AAU - Muslim Students Union
6.48K subscribers
2.76K photos
151 videos
51 files
767 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
100ብር - ሰፈረሰላም
"2 ወደ አኼራ ለሄዱ አያቶቼ ዱዓ አድርጉላቸው!"

አላህ በጀነተል-ፊርደውስ ይሞሽራየው። ከመላ ቤተሰቡ ጋር እስከ ዘላለሙ በጀነት ቤት ይሰባስባቸው:: ዱዓ አድርጉ ያ አህባቢ!!

5700 left to hit 45K !
ማን ነው ቀጣይ? main campus? Tikur anbessa ? Commerce? bishoftu?
👍3👌2
4ኪሎዎች አሁንም ከፊት ናቸው። ወንድማችን 100 ብር አስገብቷል። አላህ ይቀበለው። ኸይር ጀዛውን ይክፈል። ዱንያውን ያሳምር ። አኼራውን ይሙላ።

ሌሎቻችንስ ?
እንሳተፍ ያ አህባቢ !!

45ሺ ለመሙላት 5600 ብር ይቀረናል!
👍1
የረመዳን የመጨረሻው ቀን ሊሆን ይችላል ። 29ኛው ቀን መሆኑ ደግሞ ልዩ ያደርገዋል ። መልካም ስራዎች ይባዛሉ ።

የጀመርነው ንቅናቄ ደግሞ ይበልጥ ልዩ ያደርገዋል። የጀመርነው መንገድ የአላህን ቤት ለመገንባት ነው። "የአላህን ቤት የገነባ አላህ በጀነት ቤቶ ይገነባለታል!" የተባለለትን ማለት ነው። መስጂዱ ተማሪዎችን አንፆ ይሰራ ዘንድ መሆኑ ደግሞ ልዩ ያደርገዋል።

ስለዚህ ከተማሪዎች ለተማሪዎች መስጂድ እንረባረብ። ለሐዋሳ ሪፈራል ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ማለት ነው።

የማስገቢያ አካውንት :- 1000485306432
AAU Muslim students union :: ማስገባታችሁን screenshot በማድረግ @MOHAMMADAMMINM ላኩልኝ ::
👍1
100 ብር - ከልደታ
"ፍሬሽ ነኝ ። ሐጃ አለብኝ። ዱዓ አድርጉልኝ።" ብላለች ። አላህ ሐጃዎቿን ይሙላላት። እጥፍ ድርብ አድርጎ ይክፈላት። የኸይራት በሮችን ይክፈትላት። ዱንያ አኼራዋን ያሳምር።
👍1
200 ብር ገቢ ሆኗል!!

አላህ ይቀበላቸው። እጥፍ ድርብ አድርጎ ይክፈላቸው። ዱንያ አኼራቸውን ያሳምር።

እንንቀሳቀስ ያ አህባቢ!!
👍1
200+50+100=350

ከFBEና AAiT የገባ ነው :: አላህ ይቀበላቸው:: እጥፍ ድርብ አድርጎ ይተካቸው:: ለኸይር ነገር ሁሉ መክፈቻ ያድርግላቸው:: ዱንያቸወን ያሳምር:: አኼራቸውን ይሙላ::
👍1
🥀 Daily Reminder 81🥀

فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَصَدَفَ عَنۡهَاۗ سَنَجۡزِي ٱلَّذِينَ يَصۡدِفُونَ عَنۡ ءَايَٰتِنَا سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ بِمَا كَانُواْ يَصۡدِفُونَ(157)

"በአላህም አንቀጾች ካስተባበለና ከእርሷም ከዞረ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነዚያን አንቀጾቻችንን የሚተውትን ይተውት በነበሩት ምክንያት ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እንቀጣቸዋለን!!"

Surah Al-An'am; 157
100ብር - ከልደታ

ህንፃ ኮሌጆች አልተቻሉም :: አላህ ኸይር ጀዛዋን ይክፈልልን :: ረጂም እድሜ : ሰፊ ሀብት : ሙሉ ጤና ከኢማን ጋር ይወፍቃት :: መዘውተሪያዋን ጀነተል-ፊርደውስ ያድርግ ::
👍1
ከላይ የምትመለከቱት የሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ነው :: ቦታው ጠባብ መስጂዱ ደግሞ ሊፈርስ አንድ ሀሙስ የቀረው ይመስላል :: ቦታውን ያስፋፉና አዲስ መስጂድ ይገነቡ ዘንድ የበኩላችንን አስተዋፅዖ እንድናደርግ ጠይቀውናል ::

እኛም ጥሪውን ተቀብለን እስካሁን 40180 ብር ከ76 ሰው ሰብስበናል :: በርብርቡ ላይ የ10ኛ ክፍል ተማሪ ተሳትፏል :: ከውጭ ያሉ እናት ተሳትፈዋል :: ከAAU ተመርቀው የወጡ እህት ወንድሞች ተሳትፈዋል :: ከወራቤና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እህትና ወንድሞች ተሳትፈዋል :: ከAAUም ከተለያየ ካምፓስ ተሳትፈዋል ::

ተማሪው ግን 76 ብቻ አይደለም :: ቢያንስ 1ሺ ተማሪ 100 ብር ቢሰጥ ለወንድሞቻችን 100ሺ መስጠት እንችላለን ማለት ነው :: በሰሜን : በምስራቅ : በደቡብ : በምዕራብ ያላችሁ ወዳጆቻችን አለን በሉን :: ተመርቃችሁ የወጣችሁ ቀደምቶቻችን አለን በሉን :: ተማሪ ያልሆናችሁም ተሳተፉ :: መሳተፍ አቅማችሁ ያልሆነ share በማድረግ አሳትፉ ::

ለትውልድ የሚቀር ተቋምን በመገንባትና ወንድም እህቶቻችንን በማስደሰት ውስጥ የአኼራ ቤታችንን እንስራ !

የማስገቢያ አካውንት :- 1000485306432
AAU Muslim students union :: ማስገባታችሁን screenshot በማድረግ @MOHAMMADAMMINM ላኩልኝ ::

@aaumsu
🔥5
77ኛ - 200 ብር - ከFBE

"ለሀገራችን ሰላም ያመጣ ዘንድና ለፈለስጢን ወንድሞቻችን ድሉን ይሰጥ ዘንድ ዱዓ አድርጉ:: ሐጃዎችም አሉብኝ ዱዓ አድርጉ::" ብላለች ::

ወያ ፈለስጢን ?! ወያ ገዛህ?! አላህ ድሉን ያቅርብ :: አላህ የምዕራቡን አለም ውርደት ያሳዬን :: የሀገራችንንም ሰላም ያምጣ :: የእህታችንንም ሐጃዎች ይሙላ ::

78ኛ ከዬት ይሆን ?
ምስራቆች አለን በሉ !
ምዕራቦች አለን በሉ !
በሰሜን በደቡብ ያላችሁም አለን በሉ !

አብረን ታራክ እንስራ !!!
👍5
ሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ከምትማር እህት የተላከ መልዕክት:-

"የአንድ ግንባታ ክፍሎች አይደለን ? የአንዳችን ችግር  እኩል የሚያመን ደም ሳይሆን… ጥቅም ሳይሆን ደንቁ የአላህ ዲን ያስተሳሰረን ሙስሊሞች አይደለን ?….”እንዴት ሆነው ይሆን” ብሎ ሚያሳስበን “የራሴ” ሚባል ቃል ከ ቃላት መዝገባችን ውስጥ ቢፈለግ የሌለን ሙስሊሞች አይደለን?
ትንሷን የአላህ ቤት ያያቹሀት ግዜ፣ የቆመው አቋቋም አስፈሪ የሆነውን የመስጂዳችንን ግድግዳ ያያቹ ግዜ፣የውዷን የአላህ ቤት እንዲ መጎሳቆል በአካል ሳይሆን በምስል ያያቹሃት ግዜ ከኛ እኩል የተሰማቹ፣ እዚች መስጂድ ውስጥ ሳትሰግዱ ከሰግድነው፣ከኖርንበት ከኛ እኩል ንፋሱም፣ቀዳዳውም ሁሉም የታያቹ፣ የተሰማቹ  ያስተሳሰረን ጉዳይ ታላቅ ፣ ከጥቅምም ከመተዋወቅም ከሁሉ ነገር በላይ ስለሆነ ነዉ፡፡

ምስጋናውን ከየት እንጀምረ… እንደውም ለምን እንደዚ አይሆንም ……እሺ ካላቹን ቀጠሮ እንያዝ:: ለናነት ሚመጥን ቦታ ስንፈልግ የዱኒያዉ ሁሉ ረክሶ ታየን እና ሩቅ ቢመስልም ቅርብ ወደሆነዉ  ዱኒያ ላይ ሳይሆን ወደ አኾራ እናሻግረዉ ? ….…መሰብሰቢያችንን በዛ በጭንቅ ቀን ከአርሹ ጥላ ስር እሱዉ ዘንድ ከትቦልን፣ ለሱ ብለዉ ለተዋደዱ  ባሮቹ የሰጣቸውን ሽልማት ይዘን በዱኒያ ላይ የአላህን ቤት ለገነቡት ቃል የተገባው የጀነት ውስጥ ቤት ውስጥ…..ቀጠሮውን እዛ እናርገዉ፡፡

ተሳሰሩበት በተባልነው የአላህ ገመድ ላይ መተሳሰር ምን ማለት እንደሆነ ስላሳያቹን፣ከልብ መተሳሰብ ምን እንደሆነ ስላስተማራቹን አላህ  ኸይር ጀዛቹን በጀነት ይክፈላቹ፡፡"

@aaumsu
👍8🔥1👌1
78ኛ - 3720

45ሺ ይሙላ በሚል 3720 ብር ገቢ ሆኗል :: አላህ ይቀበላቸው :: ኸይራትን አከታትሎ በዱንያም በአኼራም ይወፍቃቸው ::

አላሁ አክበርርርርር ብለናል !!
ምስጋና ይድረሰው !!!
👍71🔥1
79ኛ - 100 ብር

አላህ ይቀበለው :: ለኸይር ነገሮች ሁሉ መክፈቻ ሰበብ ያድርግለት :: ጭንቀቶቹን ያስወግድ :: ዱንያውን ያሳምር :: የአኼራ ቤቱን በጀነተል-ፊርደውስ ይገንባ ::
👍1
AAU - Muslim Students Union
Photo
ረመዷን2️⃣9️⃣
(ወደ ጽናት)⓶
፨፨፨
<<እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡>>[አ'ሹራ፡15]
፨፨፨
ጊዜ ይሄዳል፤ቀናት ተደማምረው ወራት ይተካሉ፤አላህ ድጋሚ ከሚያገኙት ያድርገንና ረመዷንም ተመልሶ ይመጣል፤ታዲያ...የሚመጣው ረመዷን የዘንድሮው የጨመረልንን መልካም ነገር እንደ መሠረት ተጠቅሞ ወደ ሌላ የተሻለ ከፍታ የሚያደርሰን ይሆን ዘንድ ከአሁኑ አቋማችን ሳንመለስ ተዘጋጅተን ልንጠብቀው ይገባል።"አንድ ዓመት ግን ሩቅ አይደለም?"
.
*
ታዲያ!መጭው ጊዜ በጽናት እንዴት ይለፍ?
.
፨፨፨
<<አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡>>[ፋጢር:28]
፨፨፨
.
ብዙዎቻችን ስለሶላት አሰጋገድና መሠረታዊ ነገሮች ከቤተሰብ የወረስነው ተለምዷዊ ዕውቀት ይኖረን ይሆናል።ይህ መሠረታዊ ዕውቀት ጥሩ ቢሆንም፣ በአላህ መንገድ ላይ ለመጽናት ግን ዋስትና አይሆንም።አላህን ይበልጥ ስታውቀው ይበልጥ ትጠነቀቀዋለህ።የሱን ኃያልነት ስትረዳ በፍርሀት፣የእዝነቱ ስፋት ሲገባህ ደግሞ በተስፋ እየተገዛኸው ትኖራለህ።የተፈጠርክበትን ዓላማ የምታሳካው በደነገገልህ ሸሪዓ ብቻ ነውና ዲኑን ይበልጥ ማወቅ ለመጽናት ይረዳሀል።
*
አላህ የሚወሳባቸው፣ የሱ ዲን የሚማርባቸው ስብስቦች ላይ ስትዘወትር ያለህ ላይ እየጨመርክ ትሄዳለህ እንጅ መንገድ አትስትም።ያላወቁትን በማወቅ፤ያወቁትን በማስፋት ወደ አላህ ይበልጥ መቅረብ፣የጽናት ሰው መሆን ይቻላል።የወንጀልን አስከፊነት፣የኸይር ስራን ምንዳ በደንብ ስናውቅ ዓመቱን ሙሉ የዒባዳ ዓመት ማድረግ እንችላለን።
*
ከዲን አንፃር ስናየው፣ትላንትና ዛሬያችንን አንድ አድርገን እየኖርን ያለነው ጥቂት አይደለንም።ትላንትም ዛሬም ቁርኣንን ማንበብ አንችልም፤ወይም አነባበባችንን እስከዛሬ አልተስተካከለም።ስለ ዐቂዳችን ብንጠየቅ መልስ የለንም፤ሶላታችንና ጾማችንም ተለምዶ እንጅ በትክክል ከአላህ ሒሳብን በመፈለግ የሚፈፀሙ አይደሉም።
*
ትምህርትን እያጠኑና እየተረዱ፣ቀኑን በክላስ፣ሌሊቱን በንባብ እያሳለፉ  ቁርኣንን ማንበብ አለመቻልንና፣የሶላትን ደንብ በሚገባ አለማወቅን ከምንም አለመቁጠር ከተማረና የተሻለ አረዳድን አዳብሯል ከሚባል ሰው የሚጠበቅ ተግባር አይደለም።እርግጥ ግቢ የተገኘንበት የመጀመሪያ ዓላማ ዓለማዊ ትምህርትን ፍለጋ ነው።ከዚህም ፈጽሞ ልንዘናጋ አይገባም።የቤተሰብ አማና ብሎም የዚህችን ዓለም ስንቅ የምንሰንቅበት ትልቅ መሣሪያ ነውና።
*
ይህ ማለት ግን ሙሉ ነገራችንን እሱ ላይ ማጥፋት አለብን ማለት አይደለም።በሁለቱም ስኬታማ ሆኖ መመረቅ እንደሚቻል በማመን ለሁለቱም መትጋት ይገባል።ለዚህም የሚያግዘው በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ የሚባክንን ጊዜ ቀንሶ ሰዓትን በአግባቡ መጠቀም ይሆናል።
*
ከረመዷን በኋላ የዕውቀት ቦታዎች ላይ አለመገኘት ረመዷን ላይ የሸመትነውን መልካም ነገር እንድናጣና ወደቀድሞው ማንነታችን እንድንመለስ የሚያደርግ ሌላኛው ምክንያት ነው።
.
ዲንን በአግባቡ አለመረዳትና በደንብ አለማወቅ ያለው መጥፎ ውጤት በኛ እንደማይገደብ መገንዘብ መቻል አለብን።ኢስላም በኛ በኩል ለቀጣዩ ትውልድ እንደሚተላለፍ መዘንጋት የለብንም።

ወንድሜ ሆይ!ሩቅ ሊመስለህ ቢችልም የቤተሰብ አስተዳዳሪ፣የልጆች አባት መሆንህ የማይቀር ነው።አሁን ያለህበት ሁኔታ ለዛ የሚመጥን ነው?
ለልጆችህ የምታወርሰው ኢስላማዊ ዕውቀትና ስነ-ምግባር ይበልጥ የምታዳብረውስ መቼ ነው?ከአሁኑ  አይደለምን?

እህቴ ሆይ! እየተማርሽ ይሆናል።ሆኖም ግን ትክክለኛ ሚናሽና ክብርሽ ኢስላማዊ ቤተሰብ መገንባት ላይ እንደሆነ አትዘንጊ።ለዛ የሚሆን ስንቅ አለሽ?የምትውይውስ ስንቅሽን የምትሰንቂበት ቦታ ነው ወይስ ልጆችሽን ልታይበት የማትፈልጊበት ቦታ?ከጊዜሽ ቀንሰሽ ለዋናው ዓላማሽ መዘጋጀትስ የለብሽም?
.
‼️ጊዜው ከምንም ጊዜውም በላይ ዲንን ለመማር የሚጠቅሙ ዕድሎች የተመቻቹበት ጊዜ ነው።ስልክ፣ኢንተርኔትና ሌሎቹን ለዚህ ብንጠቀማቸው ከጽናት ባለቤቶች የመሆን ዕድላችን ሰፊ ነውና ጸጋዎችን በመጠቀም ላይ አደራ!
፨፨፨
«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ» በል፡፡[ጧሀ:114]
፨፨፨
🌱አላህ ሆይ!ረመዷንን በኛ ላይ መላልስልን!...አሚን!

⭕️የዕለቱ ቻሌንጅ⭕️
.
1️⃣በዕውቀት ወደ ጽናት ለመጓዝ መወሰን
.
2️⃣ የአንድ ዓመት የዒልም ዕቅድ ማውጣት፤የሚመጣውን ክረምትም በደንብ ለመጠቀም በመወሰን ከአሁኑ ዕቅድ ማውጣት፣
.
3️⃣ የጀመዓ ደርሶችና፣ፕሮግራሞች ላይ ለመገኘት መወሰን

🍀Principle of The Year🍀
A year of "firmness through Seeking Knowledge!"

🌱 አሏሁ'መ ኢነከ ዐፉውን ቱሒቡል ዐፍዎ ፈዕፉ ዐና!

#AAiTJemeaRamadanReminders2
@aaumsu
👍1
80-81ኛ - 300 ብር - SSC and FBE

እህቶቻችንን አላህ ይቀበላቸው :: ይውዳቸው :: የሚወዱትን የሚያስደስታቸውንና እሱ አላህ የሚወደውን ነገር ሁሉ ይስጣቸው :: የአኼራ ቤታቸውን በጀነተል-ፊርደውስ ይገንባ ::
👍2🔥2