በቱሉ ዲምቱ ሳይት በአዲስ እይታ እና በአማራጭ ቴክኖሎጂ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል !
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር ከሚገኙ የግንባታ ሳይቶች አንዱ በሆነው ቱሉ ዲምቱ ሳይት እየተገነቡ የሚገኙት 2B+G+10 የወለል ከፍታ ያላቸው 11 የጋራ መኖሪያ ቤት ህንጻዎች በተቀመጠው ጊዜ ለማጠናቀቅ ግንባታው እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ ::
ባለፈው ክረምት የተጀመሩትና በአስራ አንድ ስራ ተቋራጮች እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (A.A.S.T.U) አማካሪነት ግንባታ እየተሰራ የሚገኘው የጋራ መኖሪያ ቤት ህንጻዎች በአሁኑ ወቅት ጥሩ የሚባል አፈጻጸም ላይ እንደሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቱ አሳውቋል::
ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ
https://linktr.ee/aahdab

የጥምቀት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች የሚታደሙበትና በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ የከተማችን አንዱ የድምቀት ምንጭና የዓለም ሀብት ነው።
የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀና ፍፁም ባማረ መልኩ በሁሉም ስፍራዎች እንዲከበር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የጥምቀት በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ተወያይተናል። በውይይታችንም አጠቃላይ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ተመልክተናል።
አስተዳደራችን፣ እንደ ሌሎች ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ሁሉ የጥምቀት በዓልም በታላቅ ድምቀትና በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የከተራና የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
መጪውን የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ይፋ አደርጓል።
ጥር 10 እና 11 ቀን 2018 ዓ.ም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የከተራና የጥምቀት በዓል ይከበራል።
በአዲስ አበባም በዋነኝነት በጃን ሜዳ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ጥሩነሽ ቤይጂንግ፣ በለሚ ኩራ አራብሳ ሠፈራ እንዲሁም በን/ስ/ላፍቶ ሀጫሉ አደባባይ አካባቢ በሚገኙ ጥምቀተ ባህር ቦታዎች በርካታ ታቦታት ስለሚያድሩና የበዓሉ አክባሪዎች ስለሚወጡ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፦
👉 ከፈረንሳይ ለጋሲዮን ወደ 6 ኪሎ (ፈረንሳይ ኤምባሲ ድልድይ)
👉 ከቀበና አደባባይ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል (ቀበና አደባባይ)
👉 ከጀርመን ኤምባሲ ድልድይ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል (ጀርመን ኤምባሲ ድልድይ)
👉 ከኮሪያ ሰፈር ወደ ምኒልክ (ኮሪያ ሰፈር)
👉 ከግንፍሌ ወደ ሳንፎርድ ት/ቤት (ግንፍሌ ድልድይ)
👉 ከቅድስት ማርያም ወደ ጃንሜዳ (ቅድስተ ማርያም)
👉 ከገንዘብ ሚ/ር ወደ 6ኪሎ ቶታል (ገንዘብ ሚኒስቴር)
👉 ከ6 ኪሎ አደባባይ ወደ ፈረንሳይ ለጋሲዮን (6ኪሎ አደባባይ ላይ)
👉 ከቃሊቲ ማሰልጠኛ ጥሩነሽ ቤጂንግ
👉 ከዩኒሳ በዓለም ባንክ ጥሩነሽ ቤጂንግ
👉 ከኮዬ አደባባይ በዋሊያ ጥሩነሽ ቤጂንግ
👉ለሚ ኩራ አራብሳ ሠፈራ አካባቢ
👉 ን/ስ/ላፍቶ ሀጫሉ አደባባይ አካባቢ ከጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ጀምሮ በዓሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ መንገዶች የሚዘጉ መሆናቸው ተገልጿል።
አሽከርካሪዎችም ታቦታቱ በሚያልፉባቸው ቦታዎች መንገዶች ዝግ መሆናቸውን አውቀው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪ አስተላልፏል።

በበጀት ዓመቱ በ18 ሳይቶች የተጀመሩ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ከአጠቃላይ ሰራተኛው ጋር በዛሬው ዕለት ተገመገመ።
ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ካስቀመጣቸው ግቦች አንፃር በ6 ወራት ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት በተለይ በ18 ሳይቶች የተጀመሩ መኖሪያ ቤት ግንባታ አፈፃፀም ፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ፤ ከብልሹ አስራርና ሌብነት አንፃር ፤ ገቢ አሰባሰብ ፤ የስራ ባህል ፤ የስራ ዕድል ፈጠራ ፤ የግንባታ ግብአት አቅርቦት ፤ ቅንጅታዊ አስራር ፤ ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ ስራዎች የተከናወኑ ተግባራት እና ሌሎች ተግባራት በግምገማ መድረኩ በጥልቀት ታይተዋል።
በበጀት ዓመቱ በከተማ አስተዳደሩ የተያዘውን 100 ሺ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ለማሳካት ከምንጊዜውም በላይ የተሻለ ስራ እየተሰራ መሆኑን በማጠቃለያ መድረኩ የገለፁት የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ቶማስ ደበሌ በቀጣዮቹ ወራት ዕቅዳችንን ለማሳካት የአገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ በማዘመን ፤ በመንግስትና በግል አጋርነት የተጀመሩትን ግንባታዎች በአዲስ እይታ በተለወጠ የስራ ባህል ተግቶ በመስራት እና ናፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜና ጥራት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ለማጠናቀቅ ተገቢውን ስምሪት ከመስጠት ባሻገር ጠንካራ የፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ በመዘርጋት ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና የታዮ ክፍተቶችን በማረም በቅንጅትና በትብብር ሃላፊነቱን ሁሉም በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
ጥር 9 ቀን 2018 ዓ/ም