AAU - Muslim Students Union
6.48K subscribers
2.76K photos
151 videos
51 files
767 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
ከላይ የምትመለከቱት የሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ነው :: ቦታው ጠባብ መስጂዱ ደግሞ ሊፈርስ አንድ ሀሙስ የቀረው ይመስላል :: ቦታውን ያስፋፉና አዲስ መስጂድ ይገነቡ ዘንድ የበኩላችንን አስተዋፅዖ እንድናደርግ ጠይቀውናል ::

እኛም ጥሪውን ተቀብለን እስካሁን 40180 ብር ከ76 ሰው ሰብስበናል :: በርብርቡ ላይ የ10ኛ ክፍል ተማሪ ተሳትፏል :: ከውጭ ያሉ እናት ተሳትፈዋል :: ከAAU ተመርቀው የወጡ እህት ወንድሞች ተሳትፈዋል :: ከወራቤና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እህትና ወንድሞች ተሳትፈዋል :: ከAAUም ከተለያየ ካምፓስ ተሳትፈዋል ::

ተማሪው ግን 76 ብቻ አይደለም :: ቢያንስ 1ሺ ተማሪ 100 ብር ቢሰጥ ለወንድሞቻችን 100ሺ መስጠት እንችላለን ማለት ነው :: በሰሜን : በምስራቅ : በደቡብ : በምዕራብ ያላችሁ ወዳጆቻችን አለን በሉን :: ተመርቃችሁ የወጣችሁ ቀደምቶቻችን አለን በሉን :: ተማሪ ያልሆናችሁም ተሳተፉ :: መሳተፍ አቅማችሁ ያልሆነ share በማድረግ አሳትፉ ::

ለትውልድ የሚቀር ተቋምን በመገንባትና ወንድም እህቶቻችንን በማስደሰት ውስጥ የአኼራ ቤታችንን እንስራ !

የማስገቢያ አካውንት :- 1000485306432
AAU Muslim students union :: ማስገባታችሁን screenshot በማድረግ @MOHAMMADAMMINM ላኩልኝ ::

@aaumsu
🔥5
77ኛ - 200 ብር - ከFBE

"ለሀገራችን ሰላም ያመጣ ዘንድና ለፈለስጢን ወንድሞቻችን ድሉን ይሰጥ ዘንድ ዱዓ አድርጉ:: ሐጃዎችም አሉብኝ ዱዓ አድርጉ::" ብላለች ::

ወያ ፈለስጢን ?! ወያ ገዛህ?! አላህ ድሉን ያቅርብ :: አላህ የምዕራቡን አለም ውርደት ያሳዬን :: የሀገራችንንም ሰላም ያምጣ :: የእህታችንንም ሐጃዎች ይሙላ ::

78ኛ ከዬት ይሆን ?
ምስራቆች አለን በሉ !
ምዕራቦች አለን በሉ !
በሰሜን በደቡብ ያላችሁም አለን በሉ !

አብረን ታራክ እንስራ !!!
👍5
ሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ከምትማር እህት የተላከ መልዕክት:-

"የአንድ ግንባታ ክፍሎች አይደለን ? የአንዳችን ችግር  እኩል የሚያመን ደም ሳይሆን… ጥቅም ሳይሆን ደንቁ የአላህ ዲን ያስተሳሰረን ሙስሊሞች አይደለን ?….”እንዴት ሆነው ይሆን” ብሎ ሚያሳስበን “የራሴ” ሚባል ቃል ከ ቃላት መዝገባችን ውስጥ ቢፈለግ የሌለን ሙስሊሞች አይደለን?
ትንሷን የአላህ ቤት ያያቹሀት ግዜ፣ የቆመው አቋቋም አስፈሪ የሆነውን የመስጂዳችንን ግድግዳ ያያቹ ግዜ፣የውዷን የአላህ ቤት እንዲ መጎሳቆል በአካል ሳይሆን በምስል ያያቹሃት ግዜ ከኛ እኩል የተሰማቹ፣ እዚች መስጂድ ውስጥ ሳትሰግዱ ከሰግድነው፣ከኖርንበት ከኛ እኩል ንፋሱም፣ቀዳዳውም ሁሉም የታያቹ፣ የተሰማቹ  ያስተሳሰረን ጉዳይ ታላቅ ፣ ከጥቅምም ከመተዋወቅም ከሁሉ ነገር በላይ ስለሆነ ነዉ፡፡

ምስጋናውን ከየት እንጀምረ… እንደውም ለምን እንደዚ አይሆንም ……እሺ ካላቹን ቀጠሮ እንያዝ:: ለናነት ሚመጥን ቦታ ስንፈልግ የዱኒያዉ ሁሉ ረክሶ ታየን እና ሩቅ ቢመስልም ቅርብ ወደሆነዉ  ዱኒያ ላይ ሳይሆን ወደ አኾራ እናሻግረዉ ? ….…መሰብሰቢያችንን በዛ በጭንቅ ቀን ከአርሹ ጥላ ስር እሱዉ ዘንድ ከትቦልን፣ ለሱ ብለዉ ለተዋደዱ  ባሮቹ የሰጣቸውን ሽልማት ይዘን በዱኒያ ላይ የአላህን ቤት ለገነቡት ቃል የተገባው የጀነት ውስጥ ቤት ውስጥ…..ቀጠሮውን እዛ እናርገዉ፡፡

ተሳሰሩበት በተባልነው የአላህ ገመድ ላይ መተሳሰር ምን ማለት እንደሆነ ስላሳያቹን፣ከልብ መተሳሰብ ምን እንደሆነ ስላስተማራቹን አላህ  ኸይር ጀዛቹን በጀነት ይክፈላቹ፡፡"

@aaumsu
👍8🔥1👌1
78ኛ - 3720

45ሺ ይሙላ በሚል 3720 ብር ገቢ ሆኗል :: አላህ ይቀበላቸው :: ኸይራትን አከታትሎ በዱንያም በአኼራም ይወፍቃቸው ::

አላሁ አክበርርርርር ብለናል !!
ምስጋና ይድረሰው !!!
👍71🔥1
79ኛ - 100 ብር

አላህ ይቀበለው :: ለኸይር ነገሮች ሁሉ መክፈቻ ሰበብ ያድርግለት :: ጭንቀቶቹን ያስወግድ :: ዱንያውን ያሳምር :: የአኼራ ቤቱን በጀነተል-ፊርደውስ ይገንባ ::
👍1
AAU - Muslim Students Union
Photo
ረመዷን2️⃣9️⃣
(ወደ ጽናት)⓶
፨፨፨
<<እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡>>[አ'ሹራ፡15]
፨፨፨
ጊዜ ይሄዳል፤ቀናት ተደማምረው ወራት ይተካሉ፤አላህ ድጋሚ ከሚያገኙት ያድርገንና ረመዷንም ተመልሶ ይመጣል፤ታዲያ...የሚመጣው ረመዷን የዘንድሮው የጨመረልንን መልካም ነገር እንደ መሠረት ተጠቅሞ ወደ ሌላ የተሻለ ከፍታ የሚያደርሰን ይሆን ዘንድ ከአሁኑ አቋማችን ሳንመለስ ተዘጋጅተን ልንጠብቀው ይገባል።"አንድ ዓመት ግን ሩቅ አይደለም?"
.
*
ታዲያ!መጭው ጊዜ በጽናት እንዴት ይለፍ?
.
፨፨፨
<<አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡>>[ፋጢር:28]
፨፨፨
.
ብዙዎቻችን ስለሶላት አሰጋገድና መሠረታዊ ነገሮች ከቤተሰብ የወረስነው ተለምዷዊ ዕውቀት ይኖረን ይሆናል።ይህ መሠረታዊ ዕውቀት ጥሩ ቢሆንም፣ በአላህ መንገድ ላይ ለመጽናት ግን ዋስትና አይሆንም።አላህን ይበልጥ ስታውቀው ይበልጥ ትጠነቀቀዋለህ።የሱን ኃያልነት ስትረዳ በፍርሀት፣የእዝነቱ ስፋት ሲገባህ ደግሞ በተስፋ እየተገዛኸው ትኖራለህ።የተፈጠርክበትን ዓላማ የምታሳካው በደነገገልህ ሸሪዓ ብቻ ነውና ዲኑን ይበልጥ ማወቅ ለመጽናት ይረዳሀል።
*
አላህ የሚወሳባቸው፣ የሱ ዲን የሚማርባቸው ስብስቦች ላይ ስትዘወትር ያለህ ላይ እየጨመርክ ትሄዳለህ እንጅ መንገድ አትስትም።ያላወቁትን በማወቅ፤ያወቁትን በማስፋት ወደ አላህ ይበልጥ መቅረብ፣የጽናት ሰው መሆን ይቻላል።የወንጀልን አስከፊነት፣የኸይር ስራን ምንዳ በደንብ ስናውቅ ዓመቱን ሙሉ የዒባዳ ዓመት ማድረግ እንችላለን።
*
ከዲን አንፃር ስናየው፣ትላንትና ዛሬያችንን አንድ አድርገን እየኖርን ያለነው ጥቂት አይደለንም።ትላንትም ዛሬም ቁርኣንን ማንበብ አንችልም፤ወይም አነባበባችንን እስከዛሬ አልተስተካከለም።ስለ ዐቂዳችን ብንጠየቅ መልስ የለንም፤ሶላታችንና ጾማችንም ተለምዶ እንጅ በትክክል ከአላህ ሒሳብን በመፈለግ የሚፈፀሙ አይደሉም።
*
ትምህርትን እያጠኑና እየተረዱ፣ቀኑን በክላስ፣ሌሊቱን በንባብ እያሳለፉ  ቁርኣንን ማንበብ አለመቻልንና፣የሶላትን ደንብ በሚገባ አለማወቅን ከምንም አለመቁጠር ከተማረና የተሻለ አረዳድን አዳብሯል ከሚባል ሰው የሚጠበቅ ተግባር አይደለም።እርግጥ ግቢ የተገኘንበት የመጀመሪያ ዓላማ ዓለማዊ ትምህርትን ፍለጋ ነው።ከዚህም ፈጽሞ ልንዘናጋ አይገባም።የቤተሰብ አማና ብሎም የዚህችን ዓለም ስንቅ የምንሰንቅበት ትልቅ መሣሪያ ነውና።
*
ይህ ማለት ግን ሙሉ ነገራችንን እሱ ላይ ማጥፋት አለብን ማለት አይደለም።በሁለቱም ስኬታማ ሆኖ መመረቅ እንደሚቻል በማመን ለሁለቱም መትጋት ይገባል።ለዚህም የሚያግዘው በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ የሚባክንን ጊዜ ቀንሶ ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም ይሆናል።
*
ከረመዷን በኋላ የዕውቀት ቦታዎች ላይ አለመገኘት ረመዷን ላይ የሸመትነውን መልካም ነገር እንድናጣና ወደቀድሞው ማንነታችን እንድንመለስ የሚያደርግ ሌላኛው ምክንያት ነው።
.
ዲንን በአግባቡ አለመረዳትና በደንብ አለማወቅ ያለው መጥፎ ውጤት በኛ እንደማይገደብ መገንዘብ መቻል አለብን።ኢስላም በኛ በኩል ለቀጣዩ ትውልድ እንደሚተላለፍ መዘንጋት የለብንም።

ወንድሜ ሆይ!ሩቅ ሊመስለህ ቢችልም የቤተሰብ አስተዳዳሪ፣የልጆች አባት መሆንህ የማይቀር ነው።አሁን ያለህበት ሁኔታ ለዛ የሚመጥን ነው?
ለልጆችህ የምታወርሰው ኢስላማዊ ዕውቀትና ስነ-ምግባር ይበልጥ የምታዳብረውስ መቼ ነው?ከአሁኑ  አይደለምን?

እህቴ ሆይ! እየተማርሽ ይሆናል።ሆኖም ግን ትክክለኛ ሚናሽና ክብርሽ ኢስላማዊ ቤተሰብ መገንባት ላይ እንደሆነ አትዘንጊ።ለዛ የሚሆን ስንቅ አለሽ?የምትውይውስ ስንቅሽን የምትሰንቂበት ቦታ ነው ወይስ ልጆችሽን ልታይበት የማትፈልጊበት ቦታ?ከጊዜሽ ቀንሰሽ ለዋናው ዓላማሽ መዘጋጀትስ የለብሽም?
.
‼️ጊዜው ከምንም ጊዜውም በላይ ዲንን ለመማር የሚጠቅሙ ዕድሎች የተመቻቹበት ጊዜ ነው።ስልክ፣ኢንተርኔትና ሌሎቹን ለዚህ ብንጠቀማቸው ከጽናት ባለቤቶች የመሆን ዕድላችን ሰፊ ነውና ጸጋዎችን በመጠቀም ላይ አደራ!
፨፨፨
«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ» በል፡፡[ጧሀ:114]
፨፨፨
🌱አላህ ሆይ!ረመዷንን በኛ ላይ መላልስልን!...አሚን!

⭕️የዕለቱ ቻሌንጅ⭕️
.
1️⃣በዕውቀት ወደ ጽናት ለመጓዝ መወሰን
.
2️⃣ የአንድ ዓመት የዒልም ዕቅድ ማውጣት፤የሚመጣውን ክረምትም በደንብ ለመጠቀም በመወሰን ከአሁኑ ዕቅድ ማውጣት፣
.
3️⃣ የጀመዓ ደርሶችና፣ፕሮግራሞች ላይ ለመገኘት መወሰን

🍀Principle of The Year🍀
A year of "firmness through Seeking Knowledge!"

🌱 አሏሁ'መ ኢነከ ዐፉውን ቱሒቡል ዐፍዎ ፈዕፉ ዐና!

#AAiTJemeaRamadanReminders2
@aaumsu
👍1
80-81ኛ - 300 ብር - SSC and FBE

እህቶቻችንን አላህ ይቀበላቸው :: ይውዳቸው :: የሚወዱትን የሚያስደስታቸውንና እሱ አላህ የሚወደውን ነገር ሁሉ ይስጣቸው :: የአኼራ ቤታቸውን በጀነተል-ፊርደውስ ይገንባ ::
👍2🔥2
82ኛ-100 ብር - ከ4ኪሎ

አላህ ይቀበላቸው :: ኸይር ጀዛቸውን ይክፈል :: ዱንያቸውን ያሳምር :: አኼራቸውን ይሙላ ::

ተነቃቁ !
ተነቃነቁ !

እስከ ማታ 50K እንሙላ !!
እንረባረብ !!!
👍6👌21
ለሐዋሳ ሪፈራል ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ግንባታ 45500 ብር ደርሰናል !

መስጂድን የገነባ አላህ በጀነት ቤት ይገነባለታል :: መስጂዱ እንዲሰራ ሰበብ ሆንን ማለት የነገ ተስፋ የሆኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዲናቸውን በነፃነት የሚማሩበት ማዕከል አገኙ ማለት ነው ::

ተልዕኳችን ትልቅ ነውና እንረባረብ :: ከAAUMSU በትንሹ 50ሺ እንሰብስብ :: ለዚያ ደግሞ 4500 ብር ብቻ ይቀረናል :: 1 ሰው መሸፈን ይችላል :: 45 ሰውም 100 ብር ቢሰጥ ይሞላዋል ::

ኸይር ነውና እንረባረብ :: ወደ አኼራ ቀድሞን የሚሄድ ሀብት ነውና እንሽቀዳደም ::

የማስገቢያ አካውንት :- 1000485306432
AAU Muslim students union :: ማስገባታችሁን screenshot በማድረግ @MOHAMMADAMMINM ላኩልኝ ::

Let us do it my beloved ones !
👍84
83-86ኛ - 450 ብር !

ከንግድ ኮሌጅ 150 ብር : ከመሐንዲሶች ሰፈር 100 ብር : ከሰላሙ ሰፈር (ዶክተሮች) 100 ብር እንዲሁም ከቤተ-መንግስት አቅራቢያ (100 ብር) ለሐዋሳ ወንድሞቻችን መስጂድ ግንባታ አስገብተዋል ::

አላህ ይቀበላቸው :: ህይዎታቸውን ብርሃን በብርሃን ያድርግ :: ችግራቸውን ያስወግድ :: ድሎታቸውን ያብዛ :: ጥሩ ትዳርና መልካም ልጆችን ይስጣቸው :: ሰፊ ሐብትና ሙሉ ጠና ይወፍቃቸው :: ረጂም እድሜና ኢማን ይለግሳቸው :: የእርሱን ቤት ለመገንብት እንደተረባረቡት ቤታቸውን በጀነተል-ፊርደውስ ይገንባ ::

ልደታ : ጥቁር አንበሳ : main campus and... አለን በሉሉሉሉሉ !!!!
👏6👍3
87ኛ - 300 ብር - ከCommerce

ንግድ ኮሌጆች አሁንም ከፊት ናቸው:: ለሐዋሳ ወንድሞቻቸው መስጂድ እየተረባረቡ ነው :: አላህ ይቀበላቸው :: ኸይራትን አከታትሎ ይወፍቃቸው :: በሚወዱት በሚያስደስትና በሚወደው ነገር ይሸልማቸው :: ቤታቸውን በጀነት ይገንባ ::

መሐንዲሶች አለን በሉሉ!
ህንፃ ኮሌጆች አለንን በሉሉ !
ዶክተሮች አለን በሉሉሉ !!
Social ኢንጂነሪንግ ውስጥ ያላችሁም ተረባረቡ !!!
👍7
Challenge 50K - up to megrib!

Let us challenge ourselves to challenge 50K for our brothers mesjid (Hawassa referral campus Muslim students Mesjid) !
We are at 46250 !!
Left with 3750 !!!

Let us do it my beloved brothers and sisters in Islam !
Let us show our unity and strength with in fulfilling our responsibility!

The account is 1000485306432
AAU Muslim students union
. Send me the screenshot of your slip via @Mohammadamminm .
👌5😡1
ቻሌንጅ 50K በ100 ብር ተጀምሯል!

አላህ ሁልጊዜም ቢሆን ለኸይር ነገር ተሽቀዳዳሚና ቀዳሚ ያድርገው :: በዱንያም በአኼራም የሚያስደስት ነገር ይወፍቀው ::

Challenge 50K !
left with 3650 !
Challenge your account to challenge 50K!
👍4