A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
32.8K subscribers
15.3K photos
136 videos
47 files
814 links
Download Telegram
ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ የሆነችው አዲስ አበባ

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ምቹ ያልነበሩ ተሽከርካሪ እና እግረኛ እኩል የሚጋፋባቸው ለአደጋ የተጋለጡ በተለይም በየመንደሩ የሚኖሩ ታዳጊዎች አማራጭ ባለማግኘታቸው ኳስ ለመጫወት የተሽከርካሪን መንገድ የሚሻሙ ነበሩ። ዛሬ ይህ ታሪክ ሆኖ አልፏል ።

ችግሩን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ለታዳጊዎች ፣ ለወጣቶች እና ለህፃናት ምቹ ከተማን ለመገንባት በመወሰን የከተማዋ ጎዳናዎች ለሁሉም ተስማሚ እንዲሆኑ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎችን አከናውኗል ።

ዛሬ ላይ የአዲስ አበባ ውብ ጎዳናዎች ሁሉን በመልኩ አድርገው በእግረኛና በሳይክል መንገድ ተውበው ፣ በአረንጓዴ አበቦች አጊጠው ለእግር ጎዞዎች እንዲሁም ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅሰቃሴ ምቹ ሆነዋል።

አሁን ላይ በአዲስ ጎዳናዎች ሲጓዙ በተመቻቸላቸው ጎዳናዎች እና ቦታዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ወጣቶች ፣ ህፃናት፣ አረጋውያን እና ጎልማሶችን መመልከት የተለመደ ባህል ሆኗል ።

ምቹ ንፁህ ጤናማ ለሁሉ ተስማሚ ከተማ አዲስ አበባ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ
https://linktr.ee/aahdab      
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከእጅ ንክኪ የፀዳ  ደህንነቱ የተጠበቀ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ  የመንግስት ቤት ውል እድሳት

የቤቶች ልማት እና አስተደደር ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ፕሮግራም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ
https://linktr.ee/aahdab      
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የቤቶች አበይት ክንውኖች ባሳለፍነው ሳምንት
(ከታህሳስ 6 - 12/04/2018)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስለ አከራይ ተከራይ ውል (ክፍል 1)

የቤቶች ልማት እና አስተደደር ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ፕሮግራም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ
https://linktr.ee/aahdab      
"ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ። ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው።

በውይይታችን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የተለዋወጥን ሲሆን ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ንግግር ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር"።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ
https://linktr.ee/aahdab      
በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ  የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበት የአፈፃፀም ደረጃ ተገመገመ

የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያስጀመሯቸው እና የከተማ አስተዳደሩ የበጀት ዓመቱ የ100 ሺ ቤቶች ግንባታ እቅድ አካል ሆነው በተለያየ ሳይት የሚገኙ ፕሮጀክቶች ያሉበት የአፈፃፀም ደረጃ ዛሬ በገምገም ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተቀምጧል ፡፡

ፕሮጀክቶቹን በተቀመጠላቸው ጊዜ እና ጥራት ለማጠናቀቅ ከዚህ በፊት በጀርመን ፤ በግራር እና በአየርጤና ሳይቶች የነበሩ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታዎች ከተመሩበት አግባብ በላቀ መስራት ይገባልም ተብሏል፡፡

24/7  በመስራት እና የስራ ባህልን በመቀየር ኘሮጀክቶቹን በጥራት እና ባጠረ ግዜ ለማጠናቀቅ አመራሮች ስምሪት የወሰዱባቸውን ሳይቶች በጥብቅ ዲስፕሊን መደገፍ ፤ መከታተል እና መቆጣጠር እንደሚገባቸው አፅንኦት ተስጥቶበታል፡፡

በግምገማው የቤቶች ልማት እና አስተደደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ እና ኢ/ር ቶማስ ደበሌ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተርን  ጨምሮ  የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑ ክፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን  ዳይሬክቶሬት

ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ
https://linktr.ee/aahdab