ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል - Birana Culture and Art Center
361 subscribers
130 photos
15 videos
5 files
12 links
ላለዎት አስተያየትና ጥያቄ @BiranaAastu_botን ይጠቀሙ።
Download Telegram
👆👆👆👆
ስዕል በ ሜላት
ውድ ቤተሰቦቻችን ያላቹህን አስተያየት
@BiranraAastu_bot ላይ ልታደርሱን ትችላላቹህ።
ይህን ያውቃሉ
1. የረመዳን ፆም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሀይ መግቢያ የሚፆም ፆም ሲሆን በ Iceland ዋና ከተማ በ Reykkavik ከ ሌሊቱ 8:00 እስከ ሌሊቱ 6:00 ሠዓት ተፁሟል። ይህም የሆነበት ምክንያት ፀሀይ ለ 22 ሠዓታት ስላልጠለቀች ነው። ይህም ለ 22 ሠዓታት የተፆመ ፆም የአለማችን ረጅም ጊዜ የፈጀ ፆም ያያደርገዋል።
2.በአለማችን አጭር ጊዜ የፈጀው ፆም ደግሞ በ Australia,Sydney ከ 11:30-11:00 ሠዓት ማለትም ለአስር ሠዓት ተኩል ያክል ጊዜ የተፆመ ፆም ነው።
3.በግብፅ ደግሞ የረመዳን የፆም ሠዓት ለ አንድ ሠዓት ያክል እንዲጓተት ይደረጋል ይህም ድርጊት የፆሙን ሠዓት ቶሎ ያለቀ ያስመስለዋል።
💃🖌🎵🎤🎶🎙🎬🎭📄🖌🕺
ብራና የባህል እና የኪነጥበብ ማዕከል

🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠
"ለፍርሀት ድንጋጤ ሳንሆን እንግዳ
ከቤታችን ሆነን ጥበብን እንቅዳ"
🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠

📄ስነ ፅሁፍ(ግጥም፥ወግ፥ትረካ)
🎭ጭውውት
🖌ስዕል
💃🕺 ዳንስ
🎵ሙዚቃ

ዛሬ ምሽት 2:00 ላይ በ @aastuart እንዳያመልጥዎ።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@aastuart @aastuart
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
"join" ብለው ቤተሰብ ይሁኑ።
💃🖌🎵🎤🎶🎙🎬🎭📄🖌🕺
ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን የዛሬው ፕሮግራማችን ተጀምሯል።
ፍቅር አያረጅም
ሌባ ሴት ወድጄ ምትዘርፍ ቅኔ
አዳሜ ነህ ብለኝ አድርጌያት ሄዋኔ
ከሳር ፍራሼ ላይ ከቅፌ አስገብቻት እየዳበስኩ ፅጉሯን
ዳባሽ ጣቶቼ ላይ አርጋ አለንጋ ጣቷን
አይኔን እያየቺኝ እንዲህ አበሰረቺኝ
"ውዴ ፍም ቀርቦት እንዳየው እንደ ሻማ ቀሚስ ፊቴ ቢሸበሸብ
እንደ ፊደሏ 'ገ' ቢጎብጥ ያንተ ወገብ
እልፍ ብንጃጅም
እመነኝ አለሜ ፍቅር አያረጅም"
ድንገት ታወሰቺኝ እዛች ፍራሼ ላይ
ብቻዬን ተኝቼ ይቺ አነጋገሯ
እንዲህ ያለቺኝ እንስት ስትጠላኝ በወሯ
ወርቁን ስፈትነው በግዜ ዘንግ ይዤ ከቁጭቴ እሳት
በልጅነት መሞት ሆና ተፈታልኝ ያለማርጀት እውነት
©የ@ብ
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በየአብስራ
👆👆👆👆👆👆
ስዕል በብስራት( @artbisrat )
👆👆👆👆👆👆
ትረካዊ ጭውውት
ርዕስ-ሰደቃን ፈራሁ
ተዋንያን
👉 ነዋይ
👉ቤተልሔም
👉 ዳግም
የፅዋ ማህበር
(በፋኑኤል)
ጥንተ ህልውናው በደጋጎች ዘመን የተጠነሰሰ
ከትውልድ ለትውልድ በእርክክቦሽ ዛሬን የደረሰ
አንድ ማህበር አለ
ዛሬ በዚህ ሰአት
በማህበሩ ቤት
በዝቶ በተጌጠ በውብ መሶበ ወርቅ
ካህን የፈተተው ቀርቧል ፀበል ፃዲቅ
ደግሞ በውብ ገንቦ
ማየ ወይኑ ቀርቦ
በዋንጫ ተቀዶቶ ከወይኑ ቢታደል
ይህንን ጠጥቶ ግማሹ ረክቷል
ግማሹ ሰው ሰክሯል
……………………………………………
ከሰከረውና ከረካው መካከል
እሱም የሰከረ
የማህበሩ ራስ ስዩም ሙሴ ቆሟል
በስካር መንፈስም እንዲህ ይናገራል
በወርቃማው ዘመን በእኔ አስተዳደር
እንኩና ነፃነት
የተሰማችሁን ይቻላል መናገር
እንዲህ ባለገዜ
የረካው ጭብጨባ
የተጎዳው በእምባ
ሁሉም ሲያስተጋባ
የሰከረው ደግሞ እጁን እያወጣ
ራሱ ሲመልስ የጅል ጥያቄውን ራሱ እያመጣ
በዚህ ማህበር ውስጥ
ሁሉም ተናገረ ሁሉም አድማጭ አጣ
…………………………………………………………………………………
እድሉን ያገኘ አንዱ የሰከረ
የሙሴውን ዘመን ተግቶ እያማረረ
ከሰይጣን ጭንቅላት ሀሳብ እያወጣ
መናገር ጀመረ
እንደዚህም አለ
ይህ የኛ ማህበር ብዙ ሀብት አፍርቷል
እንቀመጥበት ወንበር ግን አጥተናል
ምድር ላይ አንጥፈን እስካሁን ኖረናል
ስለዚህ ወንበሩ ተገዝቶ አሁን ይድረስ
ይህ ካልተደረገ ማህበሩ ይፍረስ።
ይህን ባለ ጊዜ ይህ ሰው በመስከሩ
መጠጥና ሀሳብ ከሱ የተጋሩ
ባንድ ላይ ተነስተው እሱን ሊደግፉት
ይፍረስ ይፍረስ ይፍረስ እያሉ ጮሁበት
በማህበሩ ላይ ከንቱ አሟረቱበት
ዛሬ በዚህ ማህበር
የወትሮው አይናፋር በደጅ የሚቀመጥ የቆሎ ተማሪ
ይመርቁን ተብለው በክብር ሚጠሩ የቅኔ አስተማሪ
ሁሉም አብረው ሰክረው
የምን ዳዊት ማንገት ወድያ ጣል እያሉ
ከሰከረሰው እጅ መሳሪያ ለመንጠቅ ይተናነቃሉ
ቅኔውን ተውና ሰውን ይዘርፋሉ
........................................................................
ይህ በእንዲህ እንዳለ
ካልሰከሩት ወገን
ፅዋውን ሊመራ አንድ መልካም ሰው ቁሟል
በማህበሩ ወግ እንደዚህም ይላል
ማነህ ባለ ሳምንት
የንግሳችን ወዳጅ
ባስራ ስምንት ጠማጅ
ባለቀኝ ፅዋ የዛሬ ወር ደጋሽ የአሁን ተመሪ
ቀጣይ ጨፌ ጎዝጓዥ የሆንክ ዘካሪ

በያዝነው ወር ተራ
በጠጣው ወይን ሰክሮ
ሙሴው በበደለ
ፍርድ በገመደለ
የማህበራችንን ህጉን ባቃለለ
ማህበርተኛው ሰክሮ ሲጃጃል በዋለ
ይህንን ማህበር ይፍረስ ይፍረስ ባለ
በእዚህ እኩይ ሀሳብ እንዳትዘናጋ
በመደገሻህ ቀን ቤትህን እንዳትዘጋ
ማህበሩን ሊያፈርስ ሰክሮ ሚንገዳገድ ይህ ሁሉ ምታየው
ከጠጣው ባሻገር ነገ ጨዋ ሰው ነው።
ይህንን ረስተህ
አበቃለት ብለህ
ፅዋውን ጠጥተህ በተራህ ብትወጣ
በምታስረክበው የታሪክ ቆራጣ
ልታውቅ ይገባል እንደምትቀጣ፡፡
ይጠብቅህማል የልጅ ልጅህ ቁጣ፡፡
ባይሆን ባንተ ድግስ
የሚያሰክረውን ወይን በማር በወለላ አጣፍጠህ ቀይረህ
በጨዋነት እርሾ እንጀራውን ጋግረህ
በተስፋ ጠብቀን።
ሁሉም ባቀረብከው ማዕድ ተደስቶ
ፅዋውን ከአንተ ተረኛው ተመርቶ
ያቺ ቀን እንድታልፍ ግዳጅህ ተሳክቶ
በምትደግስበት ባንተ ተራ ሰሞን
በሰላም ዘክረህ በሰላም እንድትሸኘን
መጠጡን ቀይረህ ከመስከር ታደገን
......................................................
በዛሬው ፅዋ ላይ
ጠማቂው ስህተቱን እንደ እውቀት ቆጥሮ
በወይኑ ግብዓት ላይ የሚያሰክር ነገር ባዕድ ተጨምሮ
ገመናውን ቢገልጥ ማህበርተኛው ሰክሮ
በመካከላችን ቢሰማ አምባጓሮ
ከእኒህ ሰካራሞች ምን አንድነት አለኝ
ራሴን በጊዜ ማግለል ነው ሚሻለኝ
ብለህ ገሸሽ አትበል
አንተ ካሳለፍካት
ይችን ፅዋ ነገ ልጅህ ይከፍላታል፡፡
................................................
ማነህ ባለ ሁለት ሳምንት
የንግሳችን ወዳጅ
ባስራ ሁለት ጠማጅ
ባለግራ ፅዋ ተረኛ ተመሪ
በሁለተኛ ዙር የሆንክ ዘካሪ
ይሄንን ማህበር የተቀላቀልከው
ገና ስትወለድ
ለዚህ ቅዱስ ፅዋ አባል ተመርጠህ ነው
ይሄንን እያወቅክ
ይህ የግራው ፅዋህ ወደ ቀኝ እስኪዞር
ከቀድሞው ዘካሪ ስርዓት ህጉን ተማር
እናም ከወዲሁ
ቀድመህ በቅለህ ሰቅለህ
ተዘጋጅተህ ኑር ላለብህ አደራ
ተከታዩ ፅዋ በተሻለ ይዘት ከአንተ እንዲመራ፡፡
በዚህ ማህበር ቤት
ይሄ ፅዋ መሪ እንደዚህ ቢመራም
እኔ አለሁኝ ያለ
ፅዋውን ጨብጦ የተመራ የለም፡፡
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በፋኑኤል
ምዕራፍ አንድ በዚህ ተጠናቋል። ምዕራፍ ሁለት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።
ውድ ታዳሚዎቻችን በዝግጅቶቻችን እየተዝናናችሁ እንደሆነ ተስፋ እያደረግን ዘደ ሁለተኛው ምዕራፍ እንሻገራለን በመቀጠልም
።።ዳንስ በልዑል
።።ግጥም በአብረሀም ።አልወድሽም
።።ወግ በሙባረክ።የሱፍ ፍትፍቴ ቆይታ
።።ግጥም በብንያም።ክረምቱ ጨከነ...
👆👆👆👆👆👆
ዳንስ በልዑል( @ZRekingz )
አልወድሽም
(በአብርሃም)
. . . አልወድሽም . . .
፩ በመጀመሪያ አልወድሽም ከማለቴ በፊት
ስወድሽ ዓለሜ ፣ በፊት ቀደም ብሎ
እኔ አንቺን መፍቅዴ ልቤ ላይ ሲጸነስ
ከትኩሱ ደሜ ፣ ፍቅርሽ ተቀላቅሎ፣
በደም ስሬ ሲፈስ
ያኔ ልብሽን መሻቴ፣
የተስፋዬ ምድር
የህልሞቼ ንክር
ያጥንስስ ግሩም ጥንስስ ነበር።
በአንድ የቀን ሙሉ ወይ የቀን ጎደሎ
ከፍቅሬ አፍላ ላይ ፍቅር ተቃመስነ
ፈቅር ተዛገነ
ከስንዝር ዕድሜዬ ጥቂቱን ገምድሎ
ያ ድንቅ ጥንስስ ድንቅ ወይነ ጠጅ ሆን።
፪ ሌላው . . . ሌላ አልወድሽም ከማለቴ በፊት
በጨቅላነታቹህ የኔ ፍቅር ጨቅላው
በጨቅላ ነፍስሽ ላይ በጠዋት ተቀዳ
ያንድ ፈሬዋ አንቺ ፡ ልብሽ አንድ ፍሬው
የሱን መውደድ ሞላ ከድሜቹ ማለዳ።
ያን እሱን መፈለግ ፣ ከዚ እሱን ማጣት ጋር
አንድ ላይ ቀፍድዳ
ወዶ አለማግኘትን የናፍቆትን ፍዳ
ያን የአፍቃሪ እዳ ባንድነት ቀይዳ
ተጠናቅቃ አረጀች የልብሽ አቁማዳ።
ምወድሽ አልወድሽም ስልሽ . . .
ከውቦቹ ዓይኖችሽ ግሩም ቁልጭልጭታ
በፍንጭትሽ ሾልኮ ከሚደፋው ሳቅሽ
ከሚተርፍ ፈገግታ
ፍቅርን ዘንቀሽ የጻፍሽው ትዝታ
. . . የጠፋ እንዳይመስልሽ።
ምወድሽ አልወድሽም ስልሽ . . .
እዛ ጎዳና ላይ ፡ እዛ ባስ ስቴሽን ፣ ሳሸት ጸጉርሽን
እዛች አንድ ቦታ በስሱ ስትመጭ ደረቅ ከናፈሬን
እዛ ሲጨላልም በከዋክብት ፊት
በየጎዳናው ላይ ከጉንጭሽ የሚተርፍ እምጷዬ ሲዘራ
በአድማስ ቅላት ውበት አድምቄ እየሳልኩሽ ፍቅር ስናደራ
. . . እነዚን ምናምን ረስቼ እንዳይመስልሽ።
ምወድሽ አልወድሽም ስልሽ . . .
የዛ የፍቅርሽ ስም ድንገት እሚያመልጥሽ
እኔ አለመውደድ ከአፍሽ እሚሾልክሽ
እኔን መሰላቸት ውል ሲል ምይዘው ከኒያ ውብ ዓይኖችሽ፡
እነዚ ምናምን ላንቺ ያለኝን ፍቅር ንደው እንዳይመስልሽ።
.
.
.
እናማ እምወድሽ አልወድሽም ስልሽ
አልወድሽም ያልኩት
አዲስ ወይነ ጠጄን ባረጄ አቁማዳሽ ውስጥ
ስለፈራሁ መክተት።
ምክኒያት
ወደዚች አሮጌ ጎስቋላ አቁማዳ
የንጹሁን ልቤን አዲስ የወይን ጠጅ ደፍሬ ብቀዳ
በብርቱ ወይኔ ህይል ድንገት ብትፈነዳ በድንገት ተቀዳ
መከራው የኔ ነው የኔ ቀራንዮ የኔ ጎለጎታ ለልቤ አዲስ እዳ።
መልካም ወይነ ጠጄ የሀሳቤ ጥንስስ የምኞቴ ጨመቅ
የሚያሰክር ታምር
ተይው ባክሽ እሱን ይፍሰስ ምናባቱ
አፈር በልቶ ይቅር።
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በአብረሀም