የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን
ወ/ሪት ቅድስት ግዛቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሸከርካሪ እና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአሸከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ፡፡
ወ/ሪት ቅድስት ግዛቸው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪቸውን በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡
የአሸከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ቅድስት ግዛቸው በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ቦታዎች በሀላፊነት ሰርተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሙሁራን አደረጃጀት ሀላፊ፤ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም የኮሙኒኬሽን ሀላፊ ፤ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ኅዝብ ግንኙነት አማካሪ በመሆን ሰርተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪ እና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በሚኖራቸው ቆይታ ብቃት ያላቸው የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲኖሩ ክትትል እና ደጋፍ በማድረግ ብቁ አሽከርካሪ ማፍራት እና በዜጎች ላይ የሚደርሰው የትራፊክ አደጋ ለመከላከል በትጋት ለመስራት አቅደዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለተሽከርካሪ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ የቅርንጫፍና የማዕከል ፈፃሚዎች በተሽከርካሪ መመሪያ ላይ ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር እና አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጠፋ እንዲሆን ነው፡፡
በመመሪያው ላይ ግልፅ ያልሆኑ ነገሮችን የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ እንደሚረዳ የቦሌ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሬው ደምሴ ተናግረዋል፡፡
ከስልጠናው በኋላም ከቅርንጫፍ እና ከማዕከል ሰራተኞች በመመሪያው ዙሪያ እና በአሰራር ለገጠሙአቸው ችግሮች ጥያቄ በማንሳት ውይይት ተደርጓል፡፡
ከተነሱትም ጥያቄዎች መካከልም ቅርንጫፎች ወጥነት ያለው አሰራር ያለመከተል፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተደራጀ የህግ ክፍል ሊኖረው አንደሚገባ፤ ፎርጅድ ዶክመንቶች እየተበራከቱ በመሄዳቸው ለማጣራት ከባድ መሆኑ እና ለአሰራር እንቅፋት መሆኑ እና የመሳሰሉ ችግሮች ከስልጠናው ተሳታፊዎች ተነስቷል፡፡
በመጨረሻም የተሸከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዳዊት ዘለቀ በተነሱ ጥቄዎች ላይ መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ያሉ ችግሮች በአሰራር እና ከባለድርሻ መስሪያ ቤቶች ጋር በጋራ በመስራት ይፈታሉ ብለዋል፡፡

ታኅሳስ 19/04/ 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አዋጅ ላይ ለአሽከርካሪ ዘርፍ ፈፃሚዎችና አመራሮች ስልጠና ሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 1074/ 2010 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ መሰረት በማድረግ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው በዋናነት ስለ አዋጁ ማብራሪያ እና አዋጁ ላይ ተመስርተው ስለወጡ መመሪያዎች ፤ ሰርኩላሮች ማብራሪያ መስጠት ላይ ያተኩራል፡፡
ለስልጠናው የታደሙ ሰልጣኞችም ስለ አዋጁ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮችን እና የአሰራር ክፈተት ነው ያሉትን ሀሳቦች በስልጠናው ላይ አንስተዋል፡፡
ከነዚህም መካከል የሚወጡ ሰርኩላሮች እና መመሪዎች ለሁሉም ቅርንጫፍ ፅፈት ቤቶች በእኩል አለመሰራጨት ወይም ወጥነት ማጣት፤ ለአሽከርካሪ ዘርፍ የሚሰጠው ድጋፍ ከተሸከርካሪ ዘርፍ ያነሰ መሆን፤ የግብዓት ችግር፤ የሰው ሃይል እጥረት፤ የሲስተም እንከን መግጥም እና ከስራ ክፍሉ አፋጣኝ መልስ አለመስጠት የመሳሰሉት አስተያየት እና ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡
ስልጠናውን የሱጡት የቂርቆስ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘገየ ሀብትዬ ስለ አሽከርካሪ ፈቃድ ምድብ ፤ የሞተር ሳይክል፤ የባለሶስት እግር ሞተሮች፤ አውቶ ሞቢል፤ የህዝብ፤ የደረቅ፤ የፈሳሽ እና የልዩ መንጃ ፈቃድ አሰጣጥን እና ስለሌሎች አገልግሎቶች እና ቅድመ ሁኔታን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ያገለገሉት አቶ ቢኒያም ምክሩ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች አሸኛኘት ተደረገላቸው፡፡ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ዕውቅናና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
አቶ ቢኒያም ምክሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ https://www.facebook.com/aadvlca
የተሽከርካሪ (የመኪና) ሽያጭ ውል ለመፈፀም በዉል አዋዋይ ፊት ሲቀርቡ ሟሟላት ያለባቸዉ ሰነዶች
• በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የሽያጭ ውል ሰነድ(ፎርም)፤
• የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ፤
• የሻጭና የገዥ ህጋዊ መታወቂያ፤
• ሻጭ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ፤
• ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
• የሻጭ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
• ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት፤
• ለኮድ 1 እና 3 ከትራንስፖርት ባለስልጣን እና ከገቢዎች የሚሰጥ ክሊራንስ፤
• ለኮድ 1 እና 3 አስር ዓመት ቢሞላውም ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ ከቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍ ባለሥልጣን የተፃፈ ደብዳቤ ወይም ይህን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠው የማረጋገጫ ሰነድ፤
• ለኮድ 5 11 እና 35 የመሳሰሉት ከሐይማኖት ተቋማት በስተቀር ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የተሰጠ የማስተላለፍ የዕውቅና (የድጋፍ) ደብዳቤ፤
• ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ የምስከር ወረቀት የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ስራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
ምንጭ፣ የኤጀንሲው የአሰራር ማንዋል፡፡

18/05/ 2013 ዓ.ም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልና የተገልጋዩን ፍላጎት ለማርካት መላው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
የአሽከርካሪናተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የ 6 ወር ዕቅድ አፈፃፀሙን በማዕከልና በቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከሚገኙ አመራሮች ጋር በጋራ ገምግሟል፡፡
የባለስልጣን መ/ቤቱን የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምን ያቀረቡት የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አደም ኑሪ እንደገለፁት በግማሽ ዓመት ውስጥ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዎች አከናውኗል፡፡
በስድስት ወራት ውስጥ የተቋሙን የሰው ሀይል በማሟላት ፣ለባለሙያዎች ተከታታይ ስልጠናዎች በመስጠት፣ አሰራሮችን ለማሻሻልና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመከላከል የቅደመ ኦዲት ስራ በመጀመር፣የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በማጠናከር፣ ጥፋተኛ ሰራተኞችን ተጠያቂ ከማድረግ አንፃር የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ አስረድተዋል፡፡
አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና በኢኮቴ ለመደገፍ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ያስረዱት ዋና ስራ አስኪያጁ የተጀመሩ ስራዎች ሲጠናቀቁ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እንደሚረዳ አብራርተዋል፡፡
ከቀረበው ዕቅድ አፈፃፀም በኋላ ተሳታፊዎች በቡድን በመከፋፈል አሉ ያሉትን ችግሮች በማንሳት በአፈፃፀሙ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ከተነሱ ተግዳሮቶች መካከል የግብት እጥረት፣ከማዕከል የሚደረግ የድጋፍና ክትትል ስራ በቂ አለመሆን፣ለሚገጥሙ ችግሮች አፋጣኝ መልስ አለመስጠት፣የሲስተም ችግር፣የቢሮ አደረጃጀት ምቹ አለመሆንና የሌሎች ተቋማት ችግሮች ሁሉ ወደ ባለስልጣን መ/ቤቱ መምጣት ይጠቀሳሉ፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አደም ኑሪ እንደገለፁት ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት ደረጃ በደረጃ እንደሚሰራና

የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልና የተገልጋዩን ፍላጎት ለማርካት መላው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡