ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል - Birana Culture and Art Center
361 subscribers
130 photos
15 videos
5 files
12 links
ላለዎት አስተያየትና ጥያቄ @BiranaAastu_botን ይጠቀሙ።
Download Telegram
ስማኛለች ማርያም
✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧
©ገብረኪዳን መኳንንት
✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧
ያኔ፦ በልጅነቴ ወቅት፥
ከወተቷ ጠጥቼ ከምግቧ በልቼ
ጠጠር መላሽ እንዳልሆን ፥ ከቅፏ ወጥቼ
ለሆዴ እንዳልሸጥ ኪዳኔን ረስቼ
አስምላ አስገዝታ ለቃሌ ምልክት
ስማኛለች ማርያም የእንብርቴን አናት።

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
🎬ትዳርና ኮሮና🎬
📖ፅሁፍ 📖
እሱባለው ጋሻው
📽ትወና📽
ዳግም ተሾመ
ንዋይ ይርዳው
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
በሰላም መኩሪያ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
በናትናኤል ድሪባ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
ውድ ቤተሰቦቻችን ያላቹህን አስተያየት
@BiranraAastu_bot ላይ ልታደርሱን ትችላላቹህ።
ከቀሪ ፕሮግራማችን ጋር መልካም ቆይታ
እሺ መቼም በዝግጅቱ እየተዝናናቹ እንደሆነ ጥርጥር የለኝም....አሁን የመጨረሻው ክፍል ላይ ነን...በመቀጠል

-ግጥም በእንዳልክ
-ትረካ በንዋይ ይርዳው
-ወግ በሙባረክ
-ስዕል በ ዳግማዊ እና በ ዮሴፍ ይቀርባል።
ቆምኩኝ እኔ ለምስጋና
አንዱ እግሬ ከመከራ ተርፏልና
ቆምኩኝ እኔ ላንቋሽሽ
አንዱ እግሬ በመከራ ቢበላሽ
ቆምኩኝ እኔ ላሞግስ
አይኔ ቢተርፍ ከመፍሰስ
ቆምኩኝ እኔ ላዋርድ
አይኔ ቢፈስ
ሳይገባው ይሄ ፍርድ
ቆምኩኝ እኔ ልመርቅ
አንዱ ጎኔ ፍፁም ጤና ቢሆን እርቅ
ቆምኩኝ እኔ ልራገም
አንዱ ጎኔ ቢበላሽ እንደ ግም
አልሳደብ ባንዱ ጎኔ
ግን የማልተርፍ ባንዱ ስራ ከኩነኔ
አላወድስ ባንዱ አካሌ
ገሀነምን እንኳ ላልወርስ መታለሌ
፣፣፣፣፣፣
ሳንቋሽሸ ደግሞ ሳወድስ
ሳጠለሽ ደግሞ ሳሞግስ
መንታ መንገድ መሀል መቆሜን
እኔ ባወላኩኝ
.
.
.
አ .....ወ.....ይ ባልኩኝ።
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
"ለምን አታገባም?"......እውነተኛ ታሪክ!
~~~~~~~~~~
"ለምን አታገባም?"የእናቴ ጥያቄ ነበር!ሀሙስ ረፋድ 4:00 አከበቢ ከኪቺኑ በር አጠገብ ባላች ትንሽዬ ኩርሲ ላይ ሆኘ እናቴ ምትጋግረውን እንጀራ እየተመለከትኩ በወሬ እያጀብኳት ነበር፤የምጣዱ ግለት እና የአከምባሎው እንፋሎት መሃል ታፍነው የሚበስለው የእንጀራው ነገር የኔ ኑሮ መስሎ ታየኝ፤ስጋ እንደ አየ ውሻ አስሬ ምራቄን ስውጥ አየችኝ መሰል ትኩስ እንጀራውን ቅቤ ለቅልቃ በርበሬ ቀብታ ሰጠችኝ ገና አንድ ጉርሻ ከመጠቅለለ ታናሼ መጣና እየበላሁ ያለሁትን ትኩስ እንጅራ እኔ ሶስት ቦታ የሚጎርሰውን በአንዴ ጠቅልሎ ዋጠ፣ ጩጬዋም መጣችና የአቅሟን ቆረሰች እሷ እንኳን በርበሬው ሲለበልባት ውሃ ብላ ሮጠች፤'ሁልችሁም መዘንጋት የለለባችሁ ነገር ቢኖር የቤቱ ታላቅ መሆኔን ነው!' ብዬ ጎርነን ባለ ድምፅ አስገነዘብኩ አንስቶ ቢወረውረኝ ከሰማይ የወረደ እንቁላል የሚያደረገኝን ታናሽ ወንድሜን የጎሪት እየሾፍኩ!

"እውነቱን ነው አለች!" እናቴ እኔን በማገዝ እንጀራውን ለማውጣት ሰፌዱን ከስር እየሰደደች "በዚህ እድሜየኮ የልጅ ልጄን የማይበት ጌዜ ነው"አለች ሊጡ ወደ አለበት ባልዲ እጇን እየላከኝ" "አዎ አግባ እንጂ ምን ትጠብቃለህ" ብሎ ሰሃኗ ላይ ወደ ቀረች አንዲት ጉርሻ እንጀራ አይኑን ቀሰረ 'አንተ ምን አለብህ' አልኩት ገና የአንደኛ አመት የዩኒቬርሲቲ ተማሪ መሆኑ ትዝ እያለኝ 'ገና ለገና አምስት አመት በቤተሰብ ድጎማ አኖራለሁ የምትል ተስፈኛ ነህ" እኔኮ ለመመረቅ መቶ ቀናት የቀሩኝ እጩ ስራ አጥ እና ጡረተኛ ነኝ አልኩት የዚህ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ስራ አጥነታችን ብቻ ሳይሆን ተስፋ አጥነታችን ጭምር ከፊቴ ድቅን ሲል!!

"እሱን አላህ ያውቃል የአሁነን ግን አስብበት"ብላ እንጅራ ልትጨምርልን ስታመጣ እንደ በቃኝ ነገርኳት "እዚሁ ቤት ውስጥ ትኖራላችሁ ሳሎኑን በፈረቃ እንጠቀማለን እንግዳ ሲኖረን ትለቁልናላችሁ እንግዳ ሲኖራችሁ ደግሞ የራሳችሁ ነው"ብላ ያመጣችውን እንጅራ ለወንድሜ ሰሃኑ ላይ አደረጋለት ስትመለስ መብርት ጠፋች "ኢትዮጵያዬ እንጀራ እንኳን ተጋግሮ እስኪያልቅ የመይታገስ የመብራትሽ ሀይልሽ ግሩም ነው!!'ብዬ ስለ አባይ ግድብ እና ግብፅ ሀሳብ መሰንዘር ፈልጌ ከበላውት ትኩስ እንጀራና ከእናቴ የጋብቻ ሀሳብ ጋር ተዳብሎ ሲወብቀኝ ትቼያቸው ወደ ክፍሌ አመራሁ መብራቱ እስኪመለስ ሽንኩርቷን መላጥ ጀመረች

ወደ ክፍሌ ገብቼ ያልተነጠፈ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩና ለጓደኛዬ ልደውልላት ስልኬን ከኪሴ መዘዝኩ፦
ምን ልበላት?
እንጋባ እላታለሁ!
ከዚያስ?
እሺ ትለኛለቻ
እምቢ ቤታችሁ አይሆንም ካለችኝስ?
እንደዚያማ አትለኝ የኔ ቆንጆ
ብትለኝስ ግን?
ከራሴ ጋር ግብ ግብ ገጥሜ የክፍሌን ስፋት እና ፅዳት እየቃኘሁ የአልጋዬን ግማሽ አካል የወረረውን የቁስ አይነት መታዘብ ጀመርኩ ኮምፒውተር፣ቻርጀር፣የጆሮ ማዳመጫ፣መነበብ ላይ ያለ መፅሀፍ፣ወለሉ ላይ አይኔን ሰደድኩ ካልሲ፣የተፋቁ የሞባይል ካርዶች፣ተፅፎ ያላለቁ ፅሁፍ የያዙ ብጫቂ ወረቀቶች ይኸ ሁሉ ያለው አንዲት ሁለት በሶስት የሆነች ጠባብ ክፍል ውስጥ ነው።ሲበዛ ሰነፍ ነኝ ክፍሌን የሚያፅዱልኝ ታናናሽ ወንድሞቼ ናቸው ያውም ጉቦ ከፍዬ አልያም ሳንቲም ሲፈልጉ ለሽንት ወይም ቲቪ ለማየት ከክፍሌ ስወጣ ተፀድቶ ይጠብቀኛል ያኔ ግን የሚገፈትርላቸው ጨላ ከለለኝ ረፍት ይነሱኛል፣መልሶ ሊያቆሽሹት ሁሉ ይችላሉ!!

ለጓደኛዬ የመደወል ሀሳቤን ለነገ አስተላልፌ ስልኬን አስቀመጥኩ፤የዛሬዋን ምሽት ግን ከሷ ጋር ማሳለፍ ክፍሌ ፈለግኩኝ፤ የዚያን ቀን ምሽት ነሸጠኝ ቢያንስ አልጋዬን ማንጠፍ አለብኝ ብዬ ቆርጬ ተነሳሁ፣ባለ ትዳር ሊሆንም አይደል ተፍ ተፍ ልበላ FM እየሰማሁ ማንጠፌን ቀጠልኩ ለዘመናት ብቻዬን ስገላበጥበት የከረምኩትን አልጋ ላጋራ፣አተኛኜን ሳይቀር ላስትካክል ነው ኤታባቱ!!!
አልጋዬ ውስጥ ገባሁ ያነጠፍኩት አንሶላ ላይ የምናብ ሸራዬን ደረብኩ በግራ ጎኔ ተኝቼ በቀኜ ልስላት!! ጅስሜን ወደሷ ቀሳስሬ፣ሀስቤን ወዲህ ሸብልዬ ጀመርኩ FM ላይ የሰርግ ሙዚቃ እየተደመጠ ነው የፀጋዬ እሼቱ፦
ችቦ አይሞላም ወገቧ2×
ምን ቢሆን ነው ቀለቧ....
የሚለው ስንኝ ጆሮዬን ሰንጥቆ ገባ፣ሌላ ነገር ሳያመጣብኝ ጥርቅም አድርጌ ዘግቼ ወደ ስዕሌ ተመለስኩ ሌቱ ተጋምሷል፣ፀጥታ ሰፍኗል፣ክንዴን አንተራስኳት፣የታሰሬ ፀጉሯን ፈትቼ ለቀቅኩት፣ መደባበስ፣ትንፋሽ ለትንፋሽ መማማግ፣አብሮ የሚፈልቅ ላቦትን መጋራት፣ከስር ያነጠፍኩት አንሶላ ሲጨማደድ ተላይ የደረብነው ሲገፈፍ ሳልኩት፤ሌቱ ሊነጋጋ 11:40 ከመስጂዱ ሙዓዝኑ በለጠቀው አዛን ከምናብ አለሜ ባነንኩ።እንዲሁ ስኳትን የሱብህ ሰላት ደረሰ በምናብ ተጀምሮ በምናብ የሚያልቅ የማይዳሰስ ህይወት እስከ መች ይገፋል ብዬ ሌቱን እየረገምኩ ተነሳሁና ተጣጥቤ ሰገድኩ።
ተመልሼም ተኛሁ.....

ከእንቅልፌ ስነቃ ጠዋቱ 3:46 ይላል የስልክ ሰአቴ ከአልጋዬ ራስጌ በነበረች ትንሽዬ ወንበር ላይ ቁርሴ ተቀምጠዋል ሰሃኑን ከፈትኩት ጨጨብሳ ነበር የምግብ ፈላጎቴ የለም ተውኩት፤እናቴ በሀሳብ መሰባበሬን የተረዳች ይመስላል ከጎኑ አጥሚት ነበር እሱን ግን አልማርኩትም በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አደርኩት ፤ከትንሽ ደቂቃ በኋላ የማታ ሀሳቤ መቋጫ መንገድ ዱዓ/ፀሎት መሆኑ ሲሰማኝ ወደ ጁምዓ ሰላት ለመሄድ መሰናዳት ጀመርኩ፤ሻወር ወሰድኩ ፣ጀለቢያዬን አጠለኩ፣ጥምጣሜን ጣል አደረኩ ፣ሽቶዬን ነስነስ አድርጌ መስታወት ፊት ለፊት ተገተርኩ "ከሰማይ የወረደ መላዐክ መስለሃል"አለኝ ያ ታናሽ ወንድሜ ለነቆራውን መልስ ሳልሰጠው አላህን የሚለምናቸው ዝርዝር ጉዳዮቼን በሀሳቤ አመላለስኩ፤ከግራ ጎኔ ጋር በቀኝ እንድያውለኝ፣እኔ እና እሷ መሀል ያለውን ግርዶሽ አፍርሶ እንዳያደባልቀን ፀሎቴን ላደርስ ወደ መስጂድ አቀናሁ.....ብዙ ችግሬን ዘክዝኬ ተማፀንኩት አቤት ቻይነቱ የሰው ልጅ ቢሆንኮ ምስጢርህን ከሰማ በኋላ መልሶ በእሱ ያሾፍብሃል........ሰአት ደርሶ ተሰገደ

ከጁምዓ ሰላት መልስ ከእናቴ ጋር እዚያው መስጂዱ ፊት ለፊት ያለች አንድ ቡቲክ ገባን ለጩጬዋ ልብስ እያማረጠች እኔም ዝም ብዬ ከምወጣ አልኩና አንድ ፓንት እና ካልሲ ወሰድኩ እውነት ለመናገር የታክሲ ጨላ እንኳን ኪሴ አልነበረም ለመውጣት ስንል አይን አይኗን ተመልከትኩ ቦርሳዋን ከፍታ ቢሉን ዘጋችው። ወዲያው ከቅድቤ ስር ላብ ሲፈልቅ፣በግምባሬ ላይ ያለው ደምስሬ ሲገተር፣ማታ ሳወጣና ሳወርድ ያደርኩት የጋብቻ ሀሳቤ እንደ ጉም ጠጉሬን ፈንቅሎ ሲትን በቤቱ ግድግዳ ላይ በተንጠለጠለው መስታወት ውስጥ ራሴን ተመልከትኩ፣አዘንኩ እናቴ ሳታውቅ ሞራሌን ስብርብሩን አወጣችው፣ተረማመደችብኝ እሷ መች ይኼን አስባ የደግነቷን፣የእናትነቷን ማደረጓ ነበር።እኔ ግን የውስጥ ልብሴን መቀየርያ ሳንቲም እንኳን በኪሴ ያልያዝኩ ብኩን መሆነ ሲገለጥልኝ ሸክምነቴ ከእሷ ብላይ እኔን ተጫጫነኝ፣የእሷ ባለ እዳ ብቻ ሳልሆን እስከ አሀኗ ሰአት እኔ ራሴ እዳ እንደሆንኩ ተሰማኝ። ወደ ቤት እየተመለስን በዝምታ ማዕበል ተዋጥኩ፣የአልፎ ሂያጅን ጫጫታ ስቃኝ ቤት ደረስን።የማግባት ሀሳቤን ላልተወሰኔ ጊዜ አራዘምኩ፤ያቺ አፍ አውጥታ ብትናገር ብዙ ምስጢር የምፈነዳ ክፍሌ ገብቼ እንዲህም የሚል ፅሁፍ መፅፍ ጀመርኩ"በስርዝ ድልዝ የተሽሞነሞነች ቀፋፊ አለም"ኤጭ!
ሙባረክ
በሙባረክ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
ቡላ
✍✍✍✍ደራሲ✍✍✍✍
ቶፊቅ
🗣🗣🗣🗣ተራኪ🗣🗣🗣🗣🗣
ንዋይ
ክቡራንና ክቡራት የብራና ታዳሚዎች ከዚህ በመቀጠል ከናንተ ከቤተሰቦቻችን የተላኩ ስራዎችንና አስተያየቶችን እናቀርባለን።ለሚዎዱት ጓደኛዎ ሼር በማድረግ የቤተሰባችን አባል ያድርጉ የሚቀርቡትን ስራዎች ላይክ በማድረግ ያበረታቱን።
@aastuart
@BiranaAastu_bot
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Forwarded from Nani 🦋🌸
ምህረት ከበደ