ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል - Birana Culture and Art Center
361 subscribers
130 photos
15 videos
5 files
12 links
ላለዎት አስተያየትና ጥያቄ @BiranaAastu_botን ይጠቀሙ።
Download Telegram
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በብንያም
ሁለቱ ምዕራፎች እንዴት ነበሩ? በነገራችን ላይ በናንተ ተከታታዮች ዘንዳ የተሻለ ውዴታን ያገኙ ስራዎችን የምንሸልም በመሆኑ የናንተ መልሰ ስሜት(reaction) ዋጋ እንዳለው እንድትገነዘቡ እንወዳለን።ምዕራፍ ሶስት ከአፍታ በዋላ ይጀምራል።
👆👆👆👆👆👆
ስዕል በብስራት
ልደትሽ ተዝካሬ
(በያብስራ ግርማ)
የወለዱበትን ልደትሽን ሲያከብሩ
ከልብሽ ቅጥር ውስጥ ገፍተሽ ለቀበርሽኝ
ለኔም ሙት ዓመቴን በዚያው ይዘክሩ
በኬክ ከደመቀው ውዱ ድፍሳቸው
ትንሽ ጊዜ ወስደው
ለነፍስ ይማር ሚሆን ያልወጣ ጠጠሩ
የበቆሎ ንፍሮ በያቸው አንፍሩ
ትዝ ይልሻል
ለምዶ መዋደድን
በፈጣሪ ምልጃ ሶስትነታችንን
ውዴ አፍቅሬሃለሁ በምትል ጋሪ ቃል
ንጹህ መሳይ ልብሽ
ድናግሉ ልቤን ከእግር ጣቶቹ ስር
አጐጉዞ ሲጥል
ትዝ ይልሻል አይደል
ባንቺ ማገድዶነት በመካሪ ክብሪት
በአሽቃባጮች ቤንዚን በለኮሻት እሳት
ፍቅር ከራሱ ድስት ሸፍኖ ያስቀመጠኝ
የግዜትን ውሃ አቃጥሎ ያበሰለኝ
ልደትሽ ሲከበር
ከበተስኪያን ደጃፍ ነገን ተመስሎ ላለ የኔ ቢጤ
ዘግነሽ የምትሰጭኝ
በቆሎው እኔ ነኝ
ፍም አዘል እሳትሽ ጥሬ እኔነቴን
ቢያሳጣው አቅም
ሃያል ነበልባልሽ ፍቅሬ ገጽታ ላይ
ጥላሸት ቢቀባም
ይግረምሽ የአኔ ዓለም
ተቃርኖ መብሰሌን
የልቤ ሰሌዳ በቂም ጠመኔዎች
አይጽፍሽም አንቺን
ካንቺ ያማለደኝ ይገርማል አግዜሩ
አንቺን ከእናትሽ እኔን ደግሞ ካንቺ
በፈጠረባት ቀን
ከልብሽ አጥር ጎን
ፍቃዱን ፈቅዶልሽ እኔን ማስቀበሩ
ካንቺ ያማለደኝ ይገርማል አግዜሩ
በመገፋት ቀለም በመገለል ብዕር
ተፈቅሮ ተጠላን
ምስኪን ሀውልቴ ላይ አድምቆ ማስፈሩ
ካንቺ ያማለደኝ ይገርማል አግዜሩ
Happy birthday
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በየአብስራ
Audio
👆👆👆👆👆👆
ሙዚቃ በናትናኤል
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በኤፍሬም
ፕሮግራማችን እንደቀጠለ ነወ። ያላቹህን አስተያየት
@BiranraAastu_bot ላይ ልታደርሱን ትችላላቹህ።
ምዕራፍ 4 ይቀጥላል
አልፎ ያላለፈ እና ሌሎች በሱለይ አደም ከተሰኘው መፅሀፍ ጆሮዬን ጣፈጠኝ ከሚለው ርእስ ተቀንጭቦ የተወሰደ ትረካ
ተራኪ:- ቤተልሔም ግርማ
ማሀረቤን ያያችሁ . . . . . .
(በቃልኪዳን)
ሰፈራችን የኮብል እስቶን ምንጣፍ ባለቤት ቢሆንም አልፎ አልፎ ተኮልኩለው የተቀመጡ ከባባድ ድንጋዩችን መመልከት የተለመደ ነው። እኔም አላፊ አግዳሚውን ለመቃኘት ያክል ብዙ ጊዜ ከነዚህ ድንጋዩች መካከል በአንዱ መሰየምን አዘወትራለሁ።ከፊት ለፊቴ በተወሰኑ ሜትሮች ርቀት ህፃናት የተለመደውን ጨዋታቸውን ያቀላጥፍት ጀምረዋል። አንድ ህፃን ማሀረብን በጉያው ታቅፎ በዙሪያው ክብ ሰርተው ለሱ ደግሞ ጀርባቸውን ሰጥተው ለተቀመጡት 8 ልጆች ድምፁን ከፍ አድርጎ ማሀረብን አይተውት እንደሆነ በተማፅኖ ይጠይቃቸዋል። ሁሉም በተመሳሳይ ድምፀት "አላየንም ባካችሁ"እያሉ ያዜሙለታል። አሁንም ይሮጣል..መሀረብን ይፈልጋል መሀረብ ግን አሁንም እጁ ላይ ነው። ይኔን ከልጆቹ ላይ ልነቅለው አልቻልኩም።
"መሀረቤን ያያችሁ ..መሀረቤን ያያችሁ" ጆሮየ ላይ ድምፁ ያቃጭላል። በዚህ መካከል ነበር አንድ የእነ ሱ እኩያ የሆነ ልጅ በመምጣት እነሱን ከጨዋታቸው እኔን ደግሞ ትእይንቱን ከመከታተል ያባነነኝ። ከርደድ ያለ ጠጉር።በቅላት የተዋዛ ክብ ፊት።ጎላ ጎላ ያሉ አይኖች።።ጭረት የበዛባቸው እጆች።አመዳም ሰውነት። በፍንጋነት ውስጥ ያለ የህፃንነ ወዝ።ያሬድ ነበር።አወ ያሬድ ነው። ጎረቤታችን ያሬድ።
"ሚኪ" በማለት የትንሽ ወንድሙን ስም ተጣራ
በመጫወት ላይ የነበረው ሚኪ በስጨት እያለ
" ምን ሁነህ ነው" ይለዋል ያሬድም
"አንተ ና . . ና እኮ ነው የምልህ ቤት ማንም የለ" ወደ ስራ ልሄድ ነው እያለ እንደ መኮሳተር ሲል ህፃናቱም
"በቃ ሂድለት ተነስ ተነስ " እያሉ ማጣደፍን ተያይዘውታል እውነት ለልጁ አዝነውለት ይሆን? አላውቅም። እሱም ቀስ ብሎ ከተቀመጠበት በመነሳት ከወንድሙ ጋር ተያይዘው ሄዱ። ሚኪ ወደ ቤት ጥበቃው ያሬድ ደግሞ ወደ ሊስትሮ ተራ።

የልጆቹ ጨዋታ አሁንም እንደቀጠለ ነው።የሚኪ ከቁጥር መጉደል የጨዋታውን ለዛ አላደበዘዘውም።ምናልባትም ልጆች ስለሆኑ ይሆናል።ለኔ ግን የሚኪ አለመኖር በመጠኑም ቢሆን ስለ ያሬድ እንዳስብ እድሉን ሰጥቶኛል።በተለይ ደግሞ ባልተገራው አንደበቱ ውስጥ የሚተራመሱት ቃላቶቹ አንጀት ያላውሳሉ።"ወደ ስራ ልሄድ ነው" የሱ ጎደኞች መሀረባቸውን እጃቸው ላይ አስቀምጠው መሀረቤን ያያችሁ ይላሉ። የያሬድ መሀረብስ ምን አይነት ይሆን?ቀይ? ቢጫ ጥቁር? ትምህርት ፣ ልጅነት ወይንስ ወቶ አደርነት አላውቅም ያሬድ ገና የ8 አመት ልጅ ነው የሁለተኛ ፕ ተማሪ። የመቦረቂያ ጊዜውን በስራ ተጠምዶ እንዲውል ዋጋ ያስከፈለው የእናትና የአባቱ በህይወት አለመኖር አይደለም። የኑሮቸው ሁኔታ እንደ ኤሊ እርምጃ አዝጋሚ መሆኑ እንጅ። የሱን ሁለት ታንሽ ወንድሞች ለማስተዳደር የራሱን አስተኦፃ ካላበረከተ ጎጆው እንደሚፈርስ በመገንዘብ እንጅ። አንዳንዴ ሳስበው እንደኛ ሰፈሩ ያሬድ ስንት አይነት ያሬዶች በየቦታው ይኖሩ ይሆን? እላለሁ ገና ይህችን ምድር ከመቀላቀላቸው ጥረህ ግረህ ብላ የሚለውን የመፀሀፍ ቃል ለመተወን ልጅነታቸው የሰውስ ምን ያህሎቹ ይሆኑ? እስኪ ምን ይባላል ያሬድና መሰሎቹ ባልጠናው ጀርባቸው ፊደልን ማንገት ሲገባቸው የሊስትሮ ሳጥን ማዘል ከሆነ እጣፍንታቸው ፣ እግራቸው እስኪቀጥን ጎዳና ላይ መጎዝ ከሆነ ስራቸው? የካርቶን ሱቅ አንግተው እንዲዞሩ ከፈረድንባቸው? እነሱን ለሚመስሉ የትየለሌ ያሬዶች የህልም ምክነት ተጠያቂው ማነው? በያሬድ ዘር አለማፍራት የምትመክነው እናቱ ብቻ ነች ብሎ ማሰብ ቂልነት ሳይሆን አይቀርም።ሀገር ማለት ሰው ነው።ሰውነት ደግሞ ሚስጥሩ ሀያል ነው።ማሰብ ነው። ማዘን ነው። መራራት ነው። መረዳዳት ነው። እያተባለ ቀን ከሌት በሚደሰኮርባት ሀገር ውስጥ የእልፍ አእላፍ የያሬድ እናቶች የወላድ መካን መሆን የሀገርም ምክነት ነው ላለማለት አያስደፍርም። የያሬድን ማሀረብ ማንስ ወሰደው? እናቱ? . . . አባቱ? . . .ሀገሩ? . .
"መሀረቤን ያያችሁ . . . አላየንም ባካችሁ . . ." ይሄ ለነሱ የተዋጣለት ጨዋታ ነው።እኔም ያሬድን ከማየቴ በፊት የተደመምኩበት።አሁን ግን ተራ ድንፍታ ሆነብኝ . . .ቀልብ የለሽ ጫጫታ . . .እውነት ነው ማሀረብን በጁ የያዘ ሰው እንዴት ማሀረብን ይፈልጋል? ለዛም ይሆናል ጨዋታው ውስጥ ያሬድ ያልተካተተው። ምናልባትም የሱ መሀረብ ህልሙ ከሆነስ? ተቀምጦ ሊፈልገው አይችልም ዘወር ዘወር ብሎ እንጅ . . . .
👆👆👆👆👆👆
አጭር ልቦለድ በቃልኪዳን
የሴቷ ልቅሶ
(በኢሲራክ)
ሆድ ውስጥ ከሂሊናው ጋር ሲከራከር
"ሌላ ዓለም የለም" ብሎ ነበር
"ሰው እንዴት ይኖራል ያለእትብት?"
በማለት ለማመን በመቸገር
ካለ ግን ምን አልባት
ሰባቴ ተስሏል ሕይዎቱን ለማየት፤
ዛሬ ቀኑ ሆኖ ስለቱ ሲሰምር
ለቆ ሲወጣ ያን የጨለማ ማኅደር
በራሱ ቋንቋ “ስለቴ ሰመረ" ቢል
የናትነት ወዙ፥ርህራሄ የነበረ አዛኝነት
ጭካኔ ሲትካው ተረስቶ በድንገት
በደሟ ጥንፋፊ፥በስጋዋ ሲጨክን አንጀት
ሲጥ አ’ረገችው ለጋ ጉሮሮውን አንቃ
ያኔ አለቀሰች እናት
በስሟ ሁሉ ሲጠራበት ፥ላትተው ንቃ
አዛኝት ቀርቶ ተከናንባ ውርዴት
በዛሬነት ምጥቀት ያስተሳሰብ ልኬት
መውጣት በሚመስል የቁልቁለት ውርደት
ሆኖ ቢገኝ የተናቀ እርኩሰት
ሆዷ ርቆ ሆድ ሲብሳት
አለቀሰች እናት።
. . .
ውዴን ያያቹህ አዛኚቷን ራሔል
የተቃጠለው አንጀቷ በፍቅር ነበልባል
ፊቷ ላይ ጎልቶ ይነበባል
"ልጄ ወዳጄ
አትራቅ ከደጄ
ዓይንህ ምግቤ ነው
አዳር አይደለም ፣ ስትርቀኝ የማድረው"
ይላል።
ተሰቅሎ ስታያው በፍቅር መስቀል
አንጀቷ ተላውሶ
ደም እንባ አንብታ አይኗ የፈረጠ
ሀዘን በልቧ ላይ ያቆጠቆጠ፥
ራሔል ሆና ራሔል ያልሆነች
እሞት ብላ ልጆን ያልጠቀጠቀች
አሻፈረኝ እንቢ ብላ ታቅፋ የሞተች
ውዴን ያያቹህ ንገሩኝ ባካቹህ ትፈልገኛለች
የምወደው ልጄ የት ነው እያለች፡፡

------------------------

የአዳም ገቦ የደም ገንቦ ውብ
የፍጥረት መጨረሻ ግብ
የክብር ባለቤትየፈጣሪ ርቀት ውጤት
ዜና ነጋሪ ለትንሳኤ ብስራት
ጀግና አንበርካኪ
ጠቢብ ማራኪ
የአናብስት ድክመት
ነበረች ይቺ ሴት።
የንግድ ዕቃ ቁስ ፣
እንደሸማች ቁጥር ተወዳ ምትረክስ
የጨለማ ሸቀጥ ከነገር ምታንስ
የሙሉ ዓለም ፍርዱ
ማረፊያ የፍሳሽ ልምዱ
ስትሆን የደስታው ነፀብራቅ
ራስን በሚሸውድ ምድር
ተፈልጎ ነበር ሴት እንድትስቅ
ግን
ከታችም ታች ከስር ወድቃ
ታለቅሳለች ያቺ ሴት ላትተወው ንቃ
እሷነት ምንዝር ሲሆን እጣዋን አውቃ

. . . . .

ውዴን ያያቹህ ከገቢያው ተለላ
ውብ ናት ፀጉረ ዞማ አንጀት የምትበላ
ከናፍሮቿ የህይወት እስትንፋስ
የትውልደ ትውልድ ነፍስ፣
ሚለምኑ እያሉ ቅረቡኝ፣
ወገቧ ተጋልጦ ቅጥነቱ ሚያሳብቅ፣
ጭኗ ሚፋጅ የተዳፈነ ረመጥ ደቂቅ
“ኑ ላመት ጉርሴ”ባይ፣ሚጣራ ከሩቅ፤
ማራኪ ልብ አሸፋች ደም ግባቷ
የነጋዴ መርከብ ብርሀን ፊቷ
የተኮሰኮሰ ለተማፅኖ፣ እንዳታድር ቆማ
ከ፴ው ለመፍተልተል ለመሆን ዘማ፤
ይቺን የውቦች ውብ ውዴን ያያቹሃት
የት ነው መገኛዋ ንገሩኝ በኔ ሞት
እውነት አለኝ ከኦሪት ዘፍጥረት
ለኑሮዋ ዘጸዓት።
አለያም ከቻላቹህ አምጡልኝ ጎታቹህ
“ደም ግባት ከንቱ ነው አይሆንም እራት
ክብር ልብስሽ ይሁን ራቂ ከሀኬት”
ብሎሻል በሉልኝ ንገሯት በእኔ ሞት፡፡
-------------------------------------------
የዘንዶው ጭካኔ የበረሃ ስደት
ባዝቶ አማስኖ የፈተላት፥
ድንግል ሴት
የአባቶችን ውዳሴ ቅኔ ወዳ
በጥንታዊያን ተሸውዳ
ከኛው ብትቀር በመሀላ ተላምዳ
አለቀሰች ሲወርድባት ናዳ፤
ከድንጊያ ያየለ ከመርግ የከበደ
እልፍ ክንድ ርቀት ከማማ የተናደ
ስድብ ቢወርድባት-ክብሯን ጠብቃ
አለቀሰች ድንግል ላትተወው ንቃ።

በዘመነ ስልጣኔ ረክሳ የኔ ባይ ስታጣ
ከ'ድሜ በታች፥ፀሐይ ወጥታም ሳትወጣ
ተቆጥራ እንደ መጥፎ ያደራ እጣ
እንደ ዝክር ስትወረወር ለተገኘው
ዳኛ ጠፍቶ ሰውነትን ስሜት ሲዳኘው
አለቀሰች ድንግሏ ሴት፥ክብሯ በሀፍረት ተተክቶ
ስትሆን:የድንቁርና አርማ፥የኋላ ቀርነት ማሚቶ፤
አለቀሰች ድንግሏ፥ሔዋንነት ሲሆን ጥሬ እቃ
ከምግብ መጠጥ ረክሳ ስትገኝ ወድቃ
አለቀሰች ድንግሏ፥በደሟ መሬት ሲጠረቃ።

. . .
ውዴ ድንግሌ ሆይ ክብርሽን የጠበቅሽ
ስድብ ያዘለ ጀርባሽ ተብረክርኮ እንዳይከዳሽ
ናቂው የዘበናይነቱን ሙገሳ
በሰዎች የመከበርን አበሳ
የምንዝርነት ስሜት ውስጥሽ እንዳያገሳ
ችላ በይው አዲስ አይሁንብሽ ወቀሳ፡፡
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በኢሲራክ
ይህ ስዕል በምዕራፍ አንድ ላይ ቀርቦ የነበረው ስዕል finishing ነው።
ሁሉም ጅምር ስራዎች በአግባቡ ከተንከባከብናቸው ያማረ ፍሬ ያፈራሉ። ሰላም እደሩ🙏🙏🙏።
ውድ ቤተሰቦቻችን ያላቹህን አስተያየት
@BiranraAastu_bot ላይ ልታደርሱን ትችላላቹህ።