Forwarded from Deleted Account
Aref nw betam gin ... tezeberareke ... behonem inndezey yishalale 🙏🙏🙏
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ለሰጣቹህ አስተያየት በጣም እያመሰገንን አስተያየት መስጠት እየፈለጋቹህ ያልሰጣቹህን በ @BiranaAastu_bot ልታደርሱን ትችላላቹህ።
ለሰጣቹህ አስተያየት በጣም እያመሰገንን አስተያየት መስጠት እየፈለጋቹህ ያልሰጣቹህን በ @BiranaAastu_bot ልታደርሱን ትችላላቹህ።
ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን የዛሬው ፕሮግራማችን ተጀምሯል።
¥¥¥ እኔ በሂወቴ ¥¥¥¥
እኔ በሂወቴ
ለሄደች አፍቃሪ ....
"አፍቅሮ እንደማጣት
የሚከብድ ቅጣት"
ስል አላላዝንም
እኔ በሂወቴ
ለሌሊት ጨረቃ....
ቀን ለምትጠፋ
በፀሀይ መኖር ላይ ላለች ተደግፋ
ቅኔ አለግሳትም
ከቶ አላደንቃትም
እኔ በሂወቴ
ከቀጠሮው ቦታ አርፍዳ ለመጣች
የልብ አፍቃሪየ .....
"ቀጥረሽኝ ብትቀሪ ተጨነቀች ነፍሴ"
የሚል ግጥም ብፅፍ ፀጉር ከምላሴ
እኔ በሂወቴ
የምፅፈው ግጥም የምቀኘው ቅኔ
የማዜመው ዜማ ድርጌቴ በሞላ
ከቶ አይመሰክርም ካገር መምከን ሌላ
ያገሬ ገበሬ
የመሸበት መጥቶ እንግዳ ሲደርሰው
በማርና ወተት አንጀት የሚያርሰው
ድካሙ እንዲቀለው....
በሳት ውሀ አሙቆ እምሽቁን አላቆ
መደብ 'ሚያመቻች ምኝታውን ለቆ
ያገሬ መምህር
መፅሀፍ ቢቸግር አንድ ለሶስት ብሎ
ዳስተር መግዣ ቢያጥረው አጎዛ ተልትሎ
የደመወዙ አሳብ የትምርቱ ሂሳብ
የፖለቲካው ቃር የመገፋቱ ዳር
ሁሉን ተቋቁሞ
ፊደል ላስቆጠረን እዚህ ላደረሰን
google በሌለበት አውቀት ላጎረሰን
ያገሬ ወታደር
ጥይት እንደ ዝናብ ባሩድ እንደ ሽቶ
በግፍ እየማገ
ጥላትን ያርዳል
ነጭ ላባቸውን በቀይ ደም ያበርደል
ደም እንደ ምንጭ ውሀ ሬሳ እንደ ቀላል
በጥንባሳ አሞራ ሲተለተል አይቷል
ይህ ሁሉ ባለበት
ሂወት እንደ ዋዛ....
በከባድ መሳሪያ ስትቀጠፍ አይቶ
ወደ ኀላ ማለት አይከጅልም ከቶ
ይሄ ሁሉ ጀግና....
በሞላበት ቀየ በሞላበት ምድር
እንደትስ ይቻላል
ለሄደች አፍቃሪ
ሲያላዝኑ ውሎ ሲያላዝኑ ማደር
ላገሬ ገበሬ ወታደር መምህር
ሳይቸረው ሞገስ ሳይቸረው ክብር
አንደትስ ይቻለኝ....
ለሌሊት ጨረቃ ውዷ የኔ ፍቅር
ግጥም ልፅፍላት ቅኔን ልደረድር
ሌቦቿን አንግሳ ጀግኖቿን ማሞገስ
በተሳናት ሀገር
ተረት ናት ጨረቃ እርም ነው መፋቀር::
በሱልጣን. አ
በ28/08/12
"ክብር ለሚገባቸው ክብር እንስጥ"
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
እኔ በሂወቴ
ለሄደች አፍቃሪ ....
"አፍቅሮ እንደማጣት
የሚከብድ ቅጣት"
ስል አላላዝንም
እኔ በሂወቴ
ለሌሊት ጨረቃ....
ቀን ለምትጠፋ
በፀሀይ መኖር ላይ ላለች ተደግፋ
ቅኔ አለግሳትም
ከቶ አላደንቃትም
እኔ በሂወቴ
ከቀጠሮው ቦታ አርፍዳ ለመጣች
የልብ አፍቃሪየ .....
"ቀጥረሽኝ ብትቀሪ ተጨነቀች ነፍሴ"
የሚል ግጥም ብፅፍ ፀጉር ከምላሴ
እኔ በሂወቴ
የምፅፈው ግጥም የምቀኘው ቅኔ
የማዜመው ዜማ ድርጌቴ በሞላ
ከቶ አይመሰክርም ካገር መምከን ሌላ
ያገሬ ገበሬ
የመሸበት መጥቶ እንግዳ ሲደርሰው
በማርና ወተት አንጀት የሚያርሰው
ድካሙ እንዲቀለው....
በሳት ውሀ አሙቆ እምሽቁን አላቆ
መደብ 'ሚያመቻች ምኝታውን ለቆ
ያገሬ መምህር
መፅሀፍ ቢቸግር አንድ ለሶስት ብሎ
ዳስተር መግዣ ቢያጥረው አጎዛ ተልትሎ
የደመወዙ አሳብ የትምርቱ ሂሳብ
የፖለቲካው ቃር የመገፋቱ ዳር
ሁሉን ተቋቁሞ
ፊደል ላስቆጠረን እዚህ ላደረሰን
google በሌለበት አውቀት ላጎረሰን
ያገሬ ወታደር
ጥይት እንደ ዝናብ ባሩድ እንደ ሽቶ
በግፍ እየማገ
ጥላትን ያርዳል
ነጭ ላባቸውን በቀይ ደም ያበርደል
ደም እንደ ምንጭ ውሀ ሬሳ እንደ ቀላል
በጥንባሳ አሞራ ሲተለተል አይቷል
ይህ ሁሉ ባለበት
ሂወት እንደ ዋዛ....
በከባድ መሳሪያ ስትቀጠፍ አይቶ
ወደ ኀላ ማለት አይከጅልም ከቶ
ይሄ ሁሉ ጀግና....
በሞላበት ቀየ በሞላበት ምድር
እንደትስ ይቻላል
ለሄደች አፍቃሪ
ሲያላዝኑ ውሎ ሲያላዝኑ ማደር
ላገሬ ገበሬ ወታደር መምህር
ሳይቸረው ሞገስ ሳይቸረው ክብር
አንደትስ ይቻለኝ....
ለሌሊት ጨረቃ ውዷ የኔ ፍቅር
ግጥም ልፅፍላት ቅኔን ልደረድር
ሌቦቿን አንግሳ ጀግኖቿን ማሞገስ
በተሳናት ሀገር
ተረት ናት ጨረቃ እርም ነው መፋቀር::
በሱልጣን. አ
በ28/08/12
"ክብር ለሚገባቸው ክብር እንስጥ"
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
እሺ መቼም በዝግጅቱ እየተዝናናቹ እንደሆነ ጥርጥር የለኝም....አሁን የመጨረሻው ክፍል ላይ ነን...በመቀጠል
-ግጥም በእንዳልክ
-ትረካ በንዋይ ይርዳው
-ወግ በሙባረክ
-ስዕል በ ዳግማዊ እና በ ዮሴፍ ይቀርባል።
-ግጥም በእንዳልክ
-ትረካ በንዋይ ይርዳው
-ወግ በሙባረክ
-ስዕል በ ዳግማዊ እና በ ዮሴፍ ይቀርባል።
ቆምኩኝ እኔ ለምስጋና
አንዱ እግሬ ከመከራ ተርፏልና
ቆምኩኝ እኔ ላንቋሽሽ
አንዱ እግሬ በመከራ ቢበላሽ
ቆምኩኝ እኔ ላሞግስ
አይኔ ቢተርፍ ከመፍሰስ
ቆምኩኝ እኔ ላዋርድ
አይኔ ቢፈስ
ሳይገባው ይሄ ፍርድ
ቆምኩኝ እኔ ልመርቅ
አንዱ ጎኔ ፍፁም ጤና ቢሆን እርቅ
ቆምኩኝ እኔ ልራገም
አንዱ ጎኔ ቢበላሽ እንደ ግም
አልሳደብ ባንዱ ጎኔ
ግን የማልተርፍ ባንዱ ስራ ከኩነኔ
አላወድስ ባንዱ አካሌ
ገሀነምን እንኳ ላልወርስ መታለሌ
፣፣፣፣፣፣
ሳንቋሽሸ ደግሞ ሳወድስ
ሳጠለሽ ደግሞ ሳሞግስ
መንታ መንገድ መሀል መቆሜን
እኔ ባወላኩኝ
.
.
.
አ .....ወ.....ይ ባልኩኝ።
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart
አንዱ እግሬ ከመከራ ተርፏልና
ቆምኩኝ እኔ ላንቋሽሽ
አንዱ እግሬ በመከራ ቢበላሽ
ቆምኩኝ እኔ ላሞግስ
አይኔ ቢተርፍ ከመፍሰስ
ቆምኩኝ እኔ ላዋርድ
አይኔ ቢፈስ
ሳይገባው ይሄ ፍርድ
ቆምኩኝ እኔ ልመርቅ
አንዱ ጎኔ ፍፁም ጤና ቢሆን እርቅ
ቆምኩኝ እኔ ልራገም
አንዱ ጎኔ ቢበላሽ እንደ ግም
አልሳደብ ባንዱ ጎኔ
ግን የማልተርፍ ባንዱ ስራ ከኩነኔ
አላወድስ ባንዱ አካሌ
ገሀነምን እንኳ ላልወርስ መታለሌ
፣፣፣፣፣፣
ሳንቋሽሸ ደግሞ ሳወድስ
ሳጠለሽ ደግሞ ሳሞግስ
መንታ መንገድ መሀል መቆሜን
እኔ ባወላኩኝ
.
.
.
አ .....ወ.....ይ ባልኩኝ።
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@aastuart @aastuart @aastuart