AAU - Muslim Students Union
6.49K subscribers
2.76K photos
151 videos
51 files
767 links
This is the official channel of AAU-MSU.

Group: @aaumsu_discussion
Youtube: youtube.com/@aaumsu
Twitter: x.com/aaumsu12
Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1
Email: aaumsu12@gmail.com
Download Telegram
100 ብር - "አባቴን ጌታዬ በእዝነቱ ጀነትን እንዲወፍቀው በዱዓ አግዙኝ!"

መልካም ልጅ ቀሪ ስራ ነው :: መልካምን ይሰራል :: በዱዓ ያስታውሳል :: አላህ አባቱን በጀነት ይሞሽረው :: ሰጪውን ልጅም ለአባቱ በመልካም የሚሰራ መልካም ሰርቶ በጀነት እስከ ዘላለሙ የሚዘወትር ያድርገው ::
👍1
130 ብር - ከ4ኪሎ

ከቤተ-መንግሰት አጎራባች ነው :: አላህ ያማረ የተዋበ ህይዎትን ይስጣት :: አኼራዋን በጀነት ከምትወዳቸው ጋር ይሰብስባት !!

ጥቁር-አንበሳ ወ ልደታ ብቅ በሉ !
👍2
100ብር - ከcommerce

ንግድ ኮሌጆች አለን እያሉ ነው :: አላህ አለሁ ይበላቸው :: በእርዳታው : በእዝነቱ : በመሐርታው አይለያቸው :: ጀነተል-ፊርደውስን ቤታቸው ያድርግ ::
👍1
100 ብር - ከዋናው ግቢ

አላህ ይቀበላት :: መልካም ልጆችን ይወፍቃት :: ዱንያዋን ያሳምር :: አኼራዋን ይሙላ ::
👍1
100ብር !

"ዱዓ አድርጉልኝ!" ብሏልና ዱዓ አድርጉለት :: አላህ ይቀበለው :: ያማረ ዱንያ የሞላ አኼራ ይስጠው ::
🔥2👍1
100 - Commerce
"አላህ ለጓደኛዬ ልጅ እንዲሰጣት ዱዓ አድርጉልኝ!"

ጓደኝነት :: ጥልቅ የሆነ መተሳሰብ :: አላህ ጓደኝነታቸውን እስከ ጀነት ያዝልቀው :: ለጓደኛዋም መልካም ልጆችን ከረጅም እድሜ አፍያና ሀብት ጋር ይወፍቅላት ::

ዱዓ አድርጉላት !

ንግድ ኮሌጅ አልተቻሉም (ሲላ ይረግዳሉ እንዴ¿)
1👍1
100+200=300- ከዋናው ግቢ

ሁለት ወንድሞች ናቸው :: አላህ ይቀበላቸው :: የዱንያ የአኼራ ጭንቀታቸውን ያስወግድ :: ያማረ ዱንያ የሞላ አኼራ ይስጣቸው ::

ተንቀሳቀሱ !!
👍1
100ብር - ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ
"ዱዓ አድርጉልን! እየተጨቆን ነው!" ብሏል ::

የትላንትናዋ የሙስሊም ሱልጣኔት መናገሻ የሆነችው ሀድያ ሆሳዕና ናት :: የጴንጤዎች መፈንጫ ሆና ሙስሊሞችን አፍናለች :: አላህ ድሉን ያቅርብ :: ተማሪዎችንም የድሉ መክፈቻ ቁልፍ ያድርጋቸው ::

ደቡቦች አለን ብለዋል!
ሰሜን : ምስራቅና ምዕራብስ?
👍2
100 ብር!
አላህ ይቀበላት :: በዱንያም በአኼራም መልካምን ነገር ይወፍቃት ::
👍1
500ብር - ከAASTU

ከወደ ቃልቲ ያሉት ናቸው :: አላህ ይቀበለው :: ኸይር ጀዛውን ይክፈል :: በዱንያም በአኼራም መልካምን ነገር ይስጠው ::
👍1
የ6ኪሎ አሚር ወንድማችን ዱዓ አድርጉልኝ ብሎ 300 + ሌላ ወንድም ከmain 100 አስገብተዋል :: ዱዓ አድርጉላቸው ያ አህባቢ :: አላህ የዱንያም ሆነ የአኼራ ሐጃቸውን ይሙላ ::
👍3👌1
600 ብር - 4ኪሎ !!

አላህ ይቀበላት :: ኸይር ጀዛዋን ይክፈል :: የምትፈልገውን የምትወደውንና የሚጠቅማትን ነገር ሁሉ አከታትሎ ይስጣት :: የአኼራ ቤቷን በጀነተል-ፊርደውስ ይገንባላት ::
3
100ብር!

አላህ ይቀበላቸው :: ረጂም እድሜ : ሰፊ ሀብት : ከሙሉ አፊያና ኢማን ጋር ይወፍቃቸው :: የጀነት ቤታቸውን በፊርደውስ ውስጥ ይገንባላቸው ::
🔥2
ሪከርዱ ተሻሽሏል!
1500 ብር ከ5ኪሎ ገቢ ሆኗል!

መሐንዲሶች ዛሬም ከፊት ናቸው :: አላህ ኸይር ነገሮችን አከታትሎ ይስጣቸው :: ዱንያውንም አኼራውንም ይሙላ :: አብዝቶ ሰጥቶ አብዝተው የሚሰጡ ያድርጋቸው ::
🔥8
100ብር - ከsefereselam !

የሰላሙ ሰፈር :: ሁሌም በኸይር ስራ ላይ በዝተው ይታያሉ :: አላህ ኸይር ነገሮችን አብዝቶ አባዝቶ ይስጣቸው :: ጀነትን መዘውተሪያቸው ያድርግ ::
👍1
100ብር - ከልደታ !

ህንፃ ኮሌጆች የመጀመሪያውን ጡብ አስቀምጠዋል :: ብዙ እንጠብቃለን :: አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈል :: ዱንያ አኼራቸውን ይሙላ ::
👍1
300 ብር - ከEXTENSION

አላህ! አላህ ጨማምሮ ይስጣቸው :: ሞላልቶ ኸይራትን ይወፍቃቸው :: ዱንያ አኼራቸውን ያሳምር ::
👍1
50 ሰጥታ ቀሪ 17.92 ይላል - ከFBE ነው ::

ሐጃ አለብኝ ዱዓ አድርጉልኝ ብላለች :: አላህ ከሐጃዎቿ ሁሉ ጎን ይቁም :: የምትወደውን የሚያስደስታትን የሚጠቅማትንና የሚወጀውን ሁሉ በዱንያም በአኼራም ይስጣት ::
🥰5
1000 ብር - ከአመታት በፊት ከ6ኪሎ ተመርቃ የወጣች እህታችን!

"ለሟች እናቴ ዱዓ አድርጉ :: ልጆቼ መልካምና ጠቃሚ ልጆች እንዲሆኑም ዱዓ አድርጉ::" ብላለች :: ዱዓ አድርጉ የአኼራ ወዳጆቼ :: አላህ እናቷን በጀነት ይቀበል :: ልጆቿን ቤተሰብ አኩርተው ሀገር አስጠርተው ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ የሚቅምና ዘላለም በመልካም የሚወሳ አሻራ አሳርፈው የሚያልፉ ያድርግ :: አሚንን!!
4