ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል - Birana Culture and Art Center
361 subscribers
130 photos
15 videos
5 files
12 links
ላለዎት አስተያየትና ጥያቄ @BiranaAastu_botን ይጠቀሙ።
Download Telegram
ምዕራፍ አንድ በዚህ ተጠናቋል። ምዕራፍ ሁለት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።
ውድ ታዳሚዎቻችን በዝግጅቶቻችን እየተዝናናችሁ እንደሆነ ተስፋ እያደረግን ዘደ ሁለተኛው ምዕራፍ እንሻገራለን በመቀጠልም
።።ዳንስ በልዑል
።።ግጥም በአብረሀም ።አልወድሽም
።።ወግ በሙባረክ።የሱፍ ፍትፍቴ ቆይታ
።።ግጥም በብንያም።ክረምቱ ጨከነ...
👆👆👆👆👆👆
ዳንስ በልዑል( @ZRekingz )
አልወድሽም
(በአብርሃም)
. . . አልወድሽም . . .
፩ በመጀመሪያ አልወድሽም ከማለቴ በፊት
ስወድሽ ዓለሜ ፣ በፊት ቀደም ብሎ
እኔ አንቺን መፍቅዴ ልቤ ላይ ሲጸነስ
ከትኩሱ ደሜ ፣ ፍቅርሽ ተቀላቅሎ፣
በደም ስሬ ሲፈስ
ያኔ ልብሽን መሻቴ፣
የተስፋዬ ምድር
የህልሞቼ ንክር
ያጥንስስ ግሩም ጥንስስ ነበር።
በአንድ የቀን ሙሉ ወይ የቀን ጎደሎ
ከፍቅሬ አፍላ ላይ ፍቅር ተቃመስነ
ፈቅር ተዛገነ
ከስንዝር ዕድሜዬ ጥቂቱን ገምድሎ
ያ ድንቅ ጥንስስ ድንቅ ወይነ ጠጅ ሆን።
፪ ሌላው . . . ሌላ አልወድሽም ከማለቴ በፊት
በጨቅላነታቹህ የኔ ፍቅር ጨቅላው
በጨቅላ ነፍስሽ ላይ በጠዋት ተቀዳ
ያንድ ፈሬዋ አንቺ ፡ ልብሽ አንድ ፍሬው
የሱን መውደድ ሞላ ከድሜቹ ማለዳ።
ያን እሱን መፈለግ ፣ ከዚ እሱን ማጣት ጋር
አንድ ላይ ቀፍድዳ
ወዶ አለማግኘትን የናፍቆትን ፍዳ
ያን የአፍቃሪ እዳ ባንድነት ቀይዳ
ተጠናቅቃ አረጀች የልብሽ አቁማዳ።
ምወድሽ አልወድሽም ስልሽ . . .
ከውቦቹ ዓይኖችሽ ግሩም ቁልጭልጭታ
በፍንጭትሽ ሾልኮ ከሚደፋው ሳቅሽ
ከሚተርፍ ፈገግታ
ፍቅርን ዘንቀሽ የጻፍሽው ትዝታ
. . . የጠፋ እንዳይመስልሽ።
ምወድሽ አልወድሽም ስልሽ . . .
እዛ ጎዳና ላይ ፡ እዛ ባስ ስቴሽን ፣ ሳሸት ጸጉርሽን
እዛች አንድ ቦታ በስሱ ስትመጭ ደረቅ ከናፈሬን
እዛ ሲጨላልም በከዋክብት ፊት
በየጎዳናው ላይ ከጉንጭሽ የሚተርፍ እምጷዬ ሲዘራ
በአድማስ ቅላት ውበት አድምቄ እየሳልኩሽ ፍቅር ስናደራ
. . . እነዚን ምናምን ረስቼ እንዳይመስልሽ።
ምወድሽ አልወድሽም ስልሽ . . .
የዛ የፍቅርሽ ስም ድንገት እሚያመልጥሽ
እኔ አለመውደድ ከአፍሽ እሚሾልክሽ
እኔን መሰላቸት ውል ሲል ምይዘው ከኒያ ውብ ዓይኖችሽ፡
እነዚ ምናምን ላንቺ ያለኝን ፍቅር ንደው እንዳይመስልሽ።
.
.
.
እናማ እምወድሽ አልወድሽም ስልሽ
አልወድሽም ያልኩት
አዲስ ወይነ ጠጄን ባረጄ አቁማዳሽ ውስጥ
ስለፈራሁ መክተት።
ምክኒያት
ወደዚች አሮጌ ጎስቋላ አቁማዳ
የንጹሁን ልቤን አዲስ የወይን ጠጅ ደፍሬ ብቀዳ
በብርቱ ወይኔ ህይል ድንገት ብትፈነዳ በድንገት ተቀዳ
መከራው የኔ ነው የኔ ቀራንዮ የኔ ጎለጎታ ለልቤ አዲስ እዳ።
መልካም ወይነ ጠጄ የሀሳቤ ጥንስስ የምኞቴ ጨመቅ
የሚያሰክር ታምር
ተይው ባክሽ እሱን ይፍሰስ ምናባቱ
አፈር በልቶ ይቅር።
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በአብረሀም
የሱፍ ፍትፍቴ ቆይታ
~~~~~~~~~~
እሁድ ረፋድ 4:00 አከባቢ ከኮንደሚኒየሙ ጊርጌ ባለች 'አፊያ ቁርስ ቤት'በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ በአስተናጋጇ ፈገግታ ረሀቤን እያስታገስኩ ያዘዝኩት የሱፍ ፍትፍት ሲጠባበቅ ነበር።ነጠላ የለበሱ በቀኝ እጃቸው መጽሓፍ ቅዱስን፣በግራ እጃቸው ቄጤማ የያዙ ከቤተክርስቲያን የሚመለሱ ሴቶች ይታዩኛል።

በመሀል ረሀቡ ሲሞረሙረኝ ቅዳሜ ማታ የበላሁትን የምግብ አይነት ማስታወስ ሞከርኩ፤በሁለት ትላልቅ ቲማቲም እና በአንድ እንቁላል የታጀበ በዘይት ያበደ የእንቁላል ስልስ ከሁለት ረዣዥም ዳቦ ጋር ትዝ አለኝ ጣት ባያስቆረጥምም አንድ የላጤኔት ሌሊት ረሀቤን አስታግሶ ያሳደረኝን የምግብ አይነት መተቸት ስላልፈለግሁ ወደ ሱፍ ፍትፍቴ ቀልቤን መለስኩ። አስተናጋጇ አትታየኝም ዬነ አንዷ ጠርቷት ነው ሞት ይጥራውና....

'ከአፊያ ቁርስ ቤት' በስተ ግራ 'በላቸው ግሮሴሪ' ይገኛል እሁድ እሁድ መቀመጫ ቦታ አይኖርም አዳሜ ይኼን ጥሬ ስጋ በድራፍት ሲያወራርድ ካየህ በሰዎቹ አበላል ብቻ ምንም ገንዘብ ኪሲ ውስጥ ባይኖርህም ጥሬ የመብላት አምሮትህን ግን በነፃ ሊቀሰቅሱት ይችላሉ።
በረንዳው ላይ ያለው ልኳንዳ ፊቴ ድቅን አለ የስጋ ቆራጩ ነጭ ጋውን፣የተንዠረገገውም የበሬው ሻኛ ምራቅ የሚያስውጥ ቀይ ስጋ፣የአምፖሉ ብርሃን ተዳምሮ ያዘዝኩትን የሱፍ ፍትፍት ሊያራክስብኝ ሲታገል ተሰማኝ።

'ርግጥ ነው ሱፍ ፍትፍቴን ሳዝዝ ይኼ ሁሉ አልታየኝም ነበር ነገር ግን ልክ እንጄራው ላይ ጄሶ እንደጨመሩ ሁሉ በረቤሪውም ውስጥ ሸክላ ገባ ቢሉ ቀይ ፍርፍር አዝዤ ከምግቡ ውስጥ የማገኘውን የባዕድ ንጥረ ነገር አስልቼ እንጄራው ውስጥ ያለውን ጄሶ እንደሆን ለምደናል ቢያንስ በርበሬው ውስጥ የገባውን ሸክላ ብቀንስልኝ በማለት ነበር ሱፍ ፍትፍት ማዘዜ።

የሱፍ ፍትፍቴ ቆይታ ጥብስ ሲሆንብኝ ስራ ከሚፈታ አልኩና ሴት አስተናጋጆች ለምን አጭር ቀሚስ እንደሚለብሱና ተስተናጋጆች አጭር ቀሚስ ለባሽ አስተናጋጆች በሚገኙበት ካፌ እና ግሮሴሪ ውስጥ ሲቀመጡ ወንበር አያያዛቸው የአፍሪካ ሀገራትን መሪዎች የሚያስንቅበትን ሚስጢር ማሰላሰል ጀመርኩ።ለምንድነው ግን?

የዚህችኛዋማ ለጉድ ነው እጥረቱ የፓንቷ ቀለም ሳይቀርኮ ነው የሚታየኝ፤እውነት ለመናገር ያንን ቀይ ጭኗን የሚመለከት ሰው ያዘዘው ቁርስ ቆየብኝ ብሎ መናገር ይቅርና በተቀመጠበት እራት ቢደርስ ደስታውን አይችለውም ዳሩ ግን ምን ያደርጋል ገና ከፊትህ ቆማ ትኩር አድርገህ ማየት ከመጀመርህ ሌላኛው ተስተናጋጅ በጭብጨባ ሲጣራት ወዲህ ወዲያ ሲታርመሰምሰው ከአይንህ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአይነ ህሊና ፈልቅቆ ያወጣት ያክል ይሰማሃል..

.....አካሄዷ.....ቄንጠኛ የጠርሙስ አያያዟስ...አጎምብሳ ስታስቀምጥ ከደረቷ ላይ ወደ ጠረቤዛው የሚያፈጡ ጡቶቿ ከምግቡ ጋር የታዘዙ አፒታይዘሮች ይመስላሉ ያኔ ግን ቀልቤ ለሁለት ይከፈላል ከፊቴ በተደቀኑ ጡቶቿኗ አጠር ባለች ቀሚስ ተወጥራ ወደ ሌላኛው ተስተናጋጅ የዞረች ክብ መቀመጫዋን የሚመለከት የቤቱ ተስተናጋጅ አይን ላይ አፈጣለሁ ምናልባትም ሰበብ ፈልገ ልጣለው ሁሉ እችላለሁ።

የተስተናጋጅን ወንበር ወዳድነት ሚስጢር በራሴ ላይ ተረድቼ የአስተናጋጇን አጭር ቀሚስ ለበሽነት የቤቱ ባለቤት ለተስተናጋጅ የአይን እርካታና ለ'ራሱ ቢዝኔስ ማጧጧፍያ ዘዴ መሆኑ ሲገለጥልኝ በቤቱ በረንዳ ላይ በትልቁ የተሰቀለው "ደንበኛ ንጉስ ነው!"የሚል አክባሪ እና ትሁት ጥቅስ ትዝ አለኝ ኣሃ.......ወዲያው የአስተናጋጇ ከፊቴ ዞር ማለትና የሱፍ ፍትፍቴ ቆይታ ለሁለት ተዳብሎ እንደ መናደድ ሲያረገኝ ለመጠየቅ አንገቴን አስረዝሜ ወደ ውስጥ አጮልቀ ተመልከትኩ ፈውስ የሆነ፣ንዴትን የሚያበርድ፣ከዱካክ የሚያነቃ፣ ውብ ፈገግታ ከሚስረቀረቅ ድምፅ ጋር ታጅቦ"ይቅርታ ስላቆየሁ" አለችኝ የኔ ፍልቅልቅ ሳይበላስ ቢዋል አልኩ ለ'ራሴ ሱፍ ፍትፍቴ ደረሰ።
እንብላ!
ሙባረክ
👆👆👆👆👆👆
ወግ በሙባረክ
#"ክረምቱ ጨከነ ጨላለመ ጋራው
ከዋሻቸው ወጡ በረዶና ጭፍራው" (ርዕስ ነው!!!)
######
ከረምቱ ሲጨክን፦
ክንዱ የበረታ
በጥለው መክቶ ዶፍ ይቀለብሳል
ዲታው በቪላ ዳስ እረኛ በገሳው
እኩል ሲያማርር እኩይ ቀን የገፋል
ሠማዪም ጨፍግጎ ከሠው ፊት ይከፋል
ተከፊያና ንፋስ ጅራፉን ይገመዳል
ገራም ነው እያሉት"ውሽ-ንፍር" ያነሳል
ሆድ የባሰው አልቃሽ
የእምባ መስታወቱን በዝናም ይጠርጋል
ናፍቆት ከጅረት ጋር ተቃቅፎ ይፈሳል።
★ከረመቱ ሲጨክን፦
ባላገር ጉሽ ይዞ
"እግዚሐር ሲቆጣ አር በጎርፍ ያመጣ" እያለ ይተርታል
ሽፍታ ትጥቅ ፈቶ መለኪያ ይጨብጣል
ቆማጣ በዱሹ
ወታደር በውሹ
ቆፈን ሲጠናበት
ሚስት ሲነጣጠቅ
ቀን ይገፋል በሌት
ሚስት ያቀፈ ጎበዝ ቅምጥ ይደርባል
ቅምጥ ያስቀየመ
የእረቀ-ሰላም ልዑክ ኮሚቴ ያዋቅራል፡፡
★ከረምቱ ሲጨክን፦
ገበሬ በጉዛ ዳዋ ይመነጥራል
ጠፍ መሬት ለስልሶ ሰልስት ይሰለሳል
መቀነቷን ፈታ
ዘር ትቀበላለች ምድር ጭኗን ከፍታ
እንደ ሰካራም ዓይን ምንጩ ይደፈርሳል
ደራሽ ውሃ ጋልቦት ወንዙ ይገነፍላል
ጫን ያለው ደመና ሲገሰግስ ደርሶ
እንኳንስ የመንግስት የእግዜር ድልድይ ጥሶ
የናፈቀው ጉብል
"አባይ ጉደል ብለው አለኝ በታሳስ
በይ ደና ሰንብቺ እስከዛው ድረስ"
ብሎ እያባበለ ወዳጁን ወዲያ ሲል
ወዲህ ቃርሚያው ሙጃው በከበት ይታደናል
እረኛ ዋሽንቱን ከተሜ ውሃ-ሽንቱን
በየጎርፉ አጠፋፍ ሲያንዠቀዥቅ ይውላል
የሾጎሌን ገረድ ውሃ ይበላታልፐ
የጉለሌው ጨባሽ** እንደተለመደው ሽቅብ ይዋኝና አሳማ ይታደጋል፡፡
★ከረምቱ ሲጨክን፦
ሆዱ የተላወሰ የማንኩሳ ማቲ*
"ሠው ብርቱ ነው!"..... ይላል
"...ዝናብ ነጎድጓድ መች ይፈራል
በዶፍ መሃል አረማመድ ያሳምራል!"
እሱ ብቻ አምርሮ
አስሬ ያማትባል
ልቡ ላይ በከረምት °አሷን° መብረቅ አስሮ!!!
የሸገር ሠው እንደው
መበረቅ መቀልበሻው በየቤቱ ገብቶ
መበረቅ ባየ ቁጥር ማማተቡን ትቶ
ለ'ሰልፊ' ይሰለፋል ከቤት ተጠራርቶ!!
★ከረምቱ ሲጨክን፦
ገጣሚው በዝናም መሔጃ-አቶ ቤት ሲውል...
(መሔጃ ያለው ይመስል!!!!)
መሸሻ ያጣ ብዕር ከኪሱ ይመዝና፦
"ከረምቱ ጨከነ ጨላለመ ጋረው
ከዋሻቸው ወጡ በረዶና ጭፍራው"...
ብሎ በትካዜ ከመገጠሙ ግና
በረዶ እንዳልጣለ በመስኮቱ ያይና...
"በጣሪያው ላይ ሲረማመድ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲወለበለብ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጥዋ
ዉሃ ሲያቁር ከህዋ
በዚህ ሁሉ ፀጋ መሐል ያንቺን መሔድ ስተምነው ጸ
ምንም ነው!
ኢመንት ነው!
ልረሳሽ እየጣረኩ ነው!!"
የእርጥብ አፈር እርጥብ ሽታ
ውብ ሽቱሽን አዳፈነው
ስስ የጉም ዓየነ-እርግብ ውብ ገፅሽን ሸፋፈነው
ልረሳሽ እየጣረኩ ነው!!!"
የሚል ቤት ይደፋል
ምክንያቱም፦
★ክረምቱ ሲጨክን አመልሽን ያውቃል
ዳናሽ ይቀርና መንገድሽ ታጥቦ ያልቃል......!

@ግንቦት 9/2011- አያቴ ዘንድ ገጠር ሳለው ተገለጠልኝ(በራልኝ)😁

💔ከ" እሰከ " ያልኩት የበዕወቀቱ Bedhadha(ስዩም) ስንኝ ነው፡፡
* ደሞ ራሱ በእወቀቱ ነው!
** ተመሰጌን ገበሬ- የጉለሌው ሰካራም
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በብንያም
ሁለቱ ምዕራፎች እንዴት ነበሩ? በነገራችን ላይ በናንተ ተከታታዮች ዘንዳ የተሻለ ውዴታን ያገኙ ስራዎችን የምንሸልም በመሆኑ የናንተ መልሰ ስሜት(reaction) ዋጋ እንዳለው እንድትገነዘቡ እንወዳለን።ምዕራፍ ሶስት ከአፍታ በዋላ ይጀምራል።
👆👆👆👆👆👆
ስዕል በብስራት
ልደትሽ ተዝካሬ
(በያብስራ ግርማ)
የወለዱበትን ልደትሽን ሲያከብሩ
ከልብሽ ቅጥር ውስጥ ገፍተሽ ለቀበርሽኝ
ለኔም ሙት ዓመቴን በዚያው ይዘክሩ
በኬክ ከደመቀው ውዱ ድፍሳቸው
ትንሽ ጊዜ ወስደው
ለነፍስ ይማር ሚሆን ያልወጣ ጠጠሩ
የበቆሎ ንፍሮ በያቸው አንፍሩ
ትዝ ይልሻል
ለምዶ መዋደድን
በፈጣሪ ምልጃ ሶስትነታችንን
ውዴ አፍቅሬሃለሁ በምትል ጋሪ ቃል
ንጹህ መሳይ ልብሽ
ድናግሉ ልቤን ከእግር ጣቶቹ ስር
አጐጉዞ ሲጥል
ትዝ ይልሻል አይደል
ባንቺ ማገድዶነት በመካሪ ክብሪት
በአሽቃባጮች ቤንዚን በለኮሻት እሳት
ፍቅር ከራሱ ድስት ሸፍኖ ያስቀመጠኝ
የግዜትን ውሃ አቃጥሎ ያበሰለኝ
ልደትሽ ሲከበር
ከበተስኪያን ደጃፍ ነገን ተመስሎ ላለ የኔ ቢጤ
ዘግነሽ የምትሰጭኝ
በቆሎው እኔ ነኝ
ፍም አዘል እሳትሽ ጥሬ እኔነቴን
ቢያሳጣው አቅም
ሃያል ነበልባልሽ ፍቅሬ ገጽታ ላይ
ጥላሸት ቢቀባም
ይግረምሽ የአኔ ዓለም
ተቃርኖ መብሰሌን
የልቤ ሰሌዳ በቂም ጠመኔዎች
አይጽፍሽም አንቺን
ካንቺ ያማለደኝ ይገርማል አግዜሩ
አንቺን ከእናትሽ እኔን ደግሞ ካንቺ
በፈጠረባት ቀን
ከልብሽ አጥር ጎን
ፍቃዱን ፈቅዶልሽ እኔን ማስቀበሩ
ካንቺ ያማለደኝ ይገርማል አግዜሩ
በመገፋት ቀለም በመገለል ብዕር
ተፈቅሮ ተጠላን
ምስኪን ሀውልቴ ላይ አድምቆ ማስፈሩ
ካንቺ ያማለደኝ ይገርማል አግዜሩ
Happy birthday
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በየአብስራ
Audio
👆👆👆👆👆👆
ሙዚቃ በናትናኤል
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በኤፍሬም
ፕሮግራማችን እንደቀጠለ ነወ። ያላቹህን አስተያየት
@BiranraAastu_bot ላይ ልታደርሱን ትችላላቹህ።
ምዕራፍ 4 ይቀጥላል