ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል - Birana Culture and Art Center
361 subscribers
130 photos
15 videos
5 files
12 links
ላለዎት አስተያየትና ጥያቄ @BiranaAastu_botን ይጠቀሙ።
Download Telegram
ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማእከል ወደ መድረክ ሥራው ተመለሰ።

ታላቅ የምስራች

@aastuart

እንደቀደሙት መድረኮቻችን ሁሉ አሁንም
🎺 በሙዚቃ
📑 በሥነ ጽሑፍ
🎑 በስዕል
🕺 በውዝዋዜ
🎭 በቴአትር
የደመቀ ምሽት ማክሰኞ መጋቢት 19 አንድ ሰዓት ለማቅረብ ሽር ጉዳችን ጨርሰናል።

ይምጡና አብረን እንድመቅ። ፍትት እንበል።

@aastuart
😀ደረሰ!!😀


ቀኑ ደረሳ

የ2015 የመጀመሪያው የብራና መድረክ ሥራ የሚቀርብበት ቀን ደረሰ።

ዛሬ ማታ አንድ ሰዓት ላይ
ቅኔ ሚፈስባቸው አዝናኝና ነሻጭ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ፣ ሙዚቃዎች ፣ ቴአትርና ውዝዋዜዎች ይቀርባሉ።

እንዳይቆጩ እንዳያመልጥዎ።

@aastuart
ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማእከል የመጀመሪያውን የ2015ዓ/ም መድረክ ባማረ ሁኔታ አጠናቋል።

መድረኩን ለታደማችሁ ሁሉ ምስጋናችን እያቀረብን ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ @biranaAastu_bot ላይ ጻፉልን።

መልካም ጊዜ።
አስደሳች ዜና

ብራና የባህልና ኪነ-ጥበብ ማዕከል የማይጠገቡ ስራዎቹን ከመድረክ በተጨማሪ በsocial media ላይ ይዞ ቀርቧል።

እናንተም #በYouTube, #Tiktok እና #Instagrm ላይ

subscribe እና follow

በማድረግ የማይሰለቸውን የብራናን የጥበብ ማዕድ ይቃመሱ።


#ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል
#YouTube: https://youtube.com/@biranatube7564
#Tiktok: branaarts
#Instagram: branaarts
#telegram: @aastuart
Forwarded from Deleted Account
sene-sehuf night 2014, one of the best stages made by brana "sele Kefel"
ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም
Forwarded from This Way ......
ቀጥረሽኝ ብትቀሪ

በፍቅርሽ ወላፈን
በመቅረትሽ ሀዘን
የጠቆረው ልቤ
'በምን ቀርታ ይሆን?' በሚል የፍቅር ሳል
ሚዛን ላይ ሲቀመጥ
መኖሬ ይቀላል መሞቴ ይከሳል
አላህ ቢጠላ እንጂ
እንጀራውን ሰጥቶ መቼ ወጥ ይነሳል

ይህ ሁሉ ባለበት አይኖችሽን ሳላይ
ሀጃየ አይሳካም
ድምጽሽን ሳልሰማ በልቤ ጨለማ
ብርሀን አይነጋም

ይህ ሁሉ ባለበት
ልቤ እኔን ዘንግቶ ወዳንቺ ለመምጣት
ጎዞ ይማትራል
ብቻውን ያወራል
.
.

''ሞቼም ቢሆን እንጂ
ከእስዋ ጋ ለመድረስ ቅዋውን አላጣም
ካካሄዴ ይልቅ
ካሟሟቴ ይልቅ
ያስቀራት ጉዳይ ነው ያስጨነቀኝ በጣም''
.
.
.
ይላል::

በሱልጣን.አ
በትላንትናው ምሽት ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማእከል ከሙስሊም አባላቱ ጋር በመሆን የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጅቶ ነበር እና ድባቡ በምስሉ የምታዩትን ይመስል ነበር።
✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ የብራና ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለ 1444 ኛዉ የኢድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ።

ኢድ ሙባረክ

✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨

በአሉ የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ እና የአንድነት ይሆን ዘንድ ብራናችን ይመኛል !

✨🌙 መልካም በዓል ✨🌙
በቅርቡ ዲጂታል የግጥም መድብል እንለቃለን። ታዲያ እስከዚያው ከመጽሐፉ የተወሰደ አንድ ግጥም ተጋበዙልን።

@aastuart