A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
32.7K subscribers
15.3K photos
136 videos
47 files
814 links
Download Telegram
የፋይናንስ እምርታ በኢትዮጽያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል በተሰናዳው እና ስድስት የሀገራችንን የፋይናንስ እና የገቢ ሥርዓት በመምራት ላይ ያሉ ዐበይት ተቋማት አፈፃፀም በሚገመግሙበት እና ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የሚኖራቸውን ስትራቴጂያዊ የቅድሚያ ምልከታ በሚያደርጉበት ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት በፋይናንስ አካታችነት ተጨባጭ እድገት ያስገኙ እና ሰፊ መዳረሻ ያላቸው የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርሞች አካሂዳለች።

ከገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ሥርዓት እስከ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃፀሞች እና የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ድረስ የእነዚህ አምስት አመታት ክንዋኔ በፋይናንስ ዘርፉ ተወዳዳሪነትን በሚያሳድጉ በመንግሥት ቆራጥ እና ስኬታማ ተግባራት የሚገለጥ ነው።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ
https://linktr.ee/aahdab 
በተለያዮ ሳይቶች የተጀመሩ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑ ተጠቆመ ።

ግንባታዎች ከተጀመረባቸው 18 አዳዲስ ሳይቶች ውስጥ በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር በሚገኝው በአራብሳ ሳይት የተጀመሩት 2B+G+10 የወለል ከፍታ ያላቸው 10 ህንጻዎች የግንባታ ሂደቱን ለማፋጠንና በአዲስ እይታ ወጪን ለመቀነስ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ጥቅም ላይ በማዋል እና የግንባታ ስራውን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ /A.A.S.T.U/ እያማከረ በፍጥነት ና በጥራት እየሰራ እንደሚገኝ ቅ/ጽ/ቤቱ አሳውቋል::

ቅ/ጽ/ቤቱ አያይዞ ግንባታው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ በ24/7 የስራ ባህልን በፈረቃ የሚሰራ መሆኑ ገልፆል ::

ጥር 7 ቀን 2018 ዓ/ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ
https://linktr.ee/aahdab 
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ከታች ባለው ቪዲዮ መሰረት ሊንኩን በመጫን የሚፈልጉትን መረጃ መመልከት የሚችሉ መሆኑን እናውቃለን

http://aahdab.et/saving
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ5ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚህ መሰረት፦

1ኛ. “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ" ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ።

2ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች የዲሲፕሊን፣ ቅሬታና ይግባኝ አቀራረብና አወሳሰን ሥነ-ሥርዓት ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል ።

3ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች በምደባ ለማስተላለፍ የቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ።

4ኛ. የቦታ ደረጃ (land Grading) ጥናት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ።

በተጨማሪም በሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል ።
በቱሉ ዲምቱ ሳይት በአዲስ እይታ እና በአማራጭ ቴክኖሎጂ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል !

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር ከሚገኙ የግንባታ ሳይቶች አንዱ በሆነው ቱሉ ዲምቱ ሳይት እየተገነቡ የሚገኙት 2B+G+10  የወለል ከፍታ ያላቸው 11 የጋራ መኖሪያ ቤት ህንጻዎች በተቀመጠው ጊዜ ለማጠናቀቅ ግንባታው እየተከናወነ እንደሚገኝ  ተገለፀ ::

ባለፈው ክረምት የተጀመሩትና በአስራ አንድ ስራ ተቋራጮች እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (A.A.S.T.U) አማካሪነት ግንባታ እየተሰራ  የሚገኘው የጋራ መኖሪያ ቤት ህንጻዎች በአሁኑ ወቅት ጥሩ የሚባል አፈጻጸም ላይ እንደሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቱ አሳውቋል::

ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ
https://linktr.ee/aahdab