ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል - Birana Culture and Art Center
361 subscribers
130 photos
15 videos
5 files
12 links
ላለዎት አስተያየትና ጥያቄ @BiranaAastu_botን ይጠቀሙ።
Download Telegram
ባቄላ ምታህል ካደረኳት ጫማ
ስንጥሯን ጉልበቴን ቁልቁል እየላሰ
ቅላቱን ሲያለብሳት አካሌ ሲደማ
ውስጥህ ተደሰተ?
ንገረኝ አባቢ የወለደኝ ልብህ
ሀሴት አሸተተ?
ሽቅብ እየላከ አየሩን አሳልሞ ዳግም ሚቀበለኝ
እንደምን አስችሎት?
ጉንጮቼን ሊያቀላ እጄን ሊጠፈንግ ክንድህ ጨከነብኝ?
እኮ ሊባል ይሆን አንሶላ ገፈፈ አባት ከልጁ ጋር
የለመድኩት እኔ ያቺ ደሀ እናቴ ዳይፐር ለመተካት አንሶላውን ቀዳ ለ'ካካ' ስታስር
ይሉታል መከታ ሌሎች ላባታቸው ሲሰጡ ሙገሳ
ምነው የኔስ አባት ሳላይ የረገጥኩህ አመድ ለበስ እሳት ረመጥ ሆንከኝሳ
እኮ እስኪ ንገረኝ..
እስኪ ስሜን ጥሪ "አ ባ ቢ በይ እስኪ" የተሳሰረ አፌን አባብሎ ያስፈታኝ
ስሜት አሳውሮት ከውጥረጥ ሲፈታ
አርድሻለው ይበለኝ?

እንደው በምን አልባት የሆነ ግዜ ላይ በሆነ ሁናቴ
ወጉን ለማን ሰጠሽ ብሎ ለሚጠይቅ
እያልኩኝ ልመልስ ወስዶታል አባቴ?
መልሴን ፈልጋለው....
እስከዚያው ይወርዳል እስከዚያው ይፈሳል ውስጤን ሊሸረሽር ዘወትር እንባዬ
እንዴት ልስቅ ኖሯል ስሜን እየጠራው ስምክን አስከትዬ?
((ካንዲት ብላቴና
👆👆👆👆👆
ፅሁፍ በየአብስራ
¥¥¥¥ ጥቁር ብርሀን ¥¥¥

በዚች ቱባ አለም ጫፏ በጠፋባት
ጥያቄ አትጠይቅ መልስ አትጠብቃት

ቢሆን ብለክ አትሂድ ባይሆን ብለክ አትቀር
ለውጥ ላታመጣ....
በዝምታ አትዋጥ ባፍህ አትቀባጥር

ያንተ እንደዚ መሆን....
ሳትሞት ለመኖሮህ ነውና ምስክር 🐾🐾
@ሱልጣን.አ
👆👆👆👆👆
ፅሁፍ በሱልጣን
👆👆👆👆👆
ዳንስ በልዑል(@ZRekingz)
የዝግጅታችን ሁለተኛ ክፍል ይህን ይመስል ነበር፡፡ ያላችሁን አስተያየት በ
👉👉@BiranaAastu_bot 👈👈
አድርሱን፡፡ የወደዳችሁትን ስራ ላይክ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ሶስተኛው ክፍል ይጀምራል፡፡
👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨አብራችሁን ቆዩ፡፡👁‍🗨👁‍🗨👁‍🗨
👆👆👆👆👆
ስዕል በዮሴፍ
first date

ፏ ብልጭ ብየ፤ ባለችኝን የክት ልብስ ሽክ ብየ ከቀጠሮየ ቦታ ደርሻለሁ በሰዓቴ።
ዞር ዞር ብየ የቀጠርኳትን ልጅ ፈለኳት ከላይ ቀይ እንደምትለብስ ነበር የነገረችኝ። እያት አዛ ጥግ ላይ አለች ለማረጋገጥ ብየ ስልኬን አወጣሁና ደወልኩላት። አንስታ ሃሎ ና ወደዚህ በሚል እጇን አረገበገበችልኝ።
እንግዲህ ስቃየ ከዚህ ነው የሚጀምረው
9 ደቂቃ አርፍደሀል አለችኝ
እ አልኩኝ
9 ደቂቃ እንደምታረፍድ ብትነግረኝ 9 ደቂቃ ዘግይቸ እመጣ ነበር። ግን በቀጠሮ ማርፈድ classic የ dating part ነው አለች
ይቅርታ ስላረፈድኩ ብየ ተቀመጥኩ
Facebook ላይ እንደላከችልኝ ፎቶ ልቅም ያለች ቆንጆ ናት። እናም ፈራሁ
ሲጀመር እራሷ ናት Facebook ላይ ያዋራችኝ። እንገናኝ ያለችኝም እራሷ ነች። የሆነ ፕራንክ እየሠራችብኝ መሠለኝ። ግን አደለም።
እሽ ቤቲ እንዴት ነሽ?
physically በጣም ደህና ነኝ psychologically ግን corona ያጠቃኛል ብየ እየፈራሁ ነው።
እሱማ ሁላችንም ነን አልኩ
የኔ ትንሽ ይለያል ብለውኛል ቤተሰቦቸ እኔ የማስበው ትክክለኛውን ቅድመ ጥንቃቄ እየወሠድኩ እንደሆነ ነው ቤተሰቦቸ ግን abnormal እንደሆነ ነው የሚያስቡት
ይህን ያህል? እንዴት አርገሽ ብትጠነቀቂ ነው?
የመጀመርያው ኬዝ ከተመዘገበ ጀምሮ ከቤት ወጥቸ አላውቅም፣ እ......
ብላ ልትቀጥል ስትል
ምንም ምንም ወተሽ አታውቂም
አዎ ለምን እወጣለሁ?
ዛሬ እንዴት ወጣሽ?
ሁለት ምክንያቶች አንድ ቤት ውስጥ መዋሌ ጥቅሙ አልታይሽ ስላለኝ እናትና አባቴ በጣም ቃሉን መጠቀም ባልፈልግም ዝርክርክ ናቸው። ስለዚህ covid የሚገለኝ ከሆነ date ሳላረግ መሞት ስለማልፈልግ። ሁለት ደግሞ ከወረርሽኙ ከተረፍኩ ደግሞ ከወረርሽኙ በፊት የነበረውን የ dating trend ማወቅ ስለፈለኩ ነው። antropologically speaking የሰወች የአኗኗር ዘይቤ ከጦርነት ከወረርሽኝ እና ከባድ አፈተፈጥሮአዊ አደጋዎች ቡሀላ በሰፊው ይለወጣል።ትንሽ ብዘገይም አሁንም የተራውን ዜጋ life experience እደርሳለሁ።
ምን አይነቷ ስነዜጋ አስተማሪ ላይ ነው የጣለኝ እያልኩኝ በሆዴ
እና የት ጊቢ ነው የምትማሪው አልኳት
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ 3ተኛ አመት physics ተማሪ ነኝ

ዋው አሪፍ ነው አኔ ብየ ስለራሴ ልናገር ስል

ስላንተ አውቃለሁ። ከማላቀው ሠው ጋር አብሬ የምቀመጥ ይመስልሀል። በሚገርም ሁኔታ ከውካዋ ነገር ነህ የማያቅህ ሠው የለም።
አና ለምን እኔን መረጥሽ አልኩ ትንሽ እየፈራኋት
እንደተረዳሁት ከሆነ ተራ ሠው ነህ ተራ ኑሮ ነው የምትኖረው እኔም የተራውን ህዝብ ኑሮ ነው መኖር የምፈልገው፣ ቆንጆና ስኬታማ አይደለህም ስለዚህ ከብዙ ሴቶች ጋር ግንኙነት የለህም ይህ ደግሞ ምናልባት ወሲባዊ ግንኙነት ቢኖረን በ STD የመያዝ እድሌን ይቀንሰዋል። ጉራም የለብህም ምንም የሚያስጎርር ነገር ስለለለህ......የመሳሰሉትን

ይሄ ነገር በህልሜ ነው ወይስ

ቀጠለች
እኔ ደግሞ ለስኬታማ ለቆንጆ ለጠንካራ ወንዶች ለወሲብ የሚረታ የስሜታዊነት Evolutionary ደራጃን አልፌያለሁ። አዕምሮየ የስሜት ህዋሳቶቸን በቀላሉ ማዘዝ ይችላል.....
ለካ ሰይጣን በቆንጆም ይመሰላል የሚሉት እውነት ነው ተናደድኩ የተናኩ መሠለኝ
በቃ እንሂድ አልኩ
እኔ ለሚቀጥሉት 25 ደቂቃዎች plan የለኝም መቆየት እንችላለን
ኧረ ባክሽ ያንች plan እኔን መሳደብ ነው አልኩና በልቤ በልሳኔ ክፉ ላለመናገር እኔ ግን እቸኩላለሁ አልኩና ሂሳብ ለመክፈል ኪሴ ውስጥ ስገባ

እኔ ስለሆንኩ እንገናኝ ያልኩህ እኔ እከፍላለሁ አለች
አይ ችግር የለውም
ችግርማ አለው አንተ ይችን መቶ ብር እናትህን አስጨንቀህ ተቀብለህ ወይም የሆነ የጉልበት ስራ ሰርተህ ያመጣሀት ይሆናል፤ በኔ ላይ economical superiority እንዳለህ ለማሳየት ነው። አኔ ደግሞ አንዳልኩ ለእንደዚህ አይነት crap አልደለልም።
እሺ ክፈይ
ከፈለች
አንውጣ አልኩ
አሺ አለች
ከዛ እንዳሰብኩት መጥፎ አልነበረም ቆይታችን አትልም
ዝም
ብንደግመው ደስ ይለኛል
እህህ (የለበጣ ፈገግታ)
ቻው
😠😠😠
፧
inspired by TBBT
👆👆👆👆👆
ፅሁፍ በኪሩቤል
👆👆👆👆👆
Meme በናትናኤል
amanu:
Watch "ከሳቃቹ ተሸነፋቹ || fun video reaction Aman X Edu AUG 2020" on YouTube
https://youtu.be/Ec2d6urf_gY
ሰም እና ወርቅ
የ3ኛ ዓመት መርሐ ግብር አንዱ የሆነው
የመጻሕፍት ዓውደ ርዕዩ ሰኞ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም በወጣትነቱ ያለፈውን የመምህርና ዲዛይነር አዲሱ ተገኝ መጽሐፍን በማስመረቅ ይጠናቀቃል።

የመጽሐፍ ምረቃ
#"የታፋኙ ማስታወሻ "
#የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አዲስ መጽሐፍ
#ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም
# ግዮን ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ
# ስለ መጽሐፉ ጋዜጣዊ መግለጫ ከ9፡00- 10:00 ሰዓት
# የምርቃቱ ሥነሥርዓት ከ10:00 -11:30
# ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ :-በመጽሐፉ ላይ ዳሰሳ
#ፕ/ብርሃኑ ነጋ፣
#አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ
#አርቲስት አዜብ ወርቁ
#ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ
#አጋዥ ኪነ-ጥበባዊ ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡
ካርዱ በተለያዩ መጽሓፍት መደብር ይገኛል።
ያለ ካርድ ፈጽሞ መግባት ክልክል ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- +251 911 12 57 88
+251 944 33 23 97
ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል አዲስ አባላትን በመመዝገብ ልምምድ እንደጀመሩ ያውቃሉ?



ያፈካላወቁ Block 55 ከሚገኘው ቢሯችን በመምጣት እየተመዘገቡ አባል ይሁኑ።

በስነጽሁፍ
በሙዚቃ
በቴአትር
በውዝዋዜ
በስዕልና ቅርጻ ቅርጽ

በየትኛው ነው የእርስዎ ፍላጎት?