ብራና የባህልና ኪነጥበብ ማዕከል - Birana Culture and Art Center
361 subscribers
130 photos
15 videos
5 files
12 links
ላለዎት አስተያየትና ጥያቄ @BiranaAastu_botን ይጠቀሙ።
Download Telegram
መፈንቅለ ጫማ
⛸⛸⛸⛸⛸
ሁልጊዜ ጠዋት ስነሳ የሚቀሰቅሰኝ የወፎች ጫጫታ ወይም የአላርም ድምፅ ሳይሆን የጫማ ሽታ ነው። ዛሬም እንደተለመደው ሰከንድ ሳያሳልፍ በሰዓቱ ቀስቅሶኛል። ይህ የጫማ ሽታ የተለያዩ አስገራሚ ባህሪያት አሉት። ከነዚህም መካከል ዋንኛው በአፍንጫ ብቻ ሳይሆን በቆዳ ቀዳዳዎችም መግባት መቻሉ ነው። ያካበድኩ እንዳይመስላችሁ ካላመናችሁኝ ዶርም መታችሁ መሞከር ትችላላችሁ። ግን ከሞከራችሁት በኋላ የግድያ ሙከራ አደረገብን ብላችሁ እንዳትከሱኝ ከወዲሁ እማፀናለሁ። አንዳንዴ ከዚህ ጫማ በላይ የሚሸት ነገር የለም ብዬ አስብና የአንዳንድ አክቲቪስቶች አስተሳሰብ ትዝ ሲለኝ ሀሳቤን ወዲያው እቀይራለው። ኢትዮጵያ ውስጥ ለፖለቲካ ጥቅም መዋል እየቻለ ባክኖ የቀረው ድምፅ አልባ መሳሪያ የጫማ ሽታ ነው።የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች በቂ የጫማ ሽታ አቅርቦት ስላላቸው ይሄን መሳሪያ መንግስትም ተቃዋሚዎችም መጠቀም ይችላሉ። መንግስት ያልተፈቀደ ሰልፍና ስብሰባ ለመበተን ተቃዋሚዎች ደግሞ መንገድ ለመዝጋት መጠቀም ይችላሉ።በዚህ ጊዜ ድንጋይ በማንከባለል ጊዜን እና ጉልበትን ከሚያባክኑ አንዳፍታ መሃል መንገድ ላይ ጫማ ብቻ በመጠቀም መንገድ የመዝጋት ሱስ ካለባቸው ማስታገስ ይችላሉ።ጫማው ሁለቱም እጅ ከገባ ግን ያኔ የሚፈጠረው ለወሬም አይመች። እና ከእንቅልፌ እንደተነሳው ደባሎቼን ቀስቅሼ ብሶት የወለደው ውይይት ማድረግ ጀመርን። እንደ ሁልጊዜው የመጀመሪያው ተናጋሪ በእልህ እየተንቀጠቀጠ እንዲህ ሲል ተናገረ ፦ የጫማው ሽታ ዶርሙን ከመቆጣጠሩ የራሴ ፈስ ምን አይነት ሽታ እንዳለው ጠፍቶብኛል ምን አለበት ወግ ደርሶን እንደሌላው ሰው ፈስተን ዶርሙን ብናናፍሰው። ደግሞ አያቶቻችን በዘልማድ መጋኛ ሚሉት የጫማ ሽታን ሳይሆን አይቀርም። ከፈጣሪ ቀጥሎ የምንፈራው እኮ የዚን ዶርም በር ከፍቶ መግባት ነው ። አንድ ነገር ካላረግን ሁላችንም በተኛንበት እንዳንቀር ያሰጋኛል በማለት ንግግሩን ጨረሰ። እስካሁን በዝምታ ፀጉሩን እያፍተለተለ ሲሰማ የነበረው ደባላችን ጉሮሮውን ጠራርጎ ረጅም ዲስኩሩን ጀመረ። እኔ እንደማስበው ከሆነ መጀመሪያ የሽታው መንስኤ ምን እንደሆነ ማወቅ አለብን። እስከዛሬ ባደረኩት ጥናት መሰረት የተለያዩ ግምቶቼን አስቀምጣለው እያለ ማስታወሻውን ማንበብ ጀመረ። እኔ ደግሞ በሃሳቤ ምን አለ ሀገራችን ውስጥ ያሉ ችግሮች ተጠንተው እንደዚ ብንወያይባቸው እያልኩ ሳውጠነጥን የችግር ፈቺ እንጂ የአጥኚ ችግር እንደሌለብን አስታወስኩ። ከሃሳቤ ያነቃኝ የደባሌ ድምፅ ነበር ።የመጨረሻው መንስኤ እግሩ ሊሆን ይችላል ሲል እንዴ የመጀመሪያውስ ልል አሰብኩና በሀሳብ ስባዝን እንዳመለጠኝ ገባኝ።ለነገሩ በሀገራችን ስብሰባ ላይ ብዙ ነገር የሚያመልጣቸው በሃሳብ በመባዘን ሳይሆን በእንቅልፍ ነው። ከቀበሌ እስከ ፓርላማ ስብሰባ ላይ የመተኛት ልክፍት አለ። በበለፀጉት ሀገራት ተከፍሎህ የምተኛው ለጥናትና ምርምር ብቻ ነው። በኛ ሀገር ግን ስብሰባ ውስጥ ስተኛ በድርጎ መልክ ይከፈልሃል ፓርላማ ውስጥ ከተኛህ ከክፍያው በተጨማሪ እንቅልፍህ በቀጥታ ስርጭት በቴሌቭዥን ይተላለፍልሃል። ደባሌ ሀሳቡን ቀጥሏል ያው እንደምታውቁት ፈጣሪ ጥበቡ ድንቅ ነው ምናልባት ልጁ እግሩን ከመራመድ ባሻገር ለመፍሳት እየተጠቀመበት ይመስለኛል በማለት ንግግሩን ቋጨ ። ቀጣዩ ተናጋሪ እኔ እንደመሆኔ መጠን ሁለቱም ወደ ኔ ዞሩ። እኔ የምለው በማለት ንግግሬን ጀመርኩ እኔ የምለው የተለየ ነገር ባይኖረኝም የሽታው መንስኤ ካልሲው ይመስለኝ እንደነበር ሁላችሁም ታውቃላችሁ። ምናልባት ከቆዳ የተሰራ ካልሲ እየተጠቀመ ይሆን በሚል ጥርጣሬ ማለት ነው ። ቆዳም ቢሆን እንደዚህ ለመሽተት ቢያንስ ከሞተ ሳምንት ካለፈው እንስ ሳ ላይ መገፈፍ አለበት ስለዚህ ጥርጣሬዬ ፉርሽ ሆኖ ቀረ ስል ሁለቱም በመስማማት አንገታቸውን ነቀንቁ። አሁን ወደ መፍትሄው እንሂድ የኔ መፍትሄ ልክ ዶሮ ሲታረድ ሳፋ እንደሚከደንበት ልጁ እንዳወለቀ ጫማውን ማፈን ብንችል መልካም ነው ይህንን እቅድ ለማሳካት ግን ለልጁ ጫማህ ይሸታል ብለን በድፍረት መናገር አለብን በማለት ሀሳቤን ስሰነዝር ደባሎቼ ተቃወሙት ።እንዴ ልታስፈጀን ነው እንዴ እየቀለድንበት ቢመስለው ሌላ ችግር ነው በማለት ነገሩኝ። እሺ እናንተ የተሻለ ሃሳብ ካላችሁ ተናገሩ አልኳቸው ብዬ በምሬት ተናገርኩ ስብሰባችን እንደሃገራችን የመንግስት ስብሰባዎች አላልቅ ሲለኝ። ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት ስብሰባዎች ሶስት ክፍል አላቸው። ቅድመ ስብሰባ ስብሰባ እና ድህረ ስብሰባ ሲሰኙ በቅድመ ስብሰባ ውስጥ የስብሰባውን ቀን ለመወሰን አንድ ቀን ስብሰባው ላይ ሚነሱትን ሀሳቦች ለመናገር አንድ ቀን በአጠቃላይ ለሁለት ቀን ይሰበሰባሉ።ዋናው ስብሰባ ተሳታፊዎቹ ንቁ ከሆኑ ለአንድ ቀን እንደተለመደው ከተኙ ደግሞ እስከ ሳምንት ሊቆይ ይችላል ። በድህረ ስብሰባ የሚከወነው ከስብሰባው የተገኙ ጥቅሞችን መናገር እና በፍትሃዊ መልኩ መከፋፈል ነው። ይሄ እንኳን ከ አንድ ቀን በላይ አይፈጅም። ታድያ በምን ሰዓት ሰርተው ሃገር እንለውጣለን እንደሚሉ አይገባኝም።ደባሌ የመፍትሄ ሃሳቡን እንዲህ ሲል ጀመረ።ለምን ማታ ማታ እግሩን ውሃ አሙቀን አናጥበውም ሲል ሁለታችንም ጮህንበት ልንማር እንጂ እግር ለማጠብ አልመጣንም አልነው ልክ እንደተመካከረ ሰው በአንድ ድምፀት እሺ ምን እናርግ ከሽታው ይሻላል ብዬ እኮ ነው ብሎ በተሰላቸ ድምፅ ተናገረ።ለምን ጫማውን አንጥለውም የሚል ሃሳብ ሲሰነዘር ሶስታችንም በፍጥነት ዞርን ጓደኛችን ነበር በሩን ከፍቶ እየገባ ዛሬም ስለዚህ ጫማ ነው ምታወሩት በቃ እናንተም ካሁን በኋላ ከምትቸገሩ እንጣለው በማለት ይመለከተን ጀመር። ልጁ ጫማዬ የታለ ቢልስ የኔ ጥያቄ ነበር።ጓደኛችንም ከእግርህ ጋ ተጣልቶ ኮብልሏል በሉት አለን። እኛም አጥጋቢ መልስ ባናገኝም በጫማው መጣል ተስማምተን እንደ ሬሳ ሳጥን አንዱን ጫማ ለአራት ይዘን ወደ መስኮቱ ማዝገም ጀመርን።መስኮቱ ጋር ከመድረሳችን በሩ ተበርግዶ ተከፈተ የጫማው ባለንብረት ነበር ። እንዴ ጫማዬን ምን ልታደርጉት ነው ሲል አይ ዶርም ልናፀዳ እያነሳሳን ነው የሚል ዐረፍተ ነገር ከሁላችንም አፍ እኩል ወጣ።


✍በቢኒያም
ምዕራፍ ሁለት ምርጥ እንደነበር ጥርጥር የለኝም።
አሁንም መርሃግብሩ ይቀጥላል ከቆይታ በኋላ በምዕራፍ ሶስት እንገናኛለን።
መልካም ጊዜ
እስኪ የምዕራፍ ሶስት መርሀግብሮችን በጥበባዊ መንገድ ላስተዋውቃችሁ

ታዲያ #share ማድረጎን አይርሱ


@aastuart
@aastuart
@aastuart
@aastuart
@aastuart
👆👆👆👆
ለድብርቱም ቢሆን "motivational voice"፣
ለታዳሚዎቻችን ካላችሁበት ይድረስ።
ከተስፋ ስእሉን ጠብቄ አገኘሁት፣
ለበለጠ ስራ እንቅልፌን አራኩት።
ኪሩቤል ግጥምህን ጀባ በለን እስኪ፣
በጄዲ ሙዚቃ ልቤም እንድትረኪ፣
ብራና አለልሽ የጥበብ ተራኪ።
ስዕል
በተስፋአማኑኤል
እንደ ግሸን ማርያም
ግማደ መስቀሉ
እንደ ቁልቢ ንግስ
ለክብረ በአሉ
መሔድን እንድሻ
ላ'ጢያቴ ማርከሻ
አንግቤ እጅ መንሻ
:
እናፍቅሻለሁ
፡
እንደዛች እምቦሳ
አንደጥጃ ግልገል
ርቧት ለመጥባት
እናቷን መከተል
ሙያዋ እንዳረገች
አንደ ትንሽ ግልገል - የምትል ከል ከል
:
እናፍቅሻለሁ
:
እንደዛ ገበሬ
በርትቶ እንደሚያርሠው
ዘርቶ አጎልጉሎ
ካረመ ቡሃላ እንደሚጠብቀው
የሃምሌ ደመና
:
እናፍቅሻለሁ
:
ሞት ተበይኖበት
ባደባባይ ቀርቦ
የቅጣት ገመዱ
ካንገቱ ላይ ውሎ
የዳኛ ምህረት ቃል
ሊሠማ እንዲናፍቅ
ያ ሟች ወንጀለኛ
:
እናፍቅሻለሁ
፡
ድንጉላ እንዲናፍቅ
ንግስቱን ሊያጠቃ
ሞቱ ቢከተልም
ደስታው ሲያበቃ
እናፍቅሻለሁ
አይንሽን እሻለሁ
ባይንሽ ረክቼ
ሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ስትውይ ተመልክቼ
የድንጉላ ሞቴን ፅዋ ተጎንጭቼ
በአዲስ ቀን በአዲስ ሀይል
እናፍቅሻለሁ
ለሌላ ስቃይ ሞት ላይሽ እመጣለሁ

ድንጉላ ወንድ ንብ ሲሆን ንግስቱ ጋር ግንኙነት ካረገ (ካጠቃ) ቡሃላ ይሞታል
ማጥቃት ግንኙነት መፈፀም ማለት ነው ብዙ ጊዜ ለከብቶች ነው የሚጠቀሙበት
ቆይታችን የተከታተላችሁትን ይመስል ነበረ። ስላሳለፍነው ሰናይ ምሽት እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። ይሄን ክፉ ጊዜ ፈጣሪ አሳልፎ ዳግም በሰላም ያገናኘን። ለመዝጊያ የምቶን አጭር ግጥም እየጋበዝኳችሁ እኔ በዚሁ እሰናበታችኋለሁ በሌላ ጊዜ ለየት ባሉ ስራዎች እስከምንገናኝ በጤና ቆዩን።
✡✡የኔታ✡✡

ከሆሄ ክምችት ከአንዷ ፍቅር ቢጤ
ጠብ አርጎኝ ነበረ ሆኜ ወንደላጤ
"ታ" ናት የኔ ፊደል የሰረቀች ልቤን
እናም ተሰየምኩኝ በሷ የኔ መሆን
የኔ ትሁን ብዬ "ታ"ን ወደድኳትና
የኔታ ተባልኩኝ እሷም የኔ ሆና


✍✍ቤተልሄም ግርማ✍✍