ይመጣል፤ታዲያ...የሚመጣው ረመዷን የዘንድሮው የጨመረልንን መልካም ነገር እንደ መሠረት ተጠቅሞ ወደ ሌላ የተሻለ ከፍታ የሚያደርሰን ይሆን ዘንድ ከአሁኑ አቋማችን ሳንመለስ ተዘጋጅተን ልንጠብቀው ይገባል።"አንድ ዓመት ግን ሩቅ አይደለም?"
.
*
ታዲያ!መጭው ጊዜ በጽናት እንዴት ይለፍ?
.
፨፨፨
<<አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡>>[ፋጢር:28]
፨፨፨
.
ብዙዎቻችን ስለሶላት አሰጋገድና መሠረታዊ ነገሮች ከቤተሰብ የወረስነው ተለምዷዊ ዕውቀት ይኖረን ይሆናል።ይህ መሠረታዊ ዕውቀት ጥሩ ቢሆንም፣ በአላህ መንገድ ላይ ለመጽናት ግን ዋስትና አይሆንም።አላህን ይበልጥ ስታውቀው ይበልጥ ትጠነቀቀዋለህ።የሱን ኃያልነት ስትረዳ በፍርሀት፣የእዝነቱ ስፋት ሲገባህ ደግሞ በተስፋ እየተገዛኸው ትኖራለህ።የተፈጠርክበትን ዓላማ የምታሳካው በደነገገልህ ሸሪዓ ብቻ ነውና ዲኑን ይበልጥ ማወቅ ለመጽናት ይረዳሀል።
*
አላህ የሚወሳባቸው፣ የሱ ዲን የሚማርባቸው ስብስቦች ላይ ስትዘወትር ያለህ ላይ እየጨመርክ ትሄዳለህ እንጅ መንገድ አትስትም።ያላወቁትን በማወቅ፤ያወቁትን በማስፋት ወደ አላህ ይበልጥ መቅረብ፣የጽናት ሰው መሆን ይቻላል።የወንጀልን አስከፊነት፣የኸይር ስራን ምንዳ በደንብ ስናውቅ ዓመቱን ሙሉ የዒባዳ ዓመት ማድረግ እንችላለን።
*
ከዲን አንፃር ስናየው፣ትላንትና ዛሬያችንን አንድ አድርገን እየኖርን ያለነው ጥቂት አይደለንም።ትላንትም ዛሬም ቁርኣንን ማንበብ አንችልም፤ወይም አነባበባችንን እስከዛሬ አልተስተካከለም።ስለ ዐቂዳችን ብንጠየቅ መልስ የለንም፤ሶላታችንና ጾማችንም ተለምዶ እንጅ በትክክል ከአላህ ሒሳብን በመፈለግ የሚፈፀሙ አይደሉም።
*
ትምህርትን እያጠኑና እየተረዱ፣ቀኑን በክላስ፣ሌሊቱን በንባብ እያሳለፉ ቁርኣንን ማንበብ አለመቻልንና፣የሶላትን ደንብ በሚገባ አለማወቅን ከምንም አለመቁጠር ከተማረና የተሻለ አረዳድን አዳብሯል ከሚባል ሰው የሚጠበቅ ተግባር አይደለም።እርግጥ ግቢ የተገኘንበት የመጀመሪያ ዓላማ ዓለማዊ ትምህርትን ፍለጋ ነው።ከዚህም ፈጽሞ ልንዘናጋ አይገባም።የቤተሰብ አማና ብሎም የዚህችን ዓለም ስንቅ የምንሰንቅበት ትልቅ መሣሪያ ነውና።
*
ይህ ማለት ግን ሙሉ ነገራችንን እሱ ላይ ማጥፋት አለብን ማለት አይደለም።በሁለቱም ስኬታማ ሆኖ መመረቅ እንደሚቻል በማመን ለሁለቱም መትጋት ይገባል።ለዚህም የሚያግዘው በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ የሚባክንን ጊዜ ቀንሶ ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም ይሆናል።
*
ከረመዷን በኋላ የዕውቀት ቦታዎች ላይ አለመገኘት ረመዷን ላይ የሸመትነውን መልካም ነገር እንድናጣና ወደቀድሞው ማንነታችን እንድንመለስ የሚያደርግ ሌላኛው ምክንያት ነው።
.
ዲንን በአግባቡ አለመረዳትና በደንብ አለማወቅ ያለው መጥፎ ውጤት በኛ እንደማይገደብ መገንዘብ መቻል አለብን።ኢስላም በኛ በኩል ለቀጣዩ ትውልድ እንደሚተላለፍ መዘንጋት የለብንም።
❓ወንድሜ ሆይ!ሩቅ ሊመስለህ ቢችልም የቤተሰብ አስተዳዳሪ፣የልጆች አባት መሆንህ የማይቀር ነው።አሁን ያለህበት ሁኔታ ለዛ የሚመጥን ነው?
ለልጆችህ የምታወርሰው ኢስላማዊ ዕውቀትና ስነ-ምግባር ይበልጥ የምታዳብረውስ መቼ ነው?ከአሁኑ አይደለምን?
❓እህቴ ሆይ! እየተማርሽ ይሆናል።ሆኖም ግን ትክክለኛ ሚናሽና ክብርሽ ኢስላማዊ ቤተሰብ መገንባት ላይ እንደሆነ አትዘንጊ።ለዛ የሚሆን ስንቅ አለሽ?የምትውይውስ ስንቅሽን የምትሰንቂበት ቦታ ነው ወይስ ልጆችሽን ልታይበት የማትፈልጊበት ቦታ?ከጊዜሽ ቀንሰሽ ለዋናው ዓላማሽ መዘጋጀትስ የለብሽም?
.
‼️ጊዜው ከምንም ጊዜውም በላይ ዲንን ለመማር የሚጠቅሙ ዕድሎች የተመቻቹበት ጊዜ ነው።ስልክ፣ኢንተርኔትና ሌሎቹን ለዚህ ብንጠቀማቸው ከጽናት ባለቤቶች የመሆን ዕድላችን ሰፊ ነውና ጸጋዎችን በመጠቀም ላይ አደራ!
፨፨፨
«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ» በል፡፡[ጧሀ:114]
፨፨፨
🌱አላህ ሆይ!ረመዷንን በኛ ላይ መላልስልን!...አሚን!
⭕️የዕለቱ ቻሌንጅ⭕️
.
1️⃣በዕውቀት ወደ ጽናት ለመጓዝ መወሰን
.
2️⃣ የአንድ ዓመት የዒልም ዕቅድ ማውጣት፤የሚመጣውን ክረምትም በደንብ ለመጠቀም በመወሰን ከአሁኑ ዕቅድ ማውጣት፣
.
3️⃣ የጀመዓ ደርሶችና፣ፕሮግራሞች ላይ ለመገኘት መወሰን
🍀Principle of The Year🍀
A year of "firmness through Seeking Knowledge!"
🌱 አሏሁ'መ ኢነከ ዐፉውን ቱሒቡል ዐፍዎ ፈዕፉ ዐና!
#AAiTJemeaRamadanReminders2
@aaumsu

👍1
80-81ኛ - 300 ብር - SSC and FBE
እህቶቻችንን አላህ ይቀበላቸው :: ይውዳቸው :: የሚወዱትን የሚያስደስታቸውንና እሱ አላህ የሚወደውን ነገር ሁሉ ይስጣቸው :: የአኼራ ቤታቸውን በጀነተል-ፊርደውስ ይገንባ ::

👍2🔥2
ለሐዋሳ ሪፈራል ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ግንባታ 45500 ብር ደርሰናል !
መስጂድን የገነባ አላህ በጀነት ቤት ይገነባለታል :: መስጂዱ እንዲሰራ ሰበብ ሆንን ማለት የነገ ተስፋ የሆኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዲናቸውን በነፃነት የሚማሩበት ማዕከል አገኙ ማለት ነው ::
ተልዕኳችን ትልቅ ነውና እንረባረብ :: ከAAUMSU በትንሹ 50ሺ እንሰብስብ :: ለዚያ ደግሞ 4500 ብር ብቻ ይቀረናል :: 1 ሰው መሸፈን ይችላል :: 45 ሰውም 100 ብር ቢሰጥ ይሞላዋል ::
ኸይር ነውና እንረባረብ :: ወደ አኼራ ቀድሞን የሚሄድ ሀብት ነውና እንሽቀዳደም ::
የማስገቢያ አካውንት :- 1000485306432
AAU Muslim students union :: ማስገባታችሁን screenshot በማድረግ @MOHAMMADAMMINM ላኩልኝ ::
Let us do it my beloved ones !

👍8❤4
83-86ኛ - 450 ብር !
ከንግድ ኮሌጅ 150 ብር : ከመሐንዲሶች ሰፈር 100 ብር : ከሰላሙ ሰፈር (ዶክተሮች) 100 ብር እንዲሁም ከቤተ-መንግስት አቅራቢያ (100 ብር) ለሐዋሳ ወንድሞቻችን መስጂድ ግንባታ አስገብተዋል ::
አላህ ይቀበላቸው :: ህይዎታቸውን ብርሃን በብርሃን ያድርግ :: ችግራቸውን ያስወግድ :: ድሎታቸውን ያብዛ :: ጥሩ ትዳርና መልካም ልጆችን ይስጣቸው :: ሰፊ ሐብትና ሙሉ ጠና ይወፍቃቸው :: ረጂም እድሜና ኢማን ይለግሳቸው :: የእርሱን ቤት ለመገንብት እንደተረባረቡት ቤታቸውን በጀነተል-ፊርደውስ ይገንባ ::
ልደታ : ጥቁር አንበሳ : main campus and... አለን በሉሉሉሉሉ !!!!

👏6👍3
Challenge 50K - up to megrib!
Let us challenge ourselves to challenge 50K for our brothers mesjid (Hawassa referral campus Muslim students Mesjid) !
We are at 46250 !!
Left with 3750 !!!
Let us do it my beloved brothers and sisters in Islam !
Let us show our unity and strength with in fulfilling our responsibility!
The account is 1000485306432
AAU Muslim students union . Send me the screenshot of your slip via @Mohammadamminm .

👌5😡1
1100 ብር - አላሁ አክበርርርር !
አላህ ይቀበላቸው :: ኸይር ጀዛቸውን ይክፈል :: የዱንያ ቤታቸውን ያሳምር :: የአኼራ ቤታቸውን በጀነተል-ፊርደውስ ውስጥ ይገንባ ::
ለ50ሺ 2550 ብር ብቻ ይቀረናል!
"እሳትን በተምር ክፋይ እንኳ ቢሆን ተጠንቀቋት!" ብለዋልና አነሰ በዛ ሳትሉ ስጡ ::

👏8👍5🔥1
91ኛ - 250 ብር !
አላህ ይቀበላቸው :: ያስደስታቸው :: ይውደዳቸው :: ያስወድዳቸው :: ሰፊ ሀብት ከረጂም እድሜ ሙሉ ጤናና ኢማን ጋር ይስጣቸው :: የአኼራ ቤታቸውንም በጀነተል-ፊርደውስ ይገንባ ::
ለ50ሺ 2200 ይቀረናል!!
እንሙላው !!

👏4👍1
👌18👍7❤4
በመስጂደል ሀረም ዛሬ ምሽት የሚሰደገደውን የ1445 ረመዳን የመጨረሻ ተራዊህ ሰላት ተወዳጁ ሸይኽ ያሲር አድ-ደውሰሪ እና ሸይኽ ጁሃኒ እንደሚመሩት ታውቋል። ፕሮግራሙን ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።
👇👇👇
https://www.youtube.com/live/moQtMet7F7w?si=tGzhUtTt_3eDzNt6

🔥5🥰2👍1