ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል - Birana Culture and Art Center
361 subscribers
130 photos
15 videos
5 files
12 links
ላለዎት አስተያየትና ጥያቄ @BiranaAastu_botን ይጠቀሙ።
Download Telegram
ፕሮግራማችን እንደቀጠለ ነወ። ያላቹህን አስተያየት
@BiranraAastu_bot ላይ ልታደርሱን ትችላላቹህ።
ምዕራፍ 4 ይቀጥላል
አልፎ ያላለፈ እና ሌሎች በሱለይ አደም ከተሰኘው መፅሀፍ ጆሮዬን ጣፈጠኝ ከሚለው ርእስ ተቀንጭቦ የተወሰደ ትረካ
ተራኪ:- ቤተልሔም ግርማ
ማሀረቤን ያያችሁ . . . . . .
(በቃልኪዳን)
ሰፈራችን የኮብል እስቶን ምንጣፍ ባለቤት ቢሆንም አልፎ አልፎ ተኮልኩለው የተቀመጡ ከባባድ ድንጋዩችን መመልከት የተለመደ ነው። እኔም አላፊ አግዳሚውን ለመቃኘት ያክል ብዙ ጊዜ ከነዚህ ድንጋዩች መካከል በአንዱ መሰየምን አዘወትራለሁ።ከፊት ለፊቴ በተወሰኑ ሜትሮች ርቀት ህፃናት የተለመደውን ጨዋታቸውን ያቀላጥፍት ጀምረዋል። አንድ ህፃን ማሀረብን በጉያው ታቅፎ በዙሪያው ክብ ሰርተው ለሱ ደግሞ ጀርባቸውን ሰጥተው ለተቀመጡት 8 ልጆች ድምፁን ከፍ አድርጎ ማሀረብን አይተውት እንደሆነ በተማፅኖ ይጠይቃቸዋል። ሁሉም በተመሳሳይ ድምፀት "አላየንም ባካችሁ"እያሉ ያዜሙለታል። አሁንም ይሮጣል..መሀረብን ይፈልጋል መሀረብ ግን አሁንም እጁ ላይ ነው። ይኔን ከልጆቹ ላይ ልነቅለው አልቻልኩም።
"መሀረቤን ያያችሁ ..መሀረቤን ያያችሁ" ጆሮየ ላይ ድምፁ ያቃጭላል። በዚህ መካከል ነበር አንድ የእነ ሱ እኩያ የሆነ ልጅ በመምጣት እነሱን ከጨዋታቸው እኔን ደግሞ ትእይንቱን ከመከታተል ያባነነኝ። ከርደድ ያለ ጠጉር።በቅላት የተዋዛ ክብ ፊት።ጎላ ጎላ ያሉ አይኖች።።ጭረት የበዛባቸው እጆች።አመዳም ሰውነት። በፍንጋነት ውስጥ ያለ የህፃንነ ወዝ።ያሬድ ነበር።አወ ያሬድ ነው። ጎረቤታችን ያሬድ።
"ሚኪ" በማለት የትንሽ ወንድሙን ስም ተጣራ
በመጫወት ላይ የነበረው ሚኪ በስጨት እያለ
" ምን ሁነህ ነው" ይለዋል ያሬድም
"አንተ ና . . ና እኮ ነው የምልህ ቤት ማንም የለ" ወደ ስራ ልሄድ ነው እያለ እንደ መኮሳተር ሲል ህፃናቱም
"በቃ ሂድለት ተነስ ተነስ " እያሉ ማጣደፍን ተያይዘውታል እውነት ለልጁ አዝነውለት ይሆን? አላውቅም። እሱም ቀስ ብሎ ከተቀመጠበት በመነሳት ከወንድሙ ጋር ተያይዘው ሄዱ። ሚኪ ወደ ቤት ጥበቃው ያሬድ ደግሞ ወደ ሊስትሮ ተራ።

የልጆቹ ጨዋታ አሁንም እንደቀጠለ ነው።የሚኪ ከቁጥር መጉደል የጨዋታውን ለዛ አላደበዘዘውም።ምናልባትም ልጆች ስለሆኑ ይሆናል።ለኔ ግን የሚኪ አለመኖር በመጠኑም ቢሆን ስለ ያሬድ እንዳስብ እድሉን ሰጥቶኛል።በተለይ ደግሞ ባልተገራው አንደበቱ ውስጥ የሚተራመሱት ቃላቶቹ አንጀት ያላውሳሉ።"ወደ ስራ ልሄድ ነው" የሱ ጎደኞች መሀረባቸውን እጃቸው ላይ አስቀምጠው መሀረቤን ያያችሁ ይላሉ። የያሬድ መሀረብስ ምን አይነት ይሆን?ቀይ? ቢጫ ጥቁር? ትምህርት ፣ ልጅነት ወይንስ ወቶ አደርነት አላውቅም ያሬድ ገና የ8 አመት ልጅ ነው የሁለተኛ ፕ ተማሪ። የመቦረቂያ ጊዜውን በስራ ተጠምዶ እንዲውል ዋጋ ያስከፈለው የእናትና የአባቱ በህይወት አለመኖር አይደለም። የኑሮቸው ሁኔታ እንደ ኤሊ እርምጃ አዝጋሚ መሆኑ እንጅ። የሱን ሁለት ታንሽ ወንድሞች ለማስተዳደር የራሱን አስተኦፃ ካላበረከተ ጎጆው እንደሚፈርስ በመገንዘብ እንጅ። አንዳንዴ ሳስበው እንደኛ ሰፈሩ ያሬድ ስንት አይነት ያሬዶች በየቦታው ይኖሩ ይሆን? እላለሁ ገና ይህችን ምድር ከመቀላቀላቸው ጥረህ ግረህ ብላ የሚለውን የመፀሀፍ ቃል ለመተወን ልጅነታቸው የሰውስ ምን ያህሎቹ ይሆኑ? እስኪ ምን ይባላል ያሬድና መሰሎቹ ባልጠናው ጀርባቸው ፊደልን ማንገት ሲገባቸው የሊስትሮ ሳጥን ማዘል ከሆነ እጣፍንታቸው ፣ እግራቸው እስኪቀጥን ጎዳና ላይ መጎዝ ከሆነ ስራቸው? የካርቶን ሱቅ አንግተው እንዲዞሩ ከፈረድንባቸው? እነሱን ለሚመስሉ የትየለሌ ያሬዶች የህልም ምክነት ተጠያቂው ማነው? በያሬድ ዘር አለማፍራት የምትመክነው እናቱ ብቻ ነች ብሎ ማሰብ ቂልነት ሳይሆን አይቀርም።ሀገር ማለት ሰው ነው።ሰውነት ደግሞ ሚስጥሩ ሀያል ነው።ማሰብ ነው። ማዘን ነው። መራራት ነው። መረዳዳት ነው። እያተባለ ቀን ከሌት በሚደሰኮርባት ሀገር ውስጥ የእልፍ አእላፍ የያሬድ እናቶች የወላድ መካን መሆን የሀገርም ምክነት ነው ላለማለት አያስደፍርም። የያሬድን ማሀረብ ማንስ ወሰደው? እናቱ? . . . አባቱ? . . .ሀገሩ? . .
"መሀረቤን ያያችሁ . . . አላየንም ባካችሁ . . ." ይሄ ለነሱ የተዋጣለት ጨዋታ ነው።እኔም ያሬድን ከማየቴ በፊት የተደመምኩበት።አሁን ግን ተራ ድንፍታ ሆነብኝ . . .ቀልብ የለሽ ጫጫታ . . .እውነት ነው ማሀረብን በጁ የያዘ ሰው እንዴት ማሀረብን ይፈልጋል? ለዛም ይሆናል ጨዋታው ውስጥ ያሬድ ያልተካተተው። ምናልባትም የሱ መሀረብ ህልሙ ከሆነስ? ተቀምጦ ሊፈልገው አይችልም ዘወር ዘወር ብሎ እንጅ . . . .
👆👆👆👆👆👆
አጭር ልቦለድ በቃልኪዳን
የሴቷ ልቅሶ
(በኢሲራክ)
ሆድ ውስጥ ከሂሊናው ጋር ሲከራከር
"ሌላ ዓለም የለም" ብሎ ነበር
"ሰው እንዴት ይኖራል ያለእትብት?"
በማለት ለማመን በመቸገር
ካለ ግን ምን አልባት
ሰባቴ ተስሏል ሕይዎቱን ለማየት፤
ዛሬ ቀኑ ሆኖ ስለቱ ሲሰምር
ለቆ ሲወጣ ያን የጨለማ ማኅደር
በራሱ ቋንቋ “ስለቴ ሰመረ" ቢል
የናትነት ወዙ፥ርህራሄ የነበረ አዛኝነት
ጭካኔ ሲትካው ተረስቶ በድንገት
በደሟ ጥንፋፊ፥በስጋዋ ሲጨክን አንጀት
ሲጥ አ’ረገችው ለጋ ጉሮሮውን አንቃ
ያኔ አለቀሰች እናት
በስሟ ሁሉ ሲጠራበት ፥ላትተው ንቃ
አዛኝት ቀርቶ ተከናንባ ውርዴት
በዛሬነት ምጥቀት ያስተሳሰብ ልኬት
መውጣት በሚመስል የቁልቁለት ውርደት
ሆኖ ቢገኝ የተናቀ እርኩሰት
ሆዷ ርቆ ሆድ ሲብሳት
አለቀሰች እናት።
. . .
ውዴን ያያቹህ አዛኚቷን ራሔል
የተቃጠለው አንጀቷ በፍቅር ነበልባል
ፊቷ ላይ ጎልቶ ይነበባል
"ልጄ ወዳጄ
አትራቅ ከደጄ
ዓይንህ ምግቤ ነው
አዳር አይደለም ፣ ስትርቀኝ የማድረው"
ይላል።
ተሰቅሎ ስታያው በፍቅር መስቀል
አንጀቷ ተላውሶ
ደም እንባ አንብታ አይኗ የፈረጠ
ሀዘን በልቧ ላይ ያቆጠቆጠ፥
ራሔል ሆና ራሔል ያልሆነች
እሞት ብላ ልጆን ያልጠቀጠቀች
አሻፈረኝ እንቢ ብላ ታቅፋ የሞተች
ውዴን ያያቹህ ንገሩኝ ባካቹህ ትፈልገኛለች
የምወደው ልጄ የት ነው እያለች፡፡

------------------------

የአዳም ገቦ የደም ገንቦ ውብ
የፍጥረት መጨረሻ ግብ
የክብር ባለቤትየፈጣሪ ርቀት ውጤት
ዜና ነጋሪ ለትንሳኤ ብስራት
ጀግና አንበርካኪ
ጠቢብ ማራኪ
የአናብስት ድክመት
ነበረች ይቺ ሴት።
የንግድ ዕቃ ቁስ ፣
እንደሸማች ቁጥር ተወዳ ምትረክስ
የጨለማ ሸቀጥ ከነገር ምታንስ
የሙሉ ዓለም ፍርዱ
ማረፊያ የፍሳሽ ልምዱ
ስትሆን የደስታው ነፀብራቅ
ራስን በሚሸውድ ምድር
ተፈልጎ ነበር ሴት እንድትስቅ
ግን
ከታችም ታች ከስር ወድቃ
ታለቅሳለች ያቺ ሴት ላትተወው ንቃ
እሷነት ምንዝር ሲሆን እጣዋን አውቃ

. . . . .

ውዴን ያያቹህ ከገቢያው ተለላ
ውብ ናት ፀጉረ ዞማ አንጀት የምትበላ
ከናፍሮቿ የህይወት እስትንፋስ
የትውልደ ትውልድ ነፍስ፣
ሚለምኑ እያሉ ቅረቡኝ፣
ወገቧ ተጋልጦ ቅጥነቱ ሚያሳብቅ፣
ጭኗ ሚፋጅ የተዳፈነ ረመጥ ደቂቅ
“ኑ ላመት ጉርሴ”ባይ፣ሚጣራ ከሩቅ፤
ማራኪ ልብ አሸፋች ደም ግባቷ
የነጋዴ መርከብ ብርሀን ፊቷ
የተኮሰኮሰ ለተማፅኖ፣ እንዳታድር ቆማ
ከ፴ው ለመፍተልተል ለመሆን ዘማ፤
ይቺን የውቦች ውብ ውዴን ያያቹሃት
የት ነው መገኛዋ ንገሩኝ በኔ ሞት
እውነት አለኝ ከኦሪት ዘፍጥረት
ለኑሮዋ ዘጸዓት።
አለያም ከቻላቹህ አምጡልኝ ጎታቹህ
“ደም ግባት ከንቱ ነው አይሆንም እራት
ክብር ልብስሽ ይሁን ራቂ ከሀኬት”
ብሎሻል በሉልኝ ንገሯት በእኔ ሞት፡፡
-------------------------------------------
የዘንዶው ጭካኔ የበረሃ ስደት
ባዝቶ አማስኖ የፈተላት፥
ድንግል ሴት
የአባቶችን ውዳሴ ቅኔ ወዳ
በጥንታዊያን ተሸውዳ
ከኛው ብትቀር በመሀላ ተላምዳ
አለቀሰች ሲወርድባት ናዳ፤
ከድንጊያ ያየለ ከመርግ የከበደ
እልፍ ክንድ ርቀት ከማማ የተናደ
ስድብ ቢወርድባት-ክብሯን ጠብቃ
አለቀሰች ድንግል ላትተወው ንቃ።

በዘመነ ስልጣኔ ረክሳ የኔ ባይ ስታጣ
ከ'ድሜ በታች፥ፀሐይ ወጥታም ሳትወጣ
ተቆጥራ እንደ መጥፎ ያደራ እጣ
እንደ ዝክር ስትወረወር ለተገኘው
ዳኛ ጠፍቶ ሰውነትን ስሜት ሲዳኘው
አለቀሰች ድንግሏ ሴት፥ክብሯ በሀፍረት ተተክቶ
ስትሆን:የድንቁርና አርማ፥የኋላ ቀርነት ማሚቶ፤
አለቀሰች ድንግሏ፥ሔዋንነት ሲሆን ጥሬ እቃ
ከምግብ መጠጥ ረክሳ ስትገኝ ወድቃ
አለቀሰች ድንግሏ፥በደሟ መሬት ሲጠረቃ።

. . .
ውዴ ድንግሌ ሆይ ክብርሽን የጠበቅሽ
ስድብ ያዘለ ጀርባሽ ተብረክርኮ እንዳይከዳሽ
ናቂው የዘበናይነቱን ሙገሳ
በሰዎች የመከበርን አበሳ
የምንዝርነት ስሜት ውስጥሽ እንዳያገሳ
ችላ በይው አዲስ አይሁንብሽ ወቀሳ፡፡
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በኢሲራክ
ይህ ስዕል በምዕራፍ አንድ ላይ ቀርቦ የነበረው ስዕል finishing ነው።
ሁሉም ጅምር ስራዎች በአግባቡ ከተንከባከብናቸው ያማረ ፍሬ ያፈራሉ። ሰላም እደሩ🙏🙏🙏።
ውድ ቤተሰቦቻችን ያላቹህን አስተያየት
@BiranraAastu_bot ላይ ልታደርሱን ትችላላቹህ።
ነገ ቅዳሜ በብራናችን ትልቅ የኪነጥበብ ድግስ ከምሽቱ 2 ጀምሮ በቴሌግራም ይቀርብለወታል።


እንዳያመልጠዎ። ሊከታተሉት የሚገባ ፕሮግራም ነው።

@biranaastu @biranaastu
"አባ አለም ለምኔ" በ ሀያት ረመዳን
💐🥀🎵🎤🎶🎙🎬📄🥀💐
😍😍ልዩ የጥበብ ድግስ😍😍
⌚️ ነገ ምሽት ከ2-5 ሰዓት⌚️
በብራና የባህልና ኪነ-ጥበብ ማዕከል
📄ግጥም 📖ወግ
🎵ሙዚቃ 🎙ትረካ
🖌ስዕል 🎑meme
👉👉👉@biranaastu👈👈👈
👉👉👉@biranaastu👈👈👈
ቤተሰብ ሆነው ወዳጆችዎንም ወደዚህ ቤተሰብ ይቀላቅሉ። ከዛም ከታዳሚነት እስከ ከዋኝነት ይዘልቃሉ።
💐🥀🎵🎤🎶🎙🎬📄🥀💐
💐🥀🎵🎤🎶🎙🎬📄🥀💐
ብራና ተመልሷል
😍😍ልዩ የጥበብ ድግስ😍😍
⌚️ ዛሬ ምሽት ከ2-4 ሰዓት⌚️
በብራና የባህልና ኪነ-ጥበብ ማዕከል
📄ግጥም
📖ወግ
🖌ስዕል
🎑meme
💃🕺 ዳንስ
👉👉👉@biranaastu👈👈👈
👉👉👉@biranaastu👈👈👈
ቤተሰብ ሆነው ወዳጆችዎንም ወደዚህ ቤተሰብ ይቀላቅሉ። ከዛም ከታዳሚነት እስከ ከዋኝነት ይዘልቃሉ።
💐🥀🎵🎤🎶🎙🎬📄🥀💐
👆👆👆👆👆
Meme በናትናኤል
እናልሽ...
እግዜር ሳት ብሎት
ያደረገ እንደሁ ገጣሚ እንዲወድሽ
ለእግዜር የምትመጥኝ
ትሆኛለሽ ስንኝ
ሰምና ወርቅ ቅኔ አራት መስመር ግጥም
ካ'ንድ ትንፋሽ ንባብ ከሩብ ገጽ ባትበልጥም
እንደ ኦሎምፐስ ኔክታር እንደ ያም የምትጥም
እንደውም ላ'ንዳንዱ
ለተጠመቀው ሰው በፍቅር ሃይማኖት
ለውበት ተከታዩ በተመስጦ ፍኖት
ለመውደድ አማኙ
ለእውነት መናኙ ለኅብር መነኩሴ
እንደማያውቅ ሁሉ
ላ'ምላክ የምትቀርቢ መሆንሽን ውዳሴ
ለማን እንደሚሰግድ
እስኪጠፋው ድረስ አምላኩን ይረሳል!
ካ'ማልክቱ በላይ
የ'ነርሱን ውዳሴ አንቺን ያወድሳል!
እንዴት ያለ ፍቅር እንዴት ያለ መውደድ...
እንኳን ላ'ማልክቱ
ለውዳሴያቸውም ተንበርክኮ መስገድ...
*
እናልሽ...
አያ'ርግብሽና
እግዜር ካደረገ ገጣሚ እንዲወድሽ
ትሆኛለሽ ልኬት ትሆኛለሽ ምዕራፍ
ትነኪያለሽ ሰማይ እንደ ኦሎምፐስ ጫፍ
የአማልክቱ መንደር የእግዜሩ ቤት በራፍ
አንቺው ቤተመቅደስ አንቺው ነሽ ቅዳሴው
አንቺው ነሽ መወድስ ላ'ንቺው ነው ውዳሴው
አንቺው ነሽ መሰውያው አንቺው ነሽ መስዋ'ቱ
አንቺው ነሽ መስገጃው ላ'ንቺው ነው ስግደቱ
ብቻ ምን ልበልሽ...
እንደርሱ መረዳት
አንቺ ነሽ ቁርባኑ መገበርያ ስንዴው
አንቺው ነሽ ፋሲካው አንቺው ነሽ ሁዳዴው
'እግዜርም ራሱ
ከፍጥረታት በፊት በምልዓት የኖረ
አንቺን ለመፍጠር ነው ምድርን የፈጠረ!
የቆየ ቢሆንም አድምቆ ከሰራት
አንቺን እንድናይ ነው ጣ'ይቱን ያበራት!
እንደውም እንደውም ጨለማ 'ሚሆነው
በጣ'ይ መጥለቅ ሳይሆን ባ'ንቺ መሰወር ነው!
አዳምም 'ሚተኛው ሲመሽ ማታ ማታ
አንቺን ለማየት ነው በጨለማው ፈንታ!...'
ይባላል ውስጥ ውስጡን
ቃል ተገብቶልናል
የሚመጣው መሲህ ይነግረናል ግልጡን!
*
እናልሽ...
አይውደድሽ እንጂ ገጣሚ ሲወድሽ
ተመርጠሻልና...
ልክ እንደ ክርስቶስ መከራሽ ይበዛል
ስቃይሽ ይከፋል፤
ተረግመሻልና...
ልክ እንደ መጻጉዕ ደዌሽ ይታመማል
ሕመምሽ ይጠፋል፤
ልክ እንደ ውቅያኖስ ጥልቀትሽ ይጠልቃል
ስፋትሽ ይሰፋል፤
ልክ እንደ አርያም ርቀትሽ ይረቃል
ግዝፈትሽ ይገዝፋል።
ሁሉን ትሆኛለሽ ሁሉ አንቺን ይሆናል
እውነታሽ ኮስምኖ ምናብሽ ይገናል!
ጥጋበኛው ነብር ያፈቅራል ድኩላ
ማህበር ይጠጣሉ ጅብና አህያ ሁላ
ሸረሪትና ዝንብ
አበልጆች ናቸው የክርስትና ልጅ
የክርስትና እናት
ቀበሮ መንኩሷል ጦጢት ሰባኪ ናት
ውሮ እድርተኛ ነች አንጋፋ አይጥ ሞቶ
ሰላም አውርደዋል ምሳርና ጉቶ...
ብቻ ምን ልበልሽ
ባፈቀረሽ ግዛት በወደደሽ ዓለም
በገጣሚ አዕምሮ አይደረግ የለም!