AAU-Official
40.8K subscribers
1.12K photos
135 videos
89 files
233 links
Addis Ababa University
Download Telegram
ለ33 ቀናት የሚቆይ ነፃ የሕክምና አገልግሎት መሰጠት ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ “እሺ ለበጎ ተግባር” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የክረምት የበጎ ፈቃድ ነፃ የሕክምና አገልግሎት ዛሬ ሐምሌ 20 ቀን 12018 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል።

ይህ የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

በአገልግሎቱ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ፕሮፌሰር ማቴዎስ እንሰርሙ እና የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤግዚኪውቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ራሔል አርጋው ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና የህክምና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ከፍተኛ የሕክምና ባለሙያዎች እና ስፔሻሊስቶች እየተሳተፉበት ባለው በዚህ መርሃ ግብር በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የነፃ ሕክምናው ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸው ታውቋል።
👏7🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“እሺ ለበጎ ተግባር” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የክረምት የበጎ ፈቃድ ነፃ የሕክምና አገልግሎት ሁለተኛ ቀኑን በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

በ5ቱ ክፍለ ከተሞች (በቦሌ፣ በጉለሌ፣ በልደታ፣ በአዲስ ከተማ እና በለሚ ኩራ)፣ በመቄዶንያ፣ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንዲሁም በማረሚያ ቤቶች የሚከተሉትን አገልግሎቶች እንሰጣለን።

🔹 የውስጥ ደዌ ህክምና
🔹 የዓይን ህክምና
🔹 የካንሰር ቅድመ-ምርመራ
🔹 የልብ እና የደም ግፊት ምርመራ

ከዚህ በተጨማሪም ፣ የነገዋን አረንጓዴ እና ጤናማ ኢትዮጵያ ለመገንባት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እና የአካላዊ እንቅስቃሴ ባህልን ለማሳደግ የሚረዳ የጋራ የመንገድ ላይ ጉዞ ተዘጋጅቷል።

#እሺ_ለበጎ_ተግባር!
#ጥቁርአንበሳስፔሻላይዝድሆስፒታል #2018
👏7🔥1
AAU Connect Vol. 16 | Grad ’26

The newest edition of AAU Connect is now available!

This special graduation edition celebrates the Class of 2026 and Addis Ababa University’s 76th Graduation Ceremony, featuring inspiring graduate stories, messages from university leadership, research highlights, partnerships, and major institutional achievements.

Read the full issue and celebrate our newest graduates!

https://volume.aau.edu.et/6,3d9d335e5379f7

Congratulations to the Class of 2026!

#AAUConnect #Graduation2026 #HigherEducation #Research #Innovation #AddisAbabaUniversity
👍8🌭2👏1🙏1
Vacancy Announcement for AAU Community School.pdf
352.6 KB
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት (AAU-MCS) ለተለያዩ የስራ መደቦች ሰራተኞችን መቅጠር ይፈልጋል።

ትምህርት ቤቱ ከ2019 የኢትዮጵያ የትምህርት ዘመን ጀምሮ፣ ለአንደኛ ደረጃ (ከ1ኛ እስከ 7ኛ ክፍል) ተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት አቅዷል፡፡

ዝርዝር የስራ መደቦችና የማመልከቻ ሁኔታ ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመንካት ይመልከቱ

https://www.aau.edu.et/announcements/detail?title=Vacancy~Announcement~AAU-MCS

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
👍17😁4👏1
2018 Entry Undergraduate Regular Students.pdf
285.1 KB
NOTICE to 2018 Entry Undergraduate Regular Students

The students listed in the website (below) are requested to urgently complete your program preference selection. You can also see your names from the attached word document.

https://www.aau.edu.et/announcements/detail?title=Dear~2018~Entry~Undergraduate~Regular~Students

All other students are advised to review and verify the program preferences you have already submitted to ensure they are accurate.

In addition, students who have received an NG (No Grade) are requested to contact your respective College Registrar Offices and instructors as soon as possible.

Addis Ababa University
🥴6🔥5
🎭📽 The School of Theatre and Film Arts is now accepting applications for its Bachelor of Arts in Theatre and Film Arts program.

📍 Location: Main Campus, College of Social Sciences, Arts & Humanities

👉 Create. Inspire. Impact.
 
Scan the QR code on the poster to learn more and start your journey today!
😁13🥰6👏5
ማስታወቂያ

ልጆቻችሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሞዴል ማህበረሰብ ት/ቤት (ከ 1-7 ኛ) ክፍል ለማስተማር ያስመዘገባችሁ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ ያልሆናችሁ ማህበረሰብ በሙሉ፡

* የተማሪዎች የመግቢያ መለያ ፈተና ረቡዕ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በ 4:00 ሰዓት ይሰጣል።

* በመሆኑም ልጆቻችሁን በመያዝ ምዝገባ በተካሄደበት ቦታ (አምስት ኪሎ) 3:30 ሰዓት እንድትገኙ እናሳውቃለን።

*ይህንን የመግቢያ ፈተና ያልወሰደን ተማሪ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሞዴል ማህበረሰብ ት/ቤት
👍41🤔10🙏5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስለሚሰጣቸው የመግቢያ ፈተናዎች ለምሳሌ GAT፣ UAT በተመለከተ የሚከተለውን አጭር ማብራሪያ ይመልከቱ፡

ለበለጠ መሪጃ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ይፋዊ የዲጂታል ሚዲያ አውታሮችን ይከታተሉ

Website: https://www.aau.edu.et/

Facebook: https://www.facebook.com/p/Addis-Ababa-University-100064311447035/

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/addis-ababa-university-official

X (Twitter): https://x.com/AAU_Official

You Tube: https://youtube.com/@AddisAbabaUniversity-AAU

TikTok: https://www.tiktok.com/@aauniversity

Telegram: https://t.me/aau_official

Testing Center: https://t.me/aauGAT

Instagram: https://www.instagram.com/aau_official_/
🙏12🥴4👏2🤔2🤯1🤪1
ደም በመለገስ ሕይወት እንታደግ! 🩸❤️

አንድ ጠብታ ደም ለሌላው የሕይወት ተስፋ ነው። በደምዎ የሌላውን ሰው ህይወት ይታደጉ።

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የክረምት በጎ ፍቃድ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ደም ይለግሱ የብዙዎችን ህይወት በጋራ እንታደግ።

📍 ቦታ: ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
📅 ቀን: 29/11/2018 ዓ.ም
ሰዓት: ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ


ስለለገሱት ደም ስለሰጡት ህይወት እናመሰግናለን! 🙏

#ደምመለገስህይወትማትረፍርነው #እሺለበጎተግባር #TashCampaign #BloodDonation #GiveBloodSaveLives #Ethiopia
👍9👏5
ለ አዲስ ገቢ ተማሪዎች

የተለያዩ የአካዳሚክ መረጃ የሚያገኙበት ፕሮግራም ከ ከነሐሴ 8 -16 2018 ይካሄዳል

በመረጃ ሳምንት ውስጥ፣ የሚከተሉትን መረጃ ያገኛሉ

• የመግቢያ መስፈርቶች
• የማመልከቻ ሂደቶች
• የመጀመሪያ ዲግሪ የመግቢያ ፈተና (UAT)
• የስኮላርሺፕ አማራጮች (መንግስት፣ በግልና፣ ፕሬዝዳንታዊ)
• ስለ ምደባ መረጃ

ቦታ፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ዋናው ጊቢ፤ ፎረም ሕንፃ
👏18🔥7😁6👍4🥴1
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል “እሺ ለበጎ ተግባር” የተሰኘ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተማሪዎች አሶሴሽን ከኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን በክረምት የበጎ አድራጎት ከሚከናወኑ ተግበራት አንዱ ነዉ፡፡

ሆስፒታሉ ከሃገሪቱ የተለያየ ክፍል የሚመጡ ከፍተኛ ስፔሻሊቲ ህክምና የሚያስፈልጋቸዉ ህሙማን አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም መሆኑን የገለጹት የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሃላፊ ዶ/ር ብርሃኑ ሰንደቅ ናቸዉ፡፡

ይህ አይነቱ የደም ልገሳ መርሃ ግብር 4ተኛ አመቱን መያዙን አስታዉሰዉ፤ የተሰበሰበዉ ደም ለሆስፒታሉ ብሎም ለሌሎች የህክምና ተቋማት ደም ለሚያስፈልጋቸዉ ህሙማን የሚዉል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመርሃግብሩ ላይ ደም ሲለግሱ ያገኘናቸዉ ፕ/ር ብሩክ ላፒሶ በበኩላቸዉ ደም የሚያስፈልጋቸዉ ታካሚዎች በምንም መድሃኒት የማይተካ ብሎም የህሙማንን ህይወት የሚያስቀጥል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እሺ ለበጎ ተግባር የደም ልገሳ መርሃ ግብር የህክምና ሙያተኞች ግንዘቤ ከማስጨበጥ ባለፈ በተግባር ማህበረሰቡ የሚያስተምሩበት መሆኑን አስረድታዋል፡፡

ፕ/ር ብሩክ አክለዉ ደም መለገስ ለተቀባዩ ተካሚ ባለፈ ለለጋሹ ግለሰብ ዘርፈ ብዙ የጤና ጠቀሜታ እንዳለዉ አስገንዝባዋል፡፡

“እሺ ለበጎ ተግባር” የደም ልገሳ መርሃ ግብር የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች እና አስታማሚዎች በልገሳዉ እየተሳተፉ ሲሆን፤ይኸዉ መርሃ ግብር በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡
👏13🤯3