ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል - Birana Culture and Art Center
361 subscribers
130 photos
15 videos
5 files
12 links
ላለዎት አስተያየትና ጥያቄ @BiranaAastu_botን ይጠቀሙ።
Download Telegram
Forwarded from Abraham Addisu
አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራም ነው በርቱ።።።ቆንጆ ስራችሁን በአካል ለማየት ናፍቀኛለሁል።እየተከታተልኳችሁ ነው።
🕌🕌🕋🕋🕌🕋🕋🕌🕌
የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የብራና ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንኳን ለ1441ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ኢድ ሙባረክ!
🕌🕌🕋🕋🕌🕋🕋🕌🕌
ዛሬ ማታ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ ልዩ የበዓል መርሀግብር በቴሌግራም ቻናላችን ይከታተሉ።
@aastuart @aastuart @aastuart
ሰላም ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ያለፈውን አንድ ወር በፆም በዱአ ያሳለፋቹ ሙስሊም ወንድም እህቶቻችን ፤ በየቀኑ ከጓደኛዬ ጋር ላጥና ብለህ አመሻሽ ላይ እነ ጀማል ቤት የሄድከው ወንድማችን ፤ በየእለቱ ጤነኛ ሆና ጓደኛዬ ታማለች ብለሽ በውድቅት ሌሊት እነ ሰሚራ ቤት የሄድሽው እህታችን ፤ ሆን ብለህ የቴሌቪዥናቹን ድምፅ ቀንሰህ ebs tv ድምፁ አልሰራም አለኝ እነ የሱፍ ቤት check አድርጌ ልምጣ ብለህ በዛው የቀረኸው ወንድማችን ፤ የፀሎት ስነስርዓት በ FANA tv በቀጥታ እንደሚተላለፍ ለከድጃ ነግሬያት መጣው ብለሽ አመሻሽ ላይ ወጥተሽ ማታ 3:00 ቤትሽ የገባሽው እህታችን......
እንኳን ለዚች ቀን አደረሰሽ ፥ አደረሰህ ፥ አደረሳችሁ!!!!
ብራና የባህል እና የኪነጥበብ ማዕከል እናንተን ለማዝናናት በዓል በዓል የሚሸቱ የጥበብ ስራዎችን ይዞ ተገኝቷል።እንሆ ስራዎቹን ተጋበዙልን
¥¥¥ በረከተ ረመዳን ¥¥¥

ድሮ

እኖርለት ምክንያት ካለም አንድ አጥቼ
ሞቴን ስዳፈረው ከደጄ ጠርቼ
በላ ድፈር ስለው!"
በላ ሞክር ስለው!"
ለዚች ጥያቄየ
እንደ ሰበብ ሆና ትንኝ ብትበቃም
ሞቴ እንቅልፍ ላይ ነው
አውቆ ስለተኛ ቢጠሩት አይነቃም

ሀሜት ያደለባት ቅብልብ ምላሴ
ፌስ ቡክ ያደለዘው የቀኝ አውራ ጣቴ
ፈጣሪን ዘንግተው ለሰይጣን ታዘዋል
ህሊናየም ይላል "ሞት ይገባቸዋል"

ተስፋ ማጣት ገርቶኝ
ብቸኝነት ገፍቶኝ
ሞቴን ለመሸመት ገበየ ብወጣም
ዋጋው ጣራ ነክቷል
ባርቲፊሻል እጥረት ገበያ'ው ተሞልቷል

አሁን

ረመዳን መጣ ሰይጣናት ታሰሩ
መልካምነት በዛ ኢባዳወች ገሩ
የሀጢያቴን ክርፋት ...
በፀፀት ሳሙና አፀዳሁ አጠብኩት
በአላህ እዝነት ስር መኖሬን ወደድኩት

በቀጥታው መንገድ በተውሂድ ጎዳና
ፍቅርህን ከጅየ
ችግርን ለመቻል ፈተናን ለማለፍ ወስኛለሁና

ሞቴ እንቅልፉ ይብዛ ሌቱን አርዘምበት
ይነቃበት ሰበብ ከቶ አታስገኝለት
አረኩት ፀሎቴን
የረመዳን መምጣት ቢቀረፅው ሂወቴን

አውቆ በተኛበት ሞቴን ሞት ይውሰደው
ብልቱ ይሰለብ ዘር ግንዱን ያግደው
አረኩት ዱዐየን
በተስፋ ማጣት ውስጥ ባገኘው ተስፋየን
በሱልጣን.አ
በ26/08/12

👉👉👉 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኩዋን ለ1441 ኛው የኢድ አልፈጥር በዐል በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዐል 🙏🙏🙏
👆👆👆
ግጥም በሱልጣን
👆👆👆👆
ስዕል በ ሜላት
ውድ ቤተሰቦቻችን ያላቹህን አስተያየት
@BiranraAastu_bot ላይ ልታደርሱን ትችላላቹህ።
ይህን ያውቃሉ
1. የረመዳን ፆም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሀይ መግቢያ የሚፆም ፆም ሲሆን በ Iceland ዋና ከተማ በ Reykkavik ከ ሌሊቱ 8:00 እስከ ሌሊቱ 6:00 ሠዓት ተፁሟል። ይህም የሆነበት ምክንያት ፀሀይ ለ 22 ሠዓታት ስላልጠለቀች ነው። ይህም ለ 22 ሠዓታት የተፆመ ፆም የአለማችን ረጅም ጊዜ የፈጀ ፆም ያያደርገዋል።
2.በአለማችን አጭር ጊዜ የፈጀው ፆም ደግሞ በ Australia,Sydney ከ 11:30-11:00 ሠዓት ማለትም ለአስር ሠዓት ተኩል ያክል ጊዜ የተፆመ ፆም ነው።
3.በግብፅ ደግሞ የረመዳን የፆም ሠዓት ለ አንድ ሠዓት ያክል እንዲጓተት ይደረጋል ይህም ድርጊት የፆሙን ሠዓት ቶሎ ያለቀ ያስመስለዋል።
💃🖌🎵🎤🎶🎙🎬🎭📄🖌🕺
ብራና የባህል እና የኪነጥበብ ማዕከል

🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠
"ለፍርሀት ድንጋጤ ሳንሆን እንግዳ
ከቤታችን ሆነን ጥበብን እንቅዳ"
🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠🏠

📄ስነ ፅሁፍ(ግጥም፥ወግ፥ትረካ)
🎭ጭውውት
🖌ስዕል
💃🕺 ዳንስ
🎵ሙዚቃ

ዛሬ ምሽት 2:00 ላይ በ @aastuart እንዳያመልጥዎ።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@aastuart @aastuart
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
"join" ብለው ቤተሰብ ይሁኑ።
💃🖌🎵🎤🎶🎙🎬🎭📄🖌🕺
ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን የዛሬው ፕሮግራማችን ተጀምሯል።
ፍቅር አያረጅም
ሌባ ሴት ወድጄ ምትዘርፍ ቅኔ
አዳሜ ነህ ብለኝ አድርጌያት ሄዋኔ
ከሳር ፍራሼ ላይ ከቅፌ አስገብቻት እየዳበስኩ ፅጉሯን
ዳባሽ ጣቶቼ ላይ አርጋ አለንጋ ጣቷን
አይኔን እያየቺኝ እንዲህ አበሰረቺኝ
"ውዴ ፍም ቀርቦት እንዳየው እንደ ሻማ ቀሚስ ፊቴ ቢሸበሸብ
እንደ ፊደሏ 'ገ' ቢጎብጥ ያንተ ወገብ
እልፍ ብንጃጅም
እመነኝ አለሜ ፍቅር አያረጅም"
ድንገት ታወሰቺኝ እዛች ፍራሼ ላይ
ብቻዬን ተኝቼ ይቺ አነጋገሯ
እንዲህ ያለቺኝ እንስት ስትጠላኝ በወሯ
ወርቁን ስፈትነው በግዜ ዘንግ ይዤ ከቁጭቴ እሳት
በልጅነት መሞት ሆና ተፈታልኝ ያለማርጀት እውነት
©የ@ብ
👆👆👆👆👆👆
ግጥም በየአብስራ